የቀድሞዋ ‘ቀዳማይት እመቤት’ አዜብ መስፍን እንደገና ራሳቸውን ክፉኛ አዋረዱ!

24 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ሃያ ዓመታት ያህል በቤተ መንግሥት የመለስ ዜናዊ ፖለቲካ አካባቢ የኖሩት አዜብ መስፍን፡ ሲሳይ አጌና ስልክ ሲደውልላቸው፡ ያሳዩት የስልክ አመላለስ ባህሪና ከዚያም ወደሸፍጥና ክህደት ማምራታቸው እጅግ አሳፋሪና የግለስቧን ማንነት ከምን ጊዜውም በላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገሃድ ያደረገ አጋጣሚ ነው።

አንደኛ በስልክ አመላለሳቸው – ትምህርት የኬለው ሰው እንኳ የማያደርገውን – ሰው ቤት ሆኖ ወይንም የራሱም ቤት ስልክ ሲመልስ – የርሳቸውን ያህል ብልግና ያሳያል ብሎ ለማመን ያስቸግራል።

አንደኛ የድምጻቸው አንቋሪነት፤ ሁለተኛም፣ የአነጋገራቸው ጋጠ ወጥነት፡ ከመሠረቱ ጨዋነት ዳብሶት እንደማያውቅና፡ ለሌሎች ኢትዮጵያውያንን በሃፍረት የሚያሸማቅቅ መሆኑን እያንዳንዱ አድማጭ የሚስተው አይመስልም። የት ደረስ ያ ሁሉ የሃያ ዓመታት በቤተ መንግሥት የመንከላወስ ልምድ? ከልዩ ልዩ ሃገሮች ግለሰቦች፥ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የውጭ መንግስታት ባለሥልጣኖች የትዳር ጓደኞች ወዘተ ጋር መገናኘቱስ ምን ጠቀመ? ያ ሁሉ አጋጣሚ – በስልክ አመላለስ ደረጃ እንኳ – አዜብን ሊገራ እለመቻሉ አስገራሚው የአዲሱ ዓመት ክስተት ነው።
ለነገሩ አዜብ ውሏቸው ከሌቦች፡ ቀጣፊዎችና አቃጣሪዎች ጋር እስከሆነ ድረስ፡ ምን ሊማሩና ምን ያህል ተለውጠው ሥነ ምግባር ሊያሳዩ ይችላሉ?

አዜብ መስፍን ጉቦ ሲያሳድዱ፡ መሬትና ንብረት ሲዘርፏና ሲያዘርፉ መኖራቸው፡ በቅጥፈት ለተሞላው ባዶው ሕይወታቸው፡ የችግራቸው ምንጭና የሕዝብ ጥላቻ ዒላማ አድርጓቸዋል። አጠገባቸው ወይንም ባካባቢያቸው አብረው ካሉ ሰዎች ጋር ሲናከሱና ሲያስነክሱ፤ ሲገፉና ሲያስገፉ የኖሩ እንደመሆናቸው፡ ደግ ደጉን ለመቅሰም፡ ባህልን ለመማር እንዲሁም በእውቀት ደረጃ ራሳቸውን ሊያሻሽሉ ያልቻሉ፡ ሃያ አመታት በላይ ቤተመንግሥትና ከተማ ውስጥ አገር ሲያውኩ የኖሩ ተባይ ናቸው።

ትምህርት እንኳ ቢቀር፡ እንዴት ኢትዮጵያዊ ባህላዊ ጨዋነት አንዳልዳሰሳቸው ራሳቸውን አዋራጅ በሆነው ሞራጅና ጆሮ ጨንቋሪ ድምጻችው ራሳቸውን ምንም ካልተማረችው ተራ ኢትዮጵያዊ መንደርተኛ በታች አድርገው መገኘታቸው፡ በአጠቃላይም፡ የሕወሃትን ሰዎችም ማንነት ክፉኛ አጋልጧል።

ኢሳት በተመሳሳይ መንገድ ለኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ባለቤት ባለፈው ዓመት መስለኝ መደወሉስን አስታውሳለሁ። ሴትዮዋ በጣመ ድምጽና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ስልኩን አስተናግደው፡ ራሳቸውን አክብረውና አስከብረው የመጣውን የኢሳት ምርመራ ከበር ለመመልስ ችለዋል። ይህ የትምህርት ጉዳይ አይደለም። በዘመነ መንግሥቱም፡ ባለቤታቸው ቤተመንግሥትም ይሁን በአደባባይ እንዲሁም በመንግሥት ሥራ እንደ አዜብ የእርጎ ዝንብ አልነበሩም። በሌብነትና ዘረፋማ ከቶም አይታሙም።

ከላይ ለማለት የሞከርኩት ግልጽ ካልሆነ፡ ሁለቱን የስልክ ጥሪዎች ጎን ለጎን እንደገና በማሰማትና በማወዳደር፡ በሕዝባችን ላይ አዜብ መስፍን ያሳደሩትን የአንጀት ማረርና የዕፍረት መጠን መገንዘብ ይቻላል።
 

ተዛማጅ ስለአዜብ፡

  Ethiopian transition proceeding smoothly – except for one thing

  Azeb sticks around the palace: Is TPLF using it for power play or EFFORT blackmailing ‘em?

  New palace for Azeb Mesfin: The visible tip of the iceberg, the arrogance bleeding our nation, butt of Nigerian joke!

  Aregash Adane Vs Azeb Mesfin

  First Lady Azeb Mesfin dismisses corruption rumors.wmv – YouTube

  Breaking News:Azeb Mesfin Spent €1.2 Million On Her Wardrobe …

 

%d bloggers like this: