በ10 ዓመታት በብር 18.3 ቢሊዮን ከተሸጡ የመንግሥት ድርጅቶች የተሰበሰበው ብር 4 ቢሊዮን ብቻ ነው – እጅግ አሳፋሪና አሳዝኝ ተግባር!

23 Feb

የአዘጋጁ አስተያየት

  ከኢትዮጵያ ለሥራ ጉዳይ ውጭ ህገር መጥቶ ያገኘሁት ብዙ ልምድ ያለው የፖለቲካል ኤኮኖሚ ሊቅ እንዳጫወተኝ ከሆነ: ኢትዮጵያ ውስጥ በፖሊሲ ደረጃ ብዙ ነገሮች እየተሞከሩ ነው። ነገር ግን በውጤት ደረጃ ብዙም አያመረቃም አለኝ። አንድ ትልቁ መስናክል – መንግሥትም ሊነካካው የማይፈልግና የማይደፍረው – በአምራቹና በሸማቾች መካከል የክተሙትና በተለያየ መንግድ የኤኮኖሚና የፖለቲካው ተጠቃሚ የሆኑት መለስ ዜናዊና ሕወሃት የተከሏቸው መዝባሪዎች ናቸው። ለፈለጉት ነገርና ለድርጅቱም ፍላጎት መሳካት እስክኃይል አጠቃቀም (violence) የሚደርሱ በቡድኖች የተደራጁ ናቸው።

  እነዚህ ግለስቦች ፓለቲካው ያላበሳቸውን ሥልጣን ወይንም መከታ በመጠቀም፡ በአንድ በኩል አምራቹን ከእርሻና ፋብሪካ በር ተስልፈው ምርቱን በርካሽ ይቀበሉታል። በሌላ በኩል ደግሞ፡ እነዚሁ ግልስቦች ኣራሳቸውን ወደ አክፋፋይነት በመለወጥ: ያመጡዋቸውን ምርቶችና ሸቀጦች በግልገሎቻቸው አማካይነት በእጥፍ ድርብ ትርፍ ለሸማቹ እንዲቀርብ ያደርጋሉ። እነዚህ የሕወሃት ግልገሎችና ባለሟሎቻቸው በሚፈጽሟቸው የፖለቲካና የኤኮኖሚ ወንጀሎች አራት ወገኖች ይጠቃሉ። እነዚህም፡

   (ሀ) ባለሃብቱ ባለፋብሪካና አምራቹ ገበሬ

   (ለ) ሽማቾቹ የከተማና የገጠር ነዋሪዎች

   (ሐ) የግብር ገቢ የሚያጣው መንግሥት፡ እና

   (መ) የሀገሪቱ ፖአሊሲ በሚጠበቀውና በሚፈለገው መጠን መሠረተ ሠፊ ዕድገት ለማምጣትና የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል አለመቻሉ በክፌል ለችግሮቻችን ተጠቃሾች ናቸው።

  እነዚህ የሚያስከትሏቸው ችግሮች መገለጫ ደግሞ የዋጋ መናር (36 ወሮች በተርታ ዕጥፍ ድርብ ግሽበት እስከ የካቲት 2013 ድረስ)፤ የመግዛት አቅም መውደቅና የኑሮ ውድነት፤ የጥቂቶች ባጭር ጊዜ መበልጸግና የሀገሪቱን ፓሊሲ መቆጣጠር፤ የባለሃብቱ ተገቢውን ትርፍ ባለማግኘት ምክንያት ፋብሪካውን እርሻውን ከማስፋፋት መቆጠቡ፤ የምርት ዕጥረቶች መስፋፋት፤ የጉበኝነት መስፋፋት፤ የሕግና የፍርድ ሥነ ሥርዓት መጓደል፤ወዘተ

  የእነዚህ ድምር ደግሞ ሕዝብ በመንግሥት ተቋሞች አሠራር መበላሸት ምክንያትና (bad governance) በመንግሥት ላይ አመኔታ ከማጣቱም ባሻገር፡ መንግሥት የሚፈልጋቸው ጉዳዮች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ያለመተባበር አዝማሚያ ይሳያል። ይህም መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ይጎዳል። የሕወሃት ውርውሮች ከሰዓቷ ጥቅማቸው ባሻገር ማየት ስለማይችሉ፡ ዛሬ እነርሱ ብቻቸውን በጎረሱ መጠን፡ ላሚቷ በየደቂቃው እንዳጋተች እንድምትጠብቃቸው በመተማመን: የዘረፋ ስልታቸውን ከማሻሻል ባሻገር ለአገርም ሆነ ለሌላው ሕዝብ ደንታ የላቸውም፡፡

  ሌላው ቀርቶ የዋጋ ግሽበቱን ጉዳት ከሕዝቡ ላይ ለመቀነስ በመንግሥት ክፍያ የሚገባውን ስንዴ፡ ስኳር፡ ዘይት፡ ወዘተ ሳይቀር በእነርሱ ‘የመቅረጥና’ ቀዳሚ ተጠቃሚ መብቶች ምክንያት፡ የገባውም ምርት ውጤት ሁል ጊዜ ወደአትራፊ ቸርቻሪዎች እጅ መውደቁን መንግሥት በተደጋጋሚ አምኗል – ምንም ለማድረግ ባይችል ሳይሆን ከልብ አለመፈለግ ምክንያት – ባለሥልጣኖቹ ራሳቸው የጥቅም ተቋዳሾች ናቸውና!

  ከዚህ በታች የሠፈረው የሪፖርተር ዘገባም ይህንኑ የሚያጥናክክር ነው። የመንግግሥት ባልሥልጣቶች የጥቅም አሳዳጆች በመሆናቸው፡ በሚያገኙዋቸው የገንዘብና ሌሎች ጥቅሞች ታወረው፡ የመንግሥት ንብረቶች የተሸጡበትን ዋጋ እንኳ ከዓመታት በኋላ እንኳ መለስ በለው ለማስከፈል የሚያስገድዳቸው የሕግም ሆነ የሕሊና ግፊት ስለሌሉባቸው ሀገራችን ለምዝበራ ተጋልጣ ትገኛለች!

  በመሆኑም፡ እስከዛሬ ድረስ የሕወሃት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለሃገራቸን ያተረፈው ነገር ቢኖር፡ መንግሥታዊ ውድቀትን፡ የሃገርን ሃብቶች ምዝበራ፤ ዘረኛ አገዛዝ፤ አፈና፤ ጸረ-ዲሞክራሲያዊነትና ጸረ-ነፃነተኛነትን ነው!

  ለዚህ በምክንያትነት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኃላፊ የሰጡት መልስ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በአንድ ጊዜ ከፍሎ ለመግዛት አዳጋች ስለሚሆንባቸው፡ ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ ነው ያሉት እጅግ አሳዛኝና ሙሉ የችግሩን ምንጭ የማያነጸባርቅ ነው።

  ክፍያ ቢራዘምላቸውስ የተወሰነ የጊዜ ገደብ አይስጥምን? ለምንድነው ሼክ አላሙዲ – በዓለም ታውቂው ቢልዮኔር – እዚህ ካታጎሪ ውስጥ ገብቶ፡ 10 –15 ዓመታት ሙሉ ዕዳውን ሳይከፍል፡ ድሃ አገራችንን ማላጋጫ ለማድረግ የበቃው?

  እንደ አቶ በየነ ገብረመስቀል አባባል የእርሱም ሜጋ ኩባንያዎች እንደ ትናንሽ “የችርቻሮ መደብሮች” ተቆጥረው ይሆን? ወይንስ ይኸ የሕወሃት ወገን ጠቃሚ የንግድ አሠራር ዘይቢ (business model)?

===============================================
 

Posted by The Ethiopia Observatory
By The Ethiopian Reporter

  –   ባለፉት 20 ዓመታት 365 የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ተዛውረዋል

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ወደ ግል ካዛወራቸው ወይም ከሸጣቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች 18 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ቢኖርበትም፣ የሰበሰበው ገቢ ግን አራት ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል የኤጀንሲውን የስድስት ወራት ወይም ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. በመሥሪያ ቤታቸው መግለጫ በሰጡበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እንዳስረዱት፣ እስከ 1996 ዓ.ም. ድረስ ወደ ግል ከተዛወሩ የልማት ድርጅቶች 3.3 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል፡፡ ከ1997 ዓ.ም. እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ 15 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል፡፡ በድምሩ 18.3 ቢሊዮን ብር መገኘቱንና የተሰበሰበው ገቢ ግን አራት ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 365 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል መዛወራቸውን ወይም መሸጣቸውን ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ 85 በመቶ የሚሆኑትን ድርጅቶች የገዙት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ይኼ ደግሞ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲያድግ የተመቻቸ ሁኔታ መፈጠሩን እንደሚያሳይ አክለዋል፡፡

ከ1997 ዓ.ም. በፊት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሲሸጡ አሸናፊው ተጫራች ክፍያውን በአንድ ጊዜ ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ ይደረግ እንደነበር ያስታወሱት አቶ በየነ የችርቻሮ መደብሮች፣ ሆቴሎች፣ ሱቆችና የመሳሰሉት ሽያጭ የሚያዋጣ ቢሆንም መጠናቸው ግዙፍ የሆኑ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንዲህ ዓይነት ድርጅቶችን በአንድ ጊዜ ከፍሎ ለመግዛት አዳጋች ስለሚሆንባቸው፣ ከጨረታው ውጪ መሆን መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ለማሳተፍ እንዲቻል ኤጀንሲው በ1997 ዓ.ም. የፖሊሲ ክለሳ በማድረግ፣ የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን በትላልቅ የልማት ድርጅቶች ጨረታ ላይ ሊሳተፉ፤ ከቻሉ ሙሉ ክፍያ፣ ካልቻሉ ከመፈረማቸው በፊት 35 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽመው፣ ቀሪውን 65 በመቶ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከፍለው በማጠናቀቅ የድርጅቱ ባለቤት እንደሚደረጉ አቶ በየነ ገልጸዋል፡፡

የውጭ ባለሀብትን በሚመለከት እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት ተጠቃሚ ለማድረግ ወይም በተራዘመ ክፍያ ተጠቃሚ ለመሆን የሚችለው፣ ነባር ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥ ያለው ሆኖ የልማት ድርጅቱ መግዣ ዋጋ ከአምስት ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ከሆነ ነው፡፡ ይኼንን ያሟላ የውጭ አገር ኢንቨስተር ከሆነ፣ 50 በመቶውን ቀድሞ ይከፍልና ቀሪውን 50 በመቶ ክፍያ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንዲከፈል እንደሚደረግ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

ጨረታ በተደጋጋሚ የወጣባቸው ድርጅቶች ገዥ ስለማጣታቸው የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የጨረታ ካፒታሉ ከፍተኛ መሆን ተጫራቾች በተቋም ደረጃ ተቀናጅተው በቡድን (በኮንሰርቲየም) የመግዛት ልምድ ባለመኖሩ 45 ቀናት ብቻ የተደረገው የጨረታ ጊዜ በማነሱ መሆኑን ገልጸው፣ ጨረታው ወደ 60 ቀናት ከፍ መደረጉንና ለሁሉም ተጫራቾች ይደርሳል የሚል እምነት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

የባህር ዳርና ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ በተደጋጋሚ ለጨረታ ቢወጡም ገዥ አለማግኘታቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የሁለቱም ፋብሪካዎች ዋጋ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ የአቅም ውስንነት ሊያስከትል መቻሉን አክለዋል፡፡

ከቱርክ ኩባንያ የተነጠቁት ሐዋሳና አርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ለአገር ውስጥ ባለሀብት ተሽጠው በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ በየነ፣ በቱርኩ ባለሀብት ላይ ክስ ተመሥርቶ በሕግ በኩል ውሳኔ አግኝቶ አፈጻጸሙን በኤምባሲ በኩል እየጨረሱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወደ ግል ከማይዛወሩት ድርጅቶች መካከል አንዱ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሲሆን፣ አሠራሩን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ጥናት ተጠንቶ መጠናቀቁንና በቅርቡ በጀት ተመድቦ ወደ ሥራ ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አክለዋል፡፡

በኤጀንሲው የሚተዳደሩ 41 የልማት ድርጅቶች መኖራቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በግማሽ ዓመቱ የ7.3 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ሽያጭ ለማከናወን አቅደው 8.5 ቢሊዮን ብር ወይም 116 በመቶ የሽያጭ ገቢ ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከልማት ድርጅቶቹ የተገኘው ገቢ በቂ ስለመሆኑና ኅብረተሰቡ የድርጅቶቹ ተጠቃሚ ስለሚሆንበት ሁኔታ ተጠይቀው፣ ከዕቅዱ አንፃር አፈጻጸሙ መልካም መሆኑን፣ ድርጅቶቹ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ የሚታወቁ መሆናቸውንና ኅብረተሰቡም የምርቶቻቸው ተጠቃሚ ከመሆኑም ሌላ፣ ተቀጣሪ በመሆን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ በመሆኑ ጥቅሙ በተለያየ መልኩ ተደራሽ እንደሚሆን አውስተዋል፡፡

የ2005 በጀት ዓመት ሥራ አፈጻጸምን በምሳሌነት በማንሳት ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ድርጅቶቹ ወደ ግል በመዞራቸው፣ የተሻለ የአቅም አጠቃቀም መኖሩን፣ በመንግሥት ሥር ሆነው ከነበራቸው የሰባት ቢሊዮን ብር ሽያጭ የ4.6 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየታቸውን፣ ኢንቨስትመንትን በሚመለከት ወደ ግል ከተዛወሩ የ3.3 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ኢንቨስትመንት ወጪ መደረጉን፣ ከ14 ሺሕ በላይ ተጨማሪ የሰው ኃይል የሥራ ዕድል እንዲያገኝ መመቻቸቱን አቶ በየነ አክለዋል፡፡
 

%d bloggers like this: