ለመውደቅ ያጋደሉ አገሮች ኢንዴክስ ኢትዮጵያ ጥንቃቄ እንድታደርግ ከወዲሁ ምክሩን ይለግሳል

25 Jun

Failed states map

በከፍያለው ገብረመድኅን Posted by The Ethiopia Observatory

THE FUND FOR PEACE (FFP) በመባል የሚታወቀው ድርጅት የዓለም አገሮችን ይዞታ እየገመገመ በየዓመቱ ሪፖርት ያቀርባል። በሰኔ 2012 ባወጣው ዝገባ ላይ ትችት ማቅረቤን አስታውሳለሁ (https://ethiopiaobservatory.com/2012/06/19/the-2012-failed-states-index-released-ethiopias-ranking-reflects-deterioration/)። ለማንኛውም ድርጅቱ ያወጣው ዘገባ፡ የጻፈው ትችት ብዙ የሚያወዛግቡ ጉዳዮች ቢኖሩትም፡ ዋናው ቁም ነገር ስህተቱን መፈለጉ ላይ ሳይሆን፡ ከጠቃሚነቱ በመነሳት ራስን ለማሻሻል የሚድረግ ማናቸውም ጥረት የበለጠ ዋጋ ይኖረዋል።

ኢትዮያጵያን ለመውደቅ ካጋደሉ (failed states / failing states): አገሮች መካከል መጨመሯ – ለመጀመሪያ ጊዜ ባይሆንም – አሁንም ብዙዎችን ሳይስገርም አይቀርም። በድርጅቱ የ2013 መለኪያ መሠረትም ኢትዮጵያ ልዩ ትኩረትና ክትትል ከሚያስፈልጋቸው (Alert) አገሮች መካካል በ19ኛ ድረጃ ላይ ተመድባለች፡፡

ድርጅቱ የ177 አግሮችን ሁኔታ የተከታተለ ሲሆን፡ ልዩ ክትትል ከሚያስፈልጋቸው አገሮች መካከል ሶማልያ፡ ኮንጎ (ዲ.ሪ.)፡ ሱዳን፡ ደቡብ ሱዳን፡ የመንና አፍጋኒስታን፣ ሄይቲ፡ መካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክና ዚምባብዌ ከአንድ እስክ አሥር ያለውን ሥፍራ ይዘዋል። ለነገሩ በምደባ ደረጃ (ranking) ኢትዮጵያ ብዙ ለውጥ አይታይባትም (ከአገሮች ደረጃ መቀያየር ውጭ)።

ከዚያ ውጭ፡ ኢትዮያጵያ በተለይም የከፋ አደጋ ላይ ካሉት አገሮች በ19ኛ ደረጃ ላይ፡ ከዚያ በመለስ ባለደረጃ ደግሞ 15ኛ ላይና የጥንቃቄ ማስጠንቀቂያ ከተስጣቸው በ3ኛ ድረጃ ላይ መገኝቷ ሁኔታዋን አሳሳቢ ያድረገዋል። በዘንድሮው ጥናትና ምደባ መሠረት፡ የኢትዮጵያ መረጋጋት ከቡሩንዲ፣ ሶሪያ፣ ላይቤሪያና ኢርትራ አንሶ መገኘቱ የኢትዮጵያ የወደፊት፡ የሰላም፡ የደህንነትና የልማት ግሥጋሴ ችግሮች ከፊቷ መሆኑን ዳታዎቹ ይጠቁማሉ።

የዘንድሮው ውጤት ካለፈው ዓመት የድርጅቱ ጥናት፡ ትንተናና አመለካክት ጋር ሲነጻጸር፡ የኢትዮጵያ ሁኔታ፡ በነጥብ ደረጃ በ2012 ከነበረችበት ከ97.9 ወደ 98.9 አሽቆልቁሎ ይታያል። ለዚህም ምክንያቶቹ የአገሪቱ አመራርና አስተዳደር ሁኔታ በአንድ ሙሉ የመለኪያ ነጥብ ዝቅ ብሎ በመገኝተቱ ነው። እነዚህ ማዘቅዘቅ የታየባቸው ሁኒታዎች የሚከተሉት ሲሆኑ፤ በቅንፍ ውስጥ የተካተቱ ቁጥሮች የቅነሳውንና የመሻሻሉን መጠን እንደሚከተለው ያመለክታሉ።፡

  የሕዝብ ቁጥር ብዛት ያስከተለው ግፊትና ውጥረት (-0.1)

  የስድተኞች ብዛትና መፈናቀሎች (0.0)

  የቡድን ቂም በቀላዊ የወንጀል ሁኒታዎች መባባስ (-0.5)

  አስከፊ ሰብዓዊ ጫናና የሕዝብ ሽሽት (-0.1)

  ያልተመጣጠነ የኤኮኖሚ ዕድገት (0.3)

  የድህነት መባባስና የኤኮኖሚ ሁኒታ ማሽቆልቆል (-0.2)

  የሕዝብ አመኔታ በመንግሥት ሕጋዊነት ላይ በብዛት መቀነሱ (-0.1)

  የአገግልሎት ሁኒታ ሳይገታ ማሽቆልቆል (-0.3)

  የስበዓዊ መብቶች ረገጣው መባባሱ (-0.1)

  የድኅንነት ሥጋት መባባስ (-0.3)

  የተከፋፈሉ ቡድኖች መጠናከር (0.0)

  ከውጭ የተቃጣ አደጋ (0.1)

The Fund for Peace የኢትዮጵያ የመውደቅ አዝማሚያ ላይ በመሥራት ብቸኛው ድርጅት አይደለም። ለምሳሌም ያህል በየመስካቸው – የሰላም ኢንዴክስ፤ የረሀብ ኢንዴክስ፤ የሕዝብ ብዛት ሁኒታና ችግሮች፡ የነጻነት ኢንዴክስ ወዘተ፡ የየራሳቸውን በየጊዜው ሲያወጡ ኖረዋል። የFFP ከሞላ ጎደል ሁሉንም ለማንጸባረቅ የሞከረ ነው።

በተለያዩ ጊዜዎች ስለኢትዮጵያ የሚድረጉ ጥናቶችን ለተከታተለ፡ መንግሥት ራሱ የሚሰጣችየውን መግለጫዎችን ላዳመጠ፡ ሌላው ቀርቶ ሪፖርተርና አዲስ ፎርቹን በኢትዮጵያ ላይ በየጊዜው የሚጽፏቸው ላይ ላተኮረ ማንኛውም ግለስብ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁኒታዎች – መባባስ ወይንም መሻሻል – አዲስ ሆነው አይታዩም።

ኢትዮጵያ ለመወድቅ ከሚውተረተሩት አገሮች መካከል መሆኗን፤ የአሜሪካ መንግሥትም በየአምስት ዓመታት አንድ ጊዜ በሚያወጣው ትንበያ (Intelligence Assessment) ላይም ይኽው ተመልክቷል ። ለምሳሌ በ2012 ያወጣው ትንበያ በሁኒታዎች ሲታይ፡ ኢትዮጵያ፡ ግብጽና ናይጄርይ በ2030 የደቡብ አፍሪቃ ዕድገትን ለመቃረብ ወይንም ለማለፍ ዕድሉ አላቸው ይላል። ሆኖም ወሳኙ እነዚህ አገሮች እንዴት እንድሚተዳደሩ፡ የሰው ሃይላቸውን ምን ያህል እንደሚያዳብሩና በኤኮኖሚያቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ፖሊስ ለመቅረጽና ተግባራዊ ለማድረግ መቻላቸው ነው ይላል (but the key will be better governance to further economic growth and social and human development)።

እንደዚህ ትንበያ ከሆነ በ2008 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ለመውደቅ ካጋደሉ አገሮች በ10ኛ ደረጃ ላይ ነበረች። በ2030 ግን ኢትዮጵያን በ14ኛ ደረጃ ያሰቀምጣታል- ከቻድና ሄይቲ በፊት ።

ያም ጥናት ይፋ ከመድረጉ በፊት ኢትዮጵና የሚመለከታቸው አገሮች ሁሉ ሴሚናር ተዘጋጅቶ እንዲይውቁት መደረጉን ሪፖርቱ ይገልጻል።

ስለሆነም፡ FFP ያቀረበውን በደፈናው ከመርገጥና ከመራገም ይልቅ፡ ቆም ብሎ ማስብና ምን ብናደርግ አገራችንና ሕዝባችን ከአደጋ መከላከል እንችላለን ብሎ ማስቡ ጠቃሚ ይሆናል።

ለሥልጣኑ ብቻ ለሚራብ መንግሥት፡ ይህ ጥናት ሆነ ሌሎቹም ወደመሻሻል ጎዳና እንደሚውስደው ተድርገው ከመውስድ ይልቅ እንደጠላትነት ስለሚታዩ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሻሻል የሚኖራቸው ጠቀሜታ አጠራጣሪ ነው።

map of 2012 failed states At-risk countries listed in the Global Trends report by the USthe National Intelligence Council.

Read also:

Report: 15 Countries at Risk of Becoming Failed States

%d bloggers like this: