ወ/ሮ ዛይድ ተስፋይ፥                                     ‘ጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ሳይረሱ የማህበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል’ – አሁንም ጎዳና ላይ ቢሆኑም!

1 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

    የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮበአሰሩም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የምክር ቤት አባላት በተገኙበት ‘በአደራ ቤተሰብ ክብካቤን’ ዙሪያ ሥልጠና ሠጥቻለሁ ይላል!

 

ጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸው - ከመካከላቸው ቤቶቻቸውንና መሬቶቻቸውን በሕወሃት ሰዎች የተነጠቁ ይኖራሉ! (ፎቶ፡ ኢዜአ)

ጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸው – ከመካከላቸው ቤቶቻቸውንና መሬቶቻቸውን በሕወሃት ሰዎች የተነጠቁ ይኖራሉ! (ፎቶ፡ ኢዜአ)


 
አዲስ አበባ ግንቦት 22/2007 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት የማህበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡ ቢሮው በአሰሩም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የምክር ቤት አባላት በተገኙበት ‘በአደራ ቤተሰብ ክብካቤን’ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ዛይድ ተስፋይ እንደተናገሩት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን ሁሉ ብቁ ዜጋ እንዲሆን ለማስቻል ባደገበት ሰፈር በቋንቋው ባህሉን ሳይረሳ እንዲያድግ የማህበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።

ቢሮው ህፃናት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከመስጠትም ጎን ለጎን ቤተሰቦችን የመመልመልና ማዘጋጀትና ማሰልጠን ብቁ የማድረግ ህጻናትን የማገናኘት ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም ከአደራ እንክብካቤ በሀገሪቱ በብዛት ያልተሰራበት በመሆኑ ጉድፈቻ በብዛት እንደሚታወቅ ገልፀው ባለፉት ሳምንታት ለችግሩ የተጋለጡ 11 ህጻናትን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ከህብረተሰቡ የማድረስ ሥራ መስራቱንም ተናግረዋል።

የአደራ ቤተሰብ ክብካቤ ህጻናትን የፍርድ ቤት ውል በሌለበት ከቢሮው ጋር በተደረገ ስምምነት በፈቃደኝነት ህጻኑን በአደራ ወስዶ እንዲያሳደግ የሚደረግበት ሁኔታ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማዋ የችግሩ ስፋት አንፃር የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናት ፍቅር አግኝተው እንዲያድጉ የማስቻሉ ሥራ ለአንድ ወገን የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አሳስበዋል።

የስልጠናው ዓላማ ለጉዳዩ ባለቤት የሆኑ የምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠርና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

የኪንግ ደም ቪዝን ኢንተርናሽናል ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዮብ ቆርቻ አደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ወላጅ ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህጻናት ከተፈጥሮ ቤተሰቦቻቸው ጋር መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ሲሆኑ እነሱን ተክተው የሚያሳድጉበት ፕሮግራም መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ ሲጀር አሜሪካን፣ ከእንግሊዝ፣ ከአፍሪካ ከኡጋንዳ ተሞክሮ በመውሰድ አገሪቱን ር መተግበራቸውን አስታውቀው በእሰከ አሁኑ ውጤታማ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ተጠናክሮሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ተናግረዋል።

በአገሪቱ አጠቃላይ ካለው ህዝብ ቁጥር 52 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 5 ነጥብ4 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በከፋ ችግሩ ውስጥ የሚኖሩ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።