የገንዘብ ሚኒስትሩ የዓመቱ ባለ ልማት ያሉት የ2007 በጀት ከፍተኛ ገንዘብ ለተጠየቀለት 2008 በጀት ጥሩ መሰናዶ መሆኑ አጠራጣሪ ነው (ክፍል 1)

3 Jul

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ክፍል አንድ

I. በጀቱ ከመጽደቁ በፊትና ከጸደቀም በኋላ፡ ስሌቱን የሚያጨልሙ ደመናዎች

አሥራ አምስት ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረው የተባበሩት መንግሥታት የምዕተ ዓመቱ የልማት ዘመን (Millennium Development Goals – MDG) ባከተመበት ዓመትና እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለመተለም (Sustainable Development Goals 2015) ዝግጅት እየተጠናቀቀ ባለበት ዋዜማ፡ የተባበሩት መንግሥታት ልማት ፕሮግራም (UNDP) በቅርቡ በኢትዮጵያ የአሥራ አምስቱ ዓመት ጉዞ ክንውን ላይ ባቀረበው ግምገማ ውስጥ የሚከተለው አሳሳቢ ድምዳሜ ይገኝበታል፦

  • “Ethiopia has already achieved the MDG 4 target of reducing child mortality and is on track to reach the MDG 1 target on eradicating extreme poverty and hunger and MDG 6 on combating HIV and AIDS, malaria and other diseases.

  • Despite double-digit economic growth and substantial decreases in the percentage of the population below the national poverty line, the absolute number of the poor is roughly the same as 15 years ago and a significant proportion of the population hovers just above the poverty line and is vulnerable to shocks. Moreover, the severity of poverty increased from 2.7 per cent in 1999/2000 to 3.1 per cent in 2010/11.”

________________
ነፃ ትርጉም፦
________________

  • “ኢትዮጵያ ግብ አራትን አጠናቃ የሕጻናት ሞትን መቀነስ ችላለች፤ እንዲሁም ግብ አንድን ለመምታት ደህና ጉዞ ላይ መሆኗንና ሠቅጣጭ ድህነትን በግብ 6 አማካይነት፥ ኤድስን፡ ወባንና የተለያዩ በሽታዎችን ለማሰወገድ መንገዷ ቀና ነው።

  • ሆኖም ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ባለድርብ ቁጥር የኢኮኖሚ ዕድገትን ብታሳካና ከብሔራዊ ድህነት ወለል በታች የነበረውን በከፍተኛ መቶኛ ብትቀንስም፣ ጥቅሉ የድሃው ሕዝቧ ብዛት ቁጥር ዛሬ ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው። ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያውያን በድህንነት ወለሉ ላይ በመንሳፈፍ ላይ ናቸው። እነዚህም ለከፍተኛ ተለዋዋጭ ችግሮችና አደጋዎች ተጋላጭ ናቸው። በተጨማሪም፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የድህነቱ ጥልቀት በ1999/2000 ከነበረበት 2.7 ከመቶ በ2010/2011 ወደ 3.1 ከመቶ ዘሏል”

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው Ethiopia budget 2008ኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፊዴራል በጀት፣ ማለትም ብር2 23.4 ቢሊዮን ($11.4 ቢሊዮን) በኛ ዘመን አቆጣጠር ለ2008 ዓ.ም. (2015/16) በስሟ የተጠየቀው።

ነጻ የሆነ የሕዝብ ተሳትፎን በሚያፍን አሠራር ውስጥ፡ አሁንም ሃገሪቱ ይህ ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለተጠየቀው ተግባር መዋሉንና ሕዝቡ በእኩልነት ተጠቃሚ ለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለም። ለጊዜው የጥቂቶችን ውስጥ ለውስጥ መጠቃቀም ነቀዝነትና የሃገር ሃብት የሚያበላሸውን ሙስናን በሃሣባችን እናቆየው።

ለማንኛውም፡ ከላይ ከተጠቀስው ውስጥ ብር 141.2 ቢሊዮን ከታክስ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ብር 15.9 ቢሊዮን ደግሞ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከአግልግሎቶች ገቢና (የግል ክምና፣ የመሬት ኪራይዎች ከመንግሥት የልማት ዴርጅቶች የዱቪደንድ፣ ወዘተ)፣ ከአንዳድ ሽያጮች፣ (ሎተሪ ትኬት፣ ንብረት ሽያጭ፣ መቀጫ፣ ወዘተ) ገቢ ይኖራል ተብሎ የተሠላ በጀት ነው።

በጥቅሉ ሲታይ፡ የሃገሪቱን ዕድገት ለመምራትና ለማስተባበር እንዲሁም ለመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከሃገር ውስጥ ማሰባስብ የምትችለው ገንዘብ – የበጀት ስሌቱን መለኪያ ካደረግነው – ብር 157.1 ቢሊዮን ብቻ ነው – 70.3 ከመቶ ማለት ነው! አሁንም ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ታክስ መሠረት (tax base) ያላት ሃገር ስለሆነች፣ የታክስ ገቢው ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 12.7 በመቶ ላይ እንደቆመ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ የታክስ ሸክሙ የጥቂትች ትከሻ ላይ እንዲወድቅ አድርጎ፣ ብዙዎች በሃቅም ይሁን በፖለቲካው ሸፍጥ ወይንም ገልቱነት (gross indifference) ምክንያት ከአቅም በላይ የሆነ ታክስ እንዲከፍሉ፣ አልያም ዘብጥያ እንዲወርዱና ሃብታቸውም ለዘራፊዎች መቋደሻ ይሆናል።

እንዳለፉት ዓመታት ልምድ ከሆነ፣ እዚህ ላይ መታወስ ያለበት፣ በመንግሥት አገልግሎቶች ኪራዮችና ሽያጮች ስም የተሰሉት የገቢ ግምቶች (7.1 ከመቶ) ሙሉ ለሙሉ ለመሳካት የማይችሉ መሆናቸውን ነው – ዋናው ኦዲተር እንዳመለከቱትም የገቢ አተማመን፡ ሪፖርት አደራረግና ገቢውን በጊዜ ለመስብሰብ ያለመቻል ችግሮች በተደጋጋሚ ለመታረም አለመቻላቸውን እንደ ዋነኛ ምክንያቶች ይጠቁማሉ!

የውጭ ብድርና ዕርዳታ ይገኝ ይሆናል ተብሎ በግምት የተጠየቀው ብር 38.7 ቢሊዮን በጀት ውስጥ ተካቷል። እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው፡ የውጭ ድጋፍ (Grant)– የIMF መረጃ እንደሚያመለክተው – ከ2011 ጀምሮ እያሽቆለቆለ ስለሆነ፣ ለምሳሌም ያህል፡ በ2010/2011 3.3 ከመቶ፡ በ2011/12 ወደ 1.7፣ 2012/13 ወደ 1.6፣ በ2014/15 ወደ 1.5፣ በ2015/16 ወደ 1.3 ስለሚወርድ፣ ይህ በዕርዳታ (ስጦታ) ይገኛል ተብሎ የተሰላው ቁጥር አብዛኛው ተመንዛሪነቱ አጠርራጣሪ ነው።

የመጀመሪያው የአምስት ዓመት የልማትና ዕድገት ዕቅድ እንዳለመውና እንዲሁም ተተኪው ብሔራዊ መርሃ ግብር ያመለክታል ተብሎ እንደሚጠበቀው፣ ሃገሪቱ ካላት የማደግና የመልማት ሥራዎችና ክንውኖች አንጻር፣ በመጠኑም ቢሆን የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ይህንን ከፍተኛ ገንዘብ በበጀትነት እንዲፈቀድለት የገንዘብና ኤኮኖሚ ሚኒስቴር ቢጠይቅም፡ ሃገሪቷ ይህን በጀት ተግባራዊ ለማድረግ የምትችለው፣ ማለትም ገንዘቡን ራሱ ለማግኘት የምትችልበት ሁኔታ መኖር አለመኖሩ ገና ከጥቅቂ ወራት በኋላ የሚታይ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ገንዘቡ ሊገኝ እንደማይችል አንዳንድ ተጨባጭ ምልክቶች ይታያሉ።

የተባለው ገንዘብ ባይገኝ ምርጫዋ ምንድነው? በአማራጩስ ምን ታደርጋለች? ምን ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ታዘገያለች? የሚሉትም ራሳቸውን የቻሉ ተገቢ ጥያቄዎች ናቸው። በበጀቱ አዘጋጆቹ በኩል የተገለጹ ነገሮች የሉም።

ለማንኛውም፡ የተጠየቀው ገንዘብ በጀቱ ውስጥ ሊኖር የሚችለው ለሃገሪቱ የሚከተሉት ሁኔታዎች የተሟሉ ወይንም ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት የተወገዱ እንደሆነ፣ ወይንም አሁን የሚታዩት የፖሊሲ ማስፈጸም አቅም፡ አተርጓጎምና የሕግ ወደፖለቲካ አገልግሎት መግባትን የመሳሰሉ ችግሮችን ማስወገድ መሆኑ ይታመናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት፡ በከፊል በገንዘብ ሚኒስቴር በፖሊሲ ደረጃ ታምኖባቸዋል – ለዚያውም አማራጭም የላቸውም።

የበጀቱ አዘገጃጀትና ስሌቱ በአብዛኞቹ ከዚህ በታች በሠፈሩት መሟላት (መስተካከል) ላይ የተመሠረተ ለመሆኑ: በገንዘብ ሚኒስትሩ ፓርላማ ውስጥ ካደረጉት ንግግር የተጠቀሱት እዚህ ላይ ተመልክተዋል። በተጨማሪም ሚኒስትሩ ሊያነሱ ያልቻሉትን ወይንም ያልደፈሩትን፣ እዚህ ውስጥ የምናነሳበትን ምክንያት ማንም ጤነኛ ሰው በቀላሉ የሚገነዘበው ይመስለናል።

ለማንኛውም የሚከተሉትን መመልከቱ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሠፈሩትንና የሚከተሉትን ክፍሎች በሚገባ ለመገንዘብ ይረዳል፦

  ሀ.   ሃገሪቱ በ2008 ዓ.ም. 11.2 በመቶ የአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ይኖርባታል

  ለ.   አማካይ የዋጋ ዕድገት 8 በመቶ ሆኖ መቀጠል አለበት

  ሐ.   ከዕቃዎች በውጭ ገበያ ሽያጭ የሚገኝ ገቢና (merchandize export) በዕቃዎች ከውጭ በመግዛት የሚደረግ ወጭ (imports) መጠን ቅደም ተከተል – አቶ ሱፍያን እንዳስቀመጡት – የ28.2 በመቶ እና የ21.6 በመቶ ዕድገት ካሳዩ

  መ.   የታክስ ገቢው እስካሁን በታየው አፈጻጸምና ከተቻለም ተሻሽሎ የሚፈለገውን ገቢ ለመሰብሰብ ከበቃ፣ እንዲሁም 12.7 ከመቶ ብቻ የሆነው የገባሪው መሠረት (tax base) ሲሠፋ

  ሠ.   ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች ምንጭ በዋናነት በመንግሥት መ/ቤቶች ከሚሰጡ አገልግልቶች ክፍያ፣ ማለትም ከመንግሥት ዕቃዎች ሽያጭ፣ ከመንግሥት የልማት ዴርጅቶች የዲቪደንድ ድርሻና የዘቀጠ ትርፍ እንዲሁም ሌሎች ገቢዎች

  ረ.   ከፕሮጄክቶች ዕርዳታና ብድር እንዲሁም ከPromotion of Basic Services (PBS) ዕርዳታና በዚህ ስም ከሚገኙት ተጨማሪ ብድር ብድሮች የተገኙ እንደሆነ

  ሰ.   መንግሥት ለበጀት ጉድለት ማሟያ የሚወስደው ብድር (1.8 በመቶ ከGDP ለዛውም ቁጥሩ ሃቀኛ ከሆነ) የሃገሪቱን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ የማያሰናክልና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገትን የማያደናቅፍ መሆኑ የገንዘብ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር የበጀት ስሌታቸው እንደሆነ አሰምተዋል።

  ሸ.   በሃገሪቱ ሰላም መስፈን በተለይም በየአካባቢው የሚካሄዱ ግጭቶች ከቁጥጥር ወጥተው የሕወሃት አስተዳደር በየሥፍራው ወታደራዊ ኃይል መጠቀሙ ምክንያት የሚፈጠረው አለመረጋጋት ኤኮኖሚው ላይ ተጽእኖ የማይፈጥር ከሆነ – እንዲያውም በዛሬው ዕለት ለምሣሌ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ጦር ሐምሌ 2 ቀን 2015 ከሕወሃት አስተዳደር ጋር የጦርነት ይጀመር “ፊሽካው ተነፍቷል” በማለት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል!

  ቀ.   በታክስ መጠን መብዛት፥ በጥሬ ዕቃ ዕጦት ወይንም በፖለቲካዊ ቂም በቀል ወይንም በመብራትና ውሃ ችግር ምክንያት የሚወድቁት/የሚዘጉት የንግድ ወይንም አምራች ድርጅቶች ችግር ሊቀነስ ካልቻለ፡ ዛሬ እንደሚታየው የሃገሪቱ በዜጎቿ አማካይነት ለዜጎቿ የሥራ ዕድሎች ማስፋፋት መቻሏና የውጭ ንግዷንም ማዳበሯ አሁን እንደሚታየው ከቀጠለ የበጅቱ ሙሉ ለሙሉ መሳካት የማይታሰብ ነው

  በ.   ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተባብሶ የሚታየው በኅብረተስቡና በአስተዳደሩ መካከል ያለው ሆድና ጀርባ መሆን፡ በይበልጥ ወጣቱን ማስከፋቱ ሰለሚታይ፡ እነዚህ ሁኔታዎች ውጥረታቸው ከተባባሰ በሰላምና መረጋጋት ላይ እንዲሁም በኤኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው ጉዳት

  ተ.   በሃገር ውስጥ፡ በሕዝብ በኩል ያለውም ቅሬታ በሙስና፡ በአገልግሎቶች አሠጣጥ፥ በዘረኝነትና በመሬት ዘረፋ ዙርያ ያለው ችግር የኢትዮጵያ ኤክኖሚ የወደፊቱ መቅሠፍት እንደሚሆን የመልካም አስተዳደር ባለሙያዎች ደጋግመው አሰምተዋል።

  ቸ. በርዕስ መስተዳደርነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የተቀመጠው ግለስብ በሚፈጽማቸው ጥንግር ያሉ ነገሮች፡ በተለይም ቅጥፈትና ዐይን ያወጡ ውሸቶች ምክንያት ኢትዮጵያ ከበሬታ እያጣች ነው። በአነጋገርም የሚያሳየው የዜጎችና የኅብረተሰብ ንቀት ምክንያት የሚሰሙት ትችቶች ለዜጎችና ለሃገራችን ክብር እጅግ አሳፋሪ እየሆነ መምጣቱ ሃገሪቱ ለምታስበው ግብ እንቅፋት ይሆናል

ከላይ የተዘረዘሩትን በሚመለከት ግንዛቤው በሕወሃት አስተዳደር በኩል ሊኖር እንደሚችል፣ በአንዳንዶቹም ሊስማሙ እንደማይችሉ ይገመታል። ወደዱም ጠሉት፡ ባለፉት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በሕዝብ በኩል የበቃኝ ባይነትን ስሜት ያለፈው ምርጫ አባብሶት፡ በተለይም በተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና በወጣቱ ላይ የሚፈጸመው የአስተዳደሩ ሕገ ወጥነት የለውጥን ፍላጎት እያባባስው ስለመጣ፡ ይህም በኤኮኖሚው ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጥርጥር ሊኖር አይገባም። አዲሱም በጀት በዚህ በተበላሸ አየር ውስጥ ተጸንሶ ነው፣ የአስተዳደሩን ሥራ ለማስኬድ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመስብሰብ ዝግጅት እየተደረግ ያለው።

ምርጫውን በተመለከተ፡ ከውጭ ያለው አመለካከት ነቀፌታና ትዕዝብት አዘል ለመሆኑ፡ በቅርቡ የእንግሊዝ አምባሳደር ግሬግ ዶረይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፡ ሃገራቸው የዕርዳታ ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እያፈሠሠች – እርሳቸውም እንዳነሱት – ኢትዮጵያ ወደ ሰሜን ኮርያነት ስትለወጥ ዝም ብሎ መመልከት እንደማይቻል በቀጥታም በተዘዋዋሪም የሚጠቁም ጠንካራ አስተያየት ነው ሠንዝረዋል።

ለነገሩ በሃገሩ ተቀማጭ የሆነ አምባሳደር እንዲህ ከዲፕሎማቲክ ልምድ ውጭ በግልጽ የሚጎስም ወቀሳ ሲያቀርብ ወይንም ሲጀመር፡ የግንኝነቱን ክፉኛ መሻከር አመላካች ነው። በመሆኑም ሕወሃት በሚፈልገው የኤኮኖሚና ፖለቲካ ደጋፍ ላይ – በአዲሱ በጀት ዕርዳታ ጭምር – ትልቅ ተጽእኖ እንደሚኖረው ማንም ሊገነዘበው ይችላል።

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ የዚህ ዐይነት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት መወላከፍ በዋና ጉዳይ ላይ ያጋጠማት ልምድ፡ በኅዳር ወር 2010 ዓ.ም. ነበር። በአዲስ አበባ ተቀማጭ የነበሩት የግብጽ አምባሳደር Tarek Ghoneim ለCapital በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ሌሎች ብዙ ውሃዎችና ከፍተኛ ዝናብ ስላላት፡ ዐባይን ለግብጽ መልቀቅ ይኖርባታል ብለው ያሳስቡበት ሁኔታ ነበር። ይህም በኋላ ለጊዜውም ቢሆን መለስ ዜናዊና ሆስኒ ሞባረክ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ወደ መዘላለፍ ለመውረዳቸው ምክንያት እንደነበር ይታወሳል

ስለሆነም፡ የእንግሊዝን አምባሳደር ቃለ መጠይቅ በእርጋታ ላነበበ ሰው፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የተቀመጠው ሰው በተደጋጋሚ ባህሪው ከሆነው የውሽት ፍቅር ባሻገር፥ ከችሎታው ብዙ ደረጃዎች ልቆ ሥልጣን ላይ መቀመጡ፥ ኢትዮጵያ በአመራር ጠንቃቃነትና ትክክለኛ ዕይታ (vision) ዕጦት ላይ መሆኗን በሚገባ አሳይቷል። ከዚያም የከፋ ሃገሪቱን በብጥብጥ፣ መከፋፈልና ማስፈራራት እያወከ – ኢትዮጵያ በልጆቿ ላይ እንድትዘምትና እጇን እንድታነሳ አድርጓታል። በእንግሊዝ አምባሳደር የተነሱት ጉዳዮች ጭምር፣ በተለይም የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያን ምርጫ ያልታዘበው፣ ገንዘብ ስለቸገረው ነው የሚለው አባባል ሃስተኛነቱ ተነስቷል።

ለምሣሌ በቅርቡ ከምርጫው በፊት በፓርላማ ያደረገው ጋጠወጥና ሕገወጥ ንግግር ብዙዎች የፖለቲካ ተንታኞችን አስገርሟቸዋል። እኔንም፡ ያ ንግግር በፈረንሣይ አብዮት ወቅት Maximilien Robespierre በclub of the Feuillants አባልነቱ በ1791 ዓ.ም. ከአብዮተኛነት ወደ አሸባሪነት ተሸጋግሮ የተጫወተውን የአጥፊነትና የአሽባሪነት ሚና ከዚህ ሰው ባህሪና ሥራ ጋር ተመሳስሎብኛል – በባህሪም በታሪክ ክብደቱ ሮብስፒየርና ሁለቱ ግለሰቦች የቀንና የሌሊት ያህል ልይነቶች ያሏቸው ቢሆንም! የሮብስፒየር ለውጡ የሎጂክ – እንደዛሬው ሁሉ – አብዮቱን ለማፋጠንና ለመጠበቅ በሚል ሽፋን የተጫወተውን ሚና ስለሆነ በመጠኑ ያ ያቀራርባቸው ይሆናል።

ብዙ አርቆ ማየት ለሚሳነው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ወራቤ ሄዶ የፈጸመው፥ በመካከለኛው ምሥራቅ በቤት ሠራተኝነት በሚገኙት ሴት እህቶቻችን ላይ ያጎረፈው፣ ተቃዋሚዎች ፓርቲዎችና ዲያስፖራው ላይ በየጊዜው ያዘነበባቸው ተራ ስድቦች – ከብዙዎቹ ጥቂቱ ቢሆኑም፡ ማንነቱን በሚገባ አሳይተዋል። የሃገራችን ፖለቲካና ኤኮኖሚ ለጥቂቶች ምቹ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ፣ ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ የበቂ አመራር ዕጦቷ ከምንጊዜውም በላይ ገሃድ እየሆነ የኤኮኖሚውናም እግር መለጎም ጀምሯል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት (sustainable development) ለማግኘት ሁኔታው ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ሊታሰብ ይገባል።
 

II. IMF በቅርቡ የሠነዘራቸው አስተያየቶች/ነቀፌታዎች የበጀቱ የወደፊት ዕጣ ምን እንደሚመስል ክፊል አመላካች ነው

በAndrea Richter Hume የተመራው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ልዑካን ቡድን (IMF) ከሰኔ 3-17፥ 2015 በኢትዮጵያ ባደረገው አስገዳጅ የሥራ ጉብኝት (Article IV Consultation) ገና ከንጋቱ ለተሳካ የበጀት ታርጌት፣ ኤኮኖሚያው ፖሊሲና የሃገሪቱ ዕድገት በአጠቃላይ ያልተሟሉ ሁኔታዎች እንዳሉበት ጠቁሟል።

ከነዚህም መካከል የዘንድሮው ዕድገት በመንግሥታዊ ድርጅቶች ታግዞ የውጭ መዋዕለ ንዋይ እንዲመጣ በመጠኑ ቢረዳም፣ የውጭ ገንዘብ ክምችቱ (Reserve) አነስተኛ – አምስት ሣምንት በአሁኑ ወቅት – በመሆኑ ችግሩ ቀላል እንደማይሆን በመጠቆም፥ እንደውም በጀቱ በገንዘብ ሚኒስትር የተሰላበትን ስልት አንድ በአንድ አፍርሶታል። በነገራችን ላይ፡ ይህ Reserve የሚያስፈልገው ሃገሪቱ ላይ አንድ አደጋ ቢደርስባት፡ ቤንዚን ቢያልቅባት፥ ወይንም መድሃኒት በአሰቸኳይ ቢያስፈልግ ወዘተ የሚለው – ከውጭ ንግድ አንጻር እውነታ ቢኖረውም – የተለምዶ አነጋገር ነው። የReserve ቀዳሚ ጥቅሙ/አገልግሎቱ፡ የሃገሪቱን ገንዘብ መድከምና በውጭው ገበያ ዐይን ከሚደርስበት የመናቅና የመገፋት መከላከያ (market confidence in the national currency) ነው።

በአጠቃላይ፡ የIMF የመልዕክተኞች ቡድን ያቀረባቸው ትችቶች (የኤኮኖሚ ፖሊሲው በሚያሳየው ድክመት – ሁሉን አቀፍ በተለይም የግል ሴክተሩን ተዋናይ አለማድረጉ) እንዴት የ2008 በጀትን እንደሚጎዱት ለመገንዘብ የሚከተሉትን ምሣሌዎች እንመልከት፡፦

  (ሀ) የሃገሪቱ ኤኮኖሚ ዕድገት በያዘነው 2014/2015 በጅት ዓመት ከ8.7 ከመቶ ዕልፍ አይልም የሚል ስሌታቸውን ሠጥተዋል

  (ለ) በ2015/16 ማለትም አዲሱ በጀት በተጠየቀለትና የሕወሃት አስተዳደር አንዱ 11.2 ከመቶ ዕድገት ስሌቱ ምኞት ብቻ እንደሆነና እንዲያውም በዚያን ዓመት ዕድገቱ ከ8 በመቶ እንደማይዘል አዲስ አበባ በተካሄደው ውይይት ወቅት ይፋ አድርገዋል።

በተጨማሪም፡ የዋጋ ግሽበት አሁን ባለበት ይቆያል ለማለት አዳጋች መሆኑን በመገመት፡ በአስተዳደሩ በኩል የገንዘብ ፖሊሲው ጠንቃቃ እንዲሆን የልዑካን ቡድኑ ምክክሩን ለግሷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሃገሪቱ ዕዳ ጫና ($30 ቢሊዮን) ሰለሚባባስ፡ መንግሥታዊ ድርጅቶች ገንዘብን በመዋዕለ ንዋይ ስም ከመርጨት ተቆጥበው፡ የግል የመዋዕለ ንዋይ በመንግሥትና በግል ሴከተሩ ሽርክና ቢደረግ፡ መንግሥት በመንግሥትነቱ በታክስ ሊሰበስብ የሚችለውን ብቻ ቢጠቃም ለኤኮኖሚ ዕድገቱ ፋይዳ እንዳለው አስተያየታቸውን ሠንዝረዋል።

ለኢትዮጵያ ዘለቄታ ግን፣ ሥር ነቀል መዋቅራዊ ሕዳሴ የውጭ ንግዷን በማሻሻል ረገድ እጅግ እንዳሚረዳት የድርጅቱ የልዑካን ቡድን መክሯል። ከላይ እንደሚታየው፥ ለበጀቱ የሚፈለገውን ገንዘብ ከሃገር ውስጥ በሚገባ ለማሰባሰብ መቻሉ አጠራጣሪ የሚያደርጉ ምልክቶች እየታዩ ነው – 30 በመቶ የሚሆነውን የውጭው ብድርና ዕርዳታ የሚሸፍነውን በቀላሉና በወቅቱ ማግኘቱ ይቅርና።

ይህ ሁሉ ሲባል፡ የሕወሃት አስተዳደር የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎችንና ድርጅቱን በጠላትነንት ዐይን ሲመለከት ኖሮአል። አሁን ደግሞ ሚዛናዊነት በጎደለው አሰተሳሰብ ሰሞኑን የሚናገሩትና የሚያሰሙት ክስ፡ ከድርጅቱ ጋር በሚወያዩበት ወቅት ሃሣባቸው እየተበታተነ ማዳመጥና መገንዘብ የተሳናቸው አስመስሏቸዋል።

አጠቃላይ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ ስሌቶች የገንዘብ ድርጁቱ ሰዎች ለምን እንደሚቸገሩ ከብዙ ውጣ ውረድ በሁላ በራሱ በArticle IV Consultation ማዕቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያን ቁጥሮች መቀበል እንዳቃታቸው – ሃሣቡ አዲስ ባይሆንም – ገላጭ የሆነ በኤኮኖሚክስ ዕውቀትና የሃገሮች ልምድ ላይ የተመሠረተ አንድ ገጽ ጽሁፍ በጥቅምት ወር በ2012 አቅርበው ነበር። ያ ጽሁፍና ዳታ እስከ ዛሬ ተመራማሪዎች በምሣሌነት ይጠቅሱታል።

አንድ ሠነድ ውስጥ እንደ ንዑስ ምዕራፍ ሆኖ Ethiopia: Growth Accounting ብለው አሥፍረውታል። እዚያም ውስጥ የሠፈሩት ሃሣቦች የሚከተለውን ዕድገትን የሚወስኑትን ሁኔታዎች (ገንዘብ/መዋዕለ ንዋይ፡ የሰው ኃይልና ቴኮኖሎጂ ቅንጅት) ወይንም ኢኮኖሚስቶች Total Factor Productivity (TFP) ለኢትዮጵያ ዕድገት ሁኔታ ተርጉመው አቅርበወት አእምሮአቸውን ከቁጥሩ ውዝግብ ነጻ ለማድረግ እየሞከሩ ናቸው።

ከድርጅቱ ጋር ተከራከሮ የተለየ ሃሣብ ያለው ወገን ለመርታት ወይንም መግባባት ለመፍጠር ከሞመከር ይልቅ፣ እነርሱ ስህተተኛና የጠላት ሥራ እየሠሩ ናቸው የሚለው አስተሳሰብ ድንቁርናን ብቻ ነው የሚያስተጋባው። ስለሆነም አሁን እየተደረገ ያለው፡ ባለሥልጣኖች ሆነልን የሚሉት በአንድ በኩል ሆኖ፣ በሌላ በኩል ደግሞ፡ Labour+capital+technology መስተጋብር በኢትዮጵያ ላይ ተመሣሣይ ውጤት ሊያሳይ አልቻለም – ከሌሎቹም ሃገሮች ልምድ ጋርም ተገናዝቦ – የሕወሃት ቁጥር በሜካኒዝሙ ሊደገፍ አልቻለም፡ የሚከተለው እንደሚገልጸው፦

  “The official statistics registers remarkable economic growth in Ethiopia in the last 8 years. The real GDP growth has remained above 10 percent since 2003/04 when the Ethiopian economy recovered from a severe drought in 2002/03.

  A growth accounting applied to Ethiopian data reveals two underlying features (Table below). First, large part of the growth was driven by large capital investment in the public sector. Capital stock grew, on average, by 10.8 percent, which by far exceeds capital growth rates for sub-Saharan Africa in the 1980s (2.0 percent) and even East Asian countries in the 1980s (8.9 percent) where the growth was highly capital intensive.

  Second, the official statistics implies long-lasting rapid productivity growth between 2006/07 and 2010/11, the average contributions to the growth are estimated at 2.6 percent from the labor and 3.2 percent from the capital, implying total factor productivity (TFP) growth of 5.2 percent. The estimated TFP growth is high both by the Ethiopian historical standard and the cross-country comparison.

  For Ethiopia, existing literature finds TFP growth between 0 to 1.4 percent until the early 2000s. For other countries, studies find TFP growth of 1.6 percent for OECD countries, 0.5–1.6 percent in East Asia and 1.4–4.6 percent in China in 1984–94. Several factors that normally support high TFP were absent in Ethiopia. These factors include: initial human and physical capital conditions, terms of trade and openness, good macroeconomic environment, such as low inflation, competitive real exchange rate, low government consumption, high international reserve coverage, and low external debt.

  High implied TFP productivity growth in Ethiopia seems therefore implausible, suggesting an existence of problems in the official growth estimates. Possible issues include remaining weaknesses in national accounts compilation methodologies and the accuracy of the source data.

  With moderate TFP growth, reflecting the factors that are less supportive for Ethiopia, moderate real GDP growth would be expected over the medium term.”

ምናልባት የኢትዮጵያ ሕዝብም የሕወሃትን ቁጥሮችና የሕዝብ መገናኛ መሣሪያዎቹን ሁልጊዜ እንዲጠራጠር ያደረገው በራሱ የራሱን TFP ግምገማ አካሂዶ ሊሆን ይችላል እንበልና እንለፈው!
 

  ይቀጥላል…

%d bloggers like this: