ዘረኝነቱ በስፖርት መስክም? ትግራይ የራሷ የሆነ አትሌቲክስ ቡድን በማቋቋም ላይ ትመስላለች! ለምን አስፈለገ ይሆን በብሔራዊ ደረጃ ከሁሉም የተውጣጣ ፉክክርና ምርጫ ደህና እየተካሄደ ሳለ?

9 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

    በስፖርትም ኢትዮጵያውያን ተለያይተው እንዲፎካከሩ ሕወሃት ለብቻ የራሱን ድርጅት አቋቁሟል። አሠልጣኙም ትግራዊ፡ ስፖርተኞቹም ትግራዊያን ሲሆኑ፡ ከዚህ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ባልተደረገ መልክ፡ የገንዘብ ድጎማ ለብቻ ይደረግላቸዋል – ኢዜአ እንደዘገበው። ከውጭ ሃገሮችና አትሌቲክስ ድርጅትም፡ ለብቻ ለእነርሱ የተሳታፊነት ጥሪ ይቀርብላቸዋል– ለምሳሌ ቻይና በዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ለዛውም! ታዲያ በየት በኩል ነው እኛ እንድ ነን የምንለው፡ እነርሱ በሚያመቸው ቀዳዳ ሁሉ የራሳቸውን ብቻ መግቢያና መበልጸጊያ እንዲያዳብሩ ሕወሃት መንገዱን ሲያመቻችላቸው? ዓላማው፣ ለሕወሃት ይህ አንኳ አልዋጥለት ብሎ ኢትዮጵያ ታዋቂ የሆነችበትን አትሌቲክስ ለማዳከም ይሆን? ምናልባትም ያልተገነዘበው አፓርታይዳዊ በሆነ መንገድ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በማዳከም ትግሬዎችን ነጥሎ ማጠናከር አይቻልም እኮ! ገፋፍታችሁ እንዲህ ያለ ነገር እንድንጽፍ ስላደረጋችሁን ኃዘኑ ግን የኛ ነው!

 
መቀሌ መጋቢት 30/2007 (ኢዜአ): በቅርቡ ቻይና በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር በስድስት ኪሎ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ያገኘችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በመጪው ግንቦት ቻይና ሻንጋይ ከተማ በሚጀመረው የዳይመንድ ሊግ ውድድር እንድትሳተፍ ጥሪ የቀረበላት መሆኑን የትራንስ አትሌቲክስ ቡድን አሰልጣኝ አስታወቁ፡፡

የትራንስ አትሌትክስ ቡድን አሰልጣኝ ሀይለ እያሱ እንደገጹት አትሌት ለተሰንበት ግደይ የፊታችን ግንቦት ዘጠኝ በሚጀመረው የዲያመንድ ሊግ ውድድር እንድትሳተፍ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደረሽን ጥሪ አድርጎላታል፡፡

አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ በአህጉርና አገር አቀፍ የአትሌቲክስና ብስክሌት ውድድር ክለባቸውንና አገራቸውን [ትግራይን ወይንስ ኢትዮጵያን?] በመወከል ለተሳተፉ ብስክሌተኞችና አሰልጠኞች ትናንት የማበረታቻ ገንዘብና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ሃገራቸውን የወከሉ የተባሉ አንዳችም ከሌሎች ብኄረሰቦች የተውጣጡ ስፖርተኞች ይህ ዜና በተጻፈለት የትግራይ ቡድን ዜና ላይ አንዳቸውም ተሳታፊ ለመሆናቸው አንዳችም ነገር አልተጠቀሰም! ለጋዜጠኛው አልታይ አሉት ይሆን?ይህ እጅግ መጥፎ፡ አደገኛ አሠራርና አካሄድ ነው! (ፎቶ ኢዜአ)

አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ በአህጉርና አገር አቀፍ የአትሌቲክስና ብስክሌት ውድድር ክለባቸውንና አገራቸውን [ትግራይን ወይንስ ኢትዮጵያን?] በመወከል ለተሳተፉ ብስክሌተኞችና አሰልጠኞች ትናንት የማበረታቻ ገንዘብና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ሃገራቸውን የወከሉ የተባሉ አንዳችም ከሌሎች ብኄረሰቦች የተውጣጡ ስፖርተኞች ይህ ዜና በተጻፈለት የትግራይ ቡድን ዜና ላይ አንዳቸውም ተሳታፊ ለመሆናቸው አንዳችም ነገር አልተጠቀሰም! ለጋዜጠኛው አልታይ አሉት ይሆን?ይህ እጅግ መጥፎ፡ አደገኛ አሠራርና አካሄድ ነው! (ፎቶ ኢዜአ)

አትሌቷ በዳይመንድ ሊግ የአምስት ሺህ ሜትር ሩጫ ለመወዳደር ጠንካራ ልምምድ በመስራት ላይ መሆኗን ገልጸው አትሌቷ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ከሶስት ሺህ 500 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ በላው ቦታ ልምምድ እየሰራች መሆኗን አስታውቀዋል፡፡

በሀምሌና ነሀሴ ወራትም በሚካሄደው የታዳጊዎችና የዓለም ሻምፒየን ውድድር ከታዋቂ የአገሪቱና ዓለም አትሌቶች ጋር ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኗንም ገልፀዋል፡፡

የአትሌቲክስ ቡድኑ ከተመሰረተ አንድ ዓመት ተኩል ቢሆነውም አስር ሴትና አስር ወንድ አትሌቶች በመመልመል ተተኪ ለማፍራት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አሰልጠኝ ሀይለ እንዳሉት አትሌት ለተሰንበትን በኦሎምፒክ በአምስት ሺህ ሜትር ተሳታፊ ለማድረግ ሳይሆን አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት የአትሌትክስ ቡድኑ ግብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አትሌቷ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ውድድሮች እንድትሳተፍ ጥሪ ተደርጎላት ለምን እንደከለከሏት ተጠይቀው አትሌቷ በወቅቱ አካላዊ ብቃቷ ገና በመሆኑ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋት ስለነበር ነው ብለዋል፡፡

ከትራንስ ኩባንያ የ50 ሺህ ብርና ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ10ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት የተቀበለችው አትሌት ለተሰንበት በበኩሏ ትራንስ ኢትዮጵያ የጀርባ እጥንት በመሆን ለዚህ ድል እንዳበቃት ገልፃለች፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያንና አገሯን በመወከል ደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የብስክሌት ውድድር የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ የሆነችው ሓድነት አስመላሽም 10 ሺህ ብር ተሸለሚ ፣ጠንካራ ተወዳደሪ የነበረው ብስክሌተኛ ሓድጉ በላይ የሶስት ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት አግኘተዋል፡፡

የአትሌቲክስ ቡድኑ አሰልጣኝ ሀይለ እያሱ የ25 ሺህ ብር፣የትራንስ ብስክሌት ዋና አሰልጠኝ መሓሪ ዶሪ የ10 ሺህ ብር የቡድኑ መሪና ወጌሻ የአምስት ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት ከትራንስ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር እጅ ተቀብለዋል፡፡

በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተፈሪ ዘውዱ እንደገለፁት ስፖርት አንዱ የአገሪቱ የልማት ዘርፍ መሆኑን ኩባንያው በማመን ባለፉት ዓመታት ለስፖርት እስከ 60 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያ የአትሌቲክስና ብስክሌት ቡድኑን ለማጠናከር ዘንድሮ ከ10 ሚልዮን ብር የሚበልጥ በጀት በመመደብ አገራቸውን የሚወክሉ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች ለማፍራት ጥረት በማድርግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 

One Response to “ዘረኝነቱ በስፖርት መስክም? ትግራይ የራሷ የሆነ አትሌቲክስ ቡድን በማቋቋም ላይ ትመስላለች! ለምን አስፈለገ ይሆን በብሔራዊ ደረጃ ከሁሉም የተውጣጣ ፉክክርና ምርጫ ደህና እየተካሄደ ሳለ?”

  1. Tecola Worq Hagos April 9, 2015 at 18:22 #

    This is the first time I visited this Website. It was recommended to me by Prof Seid Hassen, one of the authors of a critical piece on the Declaration of Principles, with whom I have serious disagreements. Now, የትልቅ ወንድማችን Keffyalew Gebremedhin editorial piece on a young Ethiopian Athlete winning in China is truly disappointing, for it is sectarian and unnecessary piece. Keffyalew, no matter your disappointment in/with the current Ethiopian Government, you should have respected the “fleeting” glory of this particular young athlete who is wearing our Ethiopian uniform with pride. You have experience and a secure retirement. And yet you did not even observe carefully what the very picture you posted says. The young lady is wearing a uniform that says loud and clear, “Ethiopia.” You jumped out and spew innuendo and unsubstantiated accusations against a group of people you obviously hate. With all your experience and privileged life, must you lower yourself to the status of G7 out of control propagandists? I came to your website with an open mind, and I am deeply disappointed that you are still a bigot even in your old age, a sentiment you learned from your little village in some little corner of my Ethiopia. This form of your writing is not how one builds a great Ethiopia that would respect human dignity and individual human rights. Tecola W. Hagos

    Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: