‘ቀን የሰጠው ቅል…’፡ ሕወሃት በ40ኛ ዓመቱ በሕዝብ ላይ ወንጀለኛነቱንና ጸረ-ኢትዮጵያዊነቱን ሸፍኖ ስለፖለቲካ ብስለቱ፣ አመራር ብቃቱና ዲሞክራሲያዊነቱ ሲደሰኩር

14 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ከዚህ በታች ባለው የመጀመሪያው ቪዲዮ ውስጥ፡ መለስን የተኩት የሕወሃት ርዕሳነ ጠቢብ እንዲህ ይላሉ ስላለፉት መንግሥታት ስያወሱ፦

  “ሃሣብ ማቅረብ፡ ጥያቄ ማቅረብ፡ ልዩነት ማራመድ፡ መደራጀት፡ ሠልፍና ስብሰባ፡ ነፃ ፕሬ፡ ነፃ ፓርቲ ምናምን የሚባል ነገር ሃሣብም የለም። ሥልጣን የያዙት ንጉሣውያን ቤተሰብ የእግዚአብሔር ሹመኞች ናቸው፤ ሥዩመ እግዚአብሔር ነው ንጉሥ፤ ስለዚህ ንጉሥ አይከሰስም፡ አይወቀስም የሚል ሕገ መንግሥት ላይ ሳይቀር የተጻፈበት ሥርዓት ነው የነበረው።

  “…ይኽ ለብዙ ተማሪዎች መታሠር፡ ትምህርት መቋረጥ፡ መባረር ስደት መሄድ ምክንያት ሆኖአል – መገደል ጭምር!”

 


 

አባይ ፀሐዬ በመቀጠልም፡

“ሕወሃት በሂደት እየተማረ፡ ራሱን እያስተካከለ፡ ራሱን ሂስ እያደረገ፡ ያዛባው ነገር፡ ያልተረዳው ነገር፡ ያበላሸው ነገር እያስተካከለ፡ 1977 ዓ.ም ክረምት ያደረገው ጉባኤ የአሥር ዓመት ግምገማ የሚባለው አንድ ጠንካራ ጎን የለም ጽሁፍ ላይ። ድክመት ብቻ ነው።…ጠራርገን እናራግፍ ድክመቶቻችንን!”‘That is the tradition of TPLF!”

“…ሕወሃት የህዳሴያችን፡ የጽናታችን መሠረት ነው የካቲት ሲባል፡…ያኔ በግርድፉ ተቀይሶ ስለነበረ ነው።…
 

ደመቀ መኮንን

ይህንን ቪዲዮ ልብ ብሎ ለተመለከተው ሰው፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ውስጥ ሕወሃት እንዳስቀመጠው ግለሰብ ከዚህ በታች በሚታየው ቪዲዮ በሃገርና ሕዝብ ክህደት ሰለወንጀለኛው ሕወሃት ታላቅነት እንደሚናገረው ሁሉ፡ ደመቀ መኮንንም ሕወሃት ከፍተኛ መሥዋዕትነት ስለመክፈሉ መረጃ ለመስጠት ያላንኳኩት የምድርና የሰማይ በር የለም! በዚሁ ቪዲዮ፡ ደመቀ መኮንን ሰለሕወሃት ታላቅነትና ለዚህ ድል የተደረስው፡ ሕወሃት ጥልቅ የሆኑ እሴቶችን በመላበሱ መድረኩ የጠየቀውን መሥዋዕትነት በመክፈልሉ ነው እዚህ ለመድረስ የቻለው ብለዋል።
 

አባይ ፀሃይም ተቀብለው፡

“…አሁን ሕወሃት እንደኢሓፓ ቢንኮታኮት ኖሮ፡ ኢህዴን የት ይገባል?ሕወሃትም የለ። እሱም ተሸንፎ ይበተን ነበር። የኢትዮጵያ አብዮት ተሸንፎ ኢሕአዴግ አይመሠረት፡ የአሁኒቷ ደሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አትመሠረት፡ ይኽ ሁሉ ልማት አይጀመር…ምናልባትም ይመጣ ከሆነ ከአሥርታት በኋላ ነበር…
 

ደብረጽዮን ገብረመስቀል፡

“እኛ የምንመኘው፡ የሁሉም ብሔሮች፡ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት ያረጋገጠ አንድነት ነው። ይህን አዲስ ኢትዮጵያ ማየት ነው የምንፈልገው ባሉ ግለስቦች ነው ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው። ይሄው ውጤት አፍርቶ ይኸው የኢትዮጵያ ብሔር፡ ብሔረስቦችና ሕዝቦች የሚከባበሩበት፡ አንድነታቸውን አጠናክረው ሃገራቸውን የሚገነቡበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብቻ ሳይሆን፡ ሁሉም ብሔር፡ ብሔረስብ የሚመክርበት፡ የሚወስንበት አዲስና ልዩ ምዕራፍ በታሪካችን ተመዝግቧል!”
 

ማጠቃለያ

ያለፉትን መንግሥታት በጨቋኝነት የሚዘለዝሏቸው የሕወሃት ሰዎች፡ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊትና ሕዝቧም እኩልነት የተላበሰና የነጻትን ሙቈት የሚጎነጭ ሃገር አድርገናታል ብለው ከልባቸው ያምናሉ ብለን ለአፍታ እንኳ አንገምትም! እንዴት ሊጠፋቸው ይችላል፡ በእነርሱ አገዛዝ፡ ኢትዮጵያ፤

  * የዜጎቿ እሥር ቤት መሆኗ

  * ከሕወሃት የተለይ ሃሣብ አስተናግደዋል በማለት የተገደሉት፡ በብዙ አሥርታት ሺህ የሚቆጠሩ የታሠሩና የተሰደዱ ተማሪዎችና ጋዜጠኞች፡ ገበሬዎች፡ ሠራተኞች፤

  * በነጻነት የመደራጀት ጥያቄ በማንገባቸው፡ ሰላማዊ ሠልፍ በማድረጋቸውና ሲያደርጉ ባለፉት 23 ዓመታት በየአደባባዩ፡ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የተደበደቡት ሰዎች፣ በማህጸኖቻቸው የያዙትን ፍሬዎች በሕወሃት ኮማንዶዎች ድበድባ እንድፍረሱ የተደረጉት፤

  * በአዲስ አበባና የክፍለ ሃገሩ መሬቶቻቸው፡ ንብረቶቻቸውና ቤቶቻችው እየተዘረፉባቸው፡ ለነባር የሕወሃት አባላት፡ ትግራዊ የጦር መኮንኖችና ተተኪ የሕወሃት አባላት (ከውጭ ጭምር) ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ንብረት እንዲያፈሩ በማድረግ፡ የትግራይ ብሔረስብን የፖለቲካ በላይነት ለማበራከትና ማጥናከር በትጥቅ ጭምር የሚደረጉት ጥረቶች፤

  * እስከዛሬ በአዲስ አበባ፡ ኦሮሚያ፡ አማራ፡ ጋምቤላ፡ ቤንሻንጉል፡ ደቡብና ምሥራቅ ኢትዮጵያ ሕወሃት መሬት ለመዝረፍ ሲል የፈጸማቸውን ወረራዎች፡ የራሱን ወገር ሠፈራዎችና ሕይወት ድምሰሳዎች፤

 


 

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ፡ ሕወሃት ያሰቀመጠው ግለስብ (ጠሚቢሕያግ)፡ ተናገር ተብሎ ተጽፎ የተሰጠውን ሸምድዶ፡ በትግራይና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለማቅረብ ሞክሯል። እርሱ የሕወሃት ምርት መሆኑን ማመኑ አንድ ነገር ቢሆንም – ቪድዮ ላይ እንደሚታየውና እንደሚደመጠው – መጭዎቹን የኢትዮጵያ ትውልዶች የእርሱ ዐይነት ባርነት እንዲገቡና እንደገቡ በማስመሰል የምዕተ ዓመታት ባለዕዳነት መመኝቱ ግን የድፍረቶች ድፍረቱ ከመሆን ባሻገር በሕግና ታሪክ ተጥያቂ የሚያደርገው ወንጀል ነው!

ቀድሞ ነገር በሕዝብ ያልተመረጠና የሕዝብ ውክልና የሌው ግለስብ በምን ሂሳብ ነው እርሱ ይህንን በኢትዮጵያ ስም ለመናገር የሚደፍረው?

ከአማካሪዎቹ አንዱ የነበረውን ኩማ ደመቅሳን በአምባሳደርነት ስም ከአካባቢው ሕወሃት ማባረሩ ኦሮሞነቱ አልጣምው እንደሆነ እንጂ፡ እርሱም የከፋ ነበር። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ በትግራዊና ኤርትራዊ ታማኞች፡ ብቻ ሕወሃት ቢሮውን ማጠሩ፡ ድርጅቱ ለከፉ ተግባሮች ወደ ውስጥ ለመመልከት መገደዱን ሳይጠቁም አላለፈም።

ይህ ልበ ድፍንነት ገና ከንጋቱ ለሕወሃት የተገዥነቱን ቃለ መሃላ የእርሱ ‘በፓርላማ’ የፈጸመ ዕለት ይህ ግለስብ በኢትዮጵያውያን መብቶች መረገጥና ደም መፈሰስ እንደሚሠማራ ተምብየን ነበር! እርሱና የእርሱ መሰል አሽቃባጮች እስካሉ ድረስ ኢትዮጵያ ገና ብዙ አስክፊ ነገሮችንና ኃዘኖች ውስጥ ታልፋለች!

ለሱዳን የሃገርን ክብር ረግጦ፡ ግዛት አሳልፎ ከመስጠት የከፋ ውርደት ይመጣልን? ለጅቡቲ ሰዎች በኤኮኖሚ ጥምረት ስም፡ ጥምር ዜግነት ለመያዝ የሚያስችል ሁኔታ ለመስጠት ማነው በጦር መሣሪያ ሃገር ለያዘው ላልተመረጠው ሕወሃት ይህንን ውክልናና ሥልጣን የሠጠው?
 

ማጠቃለያ

ጠሚቢሕያግ ባለፈው ቅዳሜ በጅቡቲ ፓርላማ፣ የተለመደው ቅጥፍት የተሞላበት እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር- The Reporter እንደዘገበው፦

  “As I address you here today, high in my agenda is – protocols and formalities aside – a call to further action in our quest to meeting the perennial demands of our two peoples for an ever closer cooperation, an even greater economic and social union and, who knows, an even closer political integration that simply logically follows from our belief in and dedication to fulfilling our historic common destiny…I don’t know what name political scientists or pundits will give to that sort of closeness but we are slowly but surely inching towards it because, after all, that is what our two peoples so passionately desire and our children so richly deserve”.

እንደው ለነገሩ፡ ምን ቀንና የት ቦታ ነው የኢትዮጵያና የጂቡቲ ሕዝቦች ካልተዋሃድን ብለው ተደጋጋሚ ጥያቄ ለምንግሥቶቻቸው ያቀረቡት? የጅቡቲን መሪዎች በገንዘብና ንብረት ገዝቶ፡ የእነርሱን ስሜት የጂቡቲ ሕዝብ ጥይቄ አድርጎ ማቅረብ፡ ለሃገራችን ተጨማሪ የወደፊት ችግር መግዛት ነው!

ዋናው ጥያቄ፡ ሕወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ረግጦ እየገዛ ባለበት ሁኔታ፡ የኢኮኖሚ ምዝበራውና ድህነቱ በተስፋፋበት ሁኔታ፡ ኢትዮጵያ የደስታ፡ ነጻነትና የእኩልነት ደሴት የሆነች ይመስል፡ የጅቡቲ ሕዝብ አሁን ካለው የተሻለ ሁኔታ ለመብት ረገጣ ሃገሩን ለሕወሃት የበላይ አስተዳዳሪነት አሳልፎ የሚሰጠው?

ጅቡቲና ኢትዮጵያ እንዲወሃዱ እነ Bill Gates ናቸው ኢትዮጵያና ሕወሃት በቅርብ እንዲሠሩ በመገፋፋት ላይ ያሉት መካከል ናቸው። ሕወሃትም ሃገሪቷን ያዘረፈው የባህር ወደብ አሁን እያደረሰበት ባለው የኢኮኖሚ ዕድገትና የወደፊት ተስፋ በባህር በር ዕጦት ምክንያት ማጨለም ቁጭት ውስጥ ስለጣለው ነው አሁን የሚራወጠው።

በተጨማሪም፡ Bill Gates ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. Can the Asian Miracle Happen in Africa? በሚል ጽሁፋቸው፡ የዓለም ባንክና አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት የአፍሪካ ትንሣኤ ሙሉ በሙሉ export-oriented manufacturing አብዛኛዎች የአፍሪካ ሃገሮች ሊሆኑ መቻላቸውን ይጠራጠራሉ።

በዚህም ምክንያት፡ በእርሳቸው ግምት፡ በእርግጠኝነት export-oriented manufacturing hubs ለመሆን ሊተኮሱ ከሚችሉት ሁለት ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያና ጅቡቲ ግንባር ቀደም ናቸው ይላሉ። ይህም የሚሆነው፡ ኢትዮጵያና ጅቡቲ ለቻይና ቅርብ ከመሆናቸው ባሻገር፤ ጥማቱና (ambition) የረዥም ጊዜ የኢኮኖሚ ፕላን ስላላቸው ነው ይላሉ።

ይህን ካነሳን ዘንዳ ሌሎች ተዛማጅ በመካሄድ ላይ ያሉ ጉዳዮችም መታየት አለባቸው።

የሕወሃት ኮማንዶዎች በእርቅ ንግግር ላይ የነበሩትን ሁለት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከፍተኛ አባላት ባለፈው ጥር 2014 በድርድር ላይ ናይሮቢ ሳሉ Mr Sulub Ahmed and Ali Hussein አፍነው ከወሰዱ ወዲህ፡ ሁለቱ ወገኖች እንደገና አሁን ናይሮቢ ተገናኝተው በመነጋገር ላይ ናቸው።

ይህ የታደሰው የናይሮቢ ድርድር፡ የኬንያ መንግሥት እንደቀድሞው በሰጠው የአደራዳሪ ዋስትና ብቻ ሳይሆን፡ የኦጋዴን ጉዳይ ያሳሰባቸው የአሚሪካና የአውሮፓ ሃገሮች እጅ እንዳለበት ይገመታል። ያም ጅቡቲ ወደ ውህደቱ እንድታመራ አመኔታ እንዲያድርባት ሊያደርግ ያስችል ይሆናል! ሰላም ወርዶ ኦጋዴንም ከኢትዮጵያ ጋር በፊዴራል አስተዳደር እንድትሆንና በሞዴልነትም መስከረም 15 ቀን 1952 ዓ.ም. የተመሠረተው ፌዴሬሽን ጠንካራ ዋስትናና መሠረት እንዲሆን ይታሰብ ይሆናል!

ኤርትራም ሥ ዕሉ ውስጥ የምትገባበት ሁኔታ ያለ ይመስላል። እንደሕወሃት አመራር ሁሉ አሥመራም የምትለውና የምታደርገው የተለያየ ቢሆንም፤ ኢሳይያስ አፈወርቂ ኤርትራ ውስጥ ለሕወሃት ጋዜጠኞች ካሳዩት የሰላምና ያለፈውን የናፈቁ መስለ መታየት ሲስተዋል – ምንም እንኳ ኢትዮጵያን መናፈቃቸውን ምስክርነት የምንሠጥበት ተአምር ይፈጠራል ብለን ባንገምትም!

በአንድ በኩል ሲታይም፡ ይህ የእርቅ ድርድር ከዚሁ ሕወሃት የአካባቢውን የአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች በውህደትና በመሠረተ ልማት የመቆጣጠር ዓላማ ጋር የተያያዘ ነው! እንዲህ እስካደረገ ድረስ፡ ሕወሃት ኢትዮጵያን እስክ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ድረስ ረግጦ ለመግዛት የሚያስችለው የፖሊሲ አግጣጫ አድርጎ እየሠራበት ነው!

በሌላ በኩል ግን፡ ይህ ሌሎችን አስባስቦ የመግዛት ስሜት ለሕወሃት ዋና መለያውና እስትንፋሱ መሆኑ ባያጠራጥርም፡ በኃያላን መንግሥትቱ አካባቢ፡ ኢትዮጵያንም ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና እንዲገፋ የሚያደርግ እርምጃ እንዲሆን ማድረግ፡ በዋናዎቹ መንግሥታት በኵል፡ አካባቢውን ከአሸባሪዎችና ከድህነት የሚያካቅቅ ዓላማ ሊኖረው እንደሚችል ግምት መኖሩ ይነገራል።

በሌሎች አቅጣጫዎችም ተመሳሳይ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ሰለመኖራቸው አንዳንድ ኮሽታዎች አሉ ይባላል! በአጠቃላይ፣ እነዚህ የሰበካ ቪዲዮዎች ማንንም ያዘናጋሉ የሚል ሥጋት የለንም – ጥቂት ሆድ አደሮች በፖለቲካባርነታቸው ለጥቂት ጊዜያት ሕዝባችን ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ቢቀጥሉም!

ይዋል ይደር እንጂ፡ ጊዜና የዓለም አቀፉ አስተሳሰብም ስለሚለዋወጥ፡ እነዚህን ወንጀለኞች የኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እንደሚያስተናግዷቸው ጥርጥር የለንም!
 

%d bloggers like this: