“መጠነኛ የሁከት እንቅስቃሴ በታየባቸው አካበቢዎች አክራሪዎች በስሙ እየነገዱ ሠላም የነሱትን ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የጥፋት ሴራቸውን ለማክሸፍ ያሳየው ጨዋነት” ተደነቀ

28 Aug

አዲስ አበባ ነሐሴ 21/2005 ሕገ-መንግሥቱን በመፃረር አገርና ሕዝብን የሚጎዳ የብጥብጥና የሽብር ተግባር ላይ በሚሰማሩ ቡድኖች ላይ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም የተለያዩ የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች ስለ ሠላም የሚመክሩበት ጉባዔን ዛሬ ሲከፍቱ እንዳስታወቁት መንግሥት አክራሪነትን ጨምሮ ማንኛውም ሁከት በሚፈጥሩት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል። የአክራሪነት አስተሳሰብ አራማጆች የመረጡት የአመጽ መንገድና ያሰቡትን የፖለቲካ ትርፍ እንደማያስገኝላቸውና እንደማያዋጣቸው ተገንዝበው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም በድጋሚ አሳስበዋል።

አገርን ማተራመስ ዓላማቸው ያደረጉ አክራሪ ጽንፈኛ ኃይሎች ከጥፋት ድርጊታቸው የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ አጋጣሚ ይሆናል በሚል የፀረ-ሠላሙን እንቅስቃሴ የሚደግፉ ተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከዚህ የተሳሰተ አስተሳሰብ ፈጥነው ሊታረሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት እንዳለው የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ከማንኛውም የኃይማኖት ተቋምና አስተምህሮት ጋር የሚወግንበት አሊያም ጣልቃ የሚገባበት ምንም ምክንያት እንደሌለው አመልክተዋል። በኃይማኖት ሽፋን ሕገ-መንግሥቱን የሚፃረር ሕገ-ወጥ ተግባርን መንግሥት በጽኑ እንደሚታገለውና ድርጊቱንም ከሕዝብ ጋር በመሆን እንደሚያመክነው ገልጸዋል።

በቅርቡ መጠነኛ የሁከት እንቅስቃሴ በታየባቸ አካበቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን በተለይም አክራሪዎች በስሙ እየነገዱ ሠላም የነሱትን ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የጥፋት ሴራቸውን ለማክሸፍ ያሳየውን ጨዋነት አድንቀዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ ከመንግሥት ጎን በመቆም በቀጣይም የጥፋት ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለማምከን ያሳየውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይም በክርስትና እምነት ተከታዮችም ዘንድ እምነቱን ሽፋን በማድረግ በጥቂቶች ተስተውሎ የነበረውን የአክራሪነት መንፈስ ላይ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ ያሳዩት ቁርጠኝነት ወደፊቱም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። የአክራሪነት አደጋ በወቅታዊ እንቅስቃሴ ብቻ የሚወገድ ጉዳይ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኃይማኖት ተቻችሎና ተከባብሮ አብሮ የመኖር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ዜጎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በየትምህርት ተቋማቱና በየቤተ-እምነቱ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

ጉባዔውን ከሰባት የእምነት ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሲሆን በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በኃይልና በተጽዕኖ የተስፋፋም ሆነ የተመሰረተ ኃይማኖት አለመኖሩን ገልጸዋል። በመሆኑም ይህን የቆየውን የኃይማኖቶች የመቻቻልና ተከባብሮ የመኖር ባህል ለመጪው ትውልድ እንዳለ ማስረከብ እንደሚገባ አመልክተዋል።

ምንጭ፡ ኢዜአ

Related materials

Who is telling the world the truth – hunger for power or peaceful Moslems demanding respect for their human, civil rights?

[Must-Watch] ETV Debate – EPRDF, UDJ, Semayawi Party, Medrek & EDP debate Anti-Terrorism Law – Part 1 | August 26, 2013

[Must-Watch] ETV Debate – EPRDF, UDJ, Semayawi Party, Medrek & EDP debate Anti-Terrorism Law – Part 2 | August 27, 2013

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎ

*Modified

%d bloggers like this: