የሕወሃትና ተወካዮቹ አገር አስተዳደር – ሀስት፤ ሸፍጥ፤ ክህደት፤ ዘረፋ፤ እሥራት፤ ግርፋትና ግድያ

4 May

Posted by The Ethiopia Observatory

I. በኦሮሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ እሥራትና፡ ግርፋት አስመልክቶ የተፈጸሙ ውሸቶች – ሪፖተር እንደዘገባቸው

  ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

  -የኦሮሚያ ክልል የታሰረም ሆነ የተደበደበ ተማሪ የለም አለ

  በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞንን በአንድ የማስተር ፕላን ማቀናጀት ምክንያት፣ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኝ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት

  ተቋማት የሚማሩ የኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ስለ ተማሪዎቹ ተቃውሞ በግልጽ ያለው ነገር ባይኖርም፣ በፀጥታ ኃይሎች ድብደባና እስራት ተፈጽሞባቸዋል መባሉን ግን አስተባብሏል፡፡

  ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተዘጋጀው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ሲወያዩበት መቆየታቸውን፣ ይህንን ተከትሎ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች ማስነሳቱንም ጨምሮ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ግን የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው በተባሉ ተማሪዎች በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በተለይም በጂማ፣ በአምቦ፣ በወለጋና በሀረማያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች አዲሱ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የኦሮሚያን ጥቅም ‹‹ለማሳጣት እንጂ ለክልሉ ታስቦ አይደለም›› በማለት፣ መጠነኛ ተቃውሞ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  በተለይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ወደ ከተማ በመውጣት በአደባባይ የተቃወሙ ሲሆን፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ብቻ መሆኗን የሚያሳዩ መፈክሮችንም አሰምተዋል፡፡ እንደዚሁም በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ለተቃውሞ በወጡ ተማሪዎች ላይ ፖሊስ ተማሪዎቹን ሲበትን የተወሰኑ ተማሪዎች ከግቢው በመውጣት መሸሻቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ነገር ግን በአንዳንድ ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ኃይሎች የተማሪዎችን ሰላማዊ ተቃውሞ በጉልበት ማፈናቸውን፣ እስራትና ድብደባ በተማሪዎች ላይ መፈጸሙን እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡

  በተማሪዎች ተፈጸመ የተባለውን ድብደባና እስራት አስመልክቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ አጭር ምላሽ የሰጡት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ ‹‹አንድም የታሰረም ሆነ የተደበደበ ተማሪ የለም፣ መረጃውም አልደረሰንም፤›› ብለዋል፡፡

  መንግሥት በበኩሉ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ የልማት መሪ ዕቅድ የእርስ በርስ ትስስር ያላቸውን ከተሞች የልማት ጥያቄ ለመመለስ ያለመ ነው ሲል አስታውቋል፡፡ ‹‹… የጋራ የልማት መሪ ዕቅዱ ሕገ መንግሥቱ ለብሔር ብሔረሰቦች ያረጋገጠውን በጋራና በፍትሐዊነት የመልማት መብት የሚያረጋግጥ እንጂ ከወሰንና ከመሬት ጋር የሚያያዘው አንዳችም መሠረት የለውም፤›› በማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ለኢቲቪ ገልጸዋል፡፡

  በተጨማሪም አቶ ኩማ ጉዳዩን አጀንዳ በማድረግ ሕዝቡን የሚያሳስቱ አሉባልታዎች ተጨባጭነት እንደሌላቸውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ አቶ አብዱላዚዝ በበኩላቸው፣ የጋራ ልማት መሪ ዕቅዱ የልማት ጥያቄን የሚመልስ እንጂ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

 

========================

  “ኢትዮጵያ ያልተገደበ የመረጃ ፍሰት ስርዓትን በማስፈን ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እየሰራች ነው”– አቶ ሬድዋን የሕወሃት ፕሮፓጋንዳ ጉዳዮች ኃላፊ

  አዲስ አበባ ሚያዝያ 25/2006 ኢትዮጵያ ያልተገደበ የመረጃ ፍሰት ስርዓትን በማስፈን ኀብረተሰቡ ጠቃሚ መረጃ እንዲያገኝ እየሰራች መሆኗን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

  የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን “የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ለተሻለ ነገ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ ዛሬ ተከብሯል።

  አቶ ሬድዋን በዚህ ወቅት እንዳሉት የዜጎችን ሀሳብን በነፃነት የመግለጽና መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ መንግስት ቅድመ ምርመራ እንዲወገድ በማድረግ የፕሬስ ነፃነት በአዋጅ እንዲደነገግ አድርጓል።

  የህዝብ መገናኛ ብዙኃን ተጠሪነታቸው ለፓርላማ እንዲሆን ሲደረግ ላለፉት 20 ዓመታት የግል መገናኛ ብዙኃንን ለማጎልበት ያለ ምንም ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ብለዋል።

  የመገናኛ ብዙኃን ማበብ ዜጎች ፈርጀ ብዙ መረጃዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ከሚሰራጩት መረጃዎችና አመለካከቶች የሚጠቅማቸውን እንዲለዩ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

  ሆኖም በአንዳንድ ወገኖች የፀረ ሰላም ድርጅት አባልነትና ወኪልነትን ጨምሮ በህገ ወጥ መንገድ ለመንቀሳቀስ የጋዜጠኝነትን ሙያ እንደ መጠለያ የመጠቀም ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱ ገልጸዋል።

  በጋዜጠኝነት ሽፋን ህግን ለመተላለፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ ግን ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል።

  የእርስ በእርስ ግጭትን የሚቀሰቅሱ፣ የጥላቻ ንግግርን የሚያስተላልፉ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት የሚያደርጉና የሚደግፉ የመገናኛ ብዙኃን በህግ ከመጠየቅ እንደማይድኑ አቶ ሬድዋን አስገንዝበዋል።

  መንግስት ለፕሬስ ነፃነት አበክሮ እንደሚታገለው ሁሉ ፀረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ኃይሎችን የመመከት ኃላፊነት አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ህግን አክብረውና የሙያውን ሥነ-ምግባር ጠብቀው ከሚሰሩ መገናኛ ብዙኃን ጋር በአጋርነት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

  ትብብሩን ለማጠናከር የፕሬስ ካውንስልና የአሳታሚ አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩና እንዲጠናከሩ ለማድረግ መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።

  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ማዕከል /ዩኔስኮ/ ላይዘን ኦፊሰር ኢሪና ቦኮቫ የፕሬስ ቀን የጋዜጠኞችን መብትና ደህንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ ለህግ የበላይነት፣ ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

  በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚረቀቀው የልማት አጀንዳ ማዕቀፍ ዝግጅት መንግስታትና ዜጎች ከዩኔስኮ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

  የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማኀበር ፕሬዚዳንት ወንድወሰን መኮንን በበኩሉ ኢትዮጵያ ከ3 ሺህ ዘመን በላይ ታሪክ ያላት አገር ብትሆንም በፕሬስ ነፃነት ታሪክ 20 ዓመታት ብቻ ማስቆጠሯን ገልጿል።

  የግሉ የህትመት መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ አዲስ በመሆኑ በግልና በመንግስት የመገናኛ ብዙኃን የሚታየው ጽንፍ የመያዝ አዝማሚያ ለአገርና ለህዝብ የማይጠቅም በመሆኑ ባለሙያዎች የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባርን ጠብቀው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።

  በአዲስ አበባ በተከበረው በዓል ላይ ከመንግስትና ከግል መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

=========================

  በአንዳንድ ዩንቨርስቲዎች በተፈጠረ ግርግር በህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

  አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረ ግርግር በህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

  ጽህፈት ቤቱ ማምሻውን እንደገለፀው በአዲስ አበባና በዙሪያው የሚገኘውን የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በልማት ለማስተሳሰር የተነደፈውን የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን አስመልክቶ ከፕላኑ ፋይዳና አላማ ጋር የሚቃረን መሰረተ ቢስ አሉባልታ በአንዳንድ ወገኖች በስፋት ሲሰራጭ ቆይቷል፡፡

  ይህን መነሻ በማድረግም በበርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ዘንድ ትክክለኛውን መረጃ የማወቅ ፍላጎት መኖሩን ከግምት በማስገባት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት በእቅዱ ልማታዊ ዓላማና በሚያስገኛቸው ጥቅሞች ዙሪያ ማብራሪያ ሲሰጡ መቆየታቸውንና አሁንም በመስጠትም ላይእንደሚገኙም ነው ያመለከተው፡፡

  በምክክር መድረኮቹ የተጀመረው ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ትክክለኛው መረጃ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ላቀረቡ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችንም በውይይቶቹ ውስጥ የማሳተፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል ፡፡

  ይሁንና በሁሉም ክልሎች ከሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ይህ ህዝባዊ ምክክር ከመዳረሱ በፊት አስቀድሞ ጥርጣሬዎችን ለመንዛት ሆነ ተብለው በተሰራጩ አሳሳች አሉባልታዎችና ሃሜታዎች የተደናገሩ የተወሰኑ ተማሪዎች በፈጠሩት ሁከት በክልሉ በሚገኙ የተወሰኑ ዩንቨርስቲዎች በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል፡፡

  በዚህ በሃይል በታጀበ ግርግር ሳቢያ በመደ ወላቡ የሶስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል፡፡

  በተለይም በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተቀሰቀሰው ሁከት ወደ ከተማ በመዝለቁ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በአምቦ ከተማ ቢዝነስና ኮንስትራክሽን ባንክ ላይ በተደረገው የዘረፋ ሙከራና ሌሎችም ህገ ወጥ የነውጥ እነቅስቃሴዎች በአምቦና ቶኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ህይወት እንዳለፈና ባንኩን ጨምሮ በበርካታ የመንግስትና የሀዝብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል፡፡

  በተያያዘም በሃረማያ ዩንቨርሲቲ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በሰላም የእግር ኳስ ጨዋታ በቴሌቪዥን በመከታተል ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ፈንጂ ወደ 70 ያህል ተማሪዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን፥ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል፡፡

  በፌዴራልና በክልል የፀጥታ ሃይሎች ትብብር ሁከቱ በተፈጠረባቸው ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ተችሏል፡፡

  እስካሁን በተደረገው ማጣራት ከበስተጀርባ በመሆን ሁከቱን በማነሳሳትና በማቀነባበር ተግባር ላይ የተሰማሩት ጥቂት ፀረ ሰላም ሃይሎች መሆናቸውን ለማወቅ መቻሉን ነው መግለጫው ያመለከተው፡፡

  ፅህፈት ቤቱ እንዳለው ከዚሁ ግርግር በስተጀርባ የቆሙትና ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች እጃቸውን ሲያስገቡ የነበሩ የአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ሃይሎች በሚቆጧጠሯቸው ሚዲያዎች እየታገዙ ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ለጥፋት አላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸው ታውቋል፡፡

  እነዚሁ አካላት ህገ ወጥ እንቅስቃሴያቸውን ሰላማዊ ዜጎችን ሰለባ በማድረግ ጭምር ከማራመድ የሚቦዝኑ አልሆኑም ያለው መግለጫው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሚሹ ተማሪዎችን ተገቢ ጥያቄ በአግባቡ እንዳይስተናገድ የሚፈልጉት የነውጥ አቀንቃኞች ከአንድ ጥግ ሆነው ብዙሃኑን ሰለባ በማድረግ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በመራወጥ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡

  የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን በማጤን ብዙሃኑ ወጣት ተማሪዎች ከጉዳዩ በስተጀርባ በሚንቀሳቀሱ ጥቂት የጥፋት ሃይሎች በሚነዙት የተዛባ ዘመቻና አሉባልታ ሳይደናገሩ ትምህርታቸውን በሰላም እንዲከታተሉ መንግስት አሳስቧል፡፡

  በዚህ አጋጣሚ በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸውና ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው መንግስት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ የጥፋቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ የነበሩትን ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡

 

===============================

II. በኤኮኖሚ መስክ ባለሃብቶችን ለማሳሳት የሚደረግ ቅጥፈት

  Calvin Klein, Tommy Hilfiger owner to explore investment opportunities

  – Tadesse Haile speaks of “… double digit growth, dependable energy supply and low inflation rate…”

  The American PVH corporation’s clothing company is to consult with the government and consultants on investment opportunities in Ethiopia, according to a press conference it gave here on Monday.

  Tadesse Haile, Minister of State for Industry, stated the success and setbacks of Ethiopia’s investment opportunities. Responding to various questions from members of the delegation, he asserted that Ethiopia was ready to host giant global companies. “There are no restrictions at all,” he said. He said Ethiopia offered a hundred percent guarantee on business and no restrictions in the investment law.

  Highlighting the double digit growth, dependable energy supply and low inflation rate, Tadesse clarified the investment policy that had been reviewed to ease bureaucracy and mistreatment. “With prudent management policy and strong economic growth, we have achieved 10 per cent growth during the last two decades and lowered the inflation by 7 percent right now,” he said. The 6,000 MW hydropower from the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) project was expected to be finalized in three years’ time. The 1800 MW hydropower from Gilgel Gibe III is due to be operational one year’s time

  Bill McRaith, Chief Supply Chain Officer, PVH Corp, told The Reporter that he had seen quite an encouraging situation in Ethiopia similar to what he saw in China in 1990 while operating the company there. “We are incredibly curious,” he said. He, however, pointed out that infra structure should come ahead of need. “China is the only country whose infrastructure goes ahead of need.” Moreover, he took the opportunity to talk about labor rights as he explained some of the fastest investments in some countries had yielded bad human rights consequences. “I continue to ask this question every time I come,” he reiterated.

  PHV Corp. is the world’s largest shirt company owning brands such as Tommy Hilfiger and Calvin Klein. Ethiopian business consultants who returned from abroad also briefed the delegation citing various encouraging policies and abundant potential in the country. “We have come through quite a hard situation in facilitating such an event to occur, and here is the fruit,” Guenet Fresenet, Division Manager Southwest Sourcing, said. The delegation also paid a short visit to investment sites in Addis Ababa.

*የታከለበት
 

%d bloggers like this: