የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ የአቶ ብርሃኔ ግደይን ባለመንትያ ሕንጻ ዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተርን መርቀው ከፈቱ

17 Aug

 ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር ሲመረቅ - ሚኒስትሩ፡ የዮቤክ ባለቢት አቶ ብርሃኔ ግደይና ቤተስቦቻቸው (ፎቶ ሪፖርተር)

ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር ሲመረቅ – ሚኒስትሩ፡ የዮቤክ ባለቢት አቶ ብርሃኔ ግደይና ቤተስቦቻቸው – በ2400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባው የዩቤክ ኮሜርሻል ሴንተር መንታ ሕንፃዎች ያሉት ሲሆን፣ አንደኛው 14፣ ሁለተኛው ሕንፃ ደግሞ አሥር ወለሎች አሉት – እሪ በይ ሃገሬ በቁምሽ የተጋጥሽው!(ፎቶ ሪፖርተር)


 
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አቶ ብርሃኔ ግደይ ማናቸው? ታምረኛው የሕወሃት አብዮት በተለይ በፈጠረላቸው ዕድል ተጠቅመውና ከያዟት አርባ የኢትዮጵያ ብር ካፒታል ተነሰተው ነው እዚህ የዛሬው የሃብት ጣራ ላይ የደረሱት። ሪፖርተር ስለአነሳሳቸው ሲጽፍ እንዲህ ይላል።

ዮቤክ ኩባንያ አሁን ያለበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት አቶ ብርሃኔ “በ40 ብር ባልሞላ ካፒታል” ሥራ መጀመራቸውን ከዚያም ወደ ታክሲ ሥራ በመግባት ቀስ በቀስ እያደጉ መምጣታቸውና አሁን ያለበት ደረጃ መድረሳቸውን ኩባንያውንና የእሳቸውን የንግድ ጉዞ የሚያመላክተውና በምረቃ ሥርዓቱ ላይ የተሠራጨው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስለዚሁ ሕንጻ ሪፖርተር የሚከተለውን ነሐሴ 5/2015 ዘግቦ ነበር፦

ያልተለመደ ነው የተባለው የንግድ ማዕከሉ አገልግሎት የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያዎች ዋነኛ መገበያያ እንዲሆኑ ታስበው መደብሮቹ መሠራታቸው ተገልጿል፡፡ ከ200 በላይ የሚሆኑት መደብሮች ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያ መሸጫ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ፣ ቀሪዎቹም ከ180 በላይ የሚሆኑ ቢሮዎችም ከመደብሮቹ ሥራዎች ጋር የተያያዙ አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ኮሜርሻል ሴንተሩ በዋናነት የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያዎች መገበያያነት እንዲውል ቢደረግም፣ ለፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት፣ ለሬስቶራንትና ተያያዥ ሥራዎች የዋሉ ክፍሎችም አሉት፡፡ እንደ አቶ ብርሃኔ ገለጻ የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያዎችን በተደራጀና በተሰባሰበ ሁኔታ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡ በዘርፉ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩና ተጠቃሚ ደንበኞች የሚፈልጉትን ዕቃ ለማግኘት ከፍተኛ ችግር እየገጠማቸው ሲጉላሉ ነበርም ብለዋል፡፡

ዮቤክ ይህንን ችግር በማየት የገነባውን ሕንፃ የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያዎች ዋነኛ መገበያያ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ በመቻሉ፣ ተመሳሳይ ምርቶችን በአንድ አካባቢ መገበያየት ዕድል መፈጠሩንና እንዲህ ዓይነቱን አሠራርም ከሌሎች አገሮች ልምድ በመቅሰም ጭምር የተተገበረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የዮቤክ ኮሜርሻል ባለቤት በኤሌክትሪክና በሕንፃ መሣሪያዎች ሥራ ውስጥ በርካታ ዓመታትን አሳልፈዋል፡፡ በተለይ በ1991 ዓ.ም. በ500 ሺሕ ብር ካፒታል የተቋቋመው ኩባንያቸው ከኮንስትራክሽንና የቤቶች ልማት መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚያስፈልገውን የግብዓት ፍላጎት ከግምት በማስገባት በዋናነት የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያዎች በማቅረብ ሥራ ላይ ቆይቷል፡፡

በዚህ ሥራ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ይዞ የተጓዘና አሁንም በዚሁ ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን፣ እንደ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ያሉ ምርቶችን በአገር ውስጥ የሚያመርት ፋብሪካም አቋቁመዋል፡፡ ብክሮሜ የፒፒ ከረጢትና ፕላስቲክ ማምረቻ የሚል ስያሜ ያለው ይህ ፋብሪካ፣ በ1996 ዓ.ም. ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን ለተለያዩ ምርቶች መገልገያ ማዳበሪያ፣ የውኃ ፓምፕ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ኬብሎችና የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ያመርታል፡፡ ይህን ፋብሪካ ለማስፋፋት ውጥን እንዳላቸው አቶ ብርሃኔ ገልጸዋል፡፡ ለኮሜርሻል ሴንተሩም የሚሆን የፓርኪንግ ቦታ የሚፈልጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሕንፃው የተወሰኑ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ሥፍራ ያለው ቢሆንም፣ በሕንፃው ከሚገለገሉ ደንበኞችና ተከራዮች ብዛት አንፃር ተጨማሪ የተሽከርካሪ ማቆያ ሥፍራ የሚያስፈልገው በመሆኑ፣ ለዚሁ የሚሆን ቦታ ማግኘት የሚችሉበት መንገድ ይመቻችላቸው ዘንድ ጠይቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዮቤክ በአሁኑ ወቅት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ ባለኮከብ ሆቴል በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
****
 
በነገራችን ላይ፡ የሕወሃት አባላት ከ1997 ጀምሮ የዘረፉትን ሕጋዊ ለማድረግ በፖለቲካ ድርጅትነቱና የሕወሃት ሚዲያ ቈንጮነቱ የተዘረፈውን መሬት ሕጋዊ ለማሰረግ ዘመቻውን ከፊት ሲመራ የነበረው ፋና ብሮድካስት አንድ ስበብሰባ በራሱ ቢሮ ውስጥ አካሂዶ ነበር። ስለዚሁም በራሱ አምድርና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተዘገበው ዜና እንደሚከተለው ያጋልጣቸዋል፦
 

በፋና ጽሕፈት ቤት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ ብሩክ ከበደ የፋና ምክትል ዲሬክተር ጄነራል “በሃገሪቱ የተጀመረው ህጋዊ የካዳስተር ሥርዓት ምዝገባ ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ የመገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል” በማለት አደራቸውን አስተላልፈዋል (ፎቶ ኢዜአ)


 
የመሬት ካድስተር ምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው

አዲስ አበባ ሚያዚያ 20/2007 ዘመናዊ የመሬት ካድስተር ምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉ ዘላቂና የዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረትና መረጃ ኤጀንሲ ገለጸ።

ኤጄንሲው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ”የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና ዋስትና ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ፋይዳዎች ” በሚል ርዕስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ውይይት አካሂዷል።

የኤጀንሲው ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የካዳስተር ሥርዓቱ የመሬት ይዞታ መብት ምዝገባ፣ የቋሚ ንብረት ግመታ፣ የመሬት አጠቃቀምና መሬት ልማትን የሚያካትት ነው።

የካዳስተር ሥርዓቱ ውጤታማ የሆነ የመሬትና መሬት ነክ ግብይት በመፍጠር፣ የዋስትና አሰራርን በማመቻቸት፣ ለከተሞች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ዕድገት አስተዋጸኦ ከማበርከቱ ባለፈ ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የመሬት ካድስተር ምዝገባ ሥርዓት በአዲስ አበባ ባለፈው ታኅሳስ የተጀመረ ሲሆን በቅርቡም በ23 የአገሪቱ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል።

ምዝገባው የአገሪቱ የከተሞች የመሬት አስተዳደር ሂደቱ የተሳለጠና ውጤታማ በማድረግ ረገድ ድርሻው የላቀ መሆኑን ነው መረጃው የሚተነትነው።

የመሬት አስተዳደር ሥርዓቱ ደረጃውን በጠበቀ ካርታ የተደገፈ ከተማ አቀፍ መረጃ ለማደራጀትና በከተሞች ውስጥ ስለተያዘው መሬት የተሟላ ማብራሪያ ሚሰጥ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

ይህም በአገሪቱ ያሉት ከተሞች የመሬት አስተዳደር ሂደትና አሰራሩ ቀልጣፋና የተሳለጠ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

“በክልሎችም ተቋም የማደራጀትና ህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ነው” ያሉት ዳይሬክተሩ ነባራዊ ሁኔታ በማጥናት የክልል ምክር ቤቶች እንዲያጸድቁት በመጠባበቅ ላይ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ከ”ኢንሳ” ጋር በመተባበር ለዚህ ማዕቀፍ ሱፐርቪዥን የሚሰራ አለም አቀፍ ”አይጂኤን” የተባለው አማካሪ ድርጅት በመቅጠር አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመሬት ምዝገባ ስርዓት ለመዘርጋት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

የከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አማካሪ አቶ ይትባረክ መንግስቴ በበኩላቸው ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚቀርፍ ነው።

ለህዝቡ የሚሰጠውን የካዳስተር አገልግሎት ከጊዜ፣ ከወጪ፣ ከጥራትና ከአገልግሎት ተደራሽነት አንፃር የተሟላ ለማድረግ ድርሻው የላቀ እንደሆነም በመጥቀስ።

የካዳስተር ሥርዓቱ በተደጋጋሚ ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዘው የሚነሱ የአገልግሎት ግድፈቶችን እንደሚያስቀርም ነው ብለዋል።

የፋና ብሮድካስትንግ ኮርፖሬት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ከበደ እንዳሉት በአገሪቱ የተጀመረው ህጋዊ የካዳስተር ሥርዓት ምዝገባ ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ የመገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

አገር አቀፍ የመሬት አስተዳደር አዋጅ በ2006 ዓ.ም የካቲት ወር ላይ ወጥቶ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ይታወቃል።
****
 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥና ዙሪያዋ 93 ሺህ ለሚሆኑ የመሬት ባለይዞታዎች ማረጋገጫ ሰጥቷል

አሁን ሰሞኑን እንደተነገረው ከሆነ በግማሽ ዓመት ብቻ መሬት የዘረፉት የሕወሃት ካድሬዎች ተሳክቶላቸው፡ በአርከበ እቁባይ፡ ዶ/ር የገንዘብ ሚኒስቴር ምክትል ምኒስትር አብርሃም ተከሰተና ወዘተ ተዘርፎ ለሕወሃት ካድሬዎች፡ ጋዜጠኞች፡ ሚኒስትሮች፡ የጦር አዛዦች የተከፋፈለው መሬት ዛሬ ሕጋዊ ይዞታቸው እየተደረገ ነው። አንዳንዶቹማ – በተለይም ወታደሮቹ – የባንክ ብድር በነጻ ተሰጥቷቸው በድንጋይ ላይ ድንጋይ ክበው፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፖለቲካና የኤኮኖሚ የበላይነት ዓላማቸውን ከጥርጥር ውጭ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው!
 

በመዲናዋና ዙሪያዋ 93 ሺህ ለሚሆኑ የመሬት ባለይዞታዎች ማረጋገጫ ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት 93 ሺህ ለሚሆኑ የመሬት ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰጥቻለሁ አለ የአዲስ አበባ የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋ ወሰን ደሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የይዞታ ማረጋገጫ ከተሰጣቸው ይዞታዎች ውስጥ

10 ሺህ የሚሆኑት በተለያየ ቦታ የሚገኙና በባለይዞታዎች ጥያቄ የተከናወኑ ሲሆን፥ 83 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ለቤት በመሄድ የተከናወኑ ናቸው።

ቤት ለቤት በመሄድ የይዞታ ማረጋገጫ ለመስጠት ሲጣራም 47ቱ በህገ ወጥ ወረራ የተያዙ ሲሆኑ፥ ሶስቱ ደግሞ በጸረ ሙስና የታገዱ ሆነው መገኘታቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የይዞታ ማረጋገጫ ጥያቄ ከቀረበባቸው አጠቃላይ የመሬት ይዞታዎች ውስጥም 29 በመቶ የሚሆኑት ከህጋዊ ይዞታቸው በላይ የሆነ የመሬት መጠን ይዘው የተገኙ ሲሆን፥ በአንጻሩ 23 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከህጋዊ ይዞታቸው ያነሰ ወሰን ይዘው ተገኝተዋል።

በአራት ክፍለ ከተሞች ውስጥ የመረጃ ቋት ግንባታ መጠናቀቁንም ነው አቶ ግፋ ወሰን የገለጹት።

በአንዳንድ ባለይዞታዎች በኩል በወቅቱ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄ አለመቅረብና በቦታው በመገኘት ያለማስለካት ችግር ስራውን ከዚህ በላይ እንዳይፋጠን ማድረጉንም ተናግረዋል።

በሚቀጥለው አመት ለ80 ሺህ የመሬት ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመስጠት ታቅዷል።

በአጠቃላይ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ለ400 ሺህ የመሬት ይዞታዎችና ለ200 ሺህ መንገዶችም የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ለመስጠት በእቅድ ተይዟል።
 

ተዛማጅ ጽሁፍ:

  የሽፍታ/ወንበዴ መንግሥት በኢትዮጵያ

  የኢትዮጵያ ሙስና ስፋትና ጥልቀት አሁን ገና ሥዕሉ በትንሹ መታየት ጀመረ! ግን ማነው ያልተነካካው?

  Is the TPLF leading Ethiopia or still obsessed by its political longevity & consolidation of its domination?

  ‘የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቂ እንጂ ተጠቃሚ አይደለም’– ዳዊት ገ/እግዚአብሔር: የሕወሃት ሰዎች የራሳቸው የሆነውን አሁን ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሲጠሉት፣ ቀድሞውን ያልፈለጉትን ዘረኛውን ድርጅት ኢትዮጵያውያን በምን ሂሣብ ይገብሩለት?

  በምርጫ ማግሥት: ሕገወጥ መሬት ባለይዞታዎች ሕጋዊ ካርታ ተሰጣቸው – የሕወሃት ሰዎች ከ97 ጀምሮ በሕገ ወጥነት፥ ተንኮልና ነጠቃ የያዟቸውን እንደሚጨምር ታውቋል፤ እሪ በይ ኢትዮጵያ!

 

%d bloggers like this: