የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በምርትና በንግድ ዶላር መሳብ ሲሳነው፡ የሕወሃት ባለሥልጣኖች የተ.መ.ድ. ሰላም አስከባሪ ሥምሪቶችን ቢዝነስ አደረጉ ይባላል

4 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አድማስ እንደኔው ተገርሞ ነው መሰለኝ፡ “ሰላም አስከባሪነት” ለኢትዮጵያና ለሩዋንዳ ገቢ እያሰገኘ ነው የሚለውን በዚህ ሣምንት እትሙ አስፍሮ ሳየው፡ ብቻዪን አይደለሁም አልኩ።

ይህ ሰላም ለማስከበር ተብሎ በ1956 በዳግ ሃመርሾልድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊነት ወቅት የተጀመረው አሠራር ብዙ ሕይወትንና ሃገሮችን ያዳነ ሲሆን፡ ዛሬ፡ በኢትዮጵያ መሪዎች በአህጉራዊ ሰላምና ዲፕሎማሲ ስም ወደ ንግድና ለወታደር ላኪ ሃገሮች በሰውና በመሣሪያ ንግድ (አገልግሎት) ትርፍ ማካበቻ መቀየሩ በዓለም ዙርያ ሕዝቦችን፤ በየሃገሩ ያሉ ሰላም ወዳዶችን ሊያሳስብ ይገባል።

በወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑትን የኬንያ መሪዎች ለመርዳት በአፍሪካ ኅብረት ሽፋን – ራሳቸውን ለማትረፍ – ሕወሃት ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትን (International Criminal Court) ለማስፈረስ ከፍተኛ ጥረት ያደረገው ሳያንስ፡ አሁን ደግሞ የተ.መ.ድ.ን የሰላም ማስከበር አሠራርን ለራሱ ትርፍና ገቢ ወደ ንግድ መቀየሩ ሊወገዝ የሚገባው ከፍተኛ ወንጀል ነው።

ለዚያውም የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረት (ሠራዊቱንና ጦር መሣሪያዎቹን) ወድ ግዳጅ ሥፍራ በማሻጋገር ከተ.መ.ድ. በአገልግሎት ክፍያ ስም ገንዘብ የሚዘርፍበት ቀዳዳ ማድረጉ፡ ሃገራችን ፊት የተጋረጠውን ከፍተኛ አደጋ የሚጠቁም ነው።

Gen Samora Younis

Gen Samora Younis

ኅዳር 22፡ 2014 Arms and the African በሚል መጻጽፉ The Economist ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፍሪካውያን የመከላከያ ኃይላቸውን ለመገንባት ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያጠፉ ጠቅሶ፡ እንደ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ዐይነት ሃገሮች ደግሞ የተ.መ.ድ.ን ሰላም አስከባሪ ሥራና ስምሪት ለመከላከያ ሚኒስቴሮቻቸው “አዲሱ የቢዝነስ ሞዴል” መሆኑን አስምሮበታል።

ሕወሃትን ለዚሁ እንዲረዳው ተብሎ እንደሆነ ይገመታል፡ በቅርቡ ከዩክሬን ያዘዛቸው 200 T-72 ታንኮችም ወደ ኢትዮጵያ መላክ መጀመራቸውን መጽሔቱ ጠቅሷል። እርሱንም ወታደራዊው የበላይ አዛዥ ጄኔራል ሳሞራ ዩኒስ ያላንዳች ጨረታናሚቴ በብቸኝነት ማዘዛቸውም የአንድ ስሞን ዜና ነበር – ነገ እንደገና ለፀሐይ ቀርቦ እንደሕዝግብ መደንዘዛችንን እስኪያረጋግጥልን ድረስ!
 

ኢትዮጵያ አንደኛ ሃገር ሆነች በላከችው ሠራዊት ብዛት

የሕወሃት ‘ኤክስፐርቶች’ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የግጭት አካባቢዎች ኢትዮጵያ 12,247 ሰላም አስከባሪዎችና መሣሪያዎች በመላክ በዓለም ላይ ቀዳሚውን ሥፍራ መያዟን ሲያስተጋቡ አንድ የድል ውጤት ወይንም ልዩ ለግንባሩ ብቻ የተለየ ተሰጥኦ ያስመስሉታል። ምናልባትም በግንባር ቀደምነት ይህንን ለማስጮህ (በተቀባይ ፕሮፓጋንዲስቶች አማካይነት)፡ መንስዔ ከሆኑት ምክንያቶ አንዱ ሊሆን ይችላል ያልኩት ዶ/ር መሃሪ ታደለ ማሩ በጥቅምት ወር ላይ ላዩን በመዳሰስ ያቀረቡት Ethiopia’s Regional Diplomacies: A Dominant: Interpretation of the Horn of Africa ጥናት ሊሆን ይችላል።

እዚያ ጥናት ውስጥ የሚከተለው ይገኛል፡-

    “The external threats to the country [Ethiopia], as identified by four administrations, namely Emperor Haile Selassie, Colonel Mengistu Haile Mariam, the late Prime Minister Meles Zenawi and the current administration of Hailemariam Desalegn, have generally been quite similar. While the regimes of Haile Selassie and Mengistu were outward-looking, Ethiopia under Zenawi and now Desalegn appears more inward-looking. Previous Ethiopian regimes, particularly Mengistu’s military regime, externalised almost all the country’s problems by focusing on building military defence capabilities against the ‘historical enemies of Ethiopia’ …Entrenched in its ideological perspectives about the root causes of Ethiopia’s internal troubles and possible solutions, the Ethiopia People’s Revolutionary Democratic Front- (EPRDF) led government regards regional diplomacy as another platform for solving regional problems that affect Ethiopia’s internal governance and development challenges… Therefore, the country’s regional diplomacies are pursued through a dominant interpretation of the country’s role in the region.”

Dr. Mehari Tadele Maru (Credit: Ispionline.it)

ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ከአፍሪካ ሶስተኛዋና በዓለም ላይ ደግሞ አርባኛ መሆኗን ጸሃፊው ጠቅሰው፡ የዚህም ፖሊሲ 24 ዓመት ጉዞ ሃገራችን በወታደራዊ ጥንካሬዋ፡ በተለይም በአህጉራዊ ሰላምና ደህንነት አስገራሚ ዝናና ስም እንዲሁም በሰላም ማስከበር ተሳትፎ፡ በጸረ-ሽብር ሥራና በአስታራቂነት ያደረገችው አስተዋጾ ዘለቄታ ያለው ወዳጅነትንና ትብብሮችን በአህጉሩ ውስጥና ከዚያም ባሻገር ፈጥሮሮላታል ይላሉ።

በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ተፈላጊነት በመጠናከሩ፡ ለሰላም ጥበቃ በተ.መ.ድ. እና በአፍሪካ ኅብረት ስም በሶማልያ፡ በሱዳን (አብዪና ዳርፉር)፡ ላይቤሪያ፡ ወዘተ. 12,247 ሠራዊት እንድታቀርብ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ያወሳሉ።

አንዴም ግን ጽሁፋቸው ኢትዮጵያ ከተ.መ.ድ. ስለምታገኘው ከፍተኛ ክፍያ አያነሳም – ምንም እንኳ የአደባባይ ሚሥጢር ቢሆንም። እንደዚሁም፡ የኢትዮጵያ በባዕዳን እጅግ ተቀባይ መሆን – መሃሪ ታደለ – እንደሚሉት በዚህ መደላደል፡ የውጭ ድጋፍ መራከት፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጭቆናና አፈናው መጠናከር ውጭ ሠራዊትና ትጥቅ ማንሸራሸሩ በምን መልክ ለሃገራችን መረጋጋት፡ ሰላምና ነጻነትን፡ ለተቋሞቻችን መጠናከር፡ የኢኮኖሚያችን ዕድገትና ብሔራዊ መሠረቱ ተጠናክሮ ለእኩልነት አስተዋጽኦ እንዳደረገም አያሳዩንም!

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ፡ ሕወሃት በኢትዮጵያ ስም በእነዚሃ 20 ዓመታት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በሰላም ስም በመፈራረም በአገልግሎት ክፍያ ስም ለContingent Owned Equipment ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብሏል። ይህም ከእያንዳንዱ Memorandum of Understanding (MOU) ማየት ይቻላል። ተ.መ.ድ.ም አለው። ገንዘብ ሚኒስቲርም ስለማያውቀው፡ መከላከያ ውስጥ ያሉ ጥሩ ዜጎች ገሃድ ሊያደርጉት ይገባል!

ተ.መ.ድ. በዓመት ዘማች ሠራዊት ላዋጡ ሃገሮች ሶስት ቢሊዮን ዶላር ለወታደሮቻቸው፡ ፖሊስና ሌሎችን ዐይነት ባለሙያተኞች አገልግሎትና ለመሣሪያዎቻቸው ይከፍላል። ኢትዮጵያም የዚህ ገንዝብ ተቋዳሽ ናት።

ለምሳሌም ያህል፡ አንድ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልሥልጣን ከነዩኒፎርማቸው በቴሌቪዥን ጥቅምት ላይ ቀርበው እንደ ውስጥ አዋቂ ምሁሩ ምሥጢርና ሽፍንፍን ሳያደርጉት፡ ከተባበሩት መንግሥታት ሃገራችን የምታገኘው ክፍያ ጠቃሚ መሆኑን መጥቀሳቸው፡ በመከላከያ ውስጥ በዘረኝነት የተደራጁ ሰዎች የሚጠቃቅሙበት መሆኑንና ጉምጉምታውም እያደገ መምጣቱና የሠራዊቱ አባላት ቅሬታ መጠናከሩ በተደጋጋሚ ሲነገር ይሰማል።

ለወደፊት ሕወሃት የሚያስፈልገውን ስትራቴጂ እንዲቀይሱ ተብለው በግንባሩ የበላይ መሪዎች ተመርጠው ከሃገር ሃገር በየምርጥ ዩኒቨርሲቲው እንዲማሩ፡ በአፍሪካ አንድነት ድርጅትም በነመለስ አማካይነት ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዲሆኑላቸው ተመርጠዋል የሚባሉት መሃሪ ታደለ ማሩ ምናልባትም ዕይታቸው፡ ተጨማሪ ብርሃን ያገኛል በሚል እምነት: ጥቅምት 29፣ 2014 የሚደጋግሙት ነገር በመሆኑ፡ ብዙ የሰላም አስከባሪ ኅይል ማሠለፍ (ከሃገሪቷ የጦር መሣሪያዎች ጋር)፡ ከዲፕሎማሲያዊ ተግባራዊነትና ጠቀሜታው ውጭ፡ እርሳቸውም ራሳቸውን ወደግንባር የሚገፉበት ጉዳይ መሆኑ ስለተሰማኝ በትዊተር የሚከተለውን አስተያየት ሠንዝሬ ነበር

“@EthiObservatory ‏ Oct 29 @meharitaddele ‘Sacrifice’ whose gains TPLF has well worked out: int’l diplomatic, political support & cash payments to troops & the regime!”

በሌላ አባባል፡ ኢትዮጵያ አሁን በአፍሪካ፡ ነገ በዓለም ዙርያ ሰላምን ማስከበር መለኮታዊ ግዴታዋ ያደረገች ሃገር አድርጎ ለመሳል በሚደረግ ጥረት ይህንን ዜና አድርገው ያሠራጩት ምሁር ቀደም ሲል በየአካባቢው እንዲሁም ዲስኩር በማድረግና በኋላም በትዊተር ጭምር ጥቅምት 29፣ 2014 የሚደጋግሙት ነገር ሆነ፣ ለምሳሌም ያህል፡
“Mehari Taddele Maru ‏@meharitaddeleWith 12,247 troops under UN PSOs and AMISOM, Ethiopia is now the biggest troop-contributing nation in the world. More http://www.saiia.org.za/doc_download/600-ethiopia-s-regional-diplomacies-a-dominant-interpretation-of-the-horn-of-africa … ”

ለነገሩ፡ ከዋና ዋና ሀብታምና ኃያላን ሃገሮችም ግፊት ይኖራል። ትልልቆቹ ሃገሮች ወታደሮቻቸው በደሃ ሃገሮች ጦርነቶች መሳተፋቸውን (አስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር) አይቀበሉም። ሕዝባቸውም አይደግፈውም።

ሆኖም በዚህ ጉዳይ ዙርያ በዶ/ር መሃሪ በኩል ይመጣል ብዪ የጠብቅሁት ለውጥና መሻሻል ቀርቶ፡ እንዲያውም እንደዛሬይቷ ታሪክ ሠሪ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ኖራ አታውቅም ለማለት የሚዳዳዳቸው፡ የሕወሃት ፕሮፓጋንዲስቶች የሚቃጩበት ሁኔታ በገሃድ ፈጥረው አረፉ። ለምሳሌም ያህል፡ Tigraionline.com ዛሬ በሰላም ስም ሕወሃት የውጭ ምንዛሪ ለማሰባሰብ የሚያደረውን መሯሯጥ ወደጎን በመግፋት፡ ሕወሃትን ለብሔራዊና አህጉራዊ ሰላም የቆመ ኃይል ለማስመሰል እርሳቸው እንዳደረጉት ሁሉ፡ ብዙ ጥረት ሲያደርግ ይታያል።

እውነት ላይ መመርኮዝ ቢኖር፡ ለሃገርና ለሕዝብ ከበሬታ ቢኖር ኖሮ፡ ከሁሉም በላይ የማሰብና የማስተዋል ችሎታ ቢኖር ኖሮ፡ የዛሬውን ከጥንቱ ጋር በማነጻጸር፡ በ1950 ኢትዮጵያ ወደ ኮሪያ “በቂ ሥልጠናና ዝግጅት ያልነበራቸው 3,518 ወታደሮች” በጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ አዛዥነት መላኳን መጥቀሱ፡ ሕወሃት በትውልድ ጠላትነት ላይ የቆመ ድርጅት መሆኑን የሚመስክር ነው።

እውነቱን ለመናገር፡ የማነጻጸሩ ምክንያትና ትርጉም አልታይ፤ አልያዝ ያለኝ መሠረተ ቢስና ሃስት ከመሆኑም ባሻገር፡ ሂሣብን በሚገባ ለመገንዘብ እርሳሶችና አህዮችን አብሮ መደመሩ ድንቁርና በመሆኑም ሊሆን ይችላል።

እነዚያ ወታደሮች ብቃት ካልነበራቸው፡ ለምንድነው አብሮ ዘማቾቻው የባእድ ወገኖች የራሳቸውን ይዞታ በጠላት ሲነጠቁ፡ የኢትዮጵያ ጦር ደርሶ እነርሱንም ያተረፋቸው። የኮሪያ መንግሥትስ በእነርሱ ስም ለልጆቻቸው ያቋቋመውን የነጻ ትምህርት ዕድል የሕወሃት ግለሰቦች መጠቀም ጀመሩ ተብሎ ብዙ አወቃቃሽ የነበረው በእነዚያ ጅግኖች ስም አይደለምን?
 

በተ.መ.ድ. የሰላም አሰከባሪ ኃይል ተሳትፎ ያለው ጠቀሜታዎች

ወደ ተ.መ.ድ. አሠራርና ለስላም አስከባሪ ሃገሮች ገንዘብ ክፍያ ጉዳይ ለመወያያት፡ ስለዚህ ጉዳይ ራሱን የቻለ መመሪያ መኖሩን መገንዘብ ያስፈልጋል።

የድርጅቱ የሰላም አሰከባሪ ኃይሎች ወጭ በአባል ሃገሮች የሚሸፈን ነው። በዓለም ዙርያ ላሉት ሥምሪቶች (Peacekeeping mission/forces) በእያንዳንዱ ሃገር በግዴታ ወጭያቸውን ይከፍላል (Article 17 of the UN Charter)። ለዚህም ነው የሰላም ስምሪት ራሱን የቻለ የክፍያ ሥርዓት እንዲኖረው የተደረገበት ምክንያት፡ (scale of assessments for the apportionment of the expenses of United Nations peacekeeping operations)።

ዋናው መታውቅ ያለበት ጉዳይ ግን ተ.መ.ድ. ቋሚ ሠራዊት የለውም። ካዝና ውስጥም በድንገት ለሜመጡ ሥምሪቶች ገንዘብ የለውም። በዚህ ምክንያት ነው፡ ከብዙ ድርድር በኋላ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሚሆኑ ሃገሮች (troop contributing countries)፡ ወታደሮቻቸው የራሳቸውን መሣሪያዎች፡ ታንኮች፡ ሄሊኮፕተሮች ወዘተ ይዘው እንዲሠማሩ የሚደረግበት ምክንያት።
በሰላም አስከባሪነት ወታደሮቻቸውን የሚያሰማሩ ሃገሮች ከፍተኛ የፖለቲካ፡ ዲፕሎማቲክ፡ የቀና አመለካከትና ድጋፍ ተጠቃሚዎች ያደርጋቸዋል።

ባለፉት ዘመናት የነበረው በተ.መ.ድ. ከፍተኛ ደረጃ ተሿሚ የሚሆኑት ባለሥልጣኖች (ካቢኔ) በብዛትና በተከታታይ ወታደር በቋሚነት አሰተዋጽኦ ከሚያደርጉ ሃገሮች መካከል ነበር። በ1945 ኢትዮጵያ ከድርጅቱ የመጀመሪያ መሥራቾች መካከል ብትሆንም፡ አስከ ደርግ ውድቀት ድረስ አንድም ከፍተኛ ቦታ (Under Secretary-General (USG), Assistant Secretary-General (ASG) አላገኝችም። ከ1991ዎቹ በኋላ ግን፡ በሁለቱም ደረጃዎች (USG እና ASG) ተሻሚዎች ቦታ ይዘዋል፤ የUSGው ሹመት ለመጀመሪያ ጊዜና ከመጋቢት 2013 ጀምሮ ቢሆንም!

በአጭር አነጋገር፡ በሰላም አስከባሪነት መስተፍ ማለት ለአንድ ድህ ሃገር የዓለም አቀፉን ሥርዓት በሚያስተዳድሩት ሃገሮች ዘንድ ተቀባይነትና ድጋፍ ያስገኛል።

እስከ ጥቅምት 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ለተ.መ.ድ 7,827 ስታበረክት፡ ከነዚህም መካከል ወታደራዊ 100 ኤክስፐርቶች፣ 7,694 ፡ሠራዊት 33 ፖሊሶች ማበርከቷን የድርጅቱ ሪፖርት ያመለክታል። ቀሪው ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሃይል ሶማሊያ ውስጥ ነው።

እንደነሕንድ ዐይነት ሃገሮች ለገንዘቡ ሲሉ ላለመሰለፋቸው ብዙ ማስረጃዎች አሉ። አንደኛ ሕንድ የወደፊት ዕቅድ ስላላት – ታዳጊ ኅይል – ትኩረቷ የፖለቲካ ጥቅም ላይ ነው። ሁለተኛ ድርድጅቱ ከተመደበለትና በዓመት ለሰላም ማስከበር ከሚያስፈልገው ስምንት ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ሃገሮች መዋጮአቸውን በጊዜ ስለማይከፍሉ፡ ድርጅቱ ሠራዊት ላበረከቱ ሃገሮች ወቅታዊ ክፍያ ለማድረግ ይቸገራል። ለምሳሌ በዚህ ዓመት እስክ ጥቅምት ድረስ ሕንድ ያልተከፈላት ድርሻዊ $110 ሚልዮን መድረሱ ይነገራል።

ለማንኛውም፡ አንድ ሃገር ሠራዊቱ በተ.መ.ድ ስም እንዲዘምት ሲደረግ ቀደምት የሚጠብቅበት ተግባሮች የሚከተሉት ናቸው፦

    (ሀ) ወታደሮቹ የሚሠሩ፡ ከተበላሹም የሚጠገኑ መሣሪያዎች ይዘው እንዲደርሱ፡
    (ለ)የተበላሹም መሳሪያዎች ካሉ በአሰቸካይ በብሔራዊ ወጭ እንዲጠገኑ
    (ሐ)ለተላኩት ወታደሮች፡ መሣሪያዎችና ሌሎች መገልገያዎች ተገቢው መረጃ ለተ.መ.ድ. በወቅቱ መቅረብ።

ድርጅቱ መሣሪያዎች በግጭት ቢወድሙ የሚተካበት ሁኔታ አለ። የሠራዊቱ ይዞታም ካሉበት አካባቢ አንጻር ጥቅማቸውና ሌሎች ክፍያዎች በውቅቱ ውሳኔ እንዲያገኙ ይረዳል።

ቀደም ሲል በቴሌቪዥን ቀርበው የነበሩት የጦር መኮንን ካመለከቱት ነገሮች መካከል፡ የሠራዊትቱ አባላት በደንብ ይጠቀማሉ ነበር ያሉት። ታዲይ ሂይጆቹን የሚመለምሉት የሕወሃት የመከላከያ ባለሥልጣኖት የራሳቸው የሆን ‘ግብር’ የሚያስከፍሉበት ሥርዓት ይኖራቸው ይሆን?
 

%d bloggers like this: