Does Ethiopia have control over seeds it imports, or just relies on what companies claim?

11 Jul

By Keffyalew Gebremedhin

Ato Mulugetta Indihnew’s interview on The Reporter, “የምናስመጣቸው ዘሮች በዘረመል ምህንድስና የተለወጡ ሳይሆን በማዳቀል የተመረቱትን ነው” (11 July 2012) prompted this article. He is CEO of Green Life Trading Plc. Early on, Green Life was strictly working with the horticulture industry, importing their input requirements from Kneya, such as fertilizers and chemicals.

At present his company has moved on to quietly becoming a major importer of vegetable seeds (tomatoes, red onion, green pepper, cabbages, etc.) from Israel, even when his company does not even have presence on the internet (unless it is registered by name other than Green Life Trading), to disclose its activities to the public the scope of its activities.

While Ato Mulugetta has employed the appropriate words to describe the procedures his company follows regarding the imports of seeds and weed fighting chemicals, his interview implicitly indicates how open Ethiopia is for any product, even those that are transgenically modified GMO seeds.

A country that does not look after its interests in this world and the wellbeing of its citizens is their primary target of companies driven by the many making motive, eventually making it their prey. While there are good many good businesses, most companies, businesses usually are after their investments and the returns they could reap.

Certainly, Ethiopia has in place robust laws for treatment and control of GMOs; but the latitude in the import of seeds by companies has unofficially become sort of freewheeling.

Of course, billionaire Bill Gates was in our country at the end of March 2012 to get this thing sorted out in Ethiopia. It is presumed that he has been successful in many respects, as he indicated on 5 April in his presentation to students at Stanford University in California, partly about his visit to Ethiopia. His goal has been to get Ethiopia opening up its doors to the private sector especially international seed corporations.
 

Seeds are as good as money

The seed business should be seen like the banking industry. The Ethiopian government refused to open the banking sector to foreign banks because it is concerned that the foreign banks would slaughter all the local banks. The international giants could instantly swallow small private seed companies.

This trend has been captured in a detailed study by Prof. Philip H. Howard of Michigan State University of the international seed corporations and companies, entitled Visualizing Consolidation in the Global Seed Industry: 1996–2008, in which he states:

    “Agriculture is a sector of the economy that has been more resistant to the capitalist logic of accumulation than most others. Accumulation involves transforming capital-as-money into capital-as-commodities, and subsequently transforming this into larger amounts of capital-as-money. Agriculture poses a number of challenges to this process because production typically requires extensive amounts of land, involves long periods of time, and is highly unpredictable, due to natural forces such as weather, pests and the perishable nature of food. This makes agricultural production a risky place to seek a profit, particularly when compared to producing durable goods in a factory. Because the accumulation process requires expansion into new economic frontiers, however, large-scale capitalists have had a strong interest in reducing these risks and refashioning agriculture toward a factory model. Post-World War II technologies and research have succeeded in increasing the potential to extract profits from agriculture, particularly indirectly. The sale of agricultural inputs (e.g., seeds, chemicals, equipment), and the transformation or distribution of outputs, have been the most amenable to the process of accumulation, even if the farm itself remains fairly resistant.”

It is important to mention here that we live in a world where the so-called six ‘Life Science’ corporations control the international seed manufacturing and distribution systems. These corporations are: Monsanto, DuPont, Syngenta, Bayer, Dow and BASF. Outside these are also a few independent companies, whose future is uncertain, since they are under the constant fear of being swallowed by the six big ones.
 

Ethiopia must end its pretense & tell the nation what is going on

In Ethiopia, in spite of the laws on the books, in it appears that, as government focuses on persecution of citizens it considers noncompliant political enemies, its institutions have found no time to define parameters of operations for both national and international seed companies.

Harvest time in Kenya: The disease affected more than 150,000 farmers, with agriculture officers warning of reduced harvests (Photo courtesy: Ami Vitale/FAO.

If this situation is allowed to prevail, Ethiopia could face the prospect of losing its natural endowments as far as native seeds are concerned. Moreover, there is also the danger of bad seeds entering the country and creating havoc in a poor nation that has already failed to feed itself. With manufactured seeds, made at home or imported, Kenya’s recent experience in maize farm destruction has shown that is much closer than one can assume.

Several counties in the South Rift region in Kenya have been decimated since last May because bad seeds were sold to farmers. Kenyan farmers are now in the process of suing the government for the damages and seeking compensations, situation that nearly brought Kenya’s government to declare parts of the country national disaster zone.

We know that already a number of companies such as Du Pont have entered Ethiopia. The question is how are they operating when the laws have not changed? Simply recall the August 8, 2011 interview Sylvia Mathews, Sylvia Mathews, president of the Global Development Program in the Gates Foundation. Addis Fortune asked about the Ethiopian law prohibiting them from importing GMO foods. She replied:

    “On the importation of seeds and the ability to move products across countries, we will probably be working on our policy. For instance, eight new breeds of pigeon pea have come out from Uganda. In the next two months, they will move to South Sudan because they do not have a law prohibiting it. For South Sudan, right now, the top quality pigeon pea breeding seeds will make a very big difference.” What has not been stated makes it clearer.

While encouraging the private sector to enter agriculture is very important, it is also one area in the national economy that needs the appropriate laws and institutions, lest the country’s agriculture could become entirely dependent on the few seed corporations of the world.

In recent series of articles under the title Bill Gates vows to defeat hunger & disease in Ethiopia (Part I; Part II; Part III; Part IV; Part V), I tried to argue that opening up is a good thing, so long as there are appropriate laws and enforcement capacities. In that regard, the articles compared the experiences of Brazil, India and Korea, in which I favored the Indian model.

Why is that? To start with the laws and institutions are efficient, open to the private sector and fully conversant with India’s needs in the agricultural sector. Secondly, to the extent possible it pushed toward self-reliance, instead of dependence on foreign companies. To that end, therefore, it fostered alliances between farmers, government, businesses and universities. Thirdly, while India is very strict about GMOs, it has also made sure that it did not entirely close the door on science and technology.

In the case of Brazil and South Korea, popular struggles against GMOs are gaining ground in their different ways. For instance, in Brazil, a country known as the GMO state, a growing number of citizens are turning away from it. In South Korea, the government did not even have any plans for GMOs. It only started it as part of a trade deal with the US importing wheat and corns. Citizens are up in arms, pressuring the Seoul government to ban their imports.

In Ethiopia, we hear that new seed draft law has been before the council of ministers. However, before the laws are changed, international seed companies such as Du Pont have already started working in the country.

Furthermore, the world has become aware that when Prime Minister Meles Zenawi went to Washington last May to participate in G-8 discussions on food, the invitation was premised on the fact that those three African countries were ready for GMO seeds. Accordingly, after their return his colleagues the presidents of Ghana and Tanzania have taken the steps to allow GMOs into their countries, although in the case of Tanzania civil society activists have began putting pressure on the president to reverse.

Is Ethiopia staying quiet on this, leaving the backdoor open?

Hereunder is Ato Mulugetta Indihnew’s interview on The Reporter
 

አቶ ሙሉጌታ እንዲህነው፣የግሪን ላይፍ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ

የግሪን ላይፍ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያዩ አትክልት ዘሮችን ከውጭ በማስመጣት ለኢትዮጵያ አምራቾች ያከፋፍላል፡፡

አቶ ሙሉጌታ እንዲህነው የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ታደሰ ገብረማርያም በማህበሩ እንቅስቃሴ ዙርያ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ግሪን ላይፍ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለአበባ እርሻዎች ግብዓት አቅራቢ ነበር፡፡ ለምንድ ነውን ወደ አትክልት ዘር የማቅረብ ሥራ የተሸጋገረው?

አቶ ሙሉጌታ፡- ድርጅቱ መጀመርያ የተቋቋመው ከአበባ እርሻዎች ኢንዱስትሪ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ የአበባ እርሻዎቹ እንደተቋቋሙ ግብአት አቅራቢ አልነበራቸውም፡፡ በዚህም የተነሳ ድርጅቱ እንደተመሰረተ ለአበባ እርሻዎቹ የሚያስፈልጓቸውን ማዳበሪያና ኬሚካል ማቅረብን በስፋት ተያያዘው፡፡ ይህ ድርጅት ከመቋቋሙ በፊት አበባ እርሻዎቹ የሚፈለጉትን ግብአቶች የሚያስመጡት ከኬንያ ነበር፡፡ አቀራረቡም ወጥ አልነበረም፡፡

የሚቀርቡትም ግብአቶች የጥራት ችግር እንደነበረባቸው አይዘነጋም፡፡ ድርጅቱ ለአበባ እርሻዎቹ የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶች በማቅረብ ላይ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ የገበያ ጥናት ያካሂድ ነበር፡፡ በጥናቱም መሠረት በአትክልት ዘሮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት እንዳለ ለመረዳት ችለናል፡፡ በአትክልት ዘር አቅርቦት ላይ የሚሰራ ብዙም ድርጅት እንደሌለም ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ለረጅም ጊዜ ቢቀመጡ የማይበላሹ ምርጥ የአትክልት ዘሮችን ብናስመጣ ለአምራቹ ይጠቅማል በሚል እሳቤ ከግብርና ምርምር ድርጅት ጋር በመሆን ለሁለት ዓመት ሙከራ አደረግን፡፡ ውጤቱ በሀገር ውስጥ ካሉት የአትክልት ዝርያዎች ብልጫ እንዳለው አሳየ፡፡ ሁልጊዜ በየዓመቱ የሰርቶ ማሳያ እያዘጋጀን አርሶ አደሮች እንዲጐበኙትና ጥቅሙንም እንዲረዱት እናደርጋለን፡፡ የአትክልቱም ዘር የሚመጣው ሀዜራ ጀነቲክስ ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው በዓለም ላይ አሉ ከተባሉ ትልቅ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኩባንያው በአትክልት ስራ ላቅ ያለ ችሎታ ያለው ከመሆኑም ሌላ ከሀገራችን ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም ተግባር ያከናውናል፡፡ በዘረ መል ምህንድስና የተለወጡ ወይም (Genetically modified) የተደረጉ ዘሮችን አይሰራም፡፡ ዘሮችን የሚያመርተው ዘርን በማዳቀል (ሐይብሪድ በማድረግ) ነው፡፡ የምናስመጣቸው ዘሮችም በዘረመል ምህንድስና የተሰሩትን ሳይሆን በማዳቀል የተመረቱትን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከተጠቀሰው ሀገር የምታስገቧቸው የአትክልት ዘሮች ዋጋቸው የአምራቹን አቅም ያገናዘበ አይደለም፡-

Ato Mulugetta Indihnew, CEO Green Life Trading (Courtesy of The Reporter)

አቶ ሙሉጌታ፡- እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ማነፃፀር ያስፈልጋል፡፡ አንደኛው በጣም ርካሽ ዘር ገዝቶ መጠነኛ ምርት ማግኘት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ዋጋው ትንሽ ከፍ ያለ ዘር ገዝቶ የበለጠ ምርት ማግኘት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ከውጭ የምናስገባቸው ዝርያዎች ተመርጠውና ተዳቅለው የተገኙ ናቸው፡፡ ወይም የአሜሪካን ከብትና የሀበሻ ከብት እንደማለት ነው፡፡ ጥሩ ማኔጅመንት ባገኙ ቁጥር ደግሞ የበለጠ እየፋፉና እያዳበሩ ይሄዳሉ፡፡ የሀገር ውስጥ ዝርያ ግን እስከ መጨረሻው እንክብካቤ ቢደረግለትም የሚያስገኘው ውጤት ዝቅተኛ ነው፡፡ ከውጭ የምናስመጣቸውን የአትክልት ዝርያዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ የሰርቶ ማሳያዎች ላይ አባዝተን አምራቹ እንዲያውቃቸው አድርገናል፡፡ በተረፈ ዘሩ በእርግጥ በጣም ውድ ነው፡፡ ዋጋውንም ለመቀነስ እና የአምራቹን አቅም ያገናዘበ እንዲሆን ለማድረግ እየሰራን ነው፡፡ ዘሩ ውድ ሊሆን የቻለው በውጭ ምንዛሪ ስለሚገባና የተለያዩ የሎጂስቲክ ወጪዎች ስላሉት ነው፡፡ አምራቾች በውድ ዋጋ ቢገዙትም የበለጠ አትራፊና ተጠቃሚ በሚሆኑበት አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እንሰጣለን፡፡

ሪፖርተር፡- ስልጠናውን በምን መልክ ነው የምትሰጡት?

አቶ ሙሉጌታ፡- መጀመርያ የኛ አባሎቻችን እስራኤል ሄደው ይህን ዘር ከሚያመርተው ኩባንያ ስልጠና ወስደዋል፡፡ የኩባንያው ባለሙያዎችም ወደዚህ በመምጣት ለአባሎቻችን ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ አባሎቻችን ደግሞ የቀሰሙትን ስልጠና ለአምራቹ ወይም ለገበሬው ያስተላልፋሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት የአምራቾቹን እርሻ ደጋግሞ በመጐብኘት አስፈላጊውን ቁጥጥርና ክትትል በማካሄድ ነው፡፡ በዚህም ሒደት ብልሽት የታየባቸውን በማስተካከል የበለጠ ጠንካራ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የአሰራር ዘዴዎችን እንዲቀስሙ ሁሉ አቀፍ ጥረት ይደረጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተለያዩ በሽታዎች ሲከሰቱ፣ እንዲሁም የውኃ መብዛትና ማነስ ሲታይ የሚስተካከልበትን መንገድ በመጠቆም የእርሻው ማሳ እንክብካቤ እንዳይለየው ይደረጋል፡፡

ሪፖርተር፡- በየትኛው አካባቢ የሚገኙ አምራቾች ናቸው የድርጅቱን የአትክልት ዘር በብዛት ሲጠቀሙ የሚስተዋሉት?

አቶ ሙሉጌታ፡- አትክልት በብዛት የሚያመርቱት በስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚገኙ አምራቾች ናቸው፡፡ ለአዲስ አበባ ገበያ ልዩ ልዩ አትክልትን በብዛት የሚያቀርቡት እና ከውጭ የምናስመጣቸውንም የአትክልት ዘሮች የሚጠቀሙት እነዚሁ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ድርጅቱ የሚያስመጣውን የአትክልት ዘር የሚጠቀሙ አምራቾች የተባይ ማጥፊያ መድኃኒት ባለማግኘታቸው ተቸግረዋል፡፡ በዚህ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድነው?

አቶ ሙሉጌታ፡- መድኃኒት አጠቃቀም ላይ ሕግን መጣስ የለብንም፡፡ እዚህ ሀገር አንድ መድኃኒት ከውጪ መጥቶ በአትክልት ላይ ከመረጩ አስቀድሞ መከተል የሚገባው ቅደም ተከተሎች አሉ፡፡ ዘሩ በግብርና ምርምር ድርጅት ተፈትሾ አልፎ እንደገባ ሁሉ መድኃኒቱም በዚሁ ድርጅት ተመርምሮ ማለፍ አለበት፡፡ በአትክልት መድኃኒት አቅርቦት ላይ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ሁሉ ብዙ የመድኃኒት አማራጮችም የሉም፡፡ ይህንንም ችግር ብቻችንን የምንፈታው አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የመድኃኒት አቅራቢ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል፣ ለችግሮቹ መፍትሔ በሚሆኑ ስራዎች ላይ ቢያተኩሩ መልካም ነው የሚል እምነት አለን፡፡

ሪፖርተር፡- ይህም ማለት መንግስት ምንም ዓይነት መድኃኒት እንዳይገባ ይከለክላል ማለትዎ ነው?

አቶ ሙሉጌታ፡- አለማስገባት ሳይሆን የሰብል በሽታ ማጥፊያ መድኃኒት ሳይመዘገብና ሳይፈተሽ ዝም ብሎ መጠቀም አይቻልም ማለቴ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ የተባይ ማጥፊያ መድኃኒት ጉዳዩ በሚመለከተው መንግስታዊ አካል ይሞከራል፡፡ ውጤቱም አጥጋቢና አካባቢን ለብክለት የማይዳርግ ሆኖ ከተገኘ ይመዘገብና ይፈቀዳል፡፡ ይህንን ለማድረግ ግን ብዙ ሂደት ይኖረዋል፡፡ በቀላሉ የሚያልቅ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሙከራው ብቻ አንድ ዓመት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ሰነዶችን አቅርቦ ፋይል ማድረጉን እና የተጓደሉ ሌሎች ነገሮችን ለማሟላት ደግሞ እስከ ሦስት ዓመት ይፈጃል፡፡ በዚህም መሰረት አንድ መድኃኒት ይህንን ሂደት ሁሉ አልፎ ምዝገባ ካላገኘ በስተቀር ጥቅም ላይ አይውልም፡፡

ሪፖርተር፡- የአትክልት ዘሮች ለምዝገባ የሚበቁት በምን መልኩ ነው?

አቶ ሙሉጌታ፡- ጉዳዩ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል በተለይ የግብርና ምርምር ድርጅት የተለያዩ የሙከራ ጣቢያዎችን ይመርጣል፡፡ ብዙ ጊዜ በዓመት እስከ ሰባት የሚሆኑ የሙከራ ጣቢያዎችን የሚመርጥበት ጊዜ አለ፡፡ ጣቢያዎቹም የተለያየ የአየር ጠባይና የአካባቢ ሁኔታዎች አሏቸው፡፡ በእነዚህም ጣቢያዎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ ዘር የማባዛት ሙከራ ያካሒዳል፡፡ ይህም የሚሆነው ከውጭ የመጣው ዘርና በሀገር ውስጥ የሚገኘውን የአትክልት ዘር ጎን ለጎን ይተከላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የትኛው ዘር ነው በሽታን በበለጠ የመቋቋምና የበለጠ ምርት የሚሰጠው፣ እንዲሁም ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ የሚቆየው የሚለው ተለይቶ ይያዛል፡፡

ሪፖርተር፡- የወደፊት እቅዳችሁ ምንድነው?

አቶ ሙሉጌታ፡- የወደፊት እቅዳችን አምራቹ ዘሩን በርካሽ ዋጋ የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቴክኖሎጂው በሀገር ውስጥ ገብቶ የማዳቀሉ ስራ እዚሁ እንዲካሄድ ማድረግ ነው፡፡ የማዳቀሉ ስራ ውጭ ሀገር ከተካሄደ፣ የሰራተኛ፣ የውኃና የሎጂስቲክ ጉዳይ በጣም ውድ ነው፡፡ ነገር ግን በእኛ ሀገር መሬት ርካሽ ነው፡፡ ስለዚህ እዚሁ ብናዳቅለው፣ የዘሮቹ ዋጋ በጣም ይቀንሳል፣ ሁለተኛም አምራቹም በፈለገው ሰዓት በቀላሉ ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተረፈ በሀገራችን የገበያ ችግር መኖሩ መዘንጋት የለበትም፡፡ ለምሳሌ በዚህ ዓመት ሽንኩርት በጣም ውድ ከሆነ ሁሉም አምራች ሸንኩርት ለማምረት ነው የሚነሳው፡፡ በዚህም የተነሳ ምርቱ ይትረፈረፍ እና ፍላጐት እየወረደ ይሄዳል፡፡ ወይም ሁሉም አምራች ሸንኩርት የሚያመረት ከሆነ ገበያው ከሚፈለገው መጠን በላይ ይሄድና ዋጋው እንደሚወርድ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ሁሉም አምራቾች በሽንኩርት ምርት ላይ ከሚረባረቡ ይልቅ የተወሰኑት ደግሞ በሌላ ምርት ላይ ቢያተኩሩ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- የአትክልቱን ልማት ጥሩ ምርት ሊሰጥ የሚችለው በውኃ ጠብታ ዘዴ (ዲሪፕ) ቢለማ ነው ወይስ በመስኖ?

አቶ ሙሉጌታ፡- በድሪፕ ቢለማ የበለጠ ምርት ይገኝበታል፣ ይህንን ድሪፕ ለመስራት ግን ትንሽ ተጨማሪ ወጪን ይጠይቃል፡፡ ብዙዎቹ አምራቾች አሁን ባሉበት ሁኔታ ምናልባት አቅማቸው ላይችል ይሆናል፡፡ የተወሰኑት ግን ይችሉ ይሆናል፡፡ የድሪፕ ዘዴ ከዋጋው ውድነት ባሻገር ለሀገራችንም አዲስ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የድርጅቱ ባለሙያዎች ይህንን ቴክኖሎጂ አስመልክቶ በስፋት በማስተዋወቅ ላይ ናቸው፡፡ አምራቾቹ አቅማቸውን እያዳበሩ ሲሄዱ እንዳማራጭ ይጠቀሙበታል ብለን እናስባለን፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዘሮች ከቀረጥ ነፃ ናቸው?

አቶ ሙሉጌታ፡- ማንም ሰው ለግብርና ምርት የሚውል ማዳበርያ እና መድኃኒት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ሲያስገባ ከቀረጥ ነፃ ነው፡፡ ዘሮች ግን ቀረጥ ይከፈልባቸዋል፡፡ እንዲያውም እስከ ሱር ታክስ ድረስ ይጠየቅባቸዋል፡፡ ይህም የሆነው እንደ ግብዓት ስላልታዩ ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በበኩላችን ለገንዘብ ሚኒስቴር ለማስረዳት ትንሽ ሙከራ አድርገናል፡፡ ይህም ሆኖ ለጉዳዩ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ በአምራቹም ላይ ለሚፈጠረው ከፍተኛ የዋጋ ጫናም ዋና ምክንያት ይሔው ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገቧቸው የአትክልት ዝርያዎችንና በሔክታር የሚሰጡትን የምርት መጠን ሊያስረዱን ይችላሉ?

አቶ ሙሉጌታ፡- ወደ ሀገር ውስጥ ከምናስገባቸው ልዩ ልዩ ዓይነት የአትክልት ዝርያዎች መካከል የቲማቲም፣ የቀይ ሽንኩርት፣ የጥቅል ጎመን፣ የቃርያና የጥጥ ዘሮች ይገኙባቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የቲማቲም ዘር በሔክታር እስከ 800 ኩንታል፣ ቀይ ሽንኩርት በሔክታር እስከ 500 ኩንታል፣ የጥቅል ጎመን ዘር በሔክታር እስከ 700 ኩንታል፣ ቃሪያ በሔክታር እስከ 400 ኩንታል ምርት ይሰጣሉ፡፡ ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ፡፡ ፈጥነው ለምርት ይደርሳሉ፡፡ በተለይ ቃሪያው በጥሩ እንክብካቤ ከተያዘ ለረጅም ጊዜ ሳይቋረጥ ከፍተኛ ምርት ይሰጣል፡፡ ወፍራም ቆዳ ያለው ሲሆን በጣም የሚያቃጥልና የሚወደድ ነው፡፡ የጥጥ ዝርያዎች ደግሞ የውኃ ፍላጎታቸው ዝቅተኛ ሲሆን፣ በጣም ጠንካራ፣ ለስላሳ፣ ከፍተኛ ጥራትና ረጅም ጭረት (ፋይበር) ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ በመጣጭ ተባዮች የመጎዳት ባህርያቸው ዝቅተኛ የሆነ ድቃይ ዝርያዎች ከመሆናቸውም በላይ ጥራት ያለው ልብስ ለመሥራት የሚያገለግሉ እና በዘመናዊ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ተፈላጊ የሆኑ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ኅብረተሰቡ አትክልትን መመገብ እንዲያዘወትር ወይም እንዲለምድ የምታደርጉት ጥረት አለ?

አቶ ሙሉጌታ፡- ይህ እንኳን ስራችን አይደለም፡፡ ነገር ግን ለአምራቾቹ ከምናቀርብላቸው የአትክልት ዘር አንጻር ስናየው ኅብረተሰቡ አትክልት መመገብን እንደ ባህል አድርጎ ወይም ለጤናው ተስማሚ መሆኑን እየተገነዘበውና እየተረዳው የመጣ መሆኑን ለማወቅ አስችሎናል፡፡ ምክንያቱም አትክልት አምራቾች ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውንና ምርቱ በገበያ ላይ ከፍተኛና ተፈላጊ እየሆነ መምጣቱ ይህንኑ በሚገባ ያመላክታል የሚል እምነት አለን፡፡
 

Transforming Ethiopia TE

%d bloggers like this: