መሠረቱ የተናጋው የኢትዮጵያ 2015/2016 ፌዴራል በጀት (ክፍል 4)

18 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

በዚህ ርዕስ ሥር አቀርበዋለሁ ብዬ ቃል የገባሁትን ጽሁፍ – ማለትም ስለ ኢትዮጵያ የ2015/16 ፊዴራል በጀት (ክፍል አራት) – ላለማቅረብ በመወስኔ፣ ላቀርብ ያስብኩትን አምስት ገጽ+ ጽሁፍ በመጠኑም ቢሆን በተሻለ መንገድ ከዚህ በታች የተቀመጠው ግራፊክ ጠቅላላ ሃሣብ ያቀርባል ብዬ አምናለሁ።

በአሁኑ ወቅት የታቀደውን ክፍል አራት የማላቀርብበት ምክንያት፡ በጀቱ ከመዘጋጀቱ በፊት፡ የነበሩት መነሻ ሁኔታዎች (budgetary assumptions – ገጽ 15) በመለዋወጣቸው፣ በአሁኑ ሰዓት ምንም እንዳልተለወጠ አስመስዬ ያንን ማቅረብና ስለትርጉመ ቢስ በጀት አናሊሲስ ለማቅረብ መሞከር ትክክል ባለመሆኑ ነው!

ለመሆኑ፡ ምን ማለቴ ነው “የተለዋወጡ ሁኔታዎች” ስል? አንደኛ ቀደም ብዬ በተከታታይ ሁለት ክፍሎች ውስጥ (ክፍል ሁለትና ሶስት) እንደገለጽኩት፡ ጄኔራል ሣሞራ ዩኑስ ተጨማሪ የ$1.2 ቢሊዮን የበጀት ጥያቄዎቻቸውን ያቀረቡት የበጀቱ መሠረት (assumptions) ሲቀረጽ ሳይሆን፣ በጸደቀ ማግሥት በመሆኑ፣ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል!

በወቅቱም፡ ያንን የጄኔራሉን ተጨማሪ የበጀት ጥይቄ፡ “ለረዥም ጊዜ ግጭትንና ጦርነትን ሲመኝ የኖረው የሕወሃት አስተዳደር ሊያገኘው ይሆን? በኤታ ማዦሩ በኩል ‘ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ’ በአስቸኳይ መሣሪያ ግዥ ያስፈልገኛል አለ”“ለረዥም ጊዜ ግጭትንና ጦርነትን ሲመኝ የኖረው የሕወሃት አስተዳደር ሊያገኘው ይሆን? በኤታ ማዦሩ በኩል ‘ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ’ በአስቸኳይ መሣሪያ ግዥ ያስፈልገኛል አለ”በሚል ርዕስ አቅርቤው ነበር።

ሁለተኛ፡ በጀቱ እንደ ጸደቀ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀ መንበር ብርሃኑ ነጋ በረሃ ገብቶ የጦርነት ሥጋት ዐይኑን በሃገሪቱ ላይ ማፍጠጥ የጀመረበት ወቅት ሆኖአል!

ሶስተኛ፡ አሁን ደግሞ ምንም እንኳ ሕዋሃትና ቅጥረኞቹ ወደ ድርቅ መኖር ክህደት የገቡበትን ሁኔታ ለመመስከር ብንገደድም፡ ቢያንስ ቢያንስ በአሁኑ ወቅት መጠኑ የተለያየ ቢሆንም ሃገራችን ካላት ከ700 በላይ ወረዳዎች መካከል ቀዳሚ ዓለም አቀፍ አመላካቾች (Early Warning) እንደሚያሳየው፣ 348 ወረዳዎችና በውስጧ ያሉት ዜጎች፡ እንስሳትና የግለሰቦች ሕይወት የድርቅ አደጋ እያንዣበበ መህኑ በገሃድ የሚታይበት ወቅት ሆኖአል።

በአንድ በኩል፣ ከሰሞኑም በአዲስ አበባ የሕወሃት አስተዳደር ወዳጅ የሆኑት የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሓስላች ግንቦት 13/2015 በደቡብ ኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱትን አካባቢዎች ከጎበኙ በኋላ፡ ሰለድርቅ መኖርና ርሃብ በሰዎች ሕይወትም ላይ ጉዳት ማድረስ መጀመሩን እንደሚከተለው ገሃድ አድርገዋል!

  “We are seeing sharp increases in humanitarian needs this year at a time when contributions from the international community have declined…

  “[C]hildren under age five receive treatment for medical complications resulting from severe malnutrition. These children are at high risk of mortality and receive 24-hour care until their medical conditions have stabilized, usually five to seven days.

  “[M]others bring their malnourished children under age five for medical check-ups. While there, the mothers receive nutritional counseling and a ration of a specially formulated ready-to-use therapeutic food [የአሜሪካን ዕርዳታ] to feed their children until their nutritional status improves”

አምባሳደሯ ጉብኝት ባደረጉበት ዕለት፣ ሕወሃትም በበኩሉ በሁለት እግሩ በራሱ የቆመ ለማስመሰል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ጀመረ:-

– ከከብት አልፎ በደቡብ የሰው ሕይወት ጭምር አደጋ ላይ የመውደቁን ዜና አፈነ

– ‘በአፋርና የኢትዮጵያ ሶማሌ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም በቂ ክምችት መኖሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ’ በማለት ድምርና ቅነሳ ላይ ማተኮር መርጦ ነበር፣

– ይህም በተቻለ መጠን በስንት ጥገና የለጣጠፈውን ባለድርብ አሃዝ የኤኮኖሚ ዕድገት ገጽታ ለመንከባከብ የታቀደ ስንኩል ጥረት መሆኑን ገሃድ አድርጎበታል!

በመሆኑም፡ በጀቱ በጦርነት ዝግጅት ከተወጠረ፡ የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን ለሌላ አደጋ ከተጋለጠ፣ ሕወሃት እንዴት በራሱ መቆም እንደሚችል ግልጽ አላደረገም!

አራተኛ፡ በአሁኑ ሰዓት ሃገራችን በተባባሰ የዋጋ ግሽበት ውስጥ ገብታለች። በገንዘብ የበጀቱ ትንበያ መሠረትም ከ8 ከመቶ እንደማይበልጥ ሆኖ የተስላ ሳለ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የስታቲስቲክስ መረጃ መሠረት የዋጋ ግሽበቱ አሁኑኑ በሐምሌ ወር አጠቃላዩ 12 ከመቶና እንዲሁም የምግብ ዋጋ ግሽበት 14 ከመቶ ደርሷል!

ስለሆነም፣ እስከ በጀቱ መጽደቅ የነበሩት ቅድመ ሁኔታዎችና በበጀቱ ውስጥ ያሉት መሠረታዊ ምልከታዎች ተለዋውጠዋል!

አዘጋጅቼው በነበረው አምስት ገጽ ጽሁፍ ውስጥ ይነሱ የነበሩት ርዕሶች የሚከተሉት ነበሩ፡

  (ሀ) የኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች ባለፉት 15 ዓመታት

  (ለ) ዋናው ጥያቄ፡ ማነው በዚህ በጀት ተጠቃሚ የሚሆነው?

  (ሐ) የኢትዮጵያ ፌዴራል በጀት ችግሮች

  (መ) ምክር ለሕወሃት ሰዎች

  (ሰ) ራሳችን ላይ ስናተኩር

በዚህ ርዕስ ሥር አቀርበዋለሁ ብዬ ቃል የገባሁትን ጽሁፍ ላለማቅረብ በመወስኔ፣ ላቀርብ ያስብኩትን አምስት ገጽ+ ጽሁፍ የሕወሃት ድርጅቶችን ቡጥቦጣ ክዚህ በታች የተቀመጠው ግራፊክ በመጠኑም ቢሆን ያቀርበዋል ብዪ አምናለሁ።

የፌደራል በጀት
 
በተከታታይ በጀቱ በፓርላማ ከጸደቀ ጀምሮ ክፍል 1ክፍል 2ክፍል 3 መቅረባቸው ይታወሳል።
 
*Updated.
 

%d bloggers like this: