ለምን ይሆን ለፕሮፓጋንዳ የማያመቹት በውሃና ሳኒቴሽን ረገድ ያሉት የኢትዮጵያ ችግሮችና እውነተኛ ሥዕሉ ለሕዝቡ በሃቅ የማይገለጸው?

5 Feb

 ኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አቅምን 85% ለማድረስ ያቀመጠችውን  የተ.መ.ድን ግብ በመጭው ዓመት ልታሳካ ትችላለች :: ዩኒሴፍ ተወካይ መልስውም፡ በአገሪቱ ልዩ ድጋፍ በሚሹት ክልሎች በአፋር፤ ሶማሌ፤ ቤኒሻንጉልና  በጋምቤላ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በስፈው ይስተዋላይላል።


ኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አቅምን 85% ለማድረስ ያቀመጠችውን የተ.መ.ድን ግብ በመጭው ዓመት ልታሳካ ትችላለች (የዩኒሴፍ ተወካይ)። መልስውም፡ በአገሪቱ ልዩ ድጋፍ በሚሹት ክልሎች በአፋር፤ ሶማሌ፤ ቤኒሻንጉልና በጋምቤላ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በስፈው ይስተዋላል ይላሉ። መንግሥት ያለፈው መረጃ ሀስተኛ ነው፤ በአንዳንድ ሥፍራዎች የተተከሉት የውሃ ኢንፍራስክቸሮችና መሠረተ ልማቶችም የማይሰሩ መሆናቸውን ከዚህ ጋር አገናዝበውት ይሆን?


[click to magnify]
 
በከፍያለው ገብረመድህን – The Ethiopia Observatory

ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ድረጃ፡ ዛሬ ክሰሜን እስክ ደቡብ፡ ከምዕራብ እስክ ምሥራቅ፡ በመሃል ሃገርና በዋና ከተማችን ከፍተኛ የውሃ ዕጥረት ተከስቷል። ለዚህም ዋናው ምክንያትነት ሀገሪቷ እጅግ አስፈላጊውን በቂ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች ሳይኖሯት ወድ 21ኛው ክፍለ ዘመን መሽጋገሯ ሲሆን፡ ይህንንም ዛሬ በአስደንጋጭ ድረጃ አግጦ እንዲመጣ ያደረገውና የመንግሥትን የባወጣው ያውጣው አሠራር ያጋለጠው የሕዝባችን ቁጥር በከፍተኛ ድረጃ መጨመር ነው።

እንደተለመደው፡ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እስከዛሬ ድረስ የሀሰት ዳታና ስታቲስቲክስ እየፈጠሩ፡ የውሃ መሠረተ ልማት ተሠርቷል፡ ተዘርግቷል እያሉ ኖረዋል። የዚህን ጎጂነት ለመገንዝግ ያልቻሉ ባሥልጣኖችና ፓለቲከኞቻቸው በቀኑ ድላቸው በመርካት፡ አገራችንን በሁሉም መስክ ለጉዳት ዳርገዋታል። ይኸው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ 24 ሰዓት ውህ የሚያገኙት ቤቶችና ዜጎች ቁጥር እየተመናመነ መምጣቱ፡ አስፈሪ ከመሆን ውጭ የዕለቱ ወሬ ከመሆን ተሸጋግሯል። ፍሳሽ የራሱን መንገድ በማጣቱም፡ በተለይም አዲስ አበባና ዙሪያዋ ላይ ባሉ ውስጥብክለትን አስከትሏል። ብክለቱ ወደምግብ በመሸጋገሩ ለሕዝቡ በተለይም ለሕጻናት የጤና ጥንቅ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት ማስጠነቀቂያውን ለመንግሥት በ 2010 አስምቷል። ይባስ ብሎም፡ አዲስ አበባ የተስባስቡት ኬምካሎች የሚጠቀሙ ድርጅቶች የአዲስ አበባን ብክለት አምጥቀውታል።

በዚህም ምክንያት፡ ትልቅ ሕልም ያላት ኢትዮጵያ ትልሟን ከሃሳብ ደረጃ አሳልፋ የምግብ፡ የመኖሪያ ቤቶች፡ የመንገዶች፡ የሸቀጣሸቀጦች፡ የሠለጠኑ አስተማሪዎች፡ ሐኪሞች፡ ጋዜጠኞች፣ ዳኞች፡ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ስልክ፡ ኢንተርኔት፡ ዘመናዊ ላቦርቶሪዎች…) ዕጥረትቶችና የመልካም አስተዳደር ዕጥቶች ወዘተ፡ ሰለባ እንድትሆን ከመገደድ ባሻገር፡ የውሃ ዕጥረትና የመጸዳጃ ቦታዎች ዕጦት ከተማዋን ለተራው ሕዝብ በሁሉም በኩል አስጨናቂ አድርጓታል።

እንደተለመደው፡ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እስከዛሬ ድረስ የሀሰት ዳታና ስታቲስቲክስ እየፈጠሩ፡ ብዙ የውሃ መሠረተ ልማቶች ተሠርተዋል:ተዘርግቷል እያሉ፡ ባዶነትን ሲያስተጋቡ ክርመዋል። የዚህን ጎጂነት ለመገንዝብ ያልቻሉ ባሥልጣኖችና ፓለቲከኞቻቸው በቀኑ ድላቸው በመርካት፡ አገራችንን በሁሉም መስክ ለጉዳት ዳርገዋታል። በዚህም ምክንያት፡ ትልቅ ሕልም ያላት ኢትዮጵያ ትልሟን ከሃሳብ ደረጃ አሳልፋ የምግብ፡ የውሃ፡ የመኖሪያ ቤቶች፡ የመንገዶች፡ የሸቀጣሸቀጦች፡ የሠለጠኑ አስተማሪዎች፡ ሐኪሞች፡ ጋዜጠኞች፣ ዳኞች፡ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ስልክ፡ ኢንተርኔት፡ ዘመናዊ ላቦርቶሪዎች…) ዕጥረትቶችና የመልካም አስተዳደር ዕጥቶች ወዘተ፡ ሰለባ ወደምትሆንበት አግጣጭ ገፍትረዋታል።

CIT Minister Debretsion Gebremichael in parliament turning iron hot in May 2013 (Credit: The Reporter)

CIT Minister Debretsion Gebremichael in parliament turning into hot live wire in May 2013 (Credit: The Reporter)

ውሃን በተመለከተ፡ ለሃገሪቱ ጠቃሚ ከሆነው፡ ከመለስ ፍጻሜ በኋላ፡ ለጥቂት ወራት ትንሽ የነፃነት አየር ለመተንፈስ ተውተርትሮ የነበረው ፓርላማ በተውካይነትና ተቆርቋሪነት ስሜት ጉልበቱን ፈርጠም ለማድረግ ሞክሮ ነበር። ያለመዱትን ጥያቄዎች ለመስማት በመብቃታቸው፡ አንዳንድ ባልሥልጥኖች ከተደፈርንና አትንኩን ባይነት በመነጨ ስሜት እዚያው በቴልቪዥን መስኮት ቁንድ እስከማብቀል የደረሱ ነበሩ (ዶ/ር ደብረጽዮን ለምሳሌ)፡ እንዲሁም፡ ሥራውንም አልፈልገውም እንዲህ ከመዋረድ ያሉት የኢንቭስትመንት ሃላፊው አባባል ጭምር ዓመት ያልሞላው ትውስተቻን ነው።

ሰኔ 14፣ 2013 ፓርላማው በአባሉ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር አማክይነት አንድ ከባድ ጥያቄ ውሃን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት አዳመጠ (ቪዲዎን ይመልከቱ)። በአጭሩ የጥያቄው ይዘት የሚለው፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እስክዛሬ ድረስ ስለውሃ ሲነገር የኖረውና ተሠራ የሚባለው በአብዛኛው ተረት ተረት ነው የሚል ነበር። ኃይለማርያምን ከጉድ ያተረፈው የፓርላማ አባላት አንድ ሣምንት ከስብሰባው በፊት ጥያቄዎቻቸውን በጽሁፍ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ለማቅረብ መገደዳቸው በመሆኑ: ኃየለማርይም መልሳቸውን ሽምድድ አድርገው ነበር የቀርቡት። ጥሩነቱ ግን ሀቁን በማመን፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግቡን መቶ በመቶ አልፈናል ከሚለው የኢሬቴቪ ቃለመጠይቅ በራቀ: በጠያቂዋ እንደቀረበው፡ የተሠራው ሥራ ውጤት 60 በመቶ መድረሱን እንኳ የሚሳለቅበት ነበር።

ይህንን አሰመልክተው ሙሉ ገብረእግዚአብሔር ፓርላማው ውስጥ ጥያቄያቸውን የውሃ ሚኒስትሩ ዓለማየሁ ተገኑና በወቅቱ የመብራት ሃይል ሥር አስኪያጅ የነበሩት ምህረት ደበበ በተገኙበት እንዲህ ሲሉ አቀረቡ:: ፦

    “ስለፕሮጄክቶች ሥራ አፈጻጸም የተነሳውን በአቅም ውሱንነት ለመሸፋፈን የተደረገውን ሙከራ አላምነውም፤ አልቀበለውም። ከመንግሥት አንጻር ባየው ይኮስኩስኛል። ችግሩ ሁላችንም ውስጥ ነው ያለው። ከአስተሳስብ ችግር የመነጨ ነው። ለዚህም ነው አስቸኳይ የአስተሳስብ ለውጥ የሚያሻን… ሪፕርታችሁን በከፍተኛ ትኩርት ተመልክቼዋለሁ። ሀቀኛ አለምሆኑንም ተገንዝቤያለሁ። የሥራ ውጤታችሁም በማዕከላዊ ግምት እንኳ 60 ከመቶ መብለጡ እጠርራእጥራርለሁ።”

ይኸው ጥያቄም መንግሥትን ክፍኛ የኮረኮረ በመሆኑ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም፡ ከላይ እንደተጠቆመው ጥያቄው ተደግሞላቸው የተገአጣጠሙበት ነበር።

በገራችን ላይ በ2010 የኢትዮጵያ ታርጌት በእያንዳንዱ 0.5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የውሃ ቀረቤታ ለመፍጠር ነበር። አቅም በሌለበት የሚሞከር ዳንኪራ መስባበር እንደሚያስከትል ሁሉ፡ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያ መስከረም 21፡ 2011 የተባበሩትን መንግሥታትን የውሃ አቅርቦትና የመጸዳጃ ታርጌቶችንና የልማት ግብ መምታቷን ያላንዳች ዕፍረት ለዓለም አበሠረች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃየለማርያም፡ በዳታ አቀራረብ በኩል ያለውን ችግር በማንሳትና በመተንተን፡ እንደተባለው የኢትዮጵያ ግኝት 78 ከመቶ ተብሎ የተሰጠው ሪፓርት ሃስተኛ መሆኑን አረጋግጠው: ወደ 61 በመቶ አሽቆለቆሉት። ሙሉ ለሙሉ አጥጋቢ ወይንም ትክክል ናቸው ለማለት ቢያስችግርም. ሁለት ነግሮችን ጠቀሱ፡-

    (ሀ) ይሠራሉ ይተባሉት የውሃ መሰረት ልማቶች አይሠሩም፡

    (ለ) ብረታ ብረት ፈላጊዎችም የተተከሉትን መሠረተ ልማቶች እየነቀሉ አፈራርሰዋቸዋል።

ዋናው ቁም ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት የሚሰጡትን ዳታና ቁጥሮች እንደወረደ ከመጎርመድ በፊት ቆም ብሎ ማስብ በመንግሥት ወዳጆችም ሆነ የዚህ መንግሥት ተቃዋሚዎችም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የውጭ መንግሥታትም ሆኑ የውጭ ድርጅቶች መንግሥት የሚስጣቸውን ብቻ ለመጥቀስ ስለሚገደዱ፡ በመስክ ጥናትና ምርምር ካካሄዱት ውጭ እነዚህ የሚሉትንም ጥያቄ ውስጥ ማስገባቱ ተገቢ ነው።

ዛሬ ይህንን ጽሁፍ ለመክተብ ያነሳሳኝ ምክንያት፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አንድ አሳዛኝ ዳንኪራ በማቅረቡ ነው። ይኸውም አዲስ አበባ ውስጥ የዩኒሴፍ ተወካይ የሆኑትን ዶ/ር ፒተር ሳላማን በመጥቀስ፡ ኢትዮጵያ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ረገድ የምእተ አመቱ የልማት ግቦችን ልታሳካ ትችላለች-ተመድ የሚል የዜና ዘገባ በማቅረቡ ነው።

እነዚህ ግቦች ግን እንዴት ተግባራዊ እንድሚሆኑ የተስጠ ተጨባጭ መረጃ የለም። አንድ ለዩኒሴፍ ጠቃሚ የሚሆን ፕሮፓጋንዳዊ ጉዳይ ግን፡ ዩኒሴፍ ከየት ባመጣው ገንዘብ ነው የኢትዮጵያን የውሃና የሳኒቴሽን ግብ ለማፈጽም የሚችለው የሚለው ጥያቄ መልስ የለውም። ዩኒሴፍ ውህ በመቅረቡ ሳኒቴሽን በመሻሻሉ በሕጻናትና እናቶች ደህንነት ውጤት ተካፋይ በመሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ሚና ይኖረዋል እንጂ በተባበሩት ድርጅት ስም በውሃ ጉዳይ ላይ ሙሉ ውክልና የለውም፤ ስለሆነም፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መሪ ሚና ተጫዋች ሊሆም አይችልም።

ኢትዮጵያም ባላት ፕሮግራም መሠረት: በዚህ ጉዳይ ላይ ከዓለም ባንክና ከጃፓን መንግሥት ጋር ነው አብራ በመሥራት ላይ ያለቸው። ከአውሮፓ የልማት ባንክ ጋር 15 ከተሞች ተጠቃሚ ለማድርግ ያስችል የነበረው የውሃ ፕሮጄክት በመንግሥት ፈጥኖ ተግባራዊ አለማድረግ ምክንያት ባንኩ ለመሰርዝ ተድዷል።

እንደተለመደው፡ ፕሮጄክቱን ተግባራዊ ማድረግ አቅቷቸው ብድሩ ሲስረዝ፡ የኢትዮጵያ ባልሥልጣኖች፡ እራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማትረፍ፡ ውስጥ ለውስጥ ባንኩንና የቀጠሯቸውን የውጭ ኮንስልታንቶች ስም ማጥፋቱን ተያያዙት።

ስለውሃ አቅርቦትና ኢትዮጵያን ስላጋጠሟት ችግሮች፡ መስከረም 20፡ 20133 ላይ Addis Abeba’s renewal, massive inequality, grand land heists & the housing Russian roulette project likely to exact costly retributions – Part I በሚል ርዕስ በዚህ ገጽ ላይ ያወጣነውን ቢመለክቱ መጠነኛ ግንዛቤ ይፈጥራል።

ሳኒቴሽንን በተመለከተ፡ ሐምሌ 2013 ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባልሥልጣን በሰጠው መረጃ መሠረት፡ ኢትዮጵያ ማድረግ የቻለችው 22.3 ሚልዮን ክ/ሚ ፍሳሽ (21 ከመቶ) ነው። ስለሆነም፡ በምን ዐይነት አቋራጭ ወስዳ፡ በተለይም ኤኮኖሚዋ ተዳክሞ፡ ገንዘብ በሌላት ጊዜና ብድሩን ሁሉ ባቡሩ፡ ብረታ ብረት ኢንጂኔሪንግ፡ EFFORT፡ የአዲስ አበባ መንገዶች፡ ስኳር ፋብሪካዎች ወዘት፡ በወጠሩበት ወቅት፡ ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግ የምትችለው።

በተጨማሪም፡ እስከዛሬ ድረስ በትልቅነቷ እየተዋበች መምጣቷ ብዙ የሚነገርላት አዲስ አበባ እስካሁን የውሃን ፍሳሽ ካርታ እንኳ የሌላት ከተማ ናት። እንደአዲስ ተቆርቋሪ ከተማ በ126 ዕድሜዋ ፍሳሹንም ለማጓጓዝ መስመር እስክ ቃሊቲ ለመዘርጋት ስላበት፡ አዲስ ፎርቹን ሐምሌ 14፡ 2013 ባልሥልጣኑን ጠቅሶ እንደዘገበው፡ በሁለት ዓመታ ውስጥ የፍሳሽ መንገዱን ክስድስት ኪሎ ጀምሮ፡ በአራት ኪሎ በኩል፡ መርካቶን ይዞ ወደኮልፌ፣ 22 ማዞሪያ ድረስ፡ እንዲሁም ካዛንችስና ቦሌን እንዲጠቀልል ተደርጎ ለማሠራት ጨረታ ወጥቶ: በአንድ በኩል ስለተክኖሎጂው በሌላ በኩል ደግሞ፡ የብድር ምንጭ በማፈላለግ ላይ ትገኛለች።

ከላይ የተጠቀሱት አብዛኛዎች በሃሳብና ፕላን ደረጃ አርኪ ቢመስሉም: በተግባር አተረጓጎም ግን ባለቤት አጥ የሆነችው አገራችን አገራችን ከፍተች ችግር ላይ ናት። ብዙው ባልሥልጣን ዛሪውን በልቶ ቀኑን ለመግፋት የመሻት ብልግና ስለተጸናወተው: በሌላ በኩል ደግሞ፡ መካከለኛ ረጃ ላይ የሚገኘው ሠራተኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙያ የክሠረና ዋጋ ያጣ ምንዛሪ በመሆኑ፡ ከነዚህ ሰዎች ጋር ከመላተምና ችግር ውስጥ ከመውደቅ ይልቅ፡ በስላም ውሎ በስላም ወደቤቱ መመለስን የመረጠ ሆኖአል። ሰውበላ ካድሬዎቹ ነገን፡ መጭውን ትውልድና የአገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈታ፡ ቁማር ያደረጉት ይመስላል።

ጋዜጠኞችስ ቢሆኑ፡ ውዳሴ እንዲያበዙ ጫና እንዳለባቸው ቢታወቅም፡ ሕዝቡን የሚያዘናጋ መረጃ ማቅረቡ ነገ ከተጥያቂነት ማምለጥ የሚያስችል ኢንሹራንስ ፓሊሲ እንደሌለው ቢገነዘቡት ጠቃሚ ነው። ሕጉ ደብዳቢውን ብቻ ሳይሆን፡ አጋጋዮቹንም የሚቀጣበት አንቀጽ እንዳለው፡ ክተ.መ.ድ የሩውንዳ ፍርድ ሁኒታና ተይዘው ለብዙ ዓመታት ከተፈረደባቸው ጋዜጠኞች ጽዋ ፈታ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል። ።

ሌላው ቢቀር፡ ከ1998 ጀምሮ፡ የአዲስ አበባ የውሃ ችግር እየተባባስ እንደሚሄድ፡ የተባበሩት መንግሥታት ሲያቀርብ የክረመውን ሪፖርቶች ማጋለባጡ ለኢዜአ ለሚጻፈው ሪፖርትና ሕዝብን ለማስተማር ለሚደረገው ጥረት (የሚዲያ ተግባር እርሱ በመሆኑ) ጠቃሚ በሆነ ነበር። ሌላው ቀርቶ፡ በ1212/1213 በወጣው ሮፖርቱ ተ.መ.ድ. አዲስ አበባ፡ ዳሬስላም፡ ኢባዳን፡ ሉዋንዳ፡ ሌጎስና ናይሮቢ በውህ ጥም ሲሰቃዩ የሚኖሩ ከተሞች በማለት መዘገቡ፡ ዜናውንና የዩኒሴፍን አባባል ወደትክክለኛ አተረጓጎም ባመራ ነበር።

የኢዜአ ጋዜጠኝ ከዚህ ከላይ በጠቅስኩት ዜና ውስጥ ምን መረጃ ለዝሕቡ አቅረብኩ ብሎ በሳላም እንደሚተኛ ግራ ይገባኛል!
 

%d bloggers like this: