በአዊ ዩኒቨርሲቲ መሠረት መጣል ስም፡ የእንጂባራ ሕዝብ በ5 ቀን ብር 15 ሚሊዮን አዋጥቶ ለም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያስረክብ በታዘዘው መሠረት ጉሮሮውን ዘግቶ ክፍያውን ፈጸመ

15 Feb

የአዘጋጁ አስተያየት፦

  ይህ ዜና በጣም አስገርሞን ነው ያነበብነው። በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት የአዊ ዞን ሕዝብ በአጠቃላይ 977,334 (2014 መረጃ) ሲሆን፣ 119,165 የሚሆነው ወይንም 12.2 ከመቶ ደግሞ በከተማ ነዋሪ ነው። ይህ ማለት አብዛኛው ሕዝብ (87.8 ከመቶ) በገጠር ነዋሪና በግብርና ተዳዳሪ መሆኑን ነው።

  ለየት ያለው ሁኔታ፡ ማለትም የሕዝቡን የድህነት ጥልቀት በግልጽ የሚያሳየው፡ ከአጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር ውስጥ፡ 528,398 የሚሆኑት ወይንም 54.1 በመቶ ምንም ዐይነት የትምህርት ዕድል ያልገጠማቸው ናቸው። ኢኮኖሚያቸውም እስከዚህ ጠንካራ የሚባል አይደለም። ድህነት በብዛት የሚታይበት አካባቢ ነው። በአጠቃላይ በአዊ ዞን፡ ከላይ ከተጠቀሰው የነዋሪ ብዛት፡ 191,536 ወይንም 19.6 በመቶ መተዳደሪያ የሌላቸው ሲሆኑ፡ 16,451 ደግሞ ታዳጊ ሕጻናትና ትምህርት ቤት የሚሄዱ ናቸው።

  በተጨማሪም፡ የአኗኗር ሁኔታንና ይዞታን በተመለከተ፡ ለምሳሌ ያህል፡ በአጠቃላይ በአዊ ዞን 209,557 ቤቶች ሲኖሩ፡ 57ቱ ከቆርቆሮ፣ 36ቱ ከኮንክሪትና ሲሚንቶ ጣራቸው መሠራታቸውን መረጃዎች ሲያመለክቱ፡ 91,694 ወይንም 44.0 ከመቶ የሚሆኑት ቤቶች ከሣር: 8,856 ደግሞ ከሸንበቆ የተሠሩ ቤቶች ለመናቸው መረጃ መኖሩ የድህነቱን ስፋትና መጠን የሚጠቁም ይመስለናል።

  በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአዊ ዩኒቨርሲቲን ኢንጅባራ ላይ የመሠረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ደግሞ “ሆስፒታሉን በስፍራው ከሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ጋር ለማቀናጀት መታቀዱን ገልጸው በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተካፋይ ሆነዋል፡፡

  ባለሥልጣኖቹ የመጡት ግን መሠረት አኑረው፣ ባዶ እጃቸውን ለመመለስ አልነበረም። ሕዝቡ በፍላጎቱና በአቅሙ መጠን ተተምኖ ሳይሆን፡ በበላይ ባለሥልጣኖች በተጫነበት ግዴታ መሠረት፡ አባይ ላይ በመገንባት ላለው የአባይ ግድብ ማስጭረሻ ብር 15 ሚሊዮን የማዋጣት ግዴታ በአምስት ቀናት እንዲያጠናቅቅና እንዲከፍል ተደርጓል። ይህ ገንዘብ ከላይ የተተመነበት እንጂ የአካባባቢውን ሕዝብ ነጻ ፍላጎትና ችሎታ ያገናዘበ ነው እንዳንል እስካሁን ያለው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ዘራፍባይነትና ‘እኛ ያልነው ብቻ’ አሠራር ዜዴ እንድንጠራጠር ያደርገናል።

  ቀደም ብሎ የተጀመረው ሆስፒታል እንኳ ሊጠናቀቅ አለመቻሉን ለሕዝቡ ሌላ ቃል ተገብቶለት፡ የሚቋቋመውን ዩኒቨርሲቲና ሆስፒታሉን ለማያያዘ መታቀዱ ተግለጿል።

  የሚገርመው ግን፡ ሕዝቡ ከዚህኛው ዘረፋ ሳያገግም፡ ለመለስ ፋውንዴሽን፡ ለዚህና ለዚያ እየተባለ እየተገደደ እንድያዋጣ በመገደዱ መከላከያ ማጣቱን ከየአካባቢው ሲነገር የቆየ የባለሥልጥኖች ዘረፋ ነው!

  በመንግሥት ደረጃ፡ የዚህ ዐይነቱ የማን አለብን አሠራር የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያደቅ ከመሆኑም ባሻገር፡ ለወደፊትም እራሱን በቆጠበውና ለፍቶ በሚያጠራቅመው ገንዝብ ተማምኖ ኢኮኖሚያዊ ሕየውቱን እንዳያሻሻል ተስፋና ቁርጠኝነቱን ይሰልበዋል።

  በማይሠራና በማይሠራ ዩኑቨርሲቲ መሠረት ስም ብር 15 ሚሊዮን ስብስቦ ለሕወሃት ማስረከብ ዐይን ያጣ ዘረፋ ነው!

  ለዘለቄታው ሃገርንና ሕዝብን ጎጂና የሰብዓዊ መብቶችም ጥሰት ነው!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአዊ ዩኒቨርሲቲ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

  * የአዊ ዩኒቨርሲቲ በ200 ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው በቅርቡ ይጀመራል፡፡

  * በጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ጥሩ ውጤት ከተመዘገበባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው እንጅባራ ከተማ የተሰራው ሆስፒታል ግንባታ ከታቀደለት ጊዜ ዘግይቷል፡፡

  * በሌላ ዜና የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በእንጅባራ ከተማ መድረሱን ተከትሎ በ5 ቀናት ውስጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዊ ዩኒቨርሲቲ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። በቀጣይ ትምህርት ሚኒስቴር ሊገነባቸው ካቀደው 11 አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የአዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አማካኝነት በእንጅባራ ከተማ ተቀምጧል፡፡

በ115 ሚሊዮን ብር የተገነባው የእንጅባራ ሆስፒታል ምርቃት ስነስርአትም ተከናውኗል።

DPM Demeke Mekonnen laying the foundation of Awi University (Credit: EBC)

DPM Demeke Mekonnen laying the foundation of Awi University (Credit: EBC)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የአዊ ዩኒቨርሲቲን የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ በዩኒቨርሲቲውና በሌሎችም የመሠረተ ልማት ስራዎች የህብረተሰቡ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፥ ይህ ዘርፈ ብዙ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠይቀዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ በበኩላቸው፥ ሆስፒታሉን በስፍራው ከሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ጋር ለማቀናጀት መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ወጣቶች የከፍተኛ ትምህርትን በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ለማስቻልና በአዊ ብሔረሰብ ባህልና ቋንቋ ዙሪያ ጥናትና ምርምሮች እንዲካሄዱ በር እንደሚከፍት የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የአዊ ዩኒቨርሲቲ በ200 ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው በቅርቡ ይጀመራል፡፡

በጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ጥሩ ውጤት ከተመዘገበባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው እንጅባራ ከተማ የተሰራው ሆስፒታል ግንባታ ከታቀደለት ጊዜ ዘግይቷል፡፡

በሌላ ዜና የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በእንጅባራ ከተማ መድረሱን ተከትሎ በ5 ቀናት ውስጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል፡፡
 

%d bloggers like this: