የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 50 አዳዲስ አውቶብሶች እንደሚያስማሩ የመንገድና ትራንስፖርት ኃላፊዋ ትብለፅ አስግዶም ገለጹ

12 Feb

የአዘጋጁ አስተያየት

  የሥርዐት ዕጦትን አውቶብሶችንና መንኮራኩሮችን በማንጋጋት መፍትሄ ማግኘት አይቻልም – ምናልባትም እንደ ብረታብረት ኮርፖሬሽን መስል ብልሹ የሕወሃት ወታደራዊ መኮንኖች ከማበልጸግ ውጭ።

  አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ፡ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ተግባር – በማንኛውም መስክ፡ ዘረኝነትን ማጥፋት ነው። ሀገር ማሰተዳደር ማለት ሕወሃት እንደሚያደርገው የትውልድ መንደር በመቁጠር መስባስብ ሳይሆን፡ ሙያና ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያውን ከብኄረስብ ውጭ በሙያና ችሎታቸው ተወዳድረው እንዲሠሩ ቢደረግ፡ ለሀገርና ወገን ጠቃሚ የሆነ ሥርዐት ለመዘርጋት ጥሩ መነሻ ይሆናል!

  ያን ጊዜ የአዲስ አበባም ሆነ የአገሪቱ በአጠቃላይ የትራንስፖርቱም፡ የፍትሕ እጦት፡ የርሃቡም፡ የስልኩም፡ የመንግሥታዊ ቫዮለንስና የፕሬስ ነጻነት ችግሮች፡ መንገዶች በየቀን እየገነቡ በማግሥቱ የማፍረስም ጉዳይ በበዙ ይቀንሳል፡ ብሎም ያከትማል!ሕዝቡም ያን ጊዜ የነጻነት አየር መተንፈስ ይጀምራል!

ዕድሜ ለሕወሃቱ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና መንስፍን ኢንጂኔሪንግ በየቀኑ ደማቅ ባንዲራዊ ቀለም የተቀቡ ለወራት የሚሠሩ አውቶቡሶች ሃገራችን ታመርታለች (ክሬዲት ኤፍ.ቢ.ሲ.)

ዕድሜ ለሕወሃቱ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና መንስፍን ኢንጂኔሪንግ በየቀኑ ደማቅ ባንዲራዊ ቀለም የተቀቡ ለወራት የሚሠሩ አውቶቡሶች ሃገራችን ታመርታለች (ክሬዲት ኤፍ.ቢ.ሲ.)

Posted by The Ethiopia Observatory

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ 50 አውቶብሶች በሁለተኛው ግማሽ አመት እንደሚሰማሩ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ትብለፅ አስግዶም እንዳሉት በተጠናቀቀው ግማሽ አመት 50 አውቶብሶች ወደ ስራ ማሰማራት ተችሏል። በቀጣዩ ግማሽ አመት ተጨማሪ 50 አውቶብሶች የሚሰማሩ ሲሆን ፥ በ2007 ደግሞ 250 አውቶብሶችን ለማሰማራት አቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎን የታክሲ ዞናዊ ስምሪት ላይ ቁጥጥሩን በማጠናከር የተሻለ አገልግሎት አንዲኖር አንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። በመካከለኛ ጊዜ እቅድም የፈጣን አውቶብስ ለማስጀመር የጥናት ስራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ነው ሃላፊዋ የተናገሩት።

እነዚህ ስራዎች በሚቀጥለው አመት ከሚጠናቀቀው የባቡር መስመር ዝርጋታ ጋር ተዳምሮ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ያቃልለዋል ብለዋል።
 

2 Responses to “የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 50 አዳዲስ አውቶብሶች እንደሚያስማሩ የመንገድና ትራንስፖርት ኃላፊዋ ትብለፅ አስግዶም ገለጹ”

Trackbacks/Pingbacks

 1. በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን? | THE ETHIOPIA OBSERVATORY - February 22, 2014

  […] ቀላል ቢሆንማ፡ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ኃላፊ ወይዘሮ ትብልጽ አድ… እንደሚያስቡት በያዓመቱ 50 አዳዲስ አውቶቡሶችን ለከተማው […]

  Like

 2. በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን? | justiceethio - February 25, 2014

  […] እንደዚህ ቀላል ቢሆንማ፡ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ኃላፊ ወይዘሮ ትብልጽ አስ… […]

  Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: