ሐውዜን: የሕወሃቶች ሽፍጥና የድብብቆሽ ጨዋታ

4 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ምንም ዐይነት ነገር ቢሆን፡ የስብሃት ነጋ፡ የሥዩም መስፍን፡ የአባይ ፀሐዬና የበረከት ስምዖን ወዘተ እጅና አንደበት የነካው ነገር ተአማኒነቱ እስክዚህም ነው። አሁን ደግሞ በ40ኛው የሕወሃት በዓል አከባበር ዝግጅት ወቅት: ስብሃት ነጋ የ1987ቱን የሐውዜንን ጭፍጨፋ ሕወሃት ቀደም ሲል በደርግ ላይ የነበረውን ስሞታ በመተው፡ እሥራኤል ላይ አላክዋል። ይህ ሁሉ ዳር ዳር በትግራይ ሕዝብ ላይ ሕወሃት ከፈጸመው ጭፍፍጨፋ ራሱን ነጻ ለማድረግ የሚካሄድ ሸብ ርብ ነው!


 

ስኔ 19 ቀን 2014፣ አብርሃ ደስታ የሐውዜንን ጭፍጨፋ አስመልክቶ፡ የሐውዜን ጭፍጨፋ የሕወሃት ድራማ ስለመሆኑ እንደሚከተለው አስፍሮ ነበር።

“የሰኔ 15 ሰማዕታት ዶክሜንትሪ ፊልም
========================
(የቀድሞ የህወሓት ታጋይ የምስክርነት ቃል: Mahder Jeganu)

  በህይወቴ እንደ ህወሓት አይነት የተዋጣለት ድራማ መስራት የሚችል አርቲስት ወይም ክለብ አላየሁም። ምናልባት በአለማችን ብዙ ድራማዎች ተሰርቷል። በህወሓት የተደረገው ድራማ ግን ከአለማችን ዳይሬክተሮች አቅም በላይ ከቢቢሲ፣ ሲኤን ኤን፣ አልጀዚራና ሌሎች ታዋቂ የሰበር ዜና ካሜራዎች ውጭ እስከ ዛሬ በሪከርድ ሰባሪነቱን ዓለም ያላወቀዉ ድራማ በሰኔ 15/ 1980 ዓ/ም በሐውዜን ተደረገ።

  ነገሩ እንዲህ ነው:

  በወቅቱ በህወሓት ሰራዊት ግርግር የተፈጠረበት ግዜ ነበር። የግርግሩ መንስኤ እኛ ተዋግተን ትግራይን ነፃ በማውጣት ትግሉ እዚህ አድርሰነዋል። ስለዚህ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ሌሎች ድርጅቶች እየታገሉ ከዳር ያድርሱት የሚል ጥያቄ ከማንሳት ባሻገር ከ30,000 በላይ ተጋይ ከነትጥቁ ወደ ቤተሰቡን የተመለሰበት ነበር። ታጋዩ ጥያቄውን ዝም ብሎ ከመሬት ያነሳው አልነበረም። ምክንያቱ ህወሓት ገና ሲመሰረት ዋና አጨቃጫቂና ከኢህአፓና ኢድዩ ጋር የማይስማማባቸው ዋና ነጥብ አንዱ ነፃ ሀገረ ትግራይ መመስረት የሚል ዓላማ ነበር። ቢሆንም ኋላ ላይ ወደ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ቢቀየርም በ1980 ዓ/ም ግን ታጋዩ ይህንን ሁኔታ በተግባር በማሳየት እኛ እዚህ ድረስ መጥተናል ከዚህ በኋላ የኢህዴንና ሌሎች ድርጅቶች ትግሉ ይቀጥሉ የሚል ከፍተኛ ጫና በህወሓት አመራሮች ተፈጠረ። በዚህ ሁኔታ የረጅም ህልማቸው እዚ ተጠልፎ የሚቀር የመሰላቸው የያኔው መሪዎች ይዛሬ ሙትና አዛውንት የድርጅቱ መሪዎች አንድ መላ ዘየዱ። ይህ ጦር በግምገማና በቅጣት መመለስ አይችልም በማለት በአለማችን ድንቅ የሆነ ድራማ መስራት ጀመሩ። በወቅቱ አንድ ሰርጎ ገብ በውቅሮ አድርጎ ወደ መቐለ በማለፍ ደርግ ወደ ነበረበት ቦታ በመሄድ መረጃ ያቀብላል። መረጃውም የህወሓት ሰራዊት በሓውዜን ከተማ እየተንቀሳቀሰ ነው። በተጨማሪም ሰኔ 15/ 1980 ዓ/ም ጦሩ ትልቅ ስብሰባ በከተማዋ ያደርጋል የሚል ነበር።

  ደርግም የመረጃውን ተክክለኛነት ለማረጋገጥ በተለያዩ መንገዶች የደህንነት ሰራተኞች ወደ ከተማዋና አከባቢዋ እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል። ይሄኔ የደርግ መንቀሳቀስ የሚያውቁት እነዛ የድራማው ጠንሳሾች በበኩላቸው ለመረጃው ማሳመኛ ይሆን ዘንድ ሁለት የህወሓት ተዋጋ ሃይሎች በከተማዋ ዙርያ እንዲታዩ ከማድረግም ባሻገር ወደ ከተማዋ በርከት ያሉ ተጋዮች እንዲገቡ ያደርጋሉ። የሚገርመውን ይህ ሁሉ ሲሆን ታጋዩ የሚያውቀው ነገር የለም። ምክንያቱም በወቅቱ አንድ መሪ ወደዚ ሂድ ሲልህ ትሄዳለህ ጥያቄ ማቅረብ አልነበረም። የሆነ ሁኖ የደርግ ደህንነቶች መረጃውን አስተማማኝ መሆኑን ከበቂ በላይ ማስረጃ አግኝተው ለገሰ አስፋው እጅ አስረከቡ። አይደርስ የለም ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ የተወሰኑ ከቢቢሲ፣ ከአልጀዚራ፣ ከሲኤን ኤን የበለጡ የካሜራ ተዋንያን በሱዳን ስልጠና ወስደው ጨለማን ተገን በማድረግ ሓውዜን ደረሱ። በከተማዋ መውጫ በር አከባቢዎች የተለያዩ ጉድ ጓዶች ለሊት ለሊት መቆፈር ያዙ።

  ቀኑ ደረሰ ሰኔ 15/ 1980 ዓ/ም። እነዛን የካሜራ ተዋንያን ከሱዳን ተልከው የመጡትን ዘመናዊ ካሜራዎችን በመያዝ በተቆፈረው ጉድጋድ በመግባት ገና ከጥዋቱ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። ረፈድ ሲል የከተማው ነዋሪና ከተለያዩ አጎራባች ወረዳዎች የመጡት ገበያተኞች ከተማዋን ማጥለቅለቅ ጀመሩ። ሓውዜን የተደገሰላትን የጥፋት ፊልም ከደርግና ከነዚህ የድራማው ጠንሳሽ ሙትና አዛውንት ሌላ የሚያውቅ አልነበረም። በወቅቱ ከሽማግሌ እስከ ህፃናት፣ ነፍሰ ጡሮች፣ ወጣቶች እንዲሁም የተለያዩ የቤት እንስሳትን ጭምር ከተማዋን ሞልተው አጥለቀለቁዋት። ፀሃይዋን የድራማውን ይዞታ ለመናገር ሙቀትዋን ጨምራ ብትለቅም ማንም አላስተውላትም።
  ስዓቱ ደረሰ የደርግ ጀቶች በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተመላለሱ ከተማዋን በቁምቡላዎች ማረስ ጀመሩ። ህዝቡ ከከተማ ለመውጣት ሩጫዉን ሲጀምር በርከት ያሉ ሄሊኮፕቶሮች ዙርያውን ከበው በመትረየስ ህዝቡን ማጨድ ያዙ። ከዛማ ምኑ ይቀራል የሰውና የእንስሳ ደም በአንድ ላይ ጎረፈ። የሰው ስጋና የእንስሳ ሰጋ ተደባለቀ። በተወሰኑ ስዓታት ውስጥ 2500 በላይ ንፁሃን ዜጎች ለህልፈት ተዳረጉ። እጁና እግሩን ይተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ ብዙ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን በከተማዋ ዙርያ የነበሩ የካሜራ ተዋንያን ያ ሲደረግ የነበረው ድራማ በሚገባ ቀርፀውታል።

  አብርሃ ደስታ (ፌስ ቡክፎቶ)

  አብርሃ ደስታ (ፌስ ቡክፎቶ)

  ይህንን ፅሁፍ ማመን ያቃታችሁ ካላችሁ ቅዳሜ ወይም እሁድ ማታ በቴሌቪዥን ኢትዮጵያ የትግርኛ ቋንቋ የሰኔ 15 የሰማእታት በዓል ለማክበር ፊልሙን ሊያቀርቡት ስለምችሉ ተመልከቱት። እንደዚያ ያለ ላይቭ /በቀጥታ/ የተቀረፀ ፊልም በአለም አልታየም። ዛሬ ድረስ አልጀዚራና ቢቢሲ እንዲሁም ሲኤን ኤን ሳይቀር አንድ ድርጊት ካለፈ በኋላ ወይም ሁኔታው ከርቀት ተደብቀው ጭስ ሲወጣ ወይም እሳት ሲያያዝ ብቻ ቀርፀው ያሳያሉ። የሓውዜን ግን ሰዉ እየሮጠ ብቻ ሳይሆን ሚጎች ሲደበድቡና ቤቶችን ሲያጋዩ፣ ሄሌኮፕተሮች ህዝቡን ሲያጭዱ፣ ትኩስ ደም ሲፈስ ቤቶች ሲቃጠሉ፣ የተቆረጠ እጁን ይዞ በእሳት መካከል ሆኖ የሚያለቅስ ህዝብ ሲንቱን ንበል ዘግናኝ የሆነ ድራማ ተሰርቷል። ብቻ ፊልሙን ለማያት ያብቃችሁ።

  በወቅቱ ፊልሙን ተቀርፆ የተወሰነውን ብቻ ተቆርጦ ለነዛን የዜና አውታሮች በመሰጠቱ አለም ሁላ ጉድ አለ። በፊልሙን ብዙ ገቢ ተገኘበት። ስለ ሓውዜን ድብደባ የህወሓት ካድሬዎች የውሸት መግለጫ ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ህዝቡንና ወደ አገሩ የተመለሰውን ታጋይ በመሄድ ትግሉን እንዲቀጥሉበት ቅስቀሳ ማድረግ ጀመሩ። ድራማው የሰሩት ደራሲያን በሚገባ ተሳካላቸውና አብዛኛው ታጋይ ከነትጥቁ ተመለሰ። ብዙ አዲስ መልምልም ወደ ማሰልጠኛ ጎረፈ። ዛሬ ድረስ የህወሓት ካድሬዎች የተሞሉትን የማውራት ሂደት እየ ቀጠሉበት ይገኛሉ። ምናልባት ዛሬ በዘመናዊ መልኩ ሲቪል ሰርቪስ ብለው ስሙንና መልኩን ሊቀይሩት ቢሞክሩ ቅሉ ግን ካድሬ ካድሬ ነው።

  በጣም የሚገርመው ነገር ህወሓት የውሸት ዶክሜንትሪ ድራማ መስራት የጀመረች እዚህ ቦታ ብቻ አልነበረም። በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ድራማዎች ተሰርቷል። እስቲ ስለ አንድ ሴት ታጋይ ታሪክ ልጨምራችሁ!

  ወላጆችዋ ያወጡላት ስም ካሕሳ ተስፋይ ነበር። በ1968 ዓ/ም የ18 ዓመት ልጅ ሆና ወደ ትግሉ ስተቀላቀል ከእርስዋ በፊት በ60ዎች የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴን ያደርጉት በነበረው ትግል የተሰዋች የማርታን ስም ለዚች አዲስና የመጀመሪያዋ የህወሓት ሴት ታጋይ የትግል ስም ሆኖ ይሰጣታል። ማርታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰጣትን ስልጠና ጨረሳ ወደ ህወሓት ጦር ተቀላቀለች። እንግዲህ የዚች ታጋይ ታሪክ በድራማ መልክ መሰራት የተጀመረው ህወሓት ገና 3 ዓመት ስታስቆጥር ነበር። በወቅቱ በማርታ ስም የተደረሰውን ድራማ እራስዋን ማርታ አታውቀውም ነበር። ምክንያቱም ድራማው ለታጋዮች ሳይሆን ለህዝቡ ይፈ ተደርጎ ብዙ ወጣት ወደ ትግሉ እንዲጎርፍ አድርጓል። ብዙ ሽማሌዎች ሚሊሻና፣ ሽግ ወየንቲ እንዲሆኑ ምክንያት የሆናቸው የማርታን ድራማ ነበር። ብዙ የትግራይ ተወላጆች ከውጭ አገር ሳይቀር ወርቅና ገንዘብ ለህወሓት እንዲሰጡ ያደረጋቸው ይህ በማርታ ስም የተነገደበት ድራማ ነበር።

  ነገሩ እንዲህ ነው

  “ህወሓት ደደቢት ከገባች በኋላ ደርግ እነዚህ ሳይበዙ በፍጥነት እናጥፋቸው ብሎ ብዙ ጦር አስከትሎ በሁሉም የትግራይ ገጠሮች የህወሓት ታጋዮች ማሳደደ ያዘ። በዚህ ወቅት የህወሓት ተጋዮች በአንድ ቦታ ከደርግ ጋር በቅርብ ርቀት ተከበው መሽገዋል። ታጋዮቹን የያዙት መሳሪያ ትንሽና ዘመናዊ አልነበረም። በተጨማሪም የነበራቸው የሰው ሃይል በጣት የሚቆጠር ነበር። ስለዚህ አጠገባቸው ካለው የደርግ ሰራዊት ለመዋጋት ያላቸውን አማራጭ ድምፃቸውን ሳይሳሙ ጨለማውን ተጠቅመው በመጠጋት የማተራማስ ውግያ ከፍቶ በመምሸሽ የደርግ ጦር እርሰ በእርሱ እንዲዋጋ ማድረግ ነበር። ይህንን ስልት ለመተግበር እየተንፋቆቁ ወደ ጠላት ምሽግ ሲጠጉ ያልታሰበ አንድ አደጋ ያጋጥማቸዋል። በገቡበት ምሽግ ውስጥ አንድ ትልቕ ኣዞ እየተሳበ እነሱ ጋር ይደርሳል። በዚህ ግዜ በጥይት ተኩሰው እንዳይ ገድሉት ድምፅ ከተሰማ ደርግ ሊውጣቸው ሆነ። ሁሉም በጭንቅ ተውጠው እያለ በወቅቱ ብቸኛዋ ሴት ታጋይ ነበረች ማርታ ትጥቅዋን ፈትታ እኔን በልቶ ይሄዳል እናንተ በእኔ መስዋት አላማችን ማሳካት ትችላላችሁ ብላ ወደ ኣዞው ተጠጋች። አዘውም አፉን ከፍቶ ተንደርድሮ በመምጣት ማርታን ሙሉ ለሙሉ ከዋጠ ቡኋላ ትቶዋቸው ይሄዳል። ታጋዮቹም ያቀዱትን የማተራመስ ውግያ በማድረግ ደርግን እርሰ በእርሱ እንዲተላለቅ ከማድረግ ባሻገር ብዙ መሳሪያ መሰብሰብ ችለዋል።” ይላል ይፈጠራ ታሪኩ በጣም በጣም የሚያሳዝነው ይህ ታሪክ ፈጠራ መሆኑን ያልነቁበት ብዙ ሰዎች ዛሬ ድረስ አሉ።

  በቅርቡ በወልቃይት የግንቦት 20 በዓል አከባበር አስመልክቶ በቀረበው ዶክሜንቴርፊ ፊልም ኣንድ እናት ቃለመጣየቅ በሚደረጉበት ወቅት እንደዚህ አሉ “ወልቃይት እንደነ ማርታ ያሉ በአዞ የተበሉበት ቦታ ነው። ስለዚህ ለተቃዋሚዎች ቦታ አንሰጥም ህወሓት ብቻ ነው የምንቀበለው ሲሉ ተመልኪቸ አዘንኩላቸው። በብዙ ቦታዎች እስከ ዛሬ ድረስ ማርታ በአዞ እንደተበላች አምነው የተቀበሉ ታጋዮችና አባላት ብዙ ናቸው። በጣም በጣም ያሳዘነኝ ከአዲሱ ትውልድ የተመለመሉ የህወሓት አባላት ሳይቀሩ እንደነ ማርታ በአዞ የተበሉበት ድርጅትን የመጠበቅ አደራ አለብን ብለው በስብሰባ ሲናገሩ ስሰማ በጣም ያሳዝኑኛል።

  ድራማው ውሸት ነው። ማርታ 1968 ዓ/ም ወደ ትግል የተቀላቀለች ታጋይ ከመሆንዋ ባሻገር ድርጅቱን ለ4 ዓመታት አገልግላለች። ህወሓት በጦር ብዛት ደና በሚባል ደረጃ በደረሰበት ወቅት በታሕሳስ 1972 ዓ/ም ሽሬላ በሚባለው ቦታ ከኢህአፓ ጋር እየተዋጋችና እያዋጋች በጥይት ተመታ የተሰዋች ታጋይ ነች።

  በተጨማሪም ተስፋይ ሽላ የሚባል ታጋይ በዚህ ውግያ አብሮዋት ተሰውቷል። በኢህአፖ በኩልም እነ ጋይም የሚባል ፖሊት ቤሮ ሃላፊ የመሰሉ የተማረኩበት ግዜ ነበር። በወቅቱ በውግያው የሓይል መሪዋና ስትመታ አብረዋት የነበረውና የኑዛዜ ቃልዋን የተቀበለው ታጋይ ስሙን ልተዎውና ዛሬ በመቐለ ከተማ የመንግስት ስራ እየሰራ ይገኛል።

  ብዙ ነገሮች ማንሳት እንችላለን ከበርሃ ጀምሮ እስከ የእነ ሓየሎም፣ እያሱ ግድያ ብዙ ድራማዎች የተሰሩበት ታሪክ ማይት በቂ ማስረጃ ነው።
  ሰኔ 15 የሐውዜኑን ድብደባ ከተሰውት ታጋዮች ጋር ተደምሮ የሰማእታት ቀን ተብሎ ተስይሞ ይከበራል። ታጋዮቹ በ ሰኔ 15 አልተሰዉም ግን ለምን ከሐውዜን ጋር ተደመሩ? ለምን የካቲት 11 ወይም መጋቢት 8 ወይም ደግሞ ግንቦት 20 አልተደረገም? መልስ አልፈልግም ብዙ ድራማዎች ማየት ስለቻልኩ ከበቂም በላይ ሴራዎችን አውቃቸዋለሁ።

  ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በቴሌቪዥን እያደነቆሩ የሚገኙት የተለያዩ ከእውነት ጋር የተቀላቀሉ ድራማዎች/ዶክሜንተሪ/ፊልሞች ህወሓት ከጫካ ጀምሮ ባካበተው ልምድ መሰረት የሚተገበሩ ናቸው። ህወሓት 39 ዓመት ሙሉ የውሽት ድራማዎችን በመስራትና ፕሮፖጋንዳ በመንፋት ስልት በጅኔስ ኦፍ ወርልድ መመዝገብ አለበት። ምክንያቱም ይህም የዓለማችን ቁጥር አንድ ሪከርድ ነው።”

 

============================
ባለፈው ግንቦት ወር አብርሃ ደስታ ስለ ሃውዜን አንስቶ፡ በፊስ ቡኩ ላይ መሬት መዝረፍና የሕዝብን ሃብት መንጠቅ ገና ከንጋቱ የተለማመደበት ተግባር መሆኑን በሐውዜን መለስና ሚስቱ የፈጸመውን የሥላጣን ብልግና አስመልክቶ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር። መሬቱ ከሕዝቡ ተነጥቆ ለአዜብ መስፍን፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐየና አንድ ፈረንጂ ባለሃብት መሰጠቱንና ስማቸው የተጠቀስው ዘራፊዎች እንግዳ ማስተናገጃ ለንግድ ማሠራታቸውን አብርሃ ደስታ ዘግቧል።

Gheralta Lodge Hawzein (Tigray Region) Credit: Travelpod.com)

  አዜብ መስፍንን በሐውዜን!

  በሐውዜን ነው። ከመጋብ ወደ ድጉም በሚወስደው መንገድ ለም መሬት አለ። እዛ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሃብታሞች ነበሩ። ምክንያቱም መሬቱ ጥሩ ነው።

  አርሶአደሮቹ ራሳቸው መመገብ ይችላሉ። በህወሓት ዘመን ራሱ የሚችል አርሶአደር የመንግስት ጠላት ነው። ምክንያቱም ራሱ ከቻለ በመንግስት ጥገኛ አይሆንም። ጥገኛ ካልሆነ ካድሬዎች ያዘዙትን ላይሰራ ይችላል። እናም በዛው ለም መሬት የሚኖሩ አርሶአደሮች የካድሬዎች ትእዛዝ አያከብሩም። የመንግስት እርዳታም አይፈልጉም። እናም ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ ተደረገ። 30 አባወራዎች ከቀያቸው ተነቀሉ። ያ ለም መሬት ለማን ተሰጠ? ለአዜብ መስፍን፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐየና አንድ ፈረንጂ ባለሃብት። አራቱ ሰዎች 30 አርሶአደሮችን ነቅለው ጥለው መዝናኛ (Lodge) ሰርተውበታል። አርሶአደሮቹ ግን መሄጃ እንኳን የላቸው። መሬት የመንግስት ነው። እነ አዜብ መስፍን ደግሞ መንግስት ናቸው ተባሉ። እናቶች ያለቅሳሉ። እነሱ ደግሞ የመዝናኛ ቢዝነስ ይከፍታሉ። ከዛ ኢንቨስትመንት ይባላል።

  ወደ ሐውዜን ስትሄዱ አይታችሁ አረጋግጡ። Lodgeን ጎብኙት።

  It is so!!!”

 

==========================

  አሳዛኝ ዜና!

  የሐውዜን ህዝብ እንደገና በህወሓት እየተጨፈጨፈ ነው። “ዓረና ነህ፤ ስምህ በዓረና መዝገብ ተገኝቷል” እያሉ ሰለማዊ ሰዎችን እያስፈራሩ ለህወሓት ይቅርታ ጠይቆ እንዲመለስ እያስጠነቀቁ ካልተሳካ ደግሞ በዱላ እየደበደቡ፣ በድንጋይ እየወገሩ፣ ጥያቄ ለሚያነሳ ሰው በፖሊስ እያሳሰሩ፣ ቤቱ እየፈተሹ ይገኛሉ። አንዳንድ በሐውዜን የሚገኙ ሙሁራን “ዳግማይ ጭፍጨፋ” ብለውታል። ዓረና ይህን ተግባር ይቃወማል።

  የዓረና አባላት ያልሆኑ ሰዎች ስማቹ ተገኝቷል እየተባሉ የሚሰቃዩበት፣ ስም ዝርዝር ያልላከ ዓረና ስሙ የሚጠፋበት ስርዓት ተፈጥሯል። ደግሞ ዓረና ህጋዊ ፓርቲ አይደለም እንዴ? ሰው ዓረና የመሆን መብት የለውም እንዴ? የሐውዜን ህዝብ የዓረና አባልና ደጋፊ የመሆን መብት የለውም? የዓረና አባል ተብሎ እንዴት ይንገላታል? እንዴት ይታሰራል? የዓረና አባል መሆን ወንጀል መስራት ነውንዴ? ዓረና’ኮ ህጋዊ ፓርቲ ነው።

  የህወሓት ስጋት ምን ያህል እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። የሐውዜን ህዝብ ግን ዳግም እየተጨፈጨፈ ነው። ለህዝብ ካልቆምን ለማን ልንቆም ነው። ወይስ የሐውዜን ህዝብ ሊጨርሱት ፈልገዋል?! እንደ የሰኔው 15, 1980 ዓም ሙከራ!?

  ህወሓት ግን ሰፈሩ የበላሹሎ!

  It is so!!!”

 

============================

  ህወሓት ህዝብን እያጭበረበረ ነው!

  የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል (የምስራቃዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ) የሆነው አቶ ማሞ ገብረእግዚአብሄር “የዓረና አባላት ናችሁ” እያለ የሐውዜንን ህዝብ እየተሳደበ፣ እየገረፈ፣ እያሳሰረ ይገኛል። ሊያጠቁት የፈለጉትን ሰው እየመረጡ በጥርጣሬ “የዓረና አባል ነህ። የዓረና ፓርቲ ማህተምና የሊቀመንበሩ ፊርማ ያለበት የአባላት ስም ዝርዝር ተልኮልናል” እያሉ ህዝብ ለሦስት ቀናት ያህል አስረው አዋርደዋል፣ ገርፈዋል። ዛሬ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከ500 በላይ የሐውዜን ኗሪ የጥቃቱ ዒላማ ሆኗል። በከተማዋ ብቻ 62 ሰዎች ሰለባ ሆኗል።

  አሁን የሐውዜን ኗሪዎች ህዝብን በማጭበርበር ያጃጃለ የምሥራቃዊ ዞን አስተዳዳሪን ለመክሰስ ተዘጋጅቷል። ዓረናም ስም በማጥፋት ወንጀል ህወሓትን ይከሳል። ዓረና የአባላቱ ስም ዝርዝር ሳይልክ በሐውዜን ህዝብ እንዲጠላ ለማድረግ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ስም በማጥፋት ወንጀል የሚከሰሱ የህወሓት ባለስልጣናት ለይቷል።

  ለጥንቃቄ ያህል፡ ዓረና እንኳን የዓረና አባል ያልሆነ ሰው ስም ጠቅሶ ሊልክ የዓረና አባላት ስም ዝርዝርም ቢሆን አንድ ላይ አይፃፍም፤ ማህተም አይደረግበትም። ሰው ራሱ ካልተመዘገበ በቀር አባል ነው ተብሎ ስሙ አይፃፍም። ስለዚህ “ዓረና ናችሁ” የሚል የህወሓቶች የማደናገርያ ቋንቋ ነው። እንዳትሸወዱ። የዓረና አባላት የሆናችሁም ስም ዝርዝራቹ ህወሓት አያገኘውም።

  ህወሓት ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ህዝብን ለማሸብርና በህወሓት ዉስጥ ያሉ ሰዎችን ለመለየት የታለመ መሆኑ እንገልፃለን። ህወሓት ለመሰሪ ተግባሩ ህዝብ ይፋረድዋል። ህዝብን በማስፈራራት ትግሉ አይደናቀፍም። የሐውዜን ህዝብ ከምን ግዜም በላይ ዓረናን የሚደግፍበት አጋጣሚ ተፈጥሯል። ህወሓት ራሱ እያጋለጠ ይገኛል።

  ህዝብን በማገልገል እንጂ ህዝብን በማጃጃል ሀገር አይመራም።
  It is so!!!”

 

%d bloggers like this: