ለመለስ መታስቢያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ5 ሄክታር በላይ ፓርክ በጉለሌ ሊያስገነባ ተቋረጠ: ለልማት ብድር ከተያዘ ገንዝብ ላይ – የሕወሃት ወይንስ የመንግሥት ውሳኔ? የባንኩ ግንኙነት ምንድነው?

24 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያነት ለሚያሰራው ፓርክ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳድር ጋር ውል ፈጸመ፡፡ በጉለሌ ክፍል ከተማ የሚስራው የመስክ መታሰቢያ ፓርክ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለ 21 ዓመታት ሃገሪቱን የመሩበትን ጎዳና እንዲሁም የአቶ መለስን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ባንኩ የመለስ መታሰቢያ ፓርክን ለማስገንባት መነሻ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የአመራር ዘመን በሀገሪቱ የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች መሆናቸውን ነው የኢትዮጵያ ልማት ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረ የተናገሩት፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ አቶ ለአለም ተረፈ በበኩላቸው ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በአለም አቀፍ መድረኮች ሲሟገቱለት የነበረውን የአረንጓዴ ልማትን ጨምሮ ሌሎች ጥለዋቸው ያለፉ አሻራዎችን የሚያስታውስ ፓርክ ይገነባል ብለዋል፡፡

ፓርኩ ከ5 ሔክታት በሚበልጥ ቦታ ላይ የሚሰፍር ሲሆን ፥ ግንባታውም በአፋጣኝ እንደሚጀመር መገለጹን የዘገበው ኤሬቴድ ነው፡፡

ምንጭ፦ ፋና
 

የአዘጋጁ ትዕዝብት:

    የኢትዮጵያ የልማት ባንክ ለሕወሃት ጄኔራሎች ቪላና ትልልቅ ፎቅ ቤቶች አሰርተው እንዲያከራዩ ያስቻለ በመሆኑ፡ የልማት ትርጉም የጠፋበት አካል መሆኑን ግልጽ አድርጓል። ከመለስና ከጄኔራሎቹ ጋር ተመሳጥሮ አገራችንን ስያስበዘብዝ ክርሟል። አሁን ደግሞ ይህንን ፓርክ ለማሠራት ጥቂት የሕወሃት ባልሥልጥኖች በሕዝብ ህብትና ንብረት ፈራጅ የሆኑበት ሁኔታ ባንኩ አንዳንድ ለውጦች እንዲያደርግ ግድ ይላል። ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎች ናቸው፦

    አንደኛ ስሙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መሆኑ ቀርቶ የሕወሃት ጄኔራሎች የንግድ ባንክ እንዲባል፡

    ሁለተኛ፡ የሕወሃት አሠራር አሁንም በአባላቱ መካከል መጠቃቅም ስለሆነ፡ የሚዘርፉትን ይዝረፉ በጋራ ሆነው፡ ተጠራርገው ተጠያቂ ሲደረጉ፣ በተረፈው ላይ ተመስርቶ አገር መገንባት ይቻላል። በቀላሉ የማይታለፈው ግን አገርን በወቅቱ እየሸራረሸፉ፣ ከፍተኝ ገንዘብ ለሚከፈላቸው ሽያጭ ላይ ስለሆኑ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍፃሜያቸውን ለማፋጠን ቆርጥ መነሳት ብቻ ነው የሚያስፈልገው!

    እስከዚያ ድረስ ግን፡ ዐይናችን እያየ በሃገራችን ላይ በሕወሃትና ግብረአበሮቹ ገና ይህንን የመሰለ ብዙ ዘረፋ ይፈጸምባታል!በመለስ ፓርክ ስም ገና ተስባስበው መጋጣቸው፡ ምናልባትም ችግሩ እየባስበት ያለውን ሕዝብ ቁጣና ቁርጠኝነትን ይቀስቅስ ይሆናል!

 

%d bloggers like this: