ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ያወጣው መመርያ ተግባራዊነት እንዲዘገይ ተደረገ – ለምን ይሆን?

9 Mar

የአዘጋጁ አስተያየት፡

  ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ክፍተኛ ተጋድሎ እያድረገች ትገኛለች። ከሕወሃት ጄኔራሎችና ከመልዕክተኞቻቸው የተረፈው ጥቂቱ እስከ ድረስ ልማት ላይ እየዋለ ነው።

  በአንድ በኩል ሲታይ፡ ብሔራዊ ባንክ ሊወስድ የንበረው የሕግ ለውጥ እርምጃ ምናልባትም ከሚገመተው በላይ የዘገየና፡ ብዙዎቹ የሥርዓቱ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚ ተጠቃሚዎች ክፉኛ እንዲበሸበሱበት ሁኔታ የፈጠረ የረቀቀ ዘረፋና ምዝበራ ነበር። ነውም። በመለስ ትዕዛዝ ያለአንዳች ተጠያቂነት የሕወሃት ጂኔራሎቹና ደህንነት ባለሥልጣኖች በመንግሥት ገንዝብ የየግላቸውን ፎቆችና ቪላዎች ሠርተው ከሚያከራዩት ውጭ፡ በህብት የተንበሸበሹት ግለሰቦች፡ አንድም ይህንን የውጭ ምንዛሪ ቀዳዳ በመጠቀም መሆኑን፡ ብዙ ተንታኞች ምስክርነታቸውን በየጊዜው ሲያሰሙ ክርመዋል።

  ሌላው ቀርቶ፡ ኢትዮጵያ በመለስ ሞት ማግሥት በተፈጸማባት የሕወሃት ስዎች የሃብት ሽሽት ምክንያት የደረስውን የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ማስታወስ ይጠቅማል። በእርግጥ ለመናገር ይህ የሆነው፡ በብሔራዊ ባንክ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ይዞት ወደመቃብር ስለወረደ አልነበረም። ሃገሪቱ የምታገኘው የልፋቷ ውጤት የሆነው የውጭ ምንዛሪ ብቸኛ ብሔራዊ ተጠቃሚ ለመሆን ባለመቻሏ ነው።

  አሁን የሚያስገርመው፡ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ግፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ ሕግን ለማሻሻል ሲሠራ ክርሞ፡ ሕጉ ከወጣ በኋላ አፈጻጽሙን ወደፊት በ45 ቀናት መግፋቱ አነጋጋሪ: አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር ነው – የተሰጠው ምክንያት እስከ ድረስ አሳማኝ ቢመስልም፡ የፖለቲካና ኤኮኖሚ ሙስና በተንሠራፋባት ኢትዮጵያ ለአንድ ቀን እንኳ ቸል የሚባል አልነበረም። በአሠራር ድረጃ ሲታይም፡ ሕገቢስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ፡ ሙስና በተገታባቸው በሥነ ሥርዓትና በሕግ በሚተዳደሩ አገሮች እንኳ የውጭ ምንዛሪ ሕግን በተመለከተ፡ የዚህ ዐይነት መዋዥቅ ዕድሉ ውሱን ነው።

  ማንን ለመጥቀም ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የተደረገው? የቻይናን ከበርቴዎች፡ የሕወሃትን መዝባሪዎችና አጫፋሪዎቻቸው፡ ወይንስ ኢትዮጵያ ግሩም ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ አገር ናት ብለው ሃስትን ለሚደስኩሩት ምዕራባውያንና ኩባናያዎቻቸው? ለምንስ አሁን የእነዚህ የኢትዮጵያ ባልሥልጣኖች ዐይን በድንገት ተከፈተ IMF ለብዙ ዓመታት ሲነታረክ ኖሮ በዚህ ጉዳይ ላይ?

  የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት መግባት ሲጀምሩና ዘረፋውን (በውጭ ምንዛሪ ስለባ) ክውስጥ ሽርኮቻቸው ጋር እያጧጧፊት የሀገር ውስጥ መስፋፋትና ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ምርት መጨመር በመንግሥት ካዝና ላይ የተጠበቀውን ዕድገት ስላላስከተለ አይደለምን?

  ያም ሆኖ ሁኔታው ከተመቻቸ በኋላ እንኳ ሆዳሙ የሕወሃት አገዛዝ በታሪክ እንደሚባለው ጥልቀት የሌላትን የRubiconን ወንዝ ማቋረጥ አቃተው!

  ባንኩ ሙስኛ ሆኖ ነው ለማለት ሳይሆን፡ የደረሰው ቀጭን ትዕዛዝ፡ የጸረ-ሙስና ኮሚሽን የባልሥልጣኖችን ሃብት ከመዝገበ በኋላ፡ እስቲ ንክች አርጋት ተብሎ በየአስባቡ፡ አላስፈላጊ ያልሆነ ተጭማሪ ሶፍት ዌር እየተባለ፡ ውሃ ሥር ከረበቀረው ውሳኔ ጋር ያለው ዝምድና የግንኙነቱን ሀረግ መስወር አለመቻሉ ግልጽ በመሆኑ ነው። አሁንም ምክንያት ፈልጋችሁ አጋድሙት ስለተባለ ሊሆን ይችላል! ስለሆነም፡ ኢኔ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምመክረው፡ ከእንግዲህ ሕወሃትና አሽቃባጮቹ ለአንዲ ሺህ ሁለተኛ ጊዜ ከሚያታልሉን፡ በየአቅጣጫው በጥርጣሬ ዐይን በመመልከት፡ ብንሳሳት መምረጤን ነው!

  መረጃ ባይኖረኝም፡ የእዚህ እርምጃ በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን (ሕጉን በሥነ ሥርዓት ተፈጻሚ ማድረግ ክተቻለ)፡ አሁን አገር ውስጥ እያመረቱ፡ ለውጭ ገበያ ከሚያቀርቡት የውጭ ኢንቬስተሮችም መካከል፡ የአትራፊነታቸው አንዱ ምንጭ የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸው ዘይቤና፡ ከሽጡም በኋላ ሂሳቡን የሚተልሙበት ዘዴ ነው። እንኳን የውጭ ምንዛሪ፡ ለሃገር ዳር ድንበር ደንታ የሌለው ሕወሃትና ግብረአበሮቹ የሚዘርፉበት ቀዳዳ በመሆኑ፡ ይህንን መቆጣጠር ከተቻለ፡ ደሃውን ሕዝበ ከዘረፋና ከዋጋ ግሽበት በመከላከል፡ ኑሮውን ማሻሻል ይቻላል።

  ይህ እንዲህ እንዲሆን ግን ሕወሃትና ቅጥረኞቹ አይሹም፡ የጥቅቅም ተቋዳሾች ናቸውና!

  እስካሁን ለውጭ ገበያ ከቅረቡት ምርቶች፡ ኢትዮጵያ ተገቢ ድርሻዋን አግኝታለች የሚል ካለ፡ አንድም የዋህ ነው፡ ወይንም እንደአቶ ኃይለማርያም በትዕዛዝ ተንቀሳቃሽ ነው!

 

===============================

ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ያወጣው መመርያ ለ45 ቀናት ተራዘመ

Posted by The Ethiopia Observatory

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ግብይት አሠራርን በአዲስ የሚተካና ካለፈው ረቡዕ የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ ለማዋል ያወጣው መመርያ ተግባራዊ የሚሆንበትን ጊዜ በ45 ቀናት አራዘመ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያው ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜን ያራዘመበት ምክንያት፣ ላኪዎች አዲሱ መመርያ ችግር ውስጥ ይከተናል ብለው በማመልከታቸው ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ብሎ አውጥቶት የነበረው መመርያ ላኪዎችን የሚጐዳ በመሆኑ፣ ከዚህ መመርያ በፊት የተደረጉ ውሎች ካሉ በ45 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቁ ዕድል ለመስጠት ጭምር ታስቦ ተግባራዊ የማድረጊያ ጊዜው እንዲራዘም መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ ባለፈው ሳምንት ያወጣው መመርያ ከዚህ ቀደም ሲሠራበት የቆየውን የውጭ ምንዛሪ ግብይት አሠራር የሚለውጥ ነው፡፡ አዲሱ መመርያ ከመውጣቱ በፊት በነበረው አሠራር የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሲገዙ በዕለቱ በተቀመጠው የባንኮች የመጨረሻ የመሸጫ ዋጋ ነበር፡፡ አዲሱ መመርያ ግን ባንኮች በተለይ ከፍተኛ መጠን ያለውን የውጭ ምንዛሪ በዕለቱ የመሸጫ ዋጋ እንዳይገዙ የሚገድብ ነው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ግዥ ሲፈጽሙም በዕለቱ ለውጭ ምንዛሪ ግዥ ባስቀመጡት ዋጋ ተመን ብቻ መሆን እንዳለበትና እንደ ቀድሞው በድርድር በመሸጫ ዋጋ ግዥ መፈጸም የማይችሉ መሆኑን መመርያው ይደነግጋል፡፡

የዚህ መመርያ መውጣት ላኪዎችን እንደሚጐዳ የተገመተ ሲሆን፣ እንደተባለውም ላኪዎች መመርያው ይጐዳናል በማለት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ይህንንም አቤቱታ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያውን ባይቀለብሰውም የ45 ቀናት ማራዘሚያ ሊያደርግ ችሏል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባንክ ባለሙያዎች፣ አዲሱ መመርያ የወጣበት ምክንያት በውጭ ምንዛሪ ላይ እየታየ ያለውን ያልተገባ ውድድር ለማስቀረት፣ ያልተገባ የተባለው የውጭ ምንዛሪ ግዥና ሽያጭ ሒደት ለዋጋ ግሽበት መንስዔ መሆኑ በመታመኑ መመርያው ሊወጣ መቻሉን ይናገራሉ፡፡

እስካሁን ባለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላኪዎች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ለባንኮች ሲሸጡ ለዕለታዊ ግብይት ከተቀመጠው ምጣኔ ውጪ በመሸጫ ዋጋ ብቻ ካልሆነ በማለት ሲሸጡ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ሽያጫቸው ከፍተኛ የሚባል ትርፍ እያገኙበትና እየተጠቀሙበት ነበር ተብሏል፡፡ መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን አሠራር ፈቅዶ የነበረው ላኪዎችን ለማበረታታት በሚል ነው፡፡

ሆኖም ሌላ አደጋ እየተከሰተ በመሆኑ አሠራሩ በመመርያ እንዲስተካከል ማድረጉ አግባብ ነበር ተብሏል፡፡ አዲሱ መመርያ ተግባራዊ የሚሆንበት ቀን እንዲራዘም የተቀመጠው ምክንያት ግን ብዙዎችን ማስደመሙ አልቀረም፡፡

ላኪዎች ከሚልኩት ምርት ሳይሆን ጥቅማቸውን እያሰቡ ከውጭ የሚመጣውን የውጭ ምንዛሪ ለባንኮች ጠቀም ባለ ትርፍ በመሸጥ ላይ አትራፊነታቸው የተመሠረተ አስመስሎታል የሚሉ አሉ፡፡

ላኪዎቹ ለውጭ ገበያ ያቀረቡት ምርት የማያተርፋቸው መሆኑን እያወቁ ቢልኩም፣ ትርፋቸውን እያሰሉ ያሉት ግን ካገኙት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ በማሰብ ነው በመባሉ፣ አዲሱ መመርያ ከ45 ቀናት በኋላ ተግባራዊ ሲሆን ላኪዎች አጣብቂኝ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በተለይ አንድ የባንክ የሥራ ኃላፊ መመርያው ይፋ ከተደረገ በኋላ ላኪዎች ሰጡ የተባለው ምክንያት ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ሪፖርተር
 

%d bloggers like this: