የሕወሃት ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን 2 ቀላል የከተማ ባቡሮችን አመረተ: በ$38 ሚሊዮን 530 አገር አቋራጭ የባቡር ፉርጎዎች ያመርታል – መስፍን የሕወሃት ኢንጅኔሪንግ ድርሻ ስንት $$$ ይሆን?

30 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲሰ አበባ ነሐሴ 24/2006 (ኢዜአ): የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሁለት ቀላል የከተማ ባቡሮችን በሙከራ ደረጃ አመረተ።

በ38 ሚሊዮን ዶላር 530 አገር አቋራጭ የባቡር ፉርጎዎች የማምረት ስራ (ሥ ዕል: (ኢዜአ)

በ38 ሚሊዮን ዶላር 530 አገር አቋራጭ የባቡር ፉርጎዎች የማምረት ስራ (ሥ ዕል: (ኢዜአ)

በ38 ሚሊዮን ዶላር 530 አገር አቋራጭ የባቡር ፉርጎዎች የማምረት ስራ መጀመሩንም ገልጿል። በኮርፖሬሽኑ የሎኮሞቲቭ ንኡስ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ፀጋዬ ገብረክርስቶስ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የኢንዱስትሪው ዋና ዓላማ አገር አቋራጭ የባቡር ፉርጎዎች፣ ቀላል የከተማ እንዲሁም ከከተማ ወደ ከተማ የሚያጓጉዙ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ባቡሮችን በአገር ውስጥ ማምረት ነው።

ከአውሮፓ አገራት በባቡር ምርት ታዋቂ የሆነውን የሃንጋሪ ኩባንያ በሞዴልነት በመምረጥና ሰባት ባለሙያዎች በማስመጣት ለ20 ኢትዮጵያውያን ስልጠና ተሰጥቷል።

በዚህም የቴክኖሎጂና የዕውቀትና ክህሎት ሽግግር መደረጉንና የቴክኖሎጂው ባለቤት ለመሆንና ሽግግሩን ወደተግባር ለመቀየር ከፍተኛ ወጪ መጠየቁን ገልጸዋል።

ሻለቃ ፀጋዬ እንዳሉት የማሳያ ምርቶቹን ተግባራዊ ለማድረግ ከኮርፖሬሽኑ በተጨማሪ የጥቃቅንና አነስተኛና እንዲሁም ሌሎች ትልልቅ የግል የኢንዱስትሪ ተቋማት ተሳትፈዋል።

ንኡስ ኢንዱስትሪው ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ብቸኛ የአገር ውስጥ ምርት አቅራቢና የኢንጅነሪንግና የቴክኒክ አማካሪ በመሆን የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ነው ብለዋል።
 

===============================================================
እነዚህን ጽሁፎች ያንብቡ:

    How the TPLF regime transfers national resources to EFFORT companies: Messobo’s case

    Ethiopia’s mushrooming sugar plants fete Mesfin Engineering with billions of birr in contracts

    Dispute with MEtEC halts existing railway service operations: Why is MEtEC stone in everyone’s shoe?

================================================================

የአገር አቋራጭ፣ ቀላል የከተማና ከከተማ ወደ ከተማ የሚያጓጉዙ የጭነትና የሕዝብ ባቡሮች በአሁኑ ወቅት በዲዛይን ደረጃ መሰራታቸውን ጠቁመው ቀላል የከተማ ባቡሩ መመረቱም በጅምር ላይ ላለው ፉርጎዎች የማምረት ሂደት መሰረት መጣሉን ገልፀዋል።

ነሪንጎ የተባለው የቻይና ኩባንያ ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 1 ሺህ 100 የባቡር ጎታች ፉርጎዎችን ለማቅረብ ተስማምቷል። ከነዚህ ውስጥ 530ዎቹ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሎኮሞቲቭ ንዑስ ኢንዱስትሪ እንዲመረቱ የቻይናው ኩባንያ ተስማምቷል።

ሻለቃ ፀጋዬ እንደሚሉት “ስምምነቱን ከግብ ለማድረስ ኮርፖሬሽኑ ከመስከረም ጀምሮ በስምንት ወራት ጊዜ ውስጥ ፉርጎዎችን አምርቶ ለማስረከብ እየሰራ ነው”።

መንግስት ለባቡር ግንባታው ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ያገኘው ብድር በመለቀቁ ከመስከረም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ለመግባት ለማምረቻ አስፈላጊ ግብአቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሂደት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ቴክኖሎጂው በአገር ውስጥ መፈብረክ መቻሉ ከባለቤትነት ባሻገር የውጭ ምንዛሪ በማዳንና በስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት።

ይህም አገሪቱ ከግብርና ወደ ኢኮኖሚ መር ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ሽግግር እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሎኮሞቲቭ ንዑስ ኢንዱስትሪ የተቋቋመው በ156 ሚሊዮን ብር [$8 ሚሊዮን] መነሻ ካፒታል ነው።
 

%d bloggers like this: