ከ2015 ምርጫ በፊት የሕወሃትና ሹምባሾቹን ወንጀሎች በፓሊስ ማላከክ ዝግጅት ሊፈይድ የሚችለው ነገር ይኖር ይሆን?

2 Nov

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)

ልማትን ለማምጣት በኢትዮጵያ የሚታየው የአንድ ወገን ጥረት ምን ያህል የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበ (media and investors)፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሃገራችን በጸረ ሽብር ዘማችነት በአፍሪካ ቀንድ የሃብታሙ ዓለም ደጅንነት ስምና ድጋፍ እንድታተርፍ የረዳት ቢሆንም፡ ስሟ ግን በዓለም ላይ ካሉ ጨካኝና ክፉኛ ከተበከሉት መካከል በግንባር ቀደምነት መጠቀሱ፡ ምናልባትም ከዚህ በፊት ብዙ ባልታየ መልኩ በአሰተዳደሩ ውስጥ መከፋፈልና ድንጋጤ እንደፈጠረ ይገመታል።

ለዚህም መንስዔው በሀገር ውስጥና ድንበር በዘለለ መልኩ (ሱዳን፡ ኬንያ፡ ጂቡቲ፡ ኡጋንዳ፡ የመንና እንዲሁም በኢንተርኔት) የሕወሃት አስተዳደር የፈጸማቸውና እየፈጸማቸው የሚገኘው አስጸያፊና ወንጀለኛ ባህሪዎች ተጠቃሾች ናቸው። በተጨማሪም፡ ልማትን በማፋጠንና ድህነንትን በማስወገድ ስም ከሃስት ፕሮፓጋንዳ መጋረጃ ጀርባ የተከማቹት ማለትም – የኢትዮጵያውያን ለስደትና ለእሥር ጉስቅልና መዳረግ፡ የብዙ ሕይወቶች መጥፋት፣ ቤተስቦችና ማኅበረሰቦች መፍረስ ለሥልጣን ብልግና መሠረት የሆኑት ሠቅጣጮቹ የስብዓዊ መብቶች ጥስቶቹ ናቸው።

የሃገራችንን የሰብዓዊ መብቶች አቋም በዳታ ያነጻጸረውና ስብዓዊ መብቶችን አስከባሪ ግለስቦችንና ድርጅቶችን (Human Rights Defenders) በአባልነት የያዘው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች አከባበር ደረጃ ቀማሪ ድርጅት (International Human Rights Rank Indicator) ኢትዮጵያን ከ216 ሃገሮችና አስተዳደሮች ጋር አወዳድሮ በ210ኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡ አለምክንያት አይደለም።

የተባበሩት መንግሥታት የስብዓዊ መቦትች ምክር ቤትም ባለፈው ሚያዝያና መስከረም 2014 በተካሄዱት የአባል ሃገሮች የስብዓዊ መብቶች አከባበር ሁኔታ ኢትዮጵያን በገመገመበት ወቅት፣ የሃገራችን የፖለቲካና ኤኮኖሚ ችግሮች ቁልጭ ብለው ታይተዋል። ነገር ግን ክህደትና ሃስትን የፖሊሲው መሠረቱ ያደረገው ሕወሃት በምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ አማክይነት የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያን እንዳሞካሸ አድርገው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በኩል ሐምሌ 19፣ 2014 አሳፋሪ በሆነ መልኩ መቅረባቸው ይታወሳል! ይህንም በማጋለጥ በዚያው ወር ባለ ሁለት ክፍል የሆነ ጽሁፍ ማቅረቤ ይታወሳል – ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት

TPLF police and military fully armed & ready to attack peacefully protesting citizens (Credit: nazret.com)

TPLF police and military fully armed & ready to attack peacefully protesting citizens (Credit: nazret.com)

ሁኔታው እየከፋ የኢትዮጵያውያን ጩኸት መበራከቱና በሌላው ዓለም መደመጡም፡ ሕወሃትን ክፏኛ አሳስቦታል። ለመጀመሪያ ጊዜ እጅግ በተጠናከረ መልኩ፡ በተለይም በቅርብ ኤትዮጵያን ‘በሞግዚትነት’ የምታሰተዳድረው እንግሊዝ ሃገር ውስጥ በግብር ከፋዮች ስም ለኢትዮጵያ የሚሠጠው ዕርዳታ ለአፈናና ጭቆና መዋሉ፥ ባለህሊና የሆኑ እንግሊዛውያን እጃቸው በንጹሃን ኢትዮያውያን ደም እንዳይበከል በመስጋት ብሄራዊ ተነባቢነት ባላቸው ጋዜጦችና ቴሌቪዥኖች ላይ የሚያሰሙት እየተጠናከረ የመጣው ጉምጉምታ፡ የብዙዎችን ጭንቅላትና አስተሳሰብ ዋነኛው ጥያቄ ላይ ማጉላቱ በሕወሃት ሰዎች መካከል መደናገጥ ፈጥሯል። በዚህም ምክንያት፡ ችግሩን ለማዳፈን ሩጫው በየአካባቢው ተጠናክሯል።

Minister Sufian Ahemd & World Bank Country Director Guang Zhe Chen after signing $600 mil agt for PSNP IV (Photo credit: The Reporter)

Minister Sufian Ahemd & World Bank Country Director Guang Zhe Chen after signing $600 mil agt for PSNP IV (Photo credit: The Reporter)

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያን በሚመለከት በዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል የልማት ዕርዳታ ማሰተባበር የሚመነጨው በእንግሊዙ የልማት ኤጀንሲ ነው (Department for International Development (DFID)። የዓለም ባንክም እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ያቀረበችውን የድጋፍና ዕርዳታ ጥናትና ጥያቄ የጣለበት ጊዜ አይታወቅም። ለምሳሌም ያህል፡ በቅርቡ ከአሥር ሚልዮን በላይ በሚሰቃይበት ወቅት፡ በሚያሳዝን መልኩ ኃይለማርያም GMO ላይ በመተማመን አንዲ ስንዴ ላኪ እንሆናለን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በምግብ ምርት ኢትዮጵያ ራሷን ችላለች በሚሉበት ወቅት፡ የእንግሊዝ ፓርላማ የልማትና ዕርዳታ ኮሚቴ ኤክስፐርቶችንና ድርጅቶችን አሰባስቦ ባለፈው ጸደይ፡ ለኢትዮጵያ ከ2015-2020 ስለሚያስፈልገው ዕርዳታ ዘዴና ዐይነት መክሮ ነው የ$600 ሚልዮን ዶላር ስምምነት ውጤት የተገኘው። ያም ፕሮግራም ትኩረቱ አስፈላጊ ምግቦች (Nutrition) ላይ እንዲሆን ስምምነት አለ። Productive Safety Net Project (PSNP IV) ተብሎ በፓርላማ ኮሚቴው አባላት በኩል ስምምነት ሲደረስ፡ መሠረታዊ ስምምነታቸው እንግሊዝ ይህንን የምትደግፈው ከሌሎች አማራጮች ሁሉ ርካሽ ሆኖ በመገኘቱ ነው በማለት (በሚዲያ እንደሚሉት ለኢትዮጵያ ልማት ታስቦ ሳይሆን ማለት ነው) መዝገባቸው (Houe of Commons documents) ውስጥ ያሠፈሩትን ጠቅሼ ሰለምግብ ዋስትና በጻፍኩት ውስጥ ባለፈው ሐምሌ ወር መጥቀሴ ይታወሳል። የሕወሃት አስተዳደር ግን እንደራሱ ስምምነት በማስመሰል ለኢትዮጵያውያን ውጤቱን የገለጸው ባለፈው ወር ከተቀባይነት ፊርማው በኋላ ነበር።

ወደ ውስጣዊ የፖለቲካና ስብዓዊ መብቶች የሃገራችን ችግሮች መለስ ስንል፡ የሕወሃት ዐይነተኛው መፍትሄ ጠብመንጃና በፖለቲካ ካድሬዎች በሕዝብ መገናኛ አውታሮች የሚረጭ ሃስተኛ ፕሮፓጋንዳ ነው። በአሁኑ ወቅት እንደሚታየው ከሆነ፡ ፓሊሱና ወታደሩ የኢንተርኔት ሱቆችን ከመዝጋት ጀምሮ ወጣቶችን በማፈን፡ በማሠርና በመግደል ላይ ዘመቻቸውን እንደአዲስ ተያይዘውታል። ለምሣሌ አዲስ አበባ፡ ኦሮሚያ፡ ጋምቤላ፡ ሐረርጌ፡ ከፋ፡ ኦጋዴን፡ ሸዋ፡ አፋርና ጎንደር የሕዝቡ ፍርሃትና ሥቃይ ተበራክቷል የሚለው አቤቱታ በተደጋጋሚ ይሰማል።

እንዲሁም፡ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ረድዋን ሁሴን ከብሄራዊ ስለላ ድርጅት ጋር የጀመሩንት የሰባት ሚሊዮን ብር ትብብር ካጠናቀቁ በኋላ፡ ውሎና አዳራቸው ቲውተር ላይ ሆኖአል። የእርሳቸውም ጥረት መፍትሄ ከመሆን ይልቅ፡ ክህደት ላይ ክህደት በመረብረብ፡ ህኔታውን ከድጡ ወደ ማጡ እያዘቀጡት ነው! የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም፡ ምን ያህል ‘የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያችው’ የኤኮኖሚ ድል ለሃገሪቱ እንዳስገኘ ሲደስኩሩ፡ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሕወሃት አንደኛ ተወካይ ደግሞ፡ በዓለም ላይ ርካሽ ኢሌትሪክ ሃይልን በርካሽ በማቅረብ ኢትዮጵያን የሚፎካከር ሃገር የለም ይሉናል – ሕዝባችን መብራትና ውሃ ተነፍጎት እያለ! የውሃና የሃይል ሚኒስትሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የኃይል ዕጥረት የለም ሲሉ ተደምጠዋል ባለፈው ነሐሴ ወር! እንደሳቸው አባባል ከሆነ፡ “It is not only the Ethiopian Electric Services but our government believes that there is no power shortage.”

ምናልባት አሰተሳሰቡ ከቴክኒካል አተረጓጎም አንጻር፣ ይህ አባባል አንድ የቴክኒክ ሃሣብን ይገልጽ ይሆናል! የኢትዮጵያን ችግሮችና ገሃድ ሁኔታ ግን የሚያሳይ አይደለም! በሌላ በኩል ደግሞ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚደንቱ መብራት መጥፋትን አስመልክቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ የቅርታ መጠየቃቸውን ስናስታውስ፡ ነገሩ ምን ያህል በፖለቲካ ጭቃ እንደተለወስ መገንዘብ አያዳግትም።

እንዲሁም፡ በየአካባቢው የሚታየው የውሃ ዕጥረት የተፈጠረው በድርቅ ምክንያት ነው አቶ ዓለማየሁ አሉ ይባላል። ይህንን ሰምተው ተናደው ከሽሮ ሜዳ ሲበሩ የመጡት ለሶስት ወር መብራት ያላዩት ውሃ ያላገኙት አዛውንት የቤት እመቤት ችግራቸውን በድፍረት በአደባባይ ሲያስረዱ፣ ለምን ሽሮ ሜዳና ፒያሳ ውሃ ተነፈጉ ለሚለው የድርቁን ተዛማጅነት ሚኒስትር ዓለማየሁ መልስ አለነበራቸውም። ይህም በሕወሃት ሰዎች መካከል ያለውን የአስተሳሰብ ዝምድና ያሳያል። ለማንኛውም፡ አንባብያን እንደሚያስታውሱት፡ ኃይለማሪያም የጤፍን ከገበያ መጥፋትና የዋጋ መናር – እንዳስተማሪያቸው መለስ ሁሉ – ሕወሃት ከመጣ ጀምሮ የኢትዮጵያ “ሕዝቦች” ጤፍ በላተኛ በመሆናቸው ነው ያሉት ጸያፍና ሃሰተኛ አነጋገር ከኢትዮጵያውያን ጭንቅላት በቀላሉ መወገዱን እጠራጠራለሁ!
 

የሕወሃት ባህላዊ አብዮቱ ፓሊስ ላይ አተኩሮ ተጀመረ

በዚህ ዘመነ ክህደት፡ ሳት ብሏቸው ነው መሰለኝ አቶ አዲሱ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ችግር የአመራር ዕጦት ነው ይላሉ – በቅርቡ ለአመራሩ በምሥጢር ባቀረቡት ጥናታቸው። በአሁኑ ወቅት የባህላዊ አብዮት (እንደ ቻይና 1966-1976) አስፈላጊነትን ካሰመሩበት በኋላ፡ ሲያብራሩም፡

  “በታጋይ ባህሪው ተመልምሎ ሲያበቃ በአመራር ቦታ ላይ ሲቀመጥ በኪራይ ስብሳቢነት የሚሽፈነው ስው ሲታከልበት ለአመራር የሚታጨው ሠፊ ኃይላችን በአመራርነት የመገንባት ብቃቱና ዝግጁነቱ ደካማ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በሌላ በኩል ድግሞ መስመራችን ከ95% በላይ የሚሆነውን የኅብረተሰብ ክፍል መብትና ጥቅም የሚያስጠብቅና የሚያማልል ሰለሆነ ምልመላ ጥራት ቢጎድለውም በሂደት እየተቀየረና እየተሰተካከለ ሊሄድ የሚችል በቀላሉ የማይገመት ቁጥር ያለው ኃይል እንደሚኖር መገመት ይቻላል።”

እነሆ የሕወሃት ባህላዊ አብዮቱ ከተጀመረ ከሶስት ወራት በላይ ሲሆነው፡ በአሁኑ ወቅት ፈንቅሎ የገነፈለው ችግር መጠን ነባር ችግሮችንና አዲሶቹን እንደገና እንዲያጤን ሲያስገድደው – ሁልጊዜም አቋራጭ መንገድ ፈላጊ ስለሆነ – ትኵረቱ የሕወሃት ፖሊስ ሥነ ምግባር ብልሹነት እንዲያርፍ አስገድዶታልነ። በሰብዓዊ መብቶች አለመከበር ምክንያት ላለው ችግር መፍትሄ በቅድሚያ ስለሚያስፈልገው – የሕወሃት ሰዎች ራሳቸውን መፈተሽ ስለማይችሉ – ያጋጠማቸው ጣጣ ሁሉ ምንጩ ፓሊሱ ነው ለማለት እየዳዳቸው ነው።

ቆም ብሎ ለሚያስብ ሰው ግን፡ አስረውና ገድለው ድል የሚቀዳጁበት ምርጫው ከሰባት ወራት ያልበለጠ ጊዜ እያለው፡ እንዴት ነው አሳሪና ገዳይ ኃይላቸውን እጀ ሰባራ የሚያደርጉት የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይቻላል። ተገቢም ነው። ዳሩ ግን የሕወሃት የፖለቲካ ምህዳር በተዋጊ አሜከላ በመታጠሩ፡ በእርስ በእርስ ግጭትና መባላታቸውን ከመጀመራቸው በፊት፡ በሰበብ አስባብ የዓለምን ትኩረት ከራሳቸው ላይ ለማንሳት የሚገደዱ ይመስላል። አሁን ባለው ሁኔታ፣ መጭውን ምርጫ እንደፈለጉት አሸንፈናል ለማለት የሞራልም ሆነ የፓለቲካ ተቀባየነታቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፡ የፖሊሱን ጸረ-ሕዝብነት በ”ቆራጥ” እርምጃ ገተነዋል ሊሉ ይቻላሉ። ከዚያም ከፖሊስ ኃይሉ ውስጥ በተለይ ኦሮሞውንና አማራውን የሚሸብቡበት ሁኔታ ለመፍጠር ይሞክሩ ይህናል!

ሪፖርተር በእንግሊዝኛ እትሙ ቅዳሜ ኅዳር 2፣ 2014 በሚልኪያስ ሰብስቤ ስም ያቀረበው፡ “Rights abuse: systematic or incidental” ጽሁፍ እንደኔ ብዙ ስዎችን አስገርሟል። ድምዳሜው፡ መንግሥታዊውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን ኮምሽን በሃገሪቱ ካሉት 1,081 ፖሊስ ጣቢያዎች 170ዎቹ ላይ በማተኮር (15.7) ያደረገውን ጥናት በመጥቀስ፤ ከነዚህም ውስጥ 29 ከመቶ የሚሆኑቱ አሠራራቸው ሰብዓዊ መብቶችን የጣሰ ነው ሲል ፈርጇቸዋል – “And 29 percent of the police stations assessed exercise intimidations and other forms of human rights violations during interrogation” ይላል።

በዚህም ምክንያት በመንግሥት አነጋገር፡ ሁኔታውን “ተናጠል” (isolated incidents) አድርጎ እንደሚመለከተው ጸሐፌው ጠቅሰው፡ በሌሎች አነጋገር ችግሩ ሥርዓታዊ (ፖለቲካዊ) ወይንም የሕግና የአሠራር ሥነ ሥርዓት መጥፋት የሚለውን የተለያዩ ወገኖች ዕይታ አሳውቀው፡ ምነንቱንና የጽሁፋቸውን ዓላማ ሳያሳውቁ በእንጥልጥል ይተዉታል!

የጸሐፊው አቀራረብና ውሱንነት ያልተመቻቸውና የቀፈፋቸው ታዴዎስ/ገ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የስብዓዊ መብቶች ችግር ፖሊስ ላይ ከማላከክ ቀና ብሎ ወደ ሕወሃትና ጭፍሮቹ አቅጣጫ መመልከት የችግሩን እርግጠኛ ምንጭ ባሳየ ነበር ካሉ በኋላ፡ የጸሐፊው አቀራረብና ውሱንነት ያላማራቸው ታዴዎስ፣ እጅግ የተከፉበት አባባል፡ የስብዓዊ መብቶች መረገጥ ከፖሊስ ጋር ብቻ የተያያዘ አለመሆኑነ ግልጽ ያደርጋሉ። በራሳቸው አስተሳስብ ችግሩን ሲያቀርቡት እንደሚከተለው ያስቀምጡታል፦

  “If you ask me, when as a nation the TPLF feeds us false propaganda on television and radio we finance with our tax birr, we are being violated by the denial of truthful information. When Hailemariam pounds his chest in parliament and [pro]claims the right of his party to use public money as it sees fit is another robbery and violation of the human rights of Ethiopian people.

  It is not only violence, like the killings in the stadium or Gedeb Asassa or beatings of Ethiopian church leaders, or massacre of Oromia University students or the rape by the security forces of leaders of opposition parties, [but also it] is a crime, especially males raping males – newest phenomenon in the Ethiopia under the TPLF; or when homes are demolished without the residents being given alternative places is criminal and a demonstration of the arrogance of power.

  Recall, what former mayor Kuma Demeksa said, when he was told about Addis Abebans’ complaints [regarding] his policy of home demolishing. He told his staff, “Keep on. When you face resistance operate your dozers!”

  Over the years, I have learned through observations and analysis of the words coming out of the mouths of Ethiopian officials. The conclusion I have reached is that our leaders desires and worship of power lies at the heart of the vexing human rights problems in Ethiopia.

  Recall how the hooligan language Meles Zenawi constantly employed, when he wanted to make negative remarks about the opposition. He did this to anyone critical or opposed to him. Ethiopia has been very unlucky in many respects. Worse is his successor, who is an embodiment of lies and vulgarity, as if same parents and teachers have raised both. It is this similar embarrassing and criminal behavior that has now been passed to officials at the lower rungs of power.

  One should know better what happens, when top leadership nods and remunerates citizens’ beaters – the police, cadre or the army – like a Pavlovian dog such people would salivate to beat, torture and kill or engage in eliminating critics of the system, which now is our country’s reality.”

Why this much hatred of Ethiopians and love of power? PM Hailemariam Desalegn

Why this much hatred of Ethiopians and love of power? PM Hailemariam Desalegn

ይህ የጸሐፊው አባባል እኔንም አንድ ነገር አስታወሰኝ። ኃይለማርያም ከተ.መ.ድ. ስብሰባ ከኒውዮርክ በተመለሱ ማግሥት ጥቅምት 5፣ 2013፣ በአስቸኳይ 29 ጋዜጠኞች የተጋበዙበት ፕሬስ ኮንፈረኒስ ላይ – ለስድስት ጋዜጠኞች ብቻ የመጠየቅ መብት ሰጥተው (ሪፖርተር እንደዘገበው) – የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን በማጥላላትና በማስፈራራት፡ እንዲሁም የእስላሞች እንቅስቃሴን በማጥላላትና በሽብርተኞች ቅጠረኝነት ስም በማንኳሰስ፡ – እንደ ዋልታ ገለጻ – ያላንዳች መሸማቀቅ ሁለት ሶስት ማስፈራሪያዎች ካፋቸው አወጡ።

በተለይም፡ ወጣት ሴቶችንና ልጃገረዶችን የእስላሞች ሠልፍ ላይ እንዳይገኙ በማስፈራራት፡ ሄደው ከተገኘም “እንቆነጥጣችኋለን” ማለታቸው አይዘነጋም። ምን ዐይነት መሪ ነው ወንጀል ሳይፈጸም፡ ሕገ መንግሥታዊ የመሰብስብ በሰልፍ ተቃውሞ ማሰማትን መብት ረግጦ “እንቆነጥጣችሁላን” የሚል? አስፈራርቶ ሃገር መግዛት!አሳፋሪ የሆነውን ያህል፡ ለBBC ጋዜጠኛ ኢማኑኤል ኢጉንዛ ከጥቂት ወራት በፊት የሰጡት አሸባሪ መልስም ከዚህ የተለየ አይደለም!

ለነገሩ፡ መለስ ዜናዊስ የግል ንግድ ዘርፉን ሀብትና ንብረት በሕወሃት ሰዎች ለማስወረስ አይደል እንዴ “እንዲህ ካደረጋችሁ፡ እጅ እንቆርጣለን” ሲል የነበረው።

ታዲያ የተባለው የኃይለማርያም ማስፈራሪያ ተግባራዊ ለመሆን ብዙም አልፈጀበትም። አንዋር መስጊድ ውስጥ በተደጋጋሚ የሕወሃት የጸጥታ ስዎች በመግባት፡ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች አማንያንን በመተናኮል በፈጠሩት ግብግብ፡ ብዙዎች ተደብሴበዋል። በየወቅቱ የታሠሩትም እስካሁን እንደሚንገላቱና በስበብ አስባቡ እየተውነጀሉ መሆናቸው ይታወቃል።

ወይንሸት ሞላ [Credit: via Helen Wame]

ከሁሉም በላይ ግልጽ ሆኖ የወጣው የሰብዓዊ መብት ረገጣና ሠፋ ያለ የጋዜጦችና ጦማርያንን ዕይታ ያገኘው የሰማዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆነቸው የ23 ዓመቷ ወይንሸት ሞላ ላይ ሐምሌ 18፣ 2014 – ከቁንጥጫ በጣም በዘለለ – የተፈጸመባት ድብደባ፡ የእጇ ሰበራና ጭንቅላቷ ፍንከታ ነው። ወንጀሏ ምን ይሆን? ልጅቷ አስተዳደጓ ክርስቲያን ነው። በፖለቲካ ስሜቷ ግን የእስላሞች ትግል ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲና ለሃይማኖት ነጻነት የሚያደርጉት ትግል አካል ነው ብላ በማመኗ በዕለተ አርብ መስጊድ አካባቢ ቆማ ሁኔታውን መከታተል ትጀምራለች። በሰማያዊ ፓርቲ አባልነቷ ለሚያውቃት የሕወሃት የስለላ ባልደረባ ፖሊሶችን በማስተበበር እንደ እባብ ወጣቷን የፖለቲካ ሰው ቀጠቀጧት። ለተወሰኑ ጊዚያትም እሥር ላይ ከርማለች። በሽብር ፈጠራ ስም የተመሰረተባት ክስ ባለመሠረዙ አሁንም ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ትገኛለች!

ለዚህ ግፍ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ፖሊሶችና የስለላ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፡ በግንባር ቀደምትነት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው። ይህንን ስለተገነዘበ ይመስላል፡ የሰሞኑ የእንግሊዙ ጋዜጣ – The Telegraph – ስብዕነታቸውን ሲገልጽ “untroubled by criticism in the local press or any public opposition…” ማለቱ የችግሩን ብልት ማግኘቱን ያሳያል!
 

ሪፖርተር ምን አይቶ ይሆን የሕወሃት ፖሊሶች ሥነ ምግባር ብልሹነት ላይ ያተኮረው?

ሪፖርተር የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግሮች ልቡ ውስጥ አለ ከሚሉት ሰዎች መካከል አይደለሁም። በቤትና መሬት ዘረፋ ግንባር ቀደም ተዋናይ እንደመሆኑ፡ ያለውን የሕወሃት አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም እንደተሰለፈ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም – የቀድሞ ፕሬዚደንት ነጋሶ ጊዳዳ ስለሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት የሰጡትን ምሥክርነት በሚገባ አንብቤያለሁና! በተግባርም፡ ከ1997 ምርጫ በኋላ ይህንኑ በተግባር ማሳየቱን አስታውሳለሁ።

ቅዳሜ በእንግሊዝኛ መጽሔቱ ያወጣውን ዜና እንደገና በአማርኛ እትሙ እሁደ ዕለት ደግሞታል። የሁለቱ አቀራረብ ግን በጣም ይለያያል- በተመሳሳይ ዜና ላይ የተመሠረት ሆኖ ሳለ!

ያላንዳች ጥፋት የትራፊክ ፖሊሶች እንዴት አድርገው አንዱን ወጣት ከጥፊ እሰከዘለፋ በደረሰ በማዋከብ የተዋራጅነት ስሜት ሰለፈጠሩበት፡ መብት አለኝ ብሎ ለመክሰ ሲዘጋጅ እንዴት በማስፈራራት እንደመለሱት ይተርካል።

ጽሁፉ ምነም የሕግና የአፈጻጸም ችግሮችና ውስብስብነት የለበትም (ጥቂት እንደ እንግሊዝኛው እንኳ)። ባልሥልጣኖቹ ግን፡ “የአፈጻጸም ክፍተቶችና የግለሰቦች ስህተት” ይኖሩ ይሆናል የሚል ግምት እንዳላቸው ያሰማል። የጥርጣሬ በር ግን ክፍት ትቷል።

የትኩረቱ አጀማመር፡ እንደ እንግሊዝኛው ፖሊሶች ኃይልን በዜጎች ላይ መጠቀም አይተርክም። እንዲያው በደፈናው በትራፊክ ፖሊስ ላይ ያተኮረ ነው። ሁለቱንም ያነበበ ግለስብ፡ ጽሁፎቹ ሁለት አንባቢዎች እንዳሏቸውና መልዕክቶቻቸውም ለዚሁ የተመተሩ መሆናቸውን መገንዘብ አያዳግተውም።

የእንግሊዝኛው ጽሁፍ የግለስብ መብቶችን፡ በእሥር ቤቶች ያሉትን የመብት ረገጣ በሚገባ ያሳያል። የአማርኛው ጽሁፍ ላይ ትኩረቱ የትራፊክ ፖሊስ ጉዳይ በመሆኑ፡ ዜጎች በተለምዶ እንደሚሉት ከመብት አንጻር ከማየት ይልቅ አሸከርካሪውን አንድ ጥፋት ሠርቶ ይሆናል፡ ይህ ጥጋብ የነፋው ባለመኪና ሊሉም ይችላሉ!

ስለዚህ በሕወሃት አስተዳደር በኩል የሕግና የአፈፃጸምም ችግሮች አሉ ለማለት እንደማይደፍሩ በተዘውዋዋሪ ለማሰማት ሞክረዋል በአማርኛው ጽሁፍ ውስጥ። ዞሮ ዞሮ መንግሥት ለፖሊሶችና ደህንነት አካሉ እኔ ከናንተ ጋር ችግር የለኝም ለማለት የሚያስችል ቀዳዳ ትተዋል!

የምርጫው ሁኔታ በምን መልክ የሕወሃት አስተዳደር ለፖሊስ ኃይሉና ለደህንነቱ ድጎማ ወይንም ዱላ እንደሚሰጥ በውጤቱ – ማለትም ምን ያህል ሰዎች እንደሚጎዱ – የምርጫው ውጤት በውጭው ዓለም ዐይን በተለይም መዋቅራዊ ታዛቢዎች እንዴት እንደሚመለከቱትና የሚሰጡት አስተያየት ላይ ያርፋል።

ውጤቱ ጎጂ ከሆነ ትዕዛዝ ሰጥቶ ወገኖቻችንን እንዳስጨፈጨፈው መለስ ዜናዊ “የጸጥታ ኃይሎች ተደናግጠው የወስዱት እርምጃ ነው” የሚል በሁሉም በኩል ለመቦጨቅ የሚያስችል አቋም እየተዘጋጀ ያለ ይመስላል።

በሣምንቱ መጨረሻ ላይ ይህንን ዘመቻ ሪፖርተር ክፍቶታል። በመጭው ጊዜያትም ብዙ የሚገለበጡ ድንጋዮች መኖራቸውን ልንሰማና ልንመለከት አንደምንችል አልጠራጠርም!
*Updated
 

%d bloggers like this: