ሕወሃት የመለስ ዜናዊን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂን (GMO) ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፤ በዘር ንግዱ ከፍተኛ ድርሻውን ያዘ

24 Nov

የአዘጋጁ ማስታወሻ፡

አፋጥኑት የኢትዮጵያን በምግብ ራስን መቻል ዋስትና ምርጫው ከመደረሱ በፊት ሳይሆን አይቀርም ግፊቱ!

አቶ ኃይለማርያም ሳይንሱንም ቀድመው መጀመሪያ በጥቅምት 2013 ስንዴን አስመልክተው ከአርሲ አፍሪካን እንመግባለን ሲሉ ነበር። ከዚያ ሕወሃት የኢትዮጵያን ሠራዊት ድል ያደረገበትን ሚያዝያ 28 2014 ሲያስከብሩ በአዲስ አበባ ስታድዮም በምግብ ራሳቸንን ችለናል ብለው የሳይንሱን ማራቶን አቸንፈው ነበር! ያኔም አውቀነው ነበር፤ ዛሬም ምሥጢር አልሆነብንም!

ይህ ግን በቂ የሠለጠነ የሰው ኃይልና ሣይንሳዊ መከላከያ የሌላትን ድሃ ሃገር ምን ላይ ይጥላት ይሆን? እነ ሕንድ ከጥጥ ውጭ ያልደፈሩትን፡ ምነው የኢትዮጵያን ባልሥልጣኖች ታላላቅ የአሜሪካና የአውሮፓ ዘር አብቃይ ኮርፖሬሽንና የአሜሪካን አስተዳደር ለማስደሰት ሲሉ ጀብደኞች አደረጋቸው? የአካባቢያችን አየር በአበባዎች ምርት ኬሚካሎችና በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ዙሪያ ባሉት ወንዞች መበከሉ ሳያንስ፡ አሁን ደግሞ ዕውቅ የተፈጥሮ ሃብታችንን ልናጣ አይደለምን?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ህዳር 15/2007 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በዘንድሮው ዓመት በሽታን የሚቋቋሙና የተሻለ ምርት የሚሰጡ ከ30 በላይ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች ማውጣቱን አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂን ለመጀመር የፖሊሲ ክለሳና ማሻሻል ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፈንታሁን መንግስቱ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት እስካሁን የነበሩትን የበቆሎ፣ የስንዴ፣ የጤፍና የገብስ የሰብል ዝርያዎች በማሻሻል የተሻለ ምርት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው።

እነዚህ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በሽታን የመቋቋም አቅም ያላቸውና የተሻለ ምርት የሚሰጡ የሰብል ዝርያዎችን ለተጠቃሚ አርሶ አደሮች ለማድረስ ዝርያዎችን የማባዛት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ቁንጮ ከተባለው ጤፍ በአይነቱ የተለየና የተሻለ ምርት የሚሰጥ ጤፍ በዘንድሮው ዓመት ወጥቶ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ በብዜት ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።
===============================================================================
ይህንንም ይመልከቱ:

TPLF sneaks into Ethiopia’s seeds market, jeopardizing food security goal merely to ensure its continuity in power & privilege

===============================================================================
በአንድ አይነት ጤፍ ብቻ ሁሉንም የአገሪቱ የግብርና ስነ ምህዳሮች ማዳረስ አዳጋች መሆኑን የሚገልጹት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ አሁን የወጣው ጤፍ እንደ አማራጭ መቅረቡ በሁሉም የግብርና ስነ ምህዳሮች ለማዳረስ ያግዛል ብለዋል።

በጤፍ ላይ የሚስተዋለውን የመውደቅና የመበላሸት ባህሪ ለማስቀረት ስዊዝ አገር ከሚገኝ የምርምር ተቋም ጋር በመሆን ባህሪውን በመቀየር እንዳይወድቅና እንዳይበላሽ በማድረግ ይባክን የነበረውን ምርት ለማስቀረት የሚያስችል ምርምር እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የስንዴ ምርታማነትን እየተፈታተነ የሚገኘውን የዋግና የግንድ ዋግ በሽታ ለመከላከል በሌሎች አገሮች ተለቆ የነበረ ኬሚስበርድ የሚባል ዋግን መቋቋም የሚችል የስንዴ አይነት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት የማላመድ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።

በቆሎን ዝናብ አጠር በሆኑና በቂ ዝናብ ባላቸው አካባቢዎች ሁሉንም ስነ ምህዳሮች ያማከለ ዝርያ በማውጣት በስፋት መሰራጨቱን ገልጸው በአሁኑ ወቅት ደግሞ የፕሮቲን ይዘት ያለው በቆሎን ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በአገር ውስጥ ያልነበረ ከፍተኛ ጥራት ያለው ዘይት መስጠት የሚችል ካሚሊና የሚባል የቅባት እህል ሁለት ዝርያዎች መልቀቅ ተችሏል ብለዋል።

ዶክተር ፈንታሁን የዘረመል ምህንድስና ውጤቶች ላይ ቀደም ሲል የወጣው የደህንነት ፖሊሲ ጥብቅ በመሆኑ ቴክኖሎጂውን እስካሁን አገር ውስጥ ሳይገባ መቆየቱን ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው ምርታማነትን ለማሳደግ አዋጭነቱ ተፈትሾ ፖሊሲው እንዲሻሻል ኢንስቲትዩቱ ከግብርናና ከአካባቢና ደን ጥበቃ ሚኒስቴሮች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነ ነው ዳይሬክተሩ ያስረዱት።

የዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ከተደረገ የግብርናን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ የሰብሎች በሽታን የመቋቋም አቅምን እንደሚያጎለብት ነው የገለጹት።

ቢሆንም ቴክኖሎጂው ወደ አገር ውስጥ ከገባ ለምግብነት በሚውሉ ሰብሎች ላይ እንደማይውል ዶክተር ፋንታሁን ተናግረው ለኢንዱስትሪ ግብዓት በሚሆኑ ተክሎች በዋነኛነትም በጥጥ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከዚህም በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጉልበት ሊያግዙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በዘንድሮው አመት ውጤታማ የሆኑ የስንዴ መዝሪያ ማሽኖች መውጣታቸውን ገልጸዋል።

ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር የአየር ጸባይ መረጃን በተለይ መቼ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችልና አፈሩ እንደሚረጥብ የመሳሰሉትን መረጃዎች በአይሲቲ ቴክኖሎጂ ተደግፎ አውቶማቲክ በሆነ መንገድ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የሚያስችል ፕሮጀክት ተቀርጾ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የገለጹት።

የሚወጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከአርባ ሺ በላይ በሚሆኑ በተመረጡ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ጠቅሰው ሞዴል አርሶ አደሮች ያላቸውን ተሞክሮ ለሌሎች እንዲያካፍሉ ይደረጋል ነው ያሉት ዋና ዳሬክተሩ።

ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ኢንዱስትሪውን የሚመግብና ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችና ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ሰብሎችን ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
ተዛማጅ ጹፎች፡

GMO’s road into Ethiopia already paved long ago, now follows the enabling law, despite opposition

Ethiopia finally is headlong into new ‘improved’ seeds; do they call them GMOs?

Food security & food aid as alibi, GMO being massively pushed into Ethiopia, Africa

 

%d bloggers like this: