አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከስድስት ወራት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጆቻቸውን ጨምሮ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስልክ ተነጋገሩ: ሕወሃት ያቺን የሰንዓ አፈና ወንጀል ቀን ሳይረግም ይቀራል?

19 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም (ኢሳት ዜና): የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት ወይዘሮ የምስራች ዛሬ ለኢሳት ሲናገሩ፤ ካልታወቀ እስር ቤት ሆነው ልጆቻቸውንና የቤተሰቡን አባላት ድንገት ሲያናግሩ ደንግጠው እንደነበር በመጥቀስ፤ ድንገት የተደወለውን ስልክ ሲያነሱ ባለቤታቸውን በድምጻቸው ወዲያው እንደለዩዋቸው ግልጸዋል።

ሰላምታ ከተለዋወጡ በሁዋላ ጤንነታቸውን በተመለከተ እንደተጠያየቁና አቶ አንዳርጋቸው በደህና ጤንነት ላይ መሆናቸውን እንደገለጹላቸውም ወዘይሮ የምስራች ተናግረዋል።

“ድምጹን ሥንሰማው ደስታም፣ድንጋጤም የተቀላቀለበት፤ እንዲሁም ምንም ልናደርግለት ባለመቻላችን ቁጭት፣ ንዴት እና አቅም የመጣት ስሜት ተሰማን” ሲሉም ወይሮ የምስራች በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል።

በሚቀጥለው ወር የእንግሊዝ የፓርላማ አባላትና የጠበቆች ማህበር ተወካዮች አቶ አንዳርጋቸውን ለማዬትና ለማስፈታት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያቀኑ ሐሙስ እለት “ኢንዲፐንደንት” አስነብቧል።

አቶ አንዳርጋቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መነጋገራቸውን ተከትሎ የምክር ቤት አባላትና የጠበቆች ማህበር ተወካይ ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ተስፋ እንዳሳደረባቸውም ወይዘሮ የምስራች ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው ከስድስት ወራት በሁዋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ መነጋገራቸውን የሰሙ በርካታ ኢትዮጵያውን ወደ ኢሳት ስልክ በመደወል ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ “ክስተቱ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያበረታታን ነው”ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
 

ተዛማጅ ጽሁፎች፡

    Collected works of TPLF security on Andargachew Tsige: No tortures; how nice to be in Ethiopian prisons

    Ethiopia finally admits abducting Andargachew Tsige from Sanaa Airport!

    Open Letter to Rt. Hon. William Hague, UK’s Foreign Secretary

%d bloggers like this: