ሁለተኛው የአላሙዲ ወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተከላ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሊካሄድ መሆኑ በሚዲያ ቢገለጽም፡ ለምን ሚድሮክ ብቸኛ የሃገሪቱ ወርቅ ሞኖፖል ያዥ እንዲሆን እንደተፈለገ አልታወቀም

24 Sep

የአዘጋጁ ጥያቄ፡

  ወርቅ ለኢትዮጵያ ክፍተኛው የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። እስካሁን ክፍተኛው ገቢ ከወርቅ የተገኘው $602.4 ሚልዮን በ2011/12 ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን በ2010/11 የተገኘው $48´61.7 ሚልዮን ነበር። በ2012/13 የገቢው መጠን ወደ $584.4 ሚልዮን ወርዷል –ካለፈው ጋር ሲነጻጸር – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደዘገበው። የገቢው መለዋወጥ ከተላከው መጠን መቀያየር ወይንም ከዓለም የወርቅ ገበያ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።

  Credit: FBC

  Credit: FBC

  ሁኔታዎች ሲለዋወጡ ግን፡ ሃገሪቱ በአንድ አምራችና ውጭ ላኪ ትከሻ ላይ እምነቷን ማሳረፏ አደጋ አለው። ሐምሌ 14፣ 2013 Drab Gold Dims Mining Revenue በሚል ርዕስ
  አዲስ ፎርቹን ባቀረበው ዘገባ፡ በ2011/12 የሃገሪቱ የወርቅ ገቢ ከተጠበቀው $843.3 ሚልዮን ዝቅ ካለበት ምክንያቶች አንዱ አላሙዲ ወደ ውጭ መላክ ከሚገባው 6,064.95 ኪ/ግ ውስጥ 4,193.7 ኪ/ግ ብቻ ለመሽጥ በመፈልጉ መሆኑን ይጠቅሳል። ለዚህም ዋናው ምክንያት በዓለም ገበያ ላይ የወርቅ ዋጋ ክፉኛ በማሽቆልቆሉ ነበር።

  ለነገሩ ኢንቬስተሩ ሃብቱን አፍሶ የወርቅ ምርትና ኤክስፖርት ሲፈቀድለት ሸጦ ለማትረፍ እንጂ እንዲከስር ባለመሆኑ፡ መንግሥት አላሙዲን ሊያስገድደው ወይንም ሊገፋፈው አልደፈረም። ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በማጣት ብትቸገርም የተወስደው እርምጃ ትክክለኛ ፖሊሲ ነው።

  ነገር ግን ለቡና አምራቾችና ኤክስፖርተሮችስ ለምንድነው ተመሳሳይ የገበያ ምርጫን ነጻነት የማይሰጣቸው? በግንቦት 2009 ቡና ወደውጭ አንዳይላክ አድርገው ሕወሃትን ሳቦታጅ ለማድረግ ነው ተብሎ የታሠሩና ንብረታቸው የተወረሳባቸው ስድስት/ሰባት ያህል ከፍተኛ የቡና ነጋዴዎች መታፈሳቸውን እናስታውሳለን። በዚያም አልቆመም። ከሁለት ዓመታት በኋላ እንደገና ተደገመ። ነጋዴዎች እሥር ቤት ተወረወሩ። ሕወሃት ይህንን ምክንያት አድርጎ ነጋዴዎችን ሲያሳድድ ግን ቡና ከመጋዘን ጠፋ መባል ተጀመረ። በ2009 አሥር ሺህ ቶን እንደጉም ተነነ። በ2013፡ 12ሺህ ቶን ቡና የገባበት ሳይታወቅ ቀረ።

  የመጀመሪያው ጊዜ፡ “Our writ runs through every locality in Ethiopia more than any time before” ሲል የነበረው መለስ ዜናዊ ዘራፊዎቹን እንደርስባቸዋለን አለ። እርሱም ከዚያ በኋላ እንደ አዲስ አበባ መሬት ዘረፋ ሁሉ፡ ስሙም እንዲነሳበት አለመፈለጉን በተለያየ መንገድ እንዲታወቅ አደረገ! ይህ ደግሞ ዘግናኝና አስቀያሚ ነው!

  ከውጭ ሲታይ፡ የዋህና ተላላ ይምስል እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቡናው የት እንደገባ በልቡ አስልቶ፡ “ይገርማል” ብሎ እርሱም ፊቱን አዞረ!

  አሁንም በሌላ መልኩ ወርቁ ላይ ይህ እንዳይተረጎም፡ ጉዳዩ ሃገሪቷን ሊጎዳ ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል።

  ለማንኝውም፡ በሃገሪቱ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ከአራት ያላነሱ ወርቅ ወደወርቅ ማምረትና ለገበያ ለማቅረብ አፋፍ ላይ ያሉ ያገር ውስጥና የውጭ ድርጅትች ቢኖሩም (ኢዛና: አስኮም ኖዮታ ወዘተ)፡ በተቻለ መጠን በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች አላሙዲ ብቻ እንዲሳካለት የግል ፍላጎቶቻቸውን የመንግሥት ፖሊሲ ማድረጋቸው ኢትዮጵያን ይጎዳል። ሃገሪቱ የግድ ከአላሙዲ ጋር ተወዳድረው የወርቅ ምርትና ግብይት እንዲካሄድ ቢደረግ – በቀላሉ ኮንትራቶቹ ከሃያ ዓመት በላይ ስለሚሄዱ – መሬት ላይ በደንብ የረገጠና ለረዥም ጊዜ ተጠቃሚ ቢያደርጋት የሚያደርጋት አሠራርና ፖሊሲ ሥራ ላይ እንዲውል ያስችላል። ፖሊሲን መሣሪያ በማደረግ የሚካሄደው ዘረፋም ሊቀንስ ይችላል!ይመረጣል።

  በሻኪሶና በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩል የአላሙዲ ትከሻ ላይ ብቻ መንጠላጠል ሃገር የሚጎዳ ፓሊሲ ይመስለኛል።

 

A panoramic view of an abandoned Midroc openpit mine in the Sidamo plateau. In the distance are roads used to transport the gold rubble to and around artificial and natural lakes (Courtesy: The Guardian)

======================

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አሶሳ መስከረም 14/2007 (ኢዜአ): በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአገሪቱ ሁለተኛ የሆነ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተከላ እንደሚካሄድ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን አስታወቀ።

በክልሉ ቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ ጊላይ በሚባለው አካባቢ ላለፉት 10 ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ጥናት በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ አብይ ሰጥአርጋቸው እንደተናገሩት በስፍራው በ4 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሬት ላይ ሲካሄድ የቆየው የወርቅ ፍለጋ ጥናት በአካባቢው ከፍተኛ የወርቅ ክምችት መኖሩን አመላክቷል።

ለአሥር ዓመታት መመረት የሚችል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት የሚያሳዩ አመላካች ነገሮች መኖራቸውን ተከትሎ በ250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የፋብሪካው ተከላ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

አካባቢው ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን ክምችት ያለው በመሆኑ ከማምረት ጎን ለጎን ሌላ ጥናት በማካሄድ የምርት ዘመኑን ዕድሜ የማራዘም ሥራ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት።

ለሚገነባው ፋብሪካ የሚያስፈልገው ከ5 እስከ 6 ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል ከግልገል በለስ የኃይል ማመንጫ ለመሳብ መታቀዱን ጠቁመዋል።

ባለፉት አሥር ዓመታት በ250 ሚሊዮን ብር ሲካሄድ የቆየው የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ጥናት ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

ጥናቱ 250 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና ከእነዚሁ መካከል ደግሞ 150 ያህሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ነው ያስረዱት።

በቀጣይነት የሚገነባው የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ 800 ለሚሆኑ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አመልክተዋል።

ከፋብሪካው መገንባት ጋር ተያይዞ የአካባቢውን ነዋሪዎች ጭምር ተጠቃሚ የሚያደርጉ አዳዲስ መንደሮች እንደሚመሰረቱና እንደ መንገድ፣ መብራትና ውኃ ያሉ የመሰረተ ልማት አውታሮች የማስፋፋት ሥራዎች እንደሚከናወኑም አቶ አብይ ገልጸዋል።

መንግሥት ለማዕድኑ ዘርፍ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እንዲሁም የክልሉ መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለክልሉ ብሎም ለአገሪቱ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ሕዝብና መንግሥት በቀጣይነት ለፕሮጀክቱ ሆነ ለሌሎች መሰል የኢንቨስትመንት ሥራዎች አስፈላጊ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ሚድሮክ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ሻኪሶ የለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ እንዳለው የሚታወቅ ነው።
 

%d bloggers like this: