የገቢዎች ባለሥልጣን ለግብር ገቢ መቀነስ አስመጪዎችንና አከፋፋዮችን ወቀሰ አሉ – ገንዘብ ከሃገር የሚያሸሹት ላኪና አስመጭነትነቱን የያዙት የሕወሃት ሰዎች ሆነው ሳለ ባለሥልጣኑ ለምን በኮድ መንሾኳሸክ ፈለገ?

26 Jul

የአዘጋጁ መልዕክት

  የኢትዮጵያን ሕዝብ በገሃድ ከሚግጡት መካከል ግንባር ቀደሞቹ የሕወሃት ሰዎች መሆናቸውን እኩዩ መለስ ዜናዊ ለይቶ እያወቀ፡ የመንግሥት ሌቦችና በንግዱ ዓለም ውስጥ የተሰገሰጉት እያለ በሕዝቡ ላይ ሲያሾፍ መኖሩ ይታወሳል፡፡ እርሱም ‘የኛ’ ያላቸውንም ሆነ የሌሎቹን ሌቦች’እጅ ሳይቆርጥ’ – በመሬት መዘረፍ ምክንያት ስለማዘኑ በፓርላማ የአዞ እንባ እንዳለቀስ – የራሱ ሰዎች መሬት ዘርፈው እሲኪያገሱ ጠብቆ በክብር ቢሸኝም፣ ሰውና ወኔ በጠፋበት ዘመን አሁንም ስድስት ክንድ ከመሬት በታች ሆኖ ኢትዮጵያን ያስተዳድራል።

  ዛሬ እነደነ ዶ/ር ደበረጽዮን ገብረሚካኤልና አባይ ጸሐዬም ያንን ሚና በዋና ተዋናይነት ሲጫወቱ ማየት የዚህች ሃገር አበሳ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑነ ያመለክታል።

  የታክስ ጉዳይ ከተነሳ ዘንዳ፡ ረዳት ፕሮፌሰር ፍቃዱ ጴጥሮስ በቅርቡ አዲስ አበባ በተካሄደ ሲምፖዚየም የዓለም ባንክን መረጃ ጠቅስው እንዳመለከቱት፡ ኢትዮጵያ 13 ከመቶ ዓመታዊ ምርት በግብር መልክ በዓለም ዝቅተኛ የሆነውን ብትሰበስብም፡ ከዚሁ ውስጥ ሰባት በመቶው ወደ መንግሥት ካዝና ሲገባ፡ ቀሪው ስድስት በመቶ ደግሞ ታክስ ለማስከፈል የሚወጣውን ወጪ ይሸፍናል ብለዋል። በሌላ አነጋገር፣ ዜጎች ከሚያውቁት ውጭ፡ የሕወሃት አስተዳደር – የከሠረ የምርትና የንግድ ልውውጥ እያካሄደ ሃገር ሊመራበት ከሚገባው ውጭ በባዕዳን ምጸወታ የሚኖር ጨካኝ፡ ከሃዲና የሃገርን ዳር ድንበርና የዜጎችን ልዕልና የሚቸበችብ ጉልበተኛ ወንበዴ ነው።

  ከላይ ከተነሳው ጋር በተዛመደ፡ የሕወሃት አስተዳደር ተመጽዋችነት ከሚያረጋግጡት መካከል፥ ሰሞኑን በኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ዙሪያ በአሜሪካን ኮንግሬስ በኢትዮጵያ ያለውን የተበላሸ የስብዓዊ መብቶች አከባበር ሁኔታን አስመልተው፣ የሕዝብ ተወካይ (ካሊፎርኒያ) ኮንግሬስማን ማይክ ሆንዳ በምክር ቤቱ ውስጥ ንግግር አድርገው ነበር።

  እርሳቸውም፡ ኢትዮጵያ በራሷ ሃብት ራሷን ለማልማት ዕድሉ ቢኖራትም፡ እስከዛሬ በምጽዋት የኖረች ሃገር ናት ብለዋል። በጠቀሷቸው ቁጥሮች እንደተመለከተውም፡ በጥቁር አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የአሜሪካን ዕርዳታ ተቀባይ፣ በዓለም ደረጃ ሰባተኛው መሆኗን አስታውሰዋል። ከሌሎች ዕርዳታ ለጋሽ ሃገሮች እንዲሁ፡ ኢትዮጵያ በመንግሥታዊ የውጭ ዕርዳታ (Official Development Assistance – ODA) ተቀባይነት ግንባር ቀደም መሆኗን ጠቅሰዋል። እነዚህን ችግሮችም ስለ $11.4 ቢሊዮን የ2008 የኢትዮጵያ በጀት – እስላሁን ባለሶስት ክፍል ጽሁፍ ነካክቸዋለሁ – ክፍል አንድክፍል ሁለትክፍል ሶስት

  ረዳት ፕሮፌሰር ፍቃዱ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን የግብር አጣጣልና አሰባሰብ እንደ አንድ ከፍተኛ የተወሳሰበ ችግር አድርገው ይመለከቱታል። በአንድ በኩል ግብር ለማስከፈል የሚወጣው ወጪና ያሰከተለው ችግር ከባድ ነው። ከገንዘብ አንፃር ወጪው ብዙ መሆኑ፣ በጣም ለትንንሽ ጉዳዮች የወንጀል ተጠያቂነት መኖሩን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ደግሞ ዜጐች ወደ ንግድ ሥራ ውስጥ እንዳይገቡ እያደረጉ መሆኑንና የገቡትም ሕጋዊ በሆነ መንገድ ከመሥራት ይልቅ ግብር ወደ ማይከፈልበት ሕገ ወጥ ሥርዓት ውስጥ እንዲገቡ የሚገፋፋ በመሆኑ፣ መንግሥት መሰብሰብ የነበረበትን ገቢ እያሳጣው እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡

  የሕወሃት አስተዳደር ይኼ ጠፍቶት የሚመክረው አጥቶ ይሆን ከሚለው ይልቅ፣ ባለሥልጣኖቹ የጥቅም ሽሚያ፡ ሃብት የማካበት እሩጫና ሥልጣን ብልግናና ዘረፋው ላይ አተኩረው ነው የሚለው የሚሉት ጠንካራ ናቸውየሚሉት ጠንካራ ናቸው

  በዚህም ምክንያት ነው፡ የሚድሮኩ ዶ/ር አረጋ ይርዳው የመንግሥት ሌቦችን አታውቁ እንደሆን ሚድሮክ ይንገራችሁ የሚል ዘይቤ እስኪመስል ድረስ፡ ደብረጽዮን በተቀመጠበት፡ በዚህ ረገድ ሌቦቹን ከመንግሥትም ሆነ ከያሉበትን የመመንጠሩን ሥራ ይልቅ በደንብ እንዲሠሩ ጠይቀዋል። በአሠራር ደረጃ ጉቦን “ሰፕለመንተሪ ሳላሪ” እየተባለ እንደሚጠራም በማስታወስ ሁኔታውን ገልጸውላቸዋል።

  በሚድሮክና ሕወሃት መካከል ያለውን ጋብቻ ስናስታውስ፣ ምናልባትም የሚድሮክ አካሄድ ትኩረቱ የንግዱን ማኅበረሰበ ለቀቅ አድርጎ፡ የመንግሥት ሌቦች (ሕወሃትን ለቀቅ አድርጎ ተራው የማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ላይ) እንዲያርፍና በፖለቲካና በብሄረሰብ የተደራጀው ቡድንና አጋሮቹ ፋታ እንዲያገኙ ለማድረግ የታሰበ ሴራ ይሆን?


 
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የኢትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ሐሙስ ሐምሌ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ለመሸለም በጠራው ስብሰባ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ በ2007 በጀት ዓመት ለታየው ከዕቅድ በታች የግብር አሰባሰብ በመርካቶ የሚሠሩ አስመጪዎችንና አከፋፋዮችን ወቀሰ፡፡

“የመርካቶ ሕገወጥነት ትርምስ አላበቃም፤›› ያሉት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ፣ ባለፈው በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ገቢ አፈጻጸም አጥጋቢ አልነበረም በማለት፣ ለገቢው ማነስ የመርካቶ አስመጪዎችን፣ አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ በ2007 ዓ.ም. ከመርካቶ ይሰበሰባል ተብሎ የነበረው የታክስ መጠን 22 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፣ ከዚህ ውስጥ መሰብሰብ የተቻለው ግን 17 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር፡፡ በመሆኑም “አዲስ አበባን ለመደጎም አልቻልንም፤” ብለዋል፡፡ ‹‹የአከፋፋዮች ትልቅ እጅ ስላለበትና የችግሩ ምንጭም ስለሆኑ ያለደረሰኝ ለከተማውና ለክልሎች የሚያከፋፍሉት ተደርሶባቸዋል፤›› ካሉ በኋላ በዚህ ዓመት ትኩረት እንደሚደረግባቸው አስጠንቅቀዋል፡፡

በ2008 ዓ.ም. 142 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለጹት አቶ በከር፣ ከዚህ ውስጥ 60 ቢሊዮን ብር ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በአገሪቱ ካለው ግብር ከፋይ ውስጥ አምስት በመቶውን የሚሸፍኑት ከፍተኛ ግብር ከፋዮች 70 በመቶውን የታክስ ገቢ እንደሚያመነጩ ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡ በአንፃሩ የፌደራል የታክስ አሰባሰብ አጥጋቢ ነበር ያሉት አቶ በከር፣ 116 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 117 ቢሊዮን ብር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ በከር ማብራሪያ፣ በአገሪቱ የታክስ ማጭበርበርና ሙስና ምንጮች ከሆኑት መካከል ኮንትሮባንድ፣ የታክስ ኦዲት፣ የዋጋ ትመና፣ ያለደረሰኝ መሸጥ እንዲሁም አድበስብሶ ታክስ መክፈል በግብር ከፋዩና በአስከፋዩ መካከል ትልቅ ክፍተቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ከወትሮው የተለሳለሰ የግብር ከፋዮች ስሞታ በተስተናገደበት መድረክ፣ ሆን ብለው የሒሳብ አሠራሮችን በማጭበርበር ከታክስ ባለሥልጣኑ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ማጭበርበር እንዳለ በማስመሰል የሚሠሩ ባለሙያዎችን ባለሥልጣኑ እንዲከታተል የጠየቁት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አረጋ ይርዳው፣ በባለሥልኑና በማዘጋጃ ቤት አካባቢ በሚያጋጥም ቢሮክራሲ ሳቢያ ጉቦኝነት መስፋፋቱን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም “ጉቦን ሰፕሊመንታሪ ሳላሪ ብለን መጥራት ጀምረናል፤” በማለት ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች የሚከፈለውን ጉቦ ‹ደመወዝ ደጓሚ› እየተባለ እስከመጥራት መደረሱን ገልጸዋል፡፡ “ፋሲሊቴቲንግ ፊ” ወይም “የማስፈጸሚያ ክፍያ” እየተባለ እንደሚጠራ የገለጹ ነጋዴዎችም በስብሰባው ተገኝተዋል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ሒሳብ እስከ ስድስት ዓመታት ለድርጅቶች ሳይመለስ መቆየቱን የተቹት ዶ/ር አረጋ፣ መንግሥት መመለስ ያለበትን እንዲመልስ ጠይቀዋል፡፡ በኮንትሮባንድ እየደረሰ ያለው ኪሳራ አሥር ቢሊዮን ብር እንደሚገመት የገለጹት ነጋዴዎች፣ መንግሥት መፍትሔ ካልሰጠው ህልውናቸው እንደሚያከትምለት አሳስበዋል፡፡ ከቀረጥ ነፃ በገቡ ተሽከርካሪዎች፣ በትርፍ ድርሻ አከፋፈል (ዴቪደንድ)፣ በዊዝሆልዲንግ ታክስ፣ በጉምሩክ ዋጋ ትመናና በመሳሰሉት ላይ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሙስና ወንጀል ተጠርጠረው ወደ እስር ቤት ከተላኩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኋላ ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የዕውቅና ሽልማት በተሰጠበት ሥነ ሥርዓት ላይ 48 ኩባንያዎች የዋንጫና የምስክር ወረቀት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል እጅ ተቀብለዋል፡፡

ከእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ሰባቱን የሚድሮክ ግሩፕ እህት ኩባንያዎችና አጋሮቹ ሽልማቱን አግኝተዋል፡፡
 
/ሪፖርተር
 

%d bloggers like this: