በሕወሃት ሰዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ በየቀኑ ይብጠለጠላል፣በጥላቻ ዐይን ይታያል፤ በየቀኑም ያስሩታል፣ ይገርፉታል፤ ምሥጋና ቢስ በሆነ መንገድ ይዘርፉታል፤ መለስ ዜናዊ የጀመረው ከባንኮቻችን እየተወሰደ በማይከፈል ገንዘብ ታላቅ የማሽን ፋብሪካ በትግራይ እየተገነባ ነው!

29 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ገና ከማለዳው የሕወሃት ካድሬዎች ሃገሪቱንና አዲስ አበባን እንደተቆጣጠሩ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተተከሉትን የልማት አውታሮች እየነቀሉ ወደ ትግራይ ይጭኑ ነበር – የዐይን እማኞች ከየአቅጣጫው ይፋ ያደርጉ እንደ ነበር ሁሉም ያስታውሳል!

ካለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ወዲህ፡ ይህ ተራ ውንብድና ተራቆ፥ ሕወሃት ገንዘብ በየጊዜው ከኢትዮጵያ የልማት ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጭ እየተደረገ የትግራይን ልማት ሲያፋጥን ከርሟል! እንዲሁም ከውጭ የሚገኝውን የፕሮጄክትና ሌሎችም ዕርዳታዎችን በብዛት አቋሪዋ ትግራይ ሆናለች! ትግራይ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ግዛት የተሻለ ግስጋሴ ማድረጓን ለመገንዘብ፡ የሚከተለውን ለአቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር መልስ የሰጠህባቸውን ከብዙዎቹ ስድስቱን መስኮች የያዘ ጽሁፍ ይመልከቱ

ይህንን አጭር ጽሁፍ ያቀረብኩበት ምክንያት ትግራይ አትልማ ለማለት ወይንም የሕወሃት ዘረፋ ዘራፊነትና አጭበርባሪነት አዲስ ሆኖብኝ ሳይሆን፣ ብዛቱና ስፋቱ ይሉኝታ በማጣቱና ለዘለቄታችንም አደገኛ በመሆኑ ነው።

አንደኛ የተቀረውን የኢትዮጵያንና የትግራይን ሕዝብን ግንኙነት ከተለያዩ ወላጆች እንደተወለዱ ወንድማማቾች/እህትማሞች የእንጀራ ልጆች ዝምድና ማስመሰሉና መለወጡ እየተባባሰ ነው። እስካሁንም ባለው፡ ይህንንም እንዲያስፈጽሙ፡ ሕወሃት አብዛኛዎቹ ያልተማሩትን ካድሬዎቹን በየቦታ በሥልጣን ማማ ላይ ሰግስጎ፡ “ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ!” የሚለውን መፈክር ተግባራዊ እያደረገ ነው።

ይህንንም ሲያደርጉ ከማፈር ይልቅ፡ ከምንጊዜውም በላይ ብልግና በታከለበትና ከኛ በላይ አዋቂ፡ ለሃገር አሳቢ የለም በሚል ሽፋን ማካሄዳቸው ነው!

ሁለተኛ፡ ዘረፋው እየተጧጧፈም፡ በየዕለቱ የምንሰማው የትግሬዎች አሉባልታና ስሞታ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አስተዳደር (አስተዳደሩ የእነርሱ ሆኖ ማንን እንዲህ እንደሚሉ አላውቅም!)፣ የጦርነት አውድማ የነበረችው ትግራይ ሠፋ ያለ ምርጥ መዋዕለ ንዋይ ፈሶባት እንዳትፈወስ አድርጓታል የሚለው ሰሞኑን አገርሽቶበት ሰንብቷል – በተለይም በትግራይ ምሁራንና በአይጋ ፎረም ላይ ሲጽፉ የከረሙት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ‘ምሁራንን አተታዎች’ ለተመለክተ ሰው (መረሣ ፀሃዬበርሄ ሃጎስ፣ ወዘተ ከብዙዎች በጥቂቱ በምሣሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

በቅርቡም አቡ ዳቢ ነዋሪ የሆነው ባለሃብቱ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር የተሰኘ የሕወሃት ባለሥልጣኖች መካከል የአንዳንዶቹ ቤተሰብም፥ “የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቂ እንጂ ተጠቃሚ አይደለም” ማለቱ አይዘነጋም። በወቅቱ፡ ግልጽ ብሎ የታየኝ የግለሰቡ ድንቁርናና ጠባብነቱ ብቻ ሳይሆን– በወቅቱ እንደገለጽኩት – “መጭው ዘመን በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ኪሳራና በሃገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሕወሃት በተለያየ ግፊት በኢትዮጵያ የሃብት ቅርምት (scramble for resources) ሊጀምር ይችላል!

“አሁን አቶ ዳዊት ሌላው ኢትዮጵያዊ በማይደፍርበትና መናገር በማይችልበት ግልጽነት እንዲህ የልባቸውን የሚናገሩት፡ ብራቸው ላይ ተማምነው ብቻ ሳይሆን፡ ምናልባትም እርሳቸው ከሚመስሏቸው ድርጅቱ ውስጥ ካሉ የቀድሞ ወዳጆቻቸው የሕወሃት ባለሥልጣኖች ጋር ሸርከውም ሊሆን ይችላል” ማለቴ ይታወሳል – ምንም እንኳ ካንዣበበት ሥጋት አንጻር የሕወሃት 12ኛው ጉባኤ መሰንበት ይበልጣል ብሎ ብዙዎች ተስፋ ያደረጉባቸውን የህዳሴ ጉዳዮች ፊት ነስቶ አዳፍኖ ቢተዋቸውም!

አንዱ ሁሉም የሕወሃት ሰዎች የሚስማሙበት አንድ ነገር አለ፦ ኢትዮጵያን ዘርፎ ትግራይን ማበልጸግ መሆኑ ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያ ወዳድ ትግሬ፡ አማራ፡ ኦሮሞ፡ አፋር፡ ጋምቤላዊ፣ ኦጋዲናዊ፣ ወዘተ ጥርጥር አይኑረው!

ጉዳይ አስፈጻሚ ካድሬ አባይ ፀሃዬ፡ ከመለስ ጋር ከተስማማ በኋላ፡ በጥቅምት 1994 ዓ.ም. – ኤርምያስ ለገሠ በአስደማሚ “የመለስ ትሩፋቶች…” መጽሐፉ እንደዘገበው – ባልተለመደ የፖለቲካ ፖርቲ አሠራር በካድሬዎችና በዓሊ አብዶ አማካይነት ዳኞችን አንድነት አሰብስቦ፡ የመሬት ወረራን ሕጋዊ ያስደረገበት ወቅት ነበር (ገጽ 96-102)። አሁን በቅርቡ ምናልባትም ከአንድ አሥር ቀን በኋላ፡ አባይ ፀሃዬ በአፍቅሮተ ገንዘብና ነጋዴዎች ሂስና አልተገረምኩም።

ኢሣትም ሰሞኑን አባይ ፀሃዪ ሲመራው የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በብድር ዕዳ ተቀፍድዶ ባዶ ቀፎ መሆኑን ከውስጥ የተገኘ መረጃ በመጥቀስ ያቀረበው ዜና ይታወሳል። እንደዘገባውም፡ የኪሣራው ምንጭ የአባይ ፀሃዬ አመራር ላይ በነበረበት ወቅት ወዳጆቹን ለመጥቀም ለሃገሪቱ ፋይዳ ቢስ ወዳጆችን ጠቃሚ ክፍያዎች ሲካሄዱ ከርመዋል።

በዚህም ረገድ፡ ኢሣት እንደዘገበው፡ የግንባታ ስራዎች በተጋነነ ዋጋ ያለጨረታ መሰጠታቸውና ከተሰጡም በኋላ የዋጋ ልዩነት መጥቷል እየተባለ በድጋሚ የተጋነነ ክፍያ ሲፈጸም በመቆየቱ ኮሮፖሬሽኑ በኪሳራ ውስጥ ከተካተቱ ድርጅቶች ዋነኛው መሆኑን ከምንጮች ለመረዳት ተችሏል።

ፀጥታ! ዐባይ ፀሐዬ አስቸኳይ ሥራ ላይ – የሕወሃት/ኢሕአዴግ ሥራ    አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝግ ዝበስባ ላይ!  (Credit:https://www.facebook.com/photo.php?fbid=679080905551746&set=p.679080905551746&type=1)

ፀጥታ! ዐባይ ፀሐዬ አስቸኳይ ሥራ ላይ – የሕወሃት/ኢሕአዴግ ሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝግ ዝበስባ ላይ! (Credit:https://www.facebook.com/photo.php?fbid=679080905551746&set=p.679080905551746&type=1)

የቀድሞው የኮሮፕሬሽኑ የበላይ የነበሩት አቶ አባይ ጸሃዬ ባለባቸው የጠባብነት ችግር ምክንያት፣ የባለቤትነት ድርሻ አላቸው የሚባለውና በቀድሞ GYB ቡቲክ ባለቤት አቶ የማነ ግርማይ የተሰጠው እና ኦሞ በሚገኘው የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በተጋነነ ዋጋና ያለጨረታ ከተሰጡ ግንባታዎች መካከል ምሳሌ መሆናቸውን ምንጮች ማስረጃዎችን በማስደገፍ ለኢሳት ጠቁመዋል። ኮርፖሬሽኑ ለሌሎች ኩባንያዎች ክፍያን መፈጸም እንዳማይችል ቢገለጽም፣ ይኸኛው ግንባታ ግን ክፍያ ተቋርጦ እንደማያውቅበት ለመረዳት ተችሏል።

ኮርፖሬሽኑ ለሚዋዋላቸው የተጋነኑ ውሎችና ስምምነቶች ብድሩን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲያገኝ መቆየቱም ታውቋል። ከዚህም የተነሳ፡ ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን የተበደረው ብድር መጠን 44 ቢሊዮን ብር መድረሱን ውስጣዊ ምንጮች ገልጸዋል።

በአቶ አባይ ጸሃዬ ምትክ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሽፈራው ጃርሶ በተለያዩ መድረኮች “የተረከብኩት በቁሙ የሞተ ድርጅት ነው” ሲሉ መግለጻቸውም ተነግሯል። ቅሬታቸውን በማቅረብ ላይ የሚገኙት አቶ ሽፈራው ጃርሶ በቅርቡ የስራ መልቀቂያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እንዳቀርቡ የኮርፖሬሽኑ ምንጮች ለኢሳት አስረድተዋል።

የተከሰተውን የገንዘብ ጉድለት ተከትሎም – ኢሣት እንደዘገበው፡ – የድርጀቱ የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ቢያቀርቡም፡ እርሱም የማይደፍራቸው ኃይሎችን የሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ፣ ይህን አሳሳቢ ችግር በሚመለከት፡ እንደ ጥንታዊ የኢትዮጵያ አባባል፡ ነገሩ ቄሱም ዝም ዳዊቱም ዝም ሆኖአል። በመሆኑም፡ ሕወሃቶችና አገልጋዮቻቸው በየቦታው ጮማ ሲቆርጡ፡ ኮርፖሬሽኑ ባጋጠመው የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት በርካታ ሠራተኞች ከድርጅቱ በመልቀቅ ላይ መሆናቸው በዜናው ተመልክቷል።
 

የኦዲተር ጄነራሉ ዕይታ

በሌካ በኩል ደግሞ፡ የፌዴራሉ መንግሥት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ግንቦት 25፣ በ2007 ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት አሳሳቢውን የኢትዮጵያ ስኳር ፋብሪካዎች ደብዛቸው የጠፋ ቀጥተኛ የመንግሥት ብድር መጠንንም ማንሳታቸው አልቀረም። ዋናው ኦዲተር ይህንን ሲያቀርቡም፡ ከባንኮቻን ከውጭ መንግሥታት ብድር ውጭ ከመንግሥት ትሬዠሪ ደግሞ ሰለተወሰደው ብድር በሪፖርታቸው ገጽ 23 አንቀጽ 88 ላይ እንዲህ ይላሉ፡-

    “የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመልሶ ማበደር ለስኳር ፊብሪካዎች ከሰጠው ብድር ውስጥ እስከ ሰኔ 30/2006 ዓ.ም ድረስ መሰብሰብ የነበረበት ብድር መሰበሰቡን ለማረጋገጥ ኦዱት ሲድረግ ወለድና ቅጣትን ጨምሮ ብር 418,803,484.57 ያልተሰበሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡”

በአጠቃላይ፡ በአሠራር ድክመት ድረጃ፡ ኦዲተር ጆኔራሉ፡ ስለስኳር ፕሮጄክቶች የሚከተሉትን ወቀሳዎች በዘገባቸው በ2006 ዓ.ም. ሚያዝያ 14 ከገጽ 30-31 እንደሚከተለው አስፍረዋል

“በኮርፖሬሽኑ የአምስት ዓመታት ዕቅድ (2003-2007 ዓ.ም) መሠረት አዲስ የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች የአገዳ ተክል ልማት ዕቅድ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት 18,400 ሄክታር ሲሆን ክንውን 2,395 ሄክታር (13%)፤ በኦሞ ኩራዝ ዕቅድ 43,108 ሄክታር ሲሆን ክንውን 1,676.6 ሄክታር
(4%) እና በወልቃይት እቅድ 8,608 ሄክታር ሲሆን ክንውን 539 ሄክታር
(6.5%) መሆኑ፤

በአምስት ዓመታቱ የፊብሪካዎች ግንባታ ዕቅድ መሠረት (ከ2003 – 2005 ዓ.ም) የጣና በለስ ቁጥር አንድ እና ሁለት እስከ ጥቅምት 2005 ዓ.ም መጠናቀቅ ሲኖርበት ክንውኑ በ2005 ዓ.ም መጨረሻ፡ ቁጥር አንድ 45% እና ቁጥር ሁለት 39% መሆኑ፣ በኦሞ-ኩራዝ የፊብሪካ ግንባታው እስከ ሰኔ 2005 ዓ.ም መጠናቀቅ ሲኖርበት ክንውን 42% መሆኑ፤

ወልቃይት እስከ ጥቅምት 2006 ዓ.ም መጠናቀቅ ሲኖርበት ሥራው ይህ ኦዲት እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ አለመጀመሩ፤

የስኳር ሌማት ፕሮጄክት አካሌ የሆኑት የመስኖ ልማት፣ የአገድ ተክል እና የፋብሪካ ግንባታ ሥራዎችን በቅንጅት ባለመታቀዳቸውና አፈጻጸሙ ቅደም ተከተል ጠብቆ ባለመተግበሩ የአንደ አፈጻጸም መዘግየት በሌላው ሥራ
አፈጻጸም ሊይ ተጽእኖ ማሳደሩ፤

ለአብነት የተንዲሆ ስኳር ልማት የፊብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ምክንያት 5164.09 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ ምርት ዕድሜው በመራዘሙ እንዲወገድ በመደረጉ 102,440,145.00 ብር ፋብሪካው ማግኝት የሚገባውን ገቢ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ያሳጣ መሆኑ፤

የአገዳ ተክል ልማት፤ የመስኖ ግንባታ እና የፊብሪካ ግንባታ ፕሮጀክቶች በየድረጃው የተሰሩ ስራዎች በተቀመጠለት ዲዛይን እና እስፔሲፉኬሽን መሰረት መሆኑ በተቆጣጣሪ መሃንዱሱ ሉረጋገጥ የሚገባ ቢሆንም ኮርፖሬሽኑ ሊያስገነባቸው ላቀደላቸው አስር አዲዱስ የስኳር ፊብሪካ ግንባታዎች ሥራቸው በተጀመረበት ወቅት ጥራት የሚቆጣጠር አማካሪ ድርጅት ባለመቅጠሩ የጣናበለስና ኩራዝ ፊብሪካ ግንባታ (ፕሮጄክቱ ከተጀመረ ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2006) በየደረጃው እየተከናወኑ የነበሩ ሥራዎች (civil work)
በተቀመጠለት ዲዛይንና እስፔሲፉኬሽን መሰረት ስለመሆኑ በተቆጣጣሪ መሃንዱስ አለመረጋገጡ፤

ለጣና በለስ ቁጥር 1፤ ቁጥር 2 እና ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 የፊብሪካ ግንባታ ስራቸው የተጀመረው መጋቢት 2003 ዓ.ም ሲሆን ኮርፖሬሽኑ አማካሪ ድርጅት የቀጠረው ሥራው ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በኋላ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም መሆኑን” እንደአመራር ዕጦትና ችግር ምንጮች ይጠቁማል።
 

ዜጎች ሊወስዱ የሚገባ እርምጃ

አቶ አባይ ፀሃዬና ግብረአበሮቻቸው ተይዘው ሊመረመሩ አይገባምን?

መመርመር ይገባቸዋል ካልን፡ የሕወሃትን አሰተዳደር ዘራፊነት ለማጋለጥ፡ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ጀምሮ በቲዊተር

#AbayTsehayeAccount4SugarMoney የሚለውን ዘመቻ መጀመር አለብን!
 

%d bloggers like this: