የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘7,300 መኖሪያ ቤቶች በዕጣ አከፋፈለ’ ተባለ

20 Aug

ከ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እስከዛሬ ለኮንዶዎች ገንባታ ውሏል ይባላል። ባለፈው እሁድ 335‚117 ተመዝጋቢዎች ዕጣውን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ተዓማኒነት እንድሚጎደለው በተደጋጋሚ ባረጋገጠ አገዛዝ ቤቶቹ ለፖለቲካ ባለውለተኞችና በጎጠኝነት አለመሰጠታችውን ማን ኦዲት አደረገ?


አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ መልሶ ማልማት እና በሌሎች ነባር ሳይቶች የገነባቸውን 7300 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ከሰዓት በዕጣ አከፋፈለ፡፡

ቤቶቹ የተገቡት በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ቂርቆስና የካ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ነው።

ለ7ኛ ዙር በወጣው ዕጣ ሴቶች 30 በመቶ ቅድሚያ ወስደዋል፡፡

ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አገር አቀፍ ፕሮጀክት ከተጀመረ ወዲህ ከ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጅነር ኃይለመስቀል ተፈራ ተናግረዋል።

በሕዝብ ፊት የተደረገውን የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ያስጀመሩት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በበኩላቸው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ የመጠለያ ችግሩ ይፈታል፤ የከተማዋ ገጽታም ይለወጣል ብለዋል፡፡

ዛሬ ዕጣ የደረሳቸውን ጨምሮ በልማት የተነሱ 15ሺ ሰዎች በዚህ ዓመት የኮንዶሚኒየም ቤት ወስደዋል፡፡

ሌሎች 84 ሺ ቤቶች ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው መባሉን ባልደረባችን በልስቲ አወቀ ዘግቧል፡፡
 
Transforming Ethiopia TE

<span>%d</span> bloggers like this: