የተገኝወርቅ ጌጡ የተመድ ሹመት ሁላችንንም የዜግነት ኩራት ሊያሰማን በተገባ ነበር – በትዕዝብት፡ ለትምህርትና ዕርምት የቀረበ ዕይታ

28 Mar
ምክትል የሕግ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ልዑካን አባል አቶ አምባዬ ተወልደማርያም በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ስም የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር ሳንፍራንሲስኮ ላይ እ.ኤ.አ. ሰኔ 26፣ 1945 ዓ.ም. ሲፈርሙ UN (Photo courtesy: /McCreary)

ምክትል የሕግ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ልዑካን አባል አቶ አምባዬ ተወልደማርያም በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ስም የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር ሳንፍራንሲስኮ ላይ እ.ኤ.አ. ሰኔ 26፣ 1945 ዓ.ም. በመፈረም ኢትዮጵያ የድርጅቱን አባልነት:መብትና ግዴታዎቹን መቀብሏን ሲያረጋግጡ UN (Photo courtesy: /McCreary)

በከፍያለው ገብረመድኅን*

ባለፈው ስኞ (መጋቢት 25, 2013) የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን ኢትዮጵያዊውን ዶር ተገኝወርቅ ጌጡን የድርጅቱ አንደር ሴክሬታሪ ጄኔራል (Undersecretary General for General Assembly and Conference Management) አድርገው ሲሾሙ፤ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ሲሰተምና ግንኙነቶች ውስጥ አንድ የራሷ ታሪክ ምዕራፍ ላይ ማኅተሟን ማሳረፍ ችላለች።

አገራችን የድርጅቱን ቻርተር ከፈረሙት የመጀምሪያዎቹ 51 አገሮች ውስጥ አንዷ ግንባር ቀደም አባል ብትሆንም: ከቻርተሩ ፊርማ ቀን አንስቶ ተገኝ እስከተሾመበት ዕለት፤ ማለትም በድርጅቱ የ67 ዓመታት፣ ስምንት ወራት 12 ቀናት ታሪክ ውስጥ ሀገራችን ለዚህ ክፍተኝ ሹመት በቅታለች። ይህ መታየት ያለበት ግለስቡ በግለስብነቱ መሾሙ ብቻ ሳይሆን፡ በእኔ አመለካክት፤ ይህ ለኢትዮጵያ አኩሪና ተጠቃሽነት ያለው ሹመት መሆኑ ነው፡። ይህ ለአንድ አገር ትልቅ እርምጃ፤ የዓለም አቀፉ ኅብረተስብ እምነት መለኪያ ከመሆኑ ባሻገር privilege ነው።

በዚህ ማዕረግ ላይ የተቀመጡ በተለያየ የሥራ ድርሻ ላይ የተቀመጡ ግለስቦች፤ ክምክትል ዋና ጸሐፊው ቀጥሎ ባለው ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ የዋና ጸሐፊው ካቢኔ አባል ናችው።

በያዝነው 2012-2013 የጸደቀው የድርጅቱ በጀት $5.15 ቢሊዮን ሲሆን፤ አሁን እርሳችው ይተመደቡበት አካል ድጋፍ ስጭ አካል እንድመሆኑ ክፍ ያለ የሠራተኛ ብዛት ያለበትና ይድርጅቱን ወጭ ክፍተኛ ክሚያድርጉት መካክል ነው።

ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህን ሹመት በተመለከተ ደስታቸውን ሲገልጹ፡ የሚያደነቁር ዝምታ የተስማው ግን ከታወቁት የሕወሃት የዜና አውታሮች ነው። ለምን ይሆን? ከግለስቡ በዝርያ አለመገናኘት ይሆን? እነዚህ የታወቁት የሕወሃት የዜና አውታሮችና ባለሙያዎች ይህ ግለስብ ከትግራይ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ጸጥ ማለታቸውን እጠራጠራልሁ! ምናልባትም ከበሮአችውን እይደለቁ ይህ ሹመት ‘እኛ በመሆናችን ነው’የተስጠን የሚለውን ሙዚቃ ባስሙን ነበር! ይህ ለእያንዳንዳችን በግለስብነታችንም ሆነ ለሃግራችን አይበጅም!

ምናለበት በኢትዮጵያዊነት ዓይን ለመተያየት ቢቻል? በእኔ ግምምት ምን ያህል ብዙዎቹ ችግሮቻችን ሊቀረፉ በቻሉ ነበር።

የኢትዮጵያ የተመድ የመጀመሪይው አምባሳደር ብላቴን ጌታ ኤፍሪም ተክለመድኅን

የኢትዮጵያ የተመድ የመጀመሪይው አምባሳደር ብላቴን ጌታ ኤፍሪም ተክለመድኅን

ይህ ትዕዝብት ዝምታ የሰፈነባቸውን የታወቁትን አንዳንድ የተቃዋሚ ድኅረግጾችንም ያጠቃልላል። እኔ ግለስቡ ከመንግሥት ጋር ስላላቸው ግንኙነት የማውቀው ነገር የለም። ቢኖር እንኳ፡ ሁሉ ሰው ተሿሚ ሊሆን በማይችልበት ሁኔታ እንኳ ይሁን ለኢትዮጵያ ስም ይበጃል የሚል የፓለቲካ አስተሳስብ ባለመኖሩ፡ የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ያመላክታል።

እኛ ክሥልጣን ከወረድን አገሪቷ ትጠፋለች የሚለው የሕወሃት አባባል የሚያሳዝነኝን ያህል፤ እኛ ሥልጣን ላይ ካልወጣን አገሪቷ ትወድማለች የሚለው የተቃዋሚው ወገን ተዛማጅ ብዥታ ተገቢውን ሚዛን ሊፈልግ እንደሚገባ ይስማኛ። ማስተዋልና መቀበል አልቻልንም እንጂ: ያለፉት አሥርት ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ያሰተማረው ነገር ቢኖር፡ በመንግሥትም ሆን በፓለቲከኞች ላይ የሚጣል አመኔታ ትርፉ ጥፋትና ኪሳራና እንዲሁም በላሸቀ አስተሳስብ ጉም ለመዝገን ከሚደረግ ጥረት የማይተናነስ መሆኑን ነው።

በነግራችን ላይ በዚህ አቶ ተገኝወርቅ በተሾመብት ሥፍራ አንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ በረዳት ዋና ጸህፊነት ለጥቂት ወራት የሠሩ አንድ ኢትዪጵያዊ ነበሩ። ንገር ግን ባንኪ ሙን እንደመጡ በሆነ ምክንያት ከጥቅት ጊዜያት በኋላ አስናብተዋቸዋል። ምናልባትም በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ አጭሩ የረዳት ዋና ጸሐፊነት ዘመን ሳይሆን አይቀርም።

ክዚያ በተረፈ፡ ሁለት ሌሎች ኢትዮጵያውያን በረዳት ዋና ጸሀፊነት በተባበሩት መንግሥታተ ውስጥ ሲገኙ፡ ከዚያ ውጭ ሌሎች ያሉ አይመስለኝም።

ከሌሎች የአፍሪቃ አግሮች ጋር ሲወዳደር፡ ኢትዮጵያ ይህ የመታጨት፡ የመመረጥ ዕድል የማይገጥማት እያለፈችበት ያለችው ሂደት ጠመዝማዛ ከመሆኑ በተጨማሪም፤ የኢትዮጵያዊ ምሁር አስተሳሰብ እኔ ከሌላው ኢትዮጵያዊ እሻላለሁ በሚለው የሚመራ እንጂ ጉልበታችንን ብናጣምር ሁለታችንም ተጠቃሚ እንሆናለን ለማለት ስለማይችል ነው። ድርጅቱ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ያየሁት ነገር ኢትዮጵያውያን በጣም የተክፋፈሉና በብዙዎቹ መካከል ኢትዮጵያ አለመኖሯን ነው።

በአንጻሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስሙን ለሚያስጠሩ ልጆቹ ከፍተኛ ከበሬታ አለው። አስታውሳለሁ፡ አምባሳደር ይልማ ታደስ የአፍሪቃ ኅብረት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር ሆንው ከተመረጡ በኋላ መንገድ ላይ በፈጋገታ መጥቶ ስላም ይል የነበረው ዚጋ ብዛትና የጋለ ስሚት ለየት ያለ ሥዕል ይሥላል።

ለማንኛውም ሕወሃት አዲስ አበባ ሲገባ መጀመሪያ የጻፈው ደብዳቤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አቶ ይልማ ታደስ በኢትዮጵያ ስም በዚያ ማዕረግ እንዳይቀመጡ፤ ኢትዮጵያም ቦታውን እንድማትፈልግው ነበር። ወዲያው ያ ሃላፊነት ለሶማልያ ተላለፈ። ያንን መራር (drastic) እርምጃ ለመውሰድ የሕወሃት ምክንያት አቶ ይልማ ሱዳን አምባሳደር ሆነው ሕወሃትን ሱዳን ውስጥ መፈናፈኛ በማሳጥታችው ነበር ይባላል።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ፤ ሕወሃት የቂም በቀል ስሜቱ ጋብ ሲልለትና በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ታላቅ ጉዳት ክተፈጸም በኋላ፤ ያ ስህተት አዲስ በመሆናችን የተፈጸመ ነው በማለት አቶ መለስ ዜናዊ መናግራችው ተስምቶ ነበር።

ታዲያ የዛሬዎቹስ ስህተቶች በምን ምክንያት የተፈጠሩ ይሆን?

*ከፍያለው ገብረመድኅን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በዲፕሎማትነና ኢንተርናሽናል ስታፍ በመሆን ኒውዮርክና ጀኔቫ የሠራ ሲሆን፡ በአሁኑ ወቅት በጡረታ ላይ ሆኖ ጊዜውን በኢትዮጵያ የልማትና የድኅነት ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር በማካሂድ፡ TE – Transforming Ethiopia በተባለው ድኅረግጽ ሃሳቡን ለአንባብያን ያካፍላል።

TE – Transforming Ethiopia

<span>%d</span> bloggers like this: