በዕጦቶችና የሥልጣን ብልግና የተፈጠረው የኢትዮጵያ ምሬቶች የዛሬው ሥዕልና የነገው ሥጋት*

1 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory

ethiopiaኢትዮጵያ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉት 48 ድሃ አግሮች (LEAST DEVELOPED COUNTRIES – LDCs) አንዷ ስትሆን፡ በብዙ መልክ የኢትዮጵያውያን ድህነትና ዕጦቶች ከሌሎቹ በከፋ መልክ እጅግ ግዙፍና አስፈሪ ናቸው። በመሆኑም፡ በብዙ ዓለም አቀፍ የሕዝብ ደህንነት መለኪያዎች፡ ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ አራተኛና አምስተኛ ደርጃ ላይ ትገኛለች። ዋናው መታየት ያለበት ጉዳይ ደግማ፡ የኢትዮጵያውያን ድህነት፡ ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊና በተለይም ነጻነትን ሙሉ በሙሉ ከመገፈፍ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ነው።

ዛሬ እጅግ ታዋቂና ጠቃሚ በሆነው የተባበሩ መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) የሰው ልጆችን የኑሮ ደረጃና ሁኒታ መሻሻል መለኪያ (Human Development Index) መሰረት፡ በ2013 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ከ186 አገሮች ውስጥ በ173ኛ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ተገኝታለች። ይህም የድህነቷን ጥልቅነት በሚገባ አመላካች ነው።

ስለዚህ ጉዳይ መጋቢት 15፣ 2013 በጻፍኩት ንባብ ላይ እንዳስረዳሁት፡ ዋናው ቁም ነገር፡ ከአገሮች ጋር የሚያወዳድረው የደረጃ ቁጥር ሳይሆን፡ ጠቃሚዎቹ ነገሮች ሶስት ናቸው፡

  (ሀ) የሕዝቡ ጤናማና ረዥም ዕድሜ ለመድረስ መቻል፡

  (ለ) በትምህርት መሻሻል፡ እና

  (ሐ) የተሻሻለ ገቢ ማግኘት ናቸው።

ያለፉት ዓመታት የኢኮኖማ ዕድገት ክፍተኛ በር ከፋች ተደርጎ ቢታይም፡ ተጠቃሚዎቹ ጥቂቶች በመሆናቸው፡ የሕዝቡ ኑሮ አልተሻሻለም። ለዚህም ነው፡ በእነዚህ መለኪያዎች ኢትዮጵያ የዓለም ጭራ ከሆኑት ሃገሮች ጎን ተስልፋ የምትገኝው፡

በታሪክም ሆነ በልምድ የሚታወቀው የመንግሥት የሥራ ድርሻ ለሕዝብ አገልግልቶችን ማቅረብ፡ ደህንነትን ማረጥጋገጥና አገርን መወከል ቀዳሚ ተግብሮቹ ሲሆኑ፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት በጥቂቶች የተያዘ፡ ለሕዝብ ጥቅም ያልቆመ፡ መላውን አገሪቱን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለመወከል የአይዲኦሎጅና የፖለቲካ ችግር ያለበት፡ ከቅኝ ገዥ የክፋ ቡድን በመሆኑ እነዚህን አገልግሎቶች ለሕዝብ ማቅረብ አልቻለም። ይህም ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባስ መጥቷል።

ፖለቲካው የዚህ ዐይነት ችግሮች ሲኖሩት፡ ሕዝብ መብቱን ተገፎ፡ ሥልጣን ላይ ያሉ ግልስቦች፡ ሥልጣንና ኅይልን ተገን በማድረግ ከዕለት ዕለት በሚያደርሱት ሥነ ልቦናዊ ጉዳት፡ ኤኮኖሚውም እንደሚገባው መሥራትና የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል አልቻለም። ጥቅሙ በሚገባ ያልተከፋፈለ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለበት ሁኒታ – ማለትም እንደ ኢትዮጵያ – መንግሥት የሚጠበቅበትን አገልግሎቶች እንኳ ለሕዝቡ ማቅረብ ወደማይችልበት ድረጃ ተደርሷል። ይህ ግልጽ የሚሆነው በተለይም ኢትዮጵያ በዓመት ከአራት እስክ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ መንግሥታትና ድርጅቶች ድጎማ እየተሰጣት፡ ዲያስፓራው እስክ አራት ቢሊዮን ዶላር ለየዘመድ አዝማዱ በውጭ ምንዛሪ በሚልክበት ወቅት፡ መንግሥት የአገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከማበላሸቱም ባሻገር፡ ሕዝቡ በድህነት እይተንቆራፈተ ንብረቱን ዘርፎ ባለቤት የሌለው ይመስል፡ ለመሪዎቹና የቡድኑ አባላት ማድለቢያ አድርጎታል።

ገና ስጀመር፡ የኢትዮጵያን ሁኒታ አስፈሪ ያልኩበት ምክንያት፡ ይህንን ማስወገዱ የሚጠይቀው መሥዋዕትነት ከባድ በመሆኑና፡ ለአገራችንም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ያለውን ጎጂነት በማስብ ነው። የችግሩ ምንጭ ሕዝቡ በፖሊሲ ደደብነት መታሰሩ፡ በፍርህትና ስጋት ውስጥ መያዙ፡ ጥቂቶች መንግሥትን በመቆጣጠራቸው፡ ዘረፋዎች በማካሄዳቸው፡ና ሕዝቡ በነጻነት በዲምክራሲያዊ አስራር ሕይወቱን ለመግንባትና ለመምራት እንዳይችል ተደርጓል።

በእነዚህም ምክንያቶች፡ የኢትዮጵያውያን ችግሮች በቀላሉ ይቀረፋሉ ብሎ ማመን፡ ያለፈውን 22 ዓመታት በሚገባ አለማጣጣም ከመሆኑም ባሻገር፡ “ከዚሀ የባስ አታምጣ” በሚለው ሕዝባችን ከተተበተበት ኋላቀር አስማት ስብሮ ለመውጣት አለመቻሉ ነው። ዕድገት አልነበረም ለማለት አይደለም። እንዲያውም በተከስተው ጥሩ ህኔታ በመጠቀም፡ ኢትዮጵያ የተሻለ ሁኔታ ላይ ልትደርስ በቻለች ነበር።

ገዥው ቡድን ግን ይሀንን ወድጎን በመግፋት፡ በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ ብቻ በዕድገት እንደገስገስች አድርጎ ለማቅረብ ሲቃጣው በተደጋጋሚ ተደምጧል። ይህ እነርሱ ሲፈልጉ የ Ehiopian Exceptionalism፡ አለያም የመለስ ወይንም የሕወሃት ሲሻቸው ደግሞ የትግሪዎች ብልህነት ምን እንዳስረከበን ከላይ የጠቀስኩት የUNDP ዳታ የሰጠውን ምስክርነት፡ የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶችና እሥር ቤቶች በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ እየፈጸሟቸው ያሉትን እንያለን። በተጭባጭ ደግም የንጋናን፡ ሴኔጋልን ዲሞክራሲ፡ የኬንያና የታንዛንያን የኤኮኖሚ ግንባታና የሕዝቦቻቸውን አንጻራዊ ነጻነት ዞር ብሎ ማስታወሱ ይጠቅማል።

የዕለት ተዕለት በሆኑት ችግሮች ዓይን አገሪቱ ውስጥ ያሉት የዜና ምንጮች (የዜና ምንጮች ካልናቸው) ከተረኩት አንኳ ተነስተን ብንመለከት፡ መሪው ፓርቲና መንግሥት በዘጠነኛው የባህር ዳር ጉባዔያቸ እንደተናዘዙት ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የመልካም አስተዳደር (good governance) እጦት ዋና ዋና የህገሪቱ ተራራማ ቸግሮች ናቸው። እነዚህም የችግር ዐይነቶችና መገለጫዎች የሚከተሉት ናቸው፡

  (ሀ) መንግሥት ሊያቀርብ የሚገባችው (ዋና ኢንቬስተር እነደመሆኑ) አግልግሎቶች ለሕዝብ በሚገባ ለማቅረብ አለመቻሉ – ለምሳሌ መብራት፡ ዉሃ፡ ስልክ፡ ኢንተርኔት፡ ስኳር፡ ምግብ፡ እና

  (ለ) መንግስት ዲክታቶርያል በመሆኑ፡ የሕዝቡን ስብዓዊ መብቶችን ገፎ፡ ሕዝቡን በእሥራት፡ ድብደባና ግርፋት በማሰቃየትና አገሪቱ በሕግ የሚተዳደር አስተዳደር የሌለባት ማድረጉ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በአጭር አባባል፡ ዛሬ አገራችን የምንመኝላት ሁኒታ ላይ ካለመሆኗም ባሻገር፡ ከፊት ለፊቷ የተጋረጡት የተወሳሰቡ ችግሮች እጅግ አሸማቃቂ ናቸው። ይህ መንግሥት ለዛሬ የሚበጀውንና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለውን ብቻ የሚያደርግ በመሆኑ፡ ገና ብዙ ችግሮችን ይፈጥራል፤ ክህደቶችን በአገራችን ላይ ይፈጽማል።

መዝንጋት የሌለበት ነገር፡ ገና ከማለዳው የሕወሃት መንግሥት ከኢሳይያስ አፈውርቂ ጋር ተስማምቶ ለራሱ በገዥነነት ለመኖር ሲል፡ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ያደረገ ከሃዲና አደፍራሽ ነው። ዛሬ የኤክኖሚ ችጎርች ቁንጥጫ ሲበዛበት፡ ለጎረቤት አገሮች ንዋያችንን በማፍስስ ለኢትዮጵያ ግንባር ቀደሙ የባህር በር ፈላጊ ሆናአል አዲስ ግንባታ በጂቡቲና ላሙ (ኪንያ)። ይህ ስህተቱ የመጨረሻ ነው ብላችሁ የገመታችሁ መሳሳታችሁን በ2008/9 እንደገና አሳየ። ለመቶ አንድ ዓመታት ውዝግብ ያለበትን የኢትዮጵያን መሬት ለሰሱዳን አሳልፎ ሰጠ – ሱዳን መሬቷን ለተቃዋሚዎች መጠቀሚያ በማድረግ፡ የአገዛዝ ዘመኑን አንዳታሳጥር ነው የዚህ ገጸ በረከት ዓላማ።

አንድ ሌላ ምሳሌ ልጥቀስ፡ የእርሻ ምርት የገበሬውን ምርት የኢትዮዽያ የእህል ንግድ ድርጅት በየወቅቱ ከየቀበሌው እያሰባሰበ፡ ረሃብ ባለበት ወቅት እንኳ ወደውጭ ሲሽጥ ከርሟል። የውጭ ምንዛሪው በየአግጣጫው ከመፍሰሱም ባሻገር፡ የክተማው ሕዝብ እንዳያምጽ፡ ገና ከመጀመሪያው ስንዴ፡ ዘይት፡ ስኳር. ወዘተ፡ እየተገዛ እስከዛሬ ሲቀለብ መኖሩን ለውጭ ክበርቴዎች ለም መሬቶቻችን በማከፋፍለ ችግሩን ያለፈ መስሎት ያንን ለአሥር ዓመታት ያህል የተጠቀመበትን የፖሊሲ ሽፍጠቱንና (ከተእጭባጭ ኤኮኖሚ ልማት ይልቅ) ዘዴ ሳያስበው መለስ ዜናዊ ለFinancial Times ነሐሴ 27፣ 2008 ዓ.ም. በራሱ አነሳሽነት እንዲህ ሲል አጋልጧል።

  “The fact is that those who did not face the challenge of the pastoralists, those who did produce have benefitted enormously. So the way to help the urban poor [which is the majority of the population] is for us, for example, to use the foreign exchange earned by the farmers to buy wheat and we are doing this. We have already bought about 150,000 tonnes of wheat in Europe and we are distributing it through the market. We completed a contract for another 150,000 tonnes of wheat and that will help us dampen the prices in the urban areas and that’s the way it should be.”

ይህ ቪዥንና ችሎታ የሌለው መንግሥት በተከተላቸው ፖሊሲዎች ምክንያት የዋጋ ግሽበት አገሪቱንና ሕዝቦቿን ተስፋ ሲነሷችው (ችግሩን ሲክድ ከርሞ)፡ መጨረሻ ላይ ዋጋ ግሽበት የዕድገት ምልክት ነው ብሎ ቁጭ አለ፡፡ ችግሩ ሲክፈበት ደግም ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኩብንያዎች እንድ እነ ዎልማርት መጥተው የማከፋፈል ሥራ እንዲሰራ ተስማማ። በ 2012 ስምምነቱን ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሆነው፡ ዎልማርት ኢትዮጵያዊ ምርቶች – የግብርና ውጤቶችን ጨምሮ በእርሱ መደብሮች ውስጥ እንደማይሸጡ ካረጋገጠ በኋላ ነው። ዋናው ምክንያቱ ከድነበኞቻቸው በርካሽ ማምጣት ሲሆን፡ ዎልማርት ለለኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች የሰጠው መለዕክት የሚረባ ኳሊቲ አለመኖሩ ነው።

የሀግራችንን ምርት ውጥቶች ምን እናድርጋቸው? እነርሱ ከውጭ የግብርና ምርቶች ጭምር ሲያስመጡ፡ ገበሬዎቻችን ላይ የሞት ቅጣት አይደለምን? ከዚያ በቂ ትምህርት ያልወሰደው የሕወሃት መንግሥት፡ አሁንም 150 እንደነዎልማርት፣ ጄነራል ሞተርስ ኮርፖሬሽን፣ ጄኔራል ኤሌክትሪክ ያሉትን ታላላቅ የአሜሪካ ኩባንያዎችና ትልቅ ስብዕና ያላቸው ወድ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከነሐሴ 12-13፣ 2013 ዓ.ም. በሚካሂደው በአጎዋ ጉባዔ ላይ እንዲገኙ መጋበዙን ሪፖርተር ዘግቧል

ይህ የሕወሃት መንግሥት በሕዝብ ጥላቻ የተወጠረ፡ ኢኮኖሚውና ፖለቲካው የከስረ በመሆኑ፡ አሁንም አገራችንን በሃራጅ ሽያጭ ሊያቀርባት እንደሚችል፡ ለአፍታ እንኳ ጥርጥር ሊኖር አይገባም።

እነዚህን ቀደም ሲል ከላይ የተዘረሩትን የመጥፎ አስተዳደር ምልክቶችንና ሁኒታዎች እንዴት በራሱ በሕወሃትና ሌሎች አገሪቱ ውስጥ ባሉ ሕዝብ መግናኛ አውታሮች – ፈራ ተባ ቢሉም – እንደዘገቧቸው ከሚክተሎት ጥቂት ምሳሌዎች መመልከት ይቻላል።

መታወስ ያለበት ግን፡ እነዚህ ችግሮች በአንድ ጀምበር የተፈጠሩ አይደሉም። ክላይ እንደጠቅስኩት ፈርጠም ያለ የፖለቲካ፡ የአይዲኦልጂና መነሻ፡ በሥልጣን ጣዕምና ስካር ምክንያት: ቢፍልጉ እንኳ በያዙት ጠባብ አስተሳስብ መንስኤነት፡ ፖለቲካዊ አኤኮኖሚው ተቀናጅቶ ሊያውጠነጥን አልቻለም።

ጥያቄው፡ ያ ሁሉ ገንዘብ ከ2000 እስክ 2009 ወደ ሃገሪቱ እየፈሰሰ፡ – የዓለም ባንክ ዳታ እንደሚያሳየው – በዓለም ላይ ከአፍጋኒስታን ቀጥሎ በሁለተኛነት (ከኋላ ቀር አገሮች) – ኢትዮጵያ ለምን ከጊዜ ወደጊዘ ወደ ማዝቀጥ እያጋደለች ያለችው?

=======================================================
 

       (ሀ) የአገልግሎቶች መጥፋት ወይንም አለመሟላት
 

   

  በአዲስ አበባ የዲጂታል የንግድ ምዝገባና እድሳት የአሰራር ስርዓት ችግር ገጥሞታል

  Internet networkአዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24፣2005(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አዲሱ የንግድ ምዝገባና እድሳት የአሰራር ስርዓት ችግር ገጥሞታል። የኔት ወርክ ችግር የንግድ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ በየወረዳዎች የሚስተናገዱ ነጋዴዎችን ለቀናት እያመላለሰ ነው።

  የይዞታ መራጋገጫ ካርታ ማቅረብ ያልቻሉ ነጋዴዎች ደግሞ የንግድ ፈቃድ ለማውጣትም ሆነ ለማሳደስ እንደተቸገሩ ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፁት። የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ማስተካከል የአዲሱ የንግድ ማሻሻያ ዋነኛ ጉዳይ ሲሆን ፥ ስርዓቱን ለማስተካከልም ከሃምሌ አንድ ቀን 2005 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

  በአዲስ አበባ ከ116 ወረዳዎች 114ቱ ዘመናዊ የንግድ የመረጃ ስርዓትን ለመዘርጋት መሰረተ ልማት እንደተሟላላቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።

  የአገልግሎት አሰጣጡ በቀጥታ ወይም በኢንተርኔት/online የምዝገባ ስርዓት የንግድ ፈቃድ ምዝገባም ሆነ እድሳት ለማከናወን ያስችላል። በሂደትም ነጋዴዎች ወደ ቢሮዎች መሄድ ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው የፈለጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው ስርዓት ቢሆንም ይሄ ስርዓት ግን ችግር እንዳጋጠመው አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ተናግረዋል።

  የኔትወርክ ችግር ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ይላሉ ሰራተኞቹ ። ይህም የንግድ ፍቃዳቸውን ለማሳደስ በመጡ ነጋዴዎች ላይ መጉላላትን ፈጥሯል።

  በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ የአሰራር ስርዓቱን እንደ ቀድሞ በማንዋል እየተሰራ ይገኛል። የእድሳት ክፍያ የፈፀሙ ነጋዴዎችም የንግድ ፈቃዳቸውን እዛው ወረዳዎች ላይ እያስቀመጡ ደረሰኝ ተቀብለው የሚሄዱ ሲሆን ፥ የኔት ወርክ ችግሩ ሲፈታ ዳግም በስልክ ተጠርተው የንግድ ፈቃድ እድሳታቸውን በኦን ላይን ከፈፀሙ በኋላ የንግድ ፈቃዳቸውን እንደሚወስዱ ተነግሯቸዋል።

  የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሽሰማ ገብረ ስላሴ ችግሩ መኖሩን አምነዋል። በተለይም በንፋስ ስልክ ፣ ኮልፌ ፣ ቂርቆስ ፣ ቦሌ ፣ አቃቂ ቃሊቲና አራዳ ክፍለ ከተሞች ላይ የኔት ወርክ ችግር ጎልቶ የሚታይባቸው ናቸው።

  እንደ አቶ ሽሰማ ገለፃ ችግሩን ለመፍታት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ጥረት እንደሚደረግ ተናግረው የማይፈታ ከሆነ ግን በእጅ ወደ ተደገፈ አሰራር የምንመለስ ይሆናል ይላሉ።

  =======================================================
   

  በአዲስ አበባ በኤሌክትሪክ እጥረት ከ18 በላይ ጤና ጣቢያዎች ያለ ስራ ተቀምጠዋል

  አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ግንባታቸው ተጠናቆ እና መሰረታዊ ግብዓቶች ተሟልቶላቸው በኤሌክትሪክ እጥረት ብቻ ከ18 በላይ ጤና ጣቢያዎች ያለ ስራ መቀመጣቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

  የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ጤና ጣብያዎችን በአስሩም ክፍለ ከተሞች በተለያዩ ጊዜያት ሲያስገነባ ቆይቷል። ግንባታቸውን ጨርሰው የኤሌክትሪክ መስመር ካልተዘረጋላቸው በተጨማሪ ፥ ተመጣጣኝ እና በቂ የሆነ የኤሌከትሪክ ሃይል የሌላቸው በመሆኑ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ያልቻሉም አሉ ።

  በቢሮው የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ የስራ ሂደት መሪ አቶ እሸቱ አድነው 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ለኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ክፍያ በመፈጸም ከሃላፊዎቹ ጋር ብንነጋገርም መፍትሄ አላገኝንም ነው የሚሉት።

  በኤሌክትሪክ ሃይል እንዲጸዱ የሚደረጉ መሳርያዎች በሃይል እጥረት ምክንያት እንደተፈለገው መጠቀም ባለመቻሉመ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። ወደ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ያድጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የኮተቤ ጤና ጣብያን ጨምሮ በርካታ የጤና ተቋማት በተፈጠረው ችግር ምክንያት ፥ በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ አለመሆኑን የዚህ ዜና አዘጋጅ ባደረገችው ቅኝት ለመታዘብ ችላለች።

  በተቋማቱ የሚሰሩ ባለሙያዎች እንደሚሉት ፥ በማቀዝቀዣ ውስጥ የሚቀመጡ መድሃኒቶች በሃይል እጥረቱ ምክንያት እንደሚበላሹና በዚህም በማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ ያለባቸው መድሃኒቶች ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዘዋወር ለማስቀመጥ ተገደዋል።

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በበኩሉ ፥ በርካታ የአዳዲስ መስመር ዝርጋታና የቆጣሪ ተከላ ጥያቄ ስለሚቀርብ ያለውን አነስተኛ የግብአት አቅርቦት ቀስ በቀስ ለሁሉም ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት መጓተቶች ተፈጥረዋል ይላል።

  በኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግ ሽያጭ ስራ ሃላፊ አቶ ግርማ ለማ እንደሚሉት ፥ ትራንስፎርመሮች ገብቶላቸው የማገናኘት ስራውን ለማከናወን ለማገናኘት የሚጠቀሙ ገመዶች የግዥ ሂደት ረዥም በመሆኑ ስራዎችን ለማፋጠን ሲባል ደንበኞች ቀድመው እራሳቸው እንዲገዙ የሚደረግ በመሆኑ በዚህ በኩል ችግሮች መፈጠራቸውን ተናግረዋል።

  በኮርፖሬሽኑ በኩል የሚታየውን የግብአት አጥረትም የፈጠረውን የስራ መጓተት ለመቅረፍ ኮንቦልቻ ከሚገኘው ማከማቻ እቃዎችን በማምጣት እስከ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የጤና ተቋማቱ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ነው አቶ ግርማ የገለጹት ።

  =======================================================
   

  የኔትዎርክ መቆራረጥ ችግር አሁንም ሊፈታ አልቻለም

  mobile interruptionsአዲስ አበባ፣ ሃምሌ 17፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን እያጋጠመ ላለው የሞባይል ስልክ መቆራረጥ ችግር አንዳንድ ባለሙያዎች ከመሳሪያ ጥራት ጋር የተያያዘ መሆኑን ያነሳሉ ። የኔትዎርክ መቆራረጥ ችግር እንዳማረራቸው የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

  ከኢትዮ ቴሌኮም የሚሰጡ ምላሾች ግን አሁንም ተደጋጋሚ የሆነ የፋይበር ኦፕቲክ መቆራረጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው።

  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ያለምዘውድ ነጋሽ ፥ የችግሩ ምንጭ አሁን ካለው የስልክ ተጠቃሚ ብዛት አኳያ በየቦታው የተቀመጡት ካርዶች የኔት ወርክ አቅማቸው ደካማ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ።

  ከዚህ ባሻገርም የቴሌኮም መስመር ዝርጋታው ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት መሳሪያዎች ጥራታቸው አስተማማኝ አይደለም ይላሉ። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያናገራቸው ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንዳንድ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች እንደሚሉት ፥ የመሳሪያ ግዥ ሲፈፀም ጥራታቸውን ያልጠበቁ ኬብሎች ጭምር ይገዛሉ ።

  የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ከኔትወርክ አቅም ጋር ተያይዞ ደካማ ነው የሚባለውን ይቀበላሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አሁን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚው ቁጥር ከተገመተው በላይ ቀድሞ ከነበረው ጨምሮ 22 ሚሊዮን መድረሱን ያነሳሉ።

  ለመስመር ዝርጋታ እንዲውሉ ተብለው በሚገዙ መሳሪያዎች ጥራት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ጠቅሰው ፥ ግዥው የሚፈፀመው በኢትዮ ቴሌኮም ሳይሆን ዝርጋታውን ለማከናወን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ውል የገባው ኩባንያ መሆኑን ተናግረዋል።

  ኩባንያው የመስመር ዝርጋታውን እንዳጠናቀቀ ምን ያህል ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መዘርጋት አለመዘርጋቱም በካናዳ ኩባንያ አማካኝነት መረጋገጡን ነው የሚናገሩት። ይሁን እንጅ በተለይ በአዲስ አበባ የሚገነቡት ህንፃዎች እየተበራከቱ መሄዳቸው የራዲዮ ሞገድ እንደልብ ተንቀሳቅሶ አገልግሎቱን በተሟላ መልኩ ለማስቀጠል አልተቻለም ባይ ናቸው።

  ይህን ለማቃለልም አሁን አንቴናዎችን በህንፃዎች ላይ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። አቶ አብዱራሂም እንደሚሉት አሁን የሚታየውን ችግር ለመፍታት በዘላቂነት ማስፋፊያ ማድረግ ብቻ በመሆኑ ፥ እሱን ለማድረግ ተቋማቸው ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል።

  ========================================================
   

  The unresolved water problem of Addis (ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  We are used to not having water for a day or even a couple of days in our houses; it is common and has been happening for a really long time. Though a couple of days are nothing, Addis Ababa has started to see worsening water problems in recent years. Now, it seems that going through an entire week without water has become common in a number of areas in the city.
  This problem has created chaos for a significant portion of the populace. Carrying plastic containers and traveling to other areas, then lining up for hours to get those containers filled with water and go back home, is an everyday occurrence.

  ========================================================
   

  ለገርቢ ግድብ የውጭ ብድር በመጥፋቱ የአዲስ አበባ አስተዳደር በራሱ ወጪ ለመገንባት ወሰነ ገንዘቡ ከየት ይመጣል? ምንስ ሲሰሩ ከረሙ?

  drinking waterየአዲስ አበባ ከተማ የውኃ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ተስፋ ለተጣለባቸው ሲቪሉና ገርቢ ወንዞች ከውጭ ብድር ማግኘት ባለመቻሉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከራሱ ግምጃ ቤት ወጪ በማድረግ በገርቢ ወንዝ ላይ ግንባታ ለማስጀመር ውሳኔ አሳለፈ፡፡

  በሁለቱ ወንዞች ላይ ግድብና የውኃ ማጣሪያ ጣቢያ ለመገንባት የተወጠነው ከ20 ዓመት በፊት ቢሆንም፣ የሚፈለገው ገንዘቡ ከፍተኛ በመሆኑ ከውጭ አገር ፋይናንስ ሲፈለግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ለፕሮጀክቶቹ ከውጭ ፋይናንስ ማግኘት ባለመቻሉ የአዲስ አበባ አስተዳደር በአንዱ ወንዝ ላይ ብቻ ግንባታውን ለማስጀመር ወስኗል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የከተማ አስተዳደሩ በገርቢ ወንዝ ላይ ብቻ ፕሮጀክቱ የሚያስጀምረው በፋይናንስ አቅርቦት እጦት ነው፡፡ ምክንያቱም በሁለቱም ወንዞች ላይ ግንባታ ቢካሄድ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑ ነው፡፡

  በሁለቱም ወንዞች የግድብ ግንባታ ለማካሄድ ስምንት ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ ይህን ገንዘብ አስተዳደሩ መመደብ የማይችል በመሆኑ በገርቢ ወንዝ ላይ ብቻ ግድቡን ማስጀመር ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

  በሁለቱ ወንዞች ላይ ከዚህ ቀደም በርካታ የአዋጭነት ጥናቶች ቢሠሩም፣ ግንባታው ሳይካሄድ በመቆየቱ ጥናቶቹ ጥቅም ላይ አልዋሉም፡፡ የከተማው የውኃ እጥረት ከፍተኛ እየሆነ የሚሄድ መሆኑን አስተዳዳሩ ተገንዝቦ የግድቡ ግንባታ እንዲካሄድ በመወሰኑ የአዋጭነት ጥናቱ እንደ አዲስ ተካሂዷል፡፡

  የአዋጭነት ጥናቱን ያካሄደው የህንዱ ኩባንያ ሶሬካ ጥናቱን ለባለሥልጣኑ አስረክቧል፡፡ በዚህ የአዋጭነት ጥናት በገርቢ ወንዝ ላይ ግንባታ ለማካሄድ ከ2.5 ቢሊዮን እስከ ሦስት ቢሊዮን ብር ድረስ ይፈጃል፡፡

  ይህን ፕሮጀክት መገንባት የሚያስችለው የግንባታ ዲዛይን በአሁኑ ወቅት በመከናወን ላይ የሚገናኝ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ዓመት ግንባታውን የሚያካሂዱ ኩባንያዎችን ለመምረጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ይወጣል ተብሏል፡፡

  የሲቪሉና ገርቢ ወንዞች በሰሜን አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜርት ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ወንዞቹ የዓባይ ገባር ሲሆኑ ዓመታዊ የፍሰት መጠናቸው ጥሩ የሚባል በመሆኑ ለአዲስ አበባ ከተማ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ተመራጭ ሆነዋል፡፡

  ፕሮጀክቶቹ አንድ ላይ ቢካሄዱ 688,500 ኪዩቢክ ሜትር ውኃ በቀን እንደሚመረት፣ ይህም በአሁኑ ወቅት በሁሉም የውኃ ማመንጫዎች ከሚመረተው በእጥፍ ብልጫ ያለው ውኃ እንደሚያስገኝ ይታመናል፡፡

  በአሁኑ ወቅት ለግንባታ የተመረጠው የገርቢ ግድብ ሲጠናቀቅ እስከ 130 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ በቀን ማስገኘት ያስችላል፡፡

  በአዲስ አበባ የመጠጥ ውኃ ሽፋን 94 በመቶ ደረሰ ቢባልም ኅብረተሰቡ የውኃ እጥረት እንዳጋጠመው በሰፊው በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ በሰሜናዊው የከተማ ክፍል ለሳምንታት ውኃ ሳይመጣ የሚቆይ ሲሆን፣ በሌሎች የከተማው ክፍሎች ፈረቃ ሊባል በሚችል ሁኔታ የውኃ እጥረት እንዳለ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ አስተዳደሩ የውኃ አቅርቦት ችግሩ እንዳለ ቢያምንም መሻሻሎች መኖራቸውን አጥብቆ እየተከራከረ ይገኛል፡፡

  =======================================================
   

  Ethiopia’s drinking water coverage drops by 17% – sign of a more serious problem? (Part I)

  Monitoring information, prepared and released in April 2013 by MoWR, indicates that 52 percent of Ethiopians have access to drinking water supply. While this could be enough for MDG spot reporting today, it is far lower in terms of the needs of the nation already today and for MDG by 2015, given population growth.

  =======================================================
   

      (ለ) የስብዓዊ መብቶች ጥስት

   

  የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው ተባለ (ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየሩሳሌም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ዳግም እየተፈናቀሉ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቁ፡፡

  ሁለቱ ፓርቲዎች ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ቀደም ብሎ በጉራፈርዳ ወረዳ፣ በሸፒ ቀበሌና በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪ የነበሩት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት በአፈናቃዮቹ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ቢያሳውቅም፣ ዜጐቹ ግን እስካሁን እየተፈናቀሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተወካይ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለዓለም ሕዝብ ጭምር በሰጡት ማብራሪያ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራና የኦሮሞ (የዘር ማጥራት ወንጀል እንዳይመስል) ተወላጆችን ያፈናቀሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ፣ መንግሥት ዕርምጃ እንደሚወስድና ተፈናቃዮችም ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንደሚመለሱ የተናገሩ ቢሆንም ተግባራዊ አልሆነም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

  ቀደም ብሎ ከ21 ሺሕ በላይ የአማራ ተወላጆች ከተፈናቀሉበት፣ ከቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየሩሳሌም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ከሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ብሔር ተወላጆች እየተፈናቀሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  ======================================================
   

  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ተፈናቀልን አሉ

  ቀድሞ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ ነዋሪ የነበሩና በኋላ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገብተው በቤሌ ጃጐንፎይ ወረዳ የተዛወሩ 44 አባወራዎች፣ ‹‹በመንደር ማሰባሰብ›› ስም በ2003 ዓ.ም. የክልሉ መንግሥት እንዳፈናቀላቸው በተወካዮቻቸው አማካይነት አስታወቁ፡፡

  ተፈናቃዮቹ እንደገለጹት፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድንበር አዋሳኝ በነበረውና በ2000 ዓ.ም. ወደ ክልሉ በተቀላቀለው ይዞታቸው ላይ ለሃያ አምስት ዓመታት ኖረዋል፡፡ በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ሰብስቦ ካወያያቸው በኋላ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መቀላቀላቸውን እንዳሳወቃቸውና ጉዳዩ የመንግሥት ውሳኔን የተከተለ በመሆኑ፣ ነዋሪዎቹ ወደ ቤኒሻንጉል ክልል መቀላቀላቸውን ይናገራሉ፡፡ ከነዋሪዎቹ ጋር የተደረገው ውይይትም ሰላማዊ መሆኑን፣ ነገር ግን ወደ ቤኒሻንጉል ክልል እንዲካለሉ ከመደረጉ በፊት ድንበርተኛ እንደመሆናቸው ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

  ምንም እንኳ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲከለሉ አካሄዱ በውይይትና በማሳመን የነበረ ቢሆንም፣ ለመንደር ማሰባሰብ በሚል የክልሉ መንግሥት በ2003 ዓ.ም. ፈጽሞ ሳያሳውቃቸው ግብር ከሚገብሩበት መሬታቸው ላይ ማስነሳት መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡

  ከተፈናቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ለቀበሌ፣ ለወረዳ፣ ለዞንና ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ ዛሬም አቤቱታቸው ሰሚ ጆሮ አላገኘም ይላሉ፡፡ ለረዥም ወራት ቤትና መሬት አልባ ሆነው የነበራቸውን ሀብትና ንብረት ሸጠው በመጨረስ የዕለት ጉርስ እስከመቸገር መድረሳቸውን ይናገራሉ፡፡

  ‹‹በ2003 ዓ.ም. ሳናርስ ቀረን፤ ነገሮች ይለወጣሉ ብለን ብናስብም በ2004 ዓ.ም. እንዲሁ ስንንከራተት ጊዜው አለቀ፤›› የሚሉት ተፈናቃዮቹ፣ በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ለተፈናቀሉት አባወራዎች ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ቀነ ገደብ ቢያዝም፣ ውሳኔው ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱን አስረድተዋል፡፡

  በሐምሌ 2004 ዓ.ም. ጉዳዩን በሚመለከት ውይይት ያደረጉት የሚመለከታቸው የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የመንግሥት ኃላፊዎች፣ አሥራ ሰባት ተፈናቃይ አባወራዎችን በመንደር ለማሰባሰብ ተነስተው፣ ቤትና ትምህርት ቤት ሳይሠራበት የቀረ መሬት ላይ እያረሱ እንዲቆዩ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ብለዋል፡፡ በየካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ መሬት እንዲያገኙ መወሰኑን የሚያሳይ ቃለ ጉባዔ ቢኖርም፣ ውሳኔው ዛሬም ድረስ ተግባራዊ መሆን አልቻለም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

  በተመሳሳይ ባለፈው ወር ማብቂያ ላይ የተፈናቃዮቹ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክልሎችና የመንግሥት ኃላፊዎች ጥምር ኮሚቴ ውይይት አካሂዶ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ለተፈናቃዮቹ ተለዋጭ መሬት የመስጠቱ ሒደት እስከ ሰኔ 5 ቀን 2005 ዓ.ም. እንዲጠናቀቅ በቃለ ጉባዔ ውሳኔ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ውሳኔው ተፈጻሚ ሊሆን አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡ ስለዚህም ባለፈው ሳምንት እንደገና አቤቱታቸውን ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ማቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡

  የተፈናቃዮቹ ጉዳይ በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተያዘ መሆኑን ማረጋገጥ ያልተቻለ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው ኃላፊ ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ማግኘት አልተቻለም፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስርን በስልክ ስለጉዳዩ ተጠይቀው፣ ስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተው ነገር ግን ለምን ተፈጻሚ እንዳልሆነ አለማወቃቸውን ገልጸዋል፡፡ ችግሩ ማን ዘንድ እንዳለ እንደሚያዩት አቶ አህመድ አስረድተው፣ ለጊዜው ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማብራራት እንደማይችሉ አስታውቀዋል፡፡

  =======================================================
   

  Prisoners under persistent tortures appeal for help from Ethiopians

  በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል።

  እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት በቀጠሮአቸው ቀን እንዳይቀረቡ መከልከላቸውን ለመቃወም ለበላይ አካላት ደብዳቤ በመጻፋቸው ምክንያት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የገለጹት እስረኞቹ፣ ጉዳዩን ለቂሊንጦ ዋና አስተዳዳሪ ኦፊሰር አምባየ ስናመለክት ” እስከ መግደል ድረስ እርምጃ ለመውሰድ መብት አለን፣ አርፋችሁ ካልተቀመጣችሁ በጥይት እንቆላችሁዋለን፣ የምግብ ማቆም አድማ እናደርጋለን ብትሉም ለእኛ ደንታችን አይደለም” በማለት እንደመለሱላቸውና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየተዛተባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ለ4 ቀናት ምግብ ማቆማችንን ተከትሎ ማንም ስላልጠየቀን በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን ያሉት እስረኞቹ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግላቸውም እስረኞቹ ተማጽነዋል።

  ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ህክምና ከተከለከሉት መካከል ቀጀላ ገላና ገቢሳ፣ በላይ ኮርሜ ባይሳ፣ መንግስቱ ግርማ አየሳ፣ ተፈራ ቀበኔ ገመቹ፣ ሙላት ሽመልስ እጀታ፣ ኢብሳ አህመድ ሙሀመድ እና ሸምሰዲን የተባሉት ሲገኙበት ፣ ድብደባ ከተፈጸመባቸው መካከል ደግሞ ሌሜሳ ዲሴሳ፣ አለሙ ተሾመ ቦኬ፣ ዘርፉ መልካ አባይ፣ ቀበታ ገቢሳ ነባራ፣ ቀበና ነጋሳ ነገራ፣ መልካሙ መገርሳ፣ አዳሙ ሽፈራው፣ ቡልቻ ሱሪሳ ጌታቸው አብራ ቶሎሳ፣ ስለሺ ሶሬሳ፣ የፓርላማ አባል የነበረው ጉቱ ወልዴሳ፣ አለማየሁ ቶሎራ፣ በርሲሳ ሊሙ፣ ብርሀኑ እምሩ፣ ኡርቄና አጀማ፣ አህመድ አብደላ ጎዳ እና ለማ በዳዳ ይገኙበታል።

  በኦነግ ስም በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ያቀረቡትን ተማጽኖ ተከትሎ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቀይ መስቀል ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግ የድርጅቱ ስልክ አይነሳም። የታራሚዎች ፍትህ አስተዳዳር ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ ብርሀኔ ሀይለስላሴ ስልክ ብንደውልም፣ ስልካቸው ቢጠራም አይነሳም።

  ኢሳት በእስረኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ተከትሎ አካባቢው በደም በመበከሉ እንዲታጠብ መደረጉን መዘገቡ ይታወቃል። የቂልንጦ እስር ቤት ዋና ሃላፊ በቅጽል ስሙ ሻቢያ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በእሰረኞች ላይ መፈጸሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

  =======================================================
   

  የማንነት ጥያቄ ያቀረቡ ከ50 በላይ ሰዎች ለእስር እንደተዳረጉ የአገር ሽማግሌዎች አስታወቁ (ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ኡባ ደብረፀሐይ በሚባለው ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የኡባ ጌዞ ማኅበረሰብ አባላት የማንነት ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት የኃይል ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታወቁ፡፡

  በተወሰደባቸው ዕርምጃ በመንግሥትና በግብርና ሥራ ላይ የተሰማሩ ከ50 በላይ ሰዎች እንደታሰሩባቸው ገልጸዋል፡፡

  ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው በመሆኑ ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ በመናገር ማንነታቸው እንዳይታወቅ የጠየቁ የአገር ሽማግሌዎች እንደገለጹት፣ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ከወረዳው ጋር በመሆን በወሰደው ዕርምጃ ለእስራት የተዳረጉ ሰዎችን ጨምሮ በበርካቶች ላይ የቤት ብርበራና የማሳደድ ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ሰኔ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በወረዳው በሚገኘው ሾሌ ንዑስ ቀበሌ ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ የጋሞ ጎፋ ዞን ፀጥታ ክፍል ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመሆን ለሁለት ሳምንት የቆየ አሰሳ በማድረግ ካሰሩዋቸው የኡባ ጌዞ ማኅበረሰብ አባላት በተጨማሪ፣ በስብሰባው ወቅት ያልነበሩ በሌሊት ሳይቀር የሚታደኑ በርካቶች እንደነበሩ አስታወቀዋል፡፡ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ያቀረቡ መሆናቸውን፣ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ከማኅበረሰብነት ወደ ብሔረሰብነት የማደግ ጥያቄም ወቅታዊ ምላሽ ባለመግኘቱ አዲስ አበባ ሲንገላቱ ቆይተው ወደመጡበት ለመመለስ መገደዳቸውን አስረድተዋል፡፡

  የአገር ሽማግሌዎቹ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ የብሔረሰብ ማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 መሠረት ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት በተዋረድ ሲቀርብ የቆየ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ምላሽ አላገኘም፡፡ በ1993 ዓ.ም.፣ በ2000 ዓ.ም. እንዲሁም በ2004 ዓ.ም. ለኡባ ደብረፀሐይ ወረዳ ምክር ቤትና ለወረዳው አስተዳደር ጥያቄያቸውን ደጋግመው ሲያቀርቡ ቢቆዩም ምላሽ በማጣታቸው፣ በ2004 ዓ.ም. ለክልሉ ብሔር ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበው እንደነበር የአገር ሽማግሌዎቹ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከእነዚህ አካላት ምላሽ በማጣታችን፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ጥያቄያችንን ለማቅረብ ተገድደናል፤›› ያሉት የኡባ ጌዞ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን ወደ ቋሚ ኮሚቴ ቢመራውም ውጤቱን ሊያሳውቅ አልቻለም ብለዋል፡፡

  ======================================================
   

         (ሐ) መልካም አገዛዝ የተሳነው የሕወሃት መንግሥት

  ተግሳፅ የሚያስፈልገው መንግሥት (ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  አገሮች ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ውጥኖቻቸውን ለመፈጸም በየዓመቱ በጀት ይመድባሉ፡፡ በየትም አገር ውስጥ የበጀት ጉድለት የሚከሰት መሆኑ ደግሞ ዕሙን ነው፡፡ በኢሕአዴግ መንግሥት ታሪክ ውስጥም በየዓመቱ ከፍተኛ የበጀት ጉድለቶች ይስተዋላሉ፡፡

  ነገር ግን የትኛውም መንግሥት እንደሚያደርገው የበጀት ጉድለት በተለያዩ አማራጮች ይሸፈናሉ፡፡ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዋነኞቹ አማራጮች ናቸው፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥትም በየዓመቱ እጆቹን ለብድር ለውጭ መንግሥታት በመዘርጋት የበጀት ጉድለቱን ሲሸፍንና እየሸፈነም ይገኛል፡፡ የሚያሳዝነው ግን የበጀት ጉድለቱን ሙሉ ለሙሉ አሊያም በከፊል የሚወክሉ ቢሊዮን ብሮች በየዓመቱ ይባክናሉ፣ ይጭበረበራሉ ወይም ለምን እንደዋሉ አይታወቅም፡፡

  ይህ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የነበረ በየዓመቱም የገንዘብ መጠኑ በቢሊዮኖች እየተቆጠረና እየጨመረ የሚገኝ የሚያምን እውነት ነው፡፡ ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰብስበው ስለሚባክኑት ቢሊዮን ብሮች እውነታ የሚያውቁትና ሕመሙን የሚታመሙት ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡

  ይህ የሚያም እውነት ግን ዘንድሮም ቀጥሏል፡፡ የአስፈጻሚውን መንግሥት የገንዘብና ሀብት አስተዳደር፣ እንዲሁም የዕቅድ አፈጻጸም የሚመረምረው ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው ተቋም የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ያቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2004 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸም ኦዲት ሪፖርት 6.5 ቢሊዮን ብር በጥያቄ ውስጥ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡

  የዘንድሮውን የኦዲት ሪፖርትና ግኝቶች ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት የዜና ዓምዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ቢሆንም የዚህን ሪፖርት ጠቅለል ያለ የኦዲት ግኝት በድጋሚ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ዋና ኦዲተር በ2004 ዓ.ም. የበጀት አፈጻጸም በተመለከተ 224 የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶችን ሒሳብ የመረመረ ሲሆን፣ አንድ መሥሪያ ቤት ግን የ2004 ዓ.ም. ሒሳቡን ዘግቶ ለኦዲተር ጄነራሉ ዝግጁ ባለማድረጉ ኦዲት ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ይህ መሥሪያ ቤት በአገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት እንዲሰፍን ኃላፊነት የተጣለበት የፍትሕ ሚኒስቴር መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ይህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በግዥና በሀብት አስተዳደር ችግር ያለበት መሆኑ በፓርላማው የተረጋገጠ ነው፡፡ እናም ከተፈጸመው የሕግ ጥሰት በተጨማሪ የ6.5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የኦዲት ግኝቱ ከዚህ በላይ እንዲንር ሊያደርገው ይችላል፡፡

  ከተጠቀሰው የ2004 ዓ.ም. የኦዲት ግኝት ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በዘጠኝ መሥሪያ ቤቶች ላይ የተገኘ ሲሆን፣ ለምን ጥቅም እንደዋለ ምንም ዓይነት መረጃ ያልቀረበለት ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 3.2 ቢሊዮን ብር መከላከያ ሚኒስቴር ተጠያቂ የሆነበት ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ አስፈጻሚ የሆኑ 30 ተቋማት ደግሞ ከግዥ ሕጉም ሆነ ሌሎች ደንቦች የተጣረሰ የ353.6 ሚሊዮን ብር ግዥ ፈጽመዋል፡፡ በሌላ በኩል 11 ተቋሞች ገበያው ከሚጠይቀው ዋጋ በላይ የሆነ ለቁሳቁስና ለአገልግሎት ግዥ 1.39 ቢሊዮን ብር አጥፍተዋል፡፡ ሌሎች የመንግሥትን ገቢ በወቅቱ መሰብሰብ የሚገባቸው ተቋማት ደግሞ 1.36 ቢሊዮን ብር ሳይሰበስቡ ቀርተዋል፡፡ ከተፈቀደላቸው ዓመታዊ በጀት በላይ 212.4 ሚሊዮን ብር የተጠቀሙ ተቋማት እንዳሉም የኦዲት ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ከኦዲት ግኝቱ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

  ======================================================
   

  ኦሮሚያ ውስጥ በሙስና የተጠረጠሩ ተጨማሪ 12 ኃላፊዎች እየተፈለጉ ነው: የኦሮሚያ ሁኔታ ከሁሉ የከፋ፤ ወይንስ ፖለቲካዊ እርምጃ?(ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  በማሽኖች ግዢና ኪራይ ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል ተብለው ከሚፈለጉ 25 የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ባለስልጣናት መካከል 13ቱ የተያዙ ሲሆን፤ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅና ምክትላቸውን ጨምሮ ዋና ዋና ሃላፊዎች እስካሁን አልተያዙም፡፡

  የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው (Diagnnosing Corruption in Ethiopia) ከሆነና ክፍለ ህገሩ የተጠናከረ የሙስኝነት ባህሪ እስካልታየበት ድረስ፡ አሁን በኦርሚያ በመካሄድ ላይ ያለው ጸረ-ሙስና ዘመቻ ፖለቲካዊ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለ? አገራችን ከታሪኳና ከልምዷ በሚገባ የተማረችው ነገር ቢኖር፡ መንግሥትን አለማመን ነው።

  ስለሆነም፡ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ድርጊቱ ተቀባይነትና ተአማኒነት እንዲኖረው የሚሻ ከሆነ፡ ይህንን ለሕዝቡ በተጨባጭ ግልጽ ማድረግ ይኖርበታል!

  ይህ ማለት አጥፊዎችና ሙስኞች ሕግ ፊት አይቅረቡ ለማለት አይደለም!

  ባለፉት 22 ዓመታት እንዳየነው ከሆን፡ ጥቃቱ አንድ ሰሞን ጋምቤላዊ፡ አንድ ስሞን አማራ፡ አንድ ስሞን ኦሮሞ፡ አንድ ስሞን አፋር፡ አንድ ስሞን ኦጋዴን ሶማሌ፡ አንድ ስሞን የእስልምና እምነት ተከታዮች እያለ ሲመጣ ታይቷል። በሁሉም አጋጣሚዎች፡ የዚህ ዐይነት በየምክንያቱ ግለስቦችንና ቡድኖችን በማጥቃት መቀጠሉ፡ ከተቻለ ሃገሪቱነ ሁሉም በተንበረከከበት ሁኔታ ለገዥው ብሄረስብ ብቸኛ ተጠቃሚነት ለማመቻችት የታለመ ይመስላል።

  በሠለጠነው ዓለም፡ ጨቋኝ መንግሥታት በየጊዜው በዓለም ውስጥ በተለያዩ አግሮች ውስጥ ካደረሱት ጥፋትና ውርደት በመነሳት – ያ ሁለትኛ በምንም መልኩ የመንግሥትን ሥልጣን በጨበጡ ግለስቦችና ቡድኖች እንዳይደገም – ግለስቦች በግለስባዊነታቸው ለማያውቁት አንድ መንገደኛ መብት እንኳ የመቆም ባህል አዳብረዋል – እንኳ የራሳቸው ወገኖች በብኄረሳባቸውና ሃይማኖት ምክንያት ጥቃት ደርሶባቸው!

  በመሆኑም፡ በኢትዮጵያውያኖች በኩል በየተራ ከመታረድ ይልቅ፡ ለአንዱ የሚመጣው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አደጋ እንዳለው በመገንዝብ፡ ሁሉም የሕዝብን የጋራ ደህንነት፡ የአገርን የጋራነት (የጋርዮሽ መብቶችን equal access to opportunities) ለማስከበር ዐይን ከፍቶ እራስን በጋራ ከቅኝ ግዥዎች ከክፉ ወገኖች መጠበቅና መከላከል ወቅቱ የሚጠይቀው ብኄራዊ ግዴታ ላይ የተደረስ ይመስላል።

  ======================================================
   

  ኢትዮጵያ ወደአደገኛ አግጣጫ እያመራች ነው (ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ)

  ሀቁን እንነጋገር ከተባለ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት አገር አይደለችም። ይህ ማለት ግን ለጥቂቶች መንግስተ ሰማይ አልሆነችም ማለት አይደለም። ፍሬ ነገሩ ግን ሥልጣን ላይ ካሉት ስዎች ጋር በማበር የምዕራብ መንግሥታትና ኩባንያዎቻቸው፡ ጥቅሞቻቸውን ለማራመድና፡ አሁን ያለውን ስቴተስኮ እንዳለ ለማቆየት የፈልጉትን ያህል ቢደስኩሩም፤ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባይተዋሮችና በብዙ መልኩ ሕይወታቸው በአረብ አገሮች በግርድና ላይ ካሉ ወገኖቻችን ጋር ያለው ልዩነት መጠነ ጠባብ እየሆነ መምጣቱን መሸፈን አልቻሉም።

  በሌላ አባባል፤ የስው ልጅ ውሎውና በቀኑ መጨረሻ ላይ በስላም ወደጎጆውና ቤተስቡ መመለሰሱ ዋስትና በሌለው ሁኔታ ውስጥ፤ ባልታሰበ ቀንና ስዓት ዜጎች ንብረታችውን በመንግሥት እንዳይነጠቁ የሚሰጉበት፤ ከሁሉም የከፋ ደግሞ ወደእሥር ቤት እንዳይወረወሩ፤ ልጆቻቸው ከሀግራችው አስፈሪ ሁኔታ በሥውር ለመሸሸ በሚያደርጉት ከሀገር የመሰደድ ሁኒታ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የሚሰጉበት – በአጭሩ ሕዝቡ አንገቱን ደፍቶ ለመኖር የተገደደበት ወቅት የነጻነትና የሰላም ጊዜ ነው ብለው የሚያስቡ ግለስቦች ከራሳቸው ምቾት ባሻገር ማየት የተሳናቸው ብቻ ናችው።

  በየትኛውም ትርጓሜ፤ ይህ ሁኒታ በአንድ በኩል ከባርነትና በሥጋት ከተወጠረ ሕይወት በሌላ በኩል ደግሞ ከስላማዊና ነጻነት ጋር ሲወዳደር፤ በጉልህ የሚታየው የኢትዮጵያውያን ሕልውና ከፍርሀትና ሰቀቀን ነጻ እንዳልሆነ ነው።

*Title adjusted afterwards; materials added

%d bloggers like this: