ዶ/ር ደብረጽዮን የቀድሞው የኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት የብቃት ችግር ነበረበት ይላሉ – ምነው ይህንን ዛሬ ማመን መረጡ?

18 Dec

የአዘጋጁ አስተያየት:

  ከሩቅ ብዙ የሚታወቅ ነገር ስለሌለ፡ ብዙ ለማለት ያስቸግራል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ችግር ምንጭ የአመራር ብቃት መጥፋት ይሆን፡ ወይንም ሌላ ከርቀት ብዙ ለማለት አንችልም። ሆኖም ሁለት ጥርት ያሉ ሁኔታዎች አሉ።

  አንደኛ፡ ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገሮች መብራት ማከፋፈል ስትጀምር (ጂቡቲን ሱዳን)፣ ለሕዝቧ ግን የመብራት አግልጎት ማቅረብ አልቻለችም። ሁለተኛ፡ ችግሩ አሁን በተወስዱት እርምጃዎች ለመፈታት መቻሉ አጠያያቂ ነው። የኢትዮ ቴሌኮምን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። ያ ሁሉ ሠራተአኛ ተባሮ፡ ለፈረንሳዊ አስተዳደር ቡድን ያን ያህል ገንዘብ ከፈሰሰ በኋላ፡ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂውን በቅጡና በወቅቱ ገዝታ በሥራ ላይ ማዋል አቅቷት በሁለቱ ቻይና ኩባንያዎች መካከል ከዓመት ስድስት ወር በላይ ጊዜ አባክናለች።

  በዚህ ሁኔታ ውስጥ፡ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ምነው ምነው የአቶ ደብረጽዮንን ብቃት አይገመገምም፡ ወይንም ከቦታው ተነስተው በምትካቸው ሥራውን ማከንወን የሚችል ግለሰብ እንዲወስድ አይደረግም የሚለው አመለካከት: ጥያቄና ትችት በቀላሉ ሊገፋ አይገባውም። ነገር ግን እሳቸውን ማንሳት፡ የንጉሡን ዘውድ መገፋት ስለሚሆን፡ ብዙ ማድረግ አይቻልም – ስልኩም መብራቱም ድርግም እንዳሉ ይቀሩዋታል እንጂ!

  በሃሰት ላይ የተመሠረተና ያለብቃት የሚካሄድ አመራርና አሠራር አሁንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጋለጣል። አሁን አቶ ደብረጽዮን ያተኮሩት፡ በሕወሃት ያሰወስኑትነና እሳቸውም በግል የወስኑትን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንጂ፤ ይህንንም ሲያደርጉ፡ እውነትንም አለአግባብ ሲጫኗት ይታያሉ። ለምንኛውም እሳቸው ዛሬን እንጂ፡ ለነገው ግድ ያላቸውም አይመስሉም።

  ለምሳሌ፡ የሕንዱ ኩባንያ ((NHPC እና BSES) ከነሐሴ ጀምሮ ኮንትራቱ ተክብሮለት ያለሥራ መቀመጡን ራሱ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በBusiness Line በኩል ማሰማቱ ይታወሳል። በወቅቱ ኩባንያው ያለው መንግሥት አስፈላጊውንና እንዲመደቡለት የጠየቃቸው ሠራተኞች ሥፍራ ቦታቸውን ስላልያዙ በቅርቡ ሥራ ለመጀመር አለመቻሉን ማስማቱ ይታወቃል። አቶ ደብረጽዮን ግን የህንዱ ኩባንያ ብዙ ሥራዎችን ማገባደዱን ይነግሩናል። ከሕወሃት ባልሥልጥኖች ምንጊዜም ቢሆን እውነትን መጠበቅ ዛሬም ሆነ ነገ ፈታኝ ጉዳይ ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው።

  በሪፖርተር ላይ አቶ ደብረጽዮን የመብራት ኀይልን የቀድም አስተዳዳሪ በጎንና በሽሙጥ መራገጣቸው፡ Addis Fortune ግለስቡ የተነሱበት ምክንያት፡ የጄኔራል ክንፉ ዳኘው የቦርድ አባልነት የጥቅም ግጭት ያስከትላል በማለት ያቀረበው አቤቱታን መሠረት ለማሳጣት ከሆን የተሳካላችው አይመስልስም።

  በዚህ የተፋጠነ ገበና ገላጭ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ዘመን ተሸፋፍኖ የት ሊደረስ?

 
================================================================

በታምሩ ጽጌ፤ ከሪፖርተር
Posted by The Ethiopia Observatory

 –   “የኢንጂነር አዜብ አስናቀ ብቃት የተመሰከረለት ነው” ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል

 –   አቶ ምሕረት የሚመሰገኑትን ያህል ድክመትም እንደነበረባቸው ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት መሥራት የሚገባውን ያህል ያልሠራ፣ የብቃትና የአቅም ችግር የነበረበት መሆኑን የቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ኅዳር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ ኮርፖሬሽኑ ለሁለት መከፈሉን በማስመልከት እንዳብራሩት፣ እሳቸው የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑ ሦስት ዓመታት ሆኗቸዋል፡፡ የመሥሪያ ቤቱን አሠራር በሚመለከት ባደረጉት ግምገማ ማኔጅመንቱ መሥራት የሚገባውን ያህል አልሠራም፡፡ ማኔጅመንቱ ጥቂት አቅም ያላቸው አባላት ቢኖሩትም አቅም የሌላቸው በርካቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በየጊዜው በተደረገ የውስጥ ግምገማ የተረጋገጠው ማኔጅመንቱ አቅም ኖሮት ቢሠራ ኖሮ፣ አገልግሎቱ እየተሻሻለ ይሄድ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ማስተርስ ዲግሪ ይዞ ብቃት የሌለው የማኔጅመንት አባል መኖሩን የገለጹት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ “ይኼንን አቶ ምሕረትም ያውቃል፡፡ እሱም የሚመሰገነውን ያህል ጉድለትም እንደነበረበት ይረዳል፡፡ ከኃላፊነቱ ሲነሳም አልደነገጠም፤” ብለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚል ለሁለት መከፈሉን ዶ/ር ደብረ ጽዮን አስረድተው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ መሾማቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የኢንጂነር አዜብን የትምህርት ብቃት፣ የሥራ ልምድና በሠራተኞች ዘንድ ስላላቸው ተቀባይነት በሚመለከት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ደብረ ጽዮን በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ይመሩታል፡፡ በመሆኑም ኢንጂነር አዜብ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ተሹመዋል፡፡ በእሳቸው ሥር አራት ሥራ አስፈጻሚዎች ተሾመዋል፡፡ ኃላፊዎቹ የተመደቡበት መስፈርት አለ፡፡ የመጀመሪያው ሁለተኛ ዲግሪ ሲሆን ሁለተኛውና ትኩረት የተሰጠው መስፈርት ተሿሚው በሠራተኞች ያለው ተቀባይነት ነው፡፡ ልምድና ትምህርቱ ከፍተኛ ቢሆንም በሠራተኞች ተቀባይነት ከሌለው ዋጋ የለውም፡፡ ልምድና ብቃትም ከመስፈርቶቹ መካከል ናቸው፡፡ ኢንጂነር አዜብ የተቀመጡትን መስፈርቶች በሙሉና በብቃት ያሟሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ውስብስብ የሆነውን የግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጄክት ግንባታ በመምራት ወደ መጨረሻው ደረጃ በማድረስ የተፈተኑ ናቸው፤›› በማለት የመመረጣቸውን ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

‘Niticeable power dreams’ Courtesy of Addis Fortune

የቀድሞውን ማኔጅመንት አቅም ማነስ በመጠቆም እንዲቀየር ሲወተውት የነበረውን ሠራተኛ በተለያዩ ቦታዎች በመሰብሰብ በፕላዝማ ስለአዲሱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማኔጅመንት ኃላፊዎች ሹመትና አጠቃላይ ሁኔታ ሰሞኑን ውይይት መደረጉን የገለጹት የቦርድ ሰብሳቢው፣ ሦስት ሠራተኞች ብቻ ስለኢንጂነር አዜብ ብቃትና ልምድ ጥያቄ ከማቅረባቸው ውጪ፣ ብዙኃኑ ሠራተኞች በመሾማቸው ደስተኞች መሆናቸውን እንደገለጹ ተናግረዋል፡፡ ቦርዱ ሥልጣን ብቻ ስላለው ዝም ብሎ ሹመት የሚሰጥ ሳይሆን ለሠራተኞች በማቅረብ ካወያየ በኋላ እንደሚሾምና ተጠቁሞ ተቀባይነት ያጣን ኃላፊም እንደሚተው በመጠቆም፣ እነኢንጂነር አዜብ የተሾሙት በሠራተኞች ሙሉ የውይይት ተሳትፎ በመታገዝ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ተቋሙ ተልዕኮው ሰፊ በመሆኑ ባለው መዋቅር መቀጠል እንደማይችል በመታመኑ ለሦስት ዓመታት ጥናት መደረጉን የገለጹት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ መንግሥት ዓለም አቀፍ ልምድና ብቃት ያለው ኩባንያ በመምረጥ ጥናቱ እንደተጠና ተናግረዋል፡፡ ብቃትና ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች ከተወዳደሩ በኋላ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው ኩባንያዎች መካከል የህንዱ ፓወር ግሪድ ኩባንያ የተመረጠ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ኩባንያው ከተመረጠ በኋላ ሥራውን ለሁለት መክፈል አስፈላጊ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተብሎ ሊከፈል መቻሉን የቦርድ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው የማኔጅመንት አሠራር እንዲኖራቸው መደረጉንም አክለዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ አሠራር እንዲኖረው ለማድረግ በመሆኑ፣ ዲዛይኑ በአማካሪ ድርጅቶች ከተጠናና ይሁንታ ካገኘ በኋላ ወደ ሥራ መገባቱንም አስረድተዋል፡፡

ፓወር ግሪድ የማስተላለፊያ መስመሮችን እንደሚሠራና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በሚመለከት ደረጃውን የጠበቀ አሠራር እንደሚኖረው የገለጹት ሰብሳቢው፣ ሁለት የህንድ ኩባንያዎች ናሽናል ኃይድሮ ፓወር ኮርፖሬሽንና ቢኤስኢኤስ የሚባሉ የህንድ ኩባንያዎች አብረውት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡

ለሁለት ዓመት ከስድስት ወራት የሚቆይ ስምምነት መንግሥት ከፓወር ግሪድ ኩባንያ ጋር መፈራረሙን የገለጹት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ ከታክስ ውጪ በ16.7 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከታክስ ጋር በ21 ሚሊዮን ዶላር ውሉ የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ለኮንትራክተሩ ክፍያው የሚፈጸመው በየሦስት ወሩ በሚደረግ ግምገማ መሆኑን የጠቆሙት የቦርድ ሰብሳቢው፣ የተለያዩ መሥፈርቶች መቀመጣቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ፓወር ግሪድ በሠራው ሥራ የተቋሙ ገቢ ምን ያህል እንደጨመረ፣ ተጠቃሚው በሚያገኘው አገልግሎት ምን ያህል እንደረካ፣ የሚከሰት ችግር እንዴት እንደሚፈታ፣ ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃን በሚመለከት ያመጣው ለውጥ (Operational Efficiency)፣ በአገር ውስጥ ሠራተኞች ላይ ያመጣው የአቅም ግንባታ ውጤት የሚሉትና ሌሎች መሥፈርቶችን በጥሩ ሁኔታ አሟልቶ ከተገኘ ክፍያው እንደሚፈጸምለት ተናግረዋል፡፡

መስፈርቶቹን የማያሟላ ከሆነ ከሚከፈለው ላይ እንደሚቀነስ፣ የሚሰጠው አገልግሎት ከ60 በመቶ በታች ከወረደ ኮንትራቱ እንደሚቋረጥ በስምምነቱ መካተቱን ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገልጸዋል፡፡

የማኔጅመንቱ የሽግግር ጊዜ የተጀመረው በነሐሴ ወር 2005 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወሱት የቦርድ ሰብሳቢው፣ እስካሁን ድረስ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠሩ መቆየታቸውንና በአጠቃላይ በርካታ ዝርዝር ጥናቶችና ሥራዎች መከናወናቸውን አውስተዋል፡፡

የኃይል አቅራቢው የሥራ ዘርፍ በኢትዮጵያውያን እንዲሁም የአገልግሎት የሥራ ዘርፍ በፓወር ግሪድ በአስቸኳይ እንዲጀመር ከታኅሳስ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ተግባር መገባቱንና ከኃላፊዎች የሚጀምር የሥራ ውድድር በማድረግ ምደባ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ሁሉንም ሠራተኞች ቢበዛ በሁለት ወር ውስጥ አጠቃሎ በመመደብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ለተቋሙ 17,484 ሠራተኞች የሚያስፈልጉ መሆኑን፣ አሁን ያሉት ሠራተኞች የማይበቁ በመሆናቸው 4,100 ሠራተኞች (ኢትዮጵያውያን) ከኢንጂነር እስከ ቲቪቲ ምሩቃን እንደሚቀጠሩም የቦርድ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

ሃያ ሁለት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሚመደቡ መሆኑን፣ 17 በህንዶቹ የተያዙ ኃላፊነቶች መሆናቸውን፣ አምስቱ ግን በኢትዮጵያውያን እንደሚያዙ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ በኢትዮጵያውያን እየተተኩ እንደሚሄዱና ከሁለት ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ ቦታው በኢትዮጵያውያን እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ሁሉም የኃላፊነትም ሆኑ ተራ የሥራ መደቦች በውድድር እንደሚሰጡ፣ ችሎታ ያለው እንደሚቀጥል፣ ችሎታ የሌለው ቦታ እንደማይኖረው ጠቁመዋል፡፡

የዓለም አቀፍ አበዳሪዎችን ሥጋት በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ፣ የፋይናንስ አከፋፈልን በሚመለከት የትኛው ተቋም የትኛውን ክፍያ ማከናወን እንዳለበት የተጠና መሆኑንና ገንዘብ ሚኒስቴርም በጥናቱ የተካተተ እንደነበር በመጠቆም፣ ብድር ሰጪዎችን ግራ የሚያጋባ ነገር እንደሌለና ‹‹መቸኮል አያስፈልግም›› የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ዶ/ር ደብረ ጽዮን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሠራተኞች በዝምድና የተሳሰሩ በመሆናቸው የአንድ ኃላፊ ዘመድ ሲሞት በርካታ ቢሮዎች ተዘግተው ይውሉ እንደነበር በመጠቆም፣ በቀጣይ ስለሚኖረው በዝምድናና በጥቅማ ጥቅም የመመደብ አካሄድ ላይ የተደረገ ጥንቃቄን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “በፊት ሊኖር ይችላል፡፡ ዝምድና ስንቆጥር አንውልም፡፡ እንዳለም ይሰማል፡፡ አሁን ግን ባል፣ ሚስትና ልጅ ቢኖሩ፣ የሚመደቡት የወጣውን መሥፈርት ማሟላት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ይኼ መስፈርት ደግሞ የነበረውን ያልተገባ ትስስር ይበትነዋል፤” ብለዋል፡፡
 

ተዛማጅ ጽሁፎች

India blames Ethiopian side for delays in recruiting staff for power-grid project; firm delays takeover
 

%d bloggers like this: