ከሥልጣናቸው በመጥፎ ሥነ ምግባር ተባረው የነበሩትን የቀድሞው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን ዛይድ ወ. ገብርኤልን ሕወሃት የዓለም አየር መንገዶች ባለሥልጣን ውስጥ የኢትዮጵያ ተወካይ እንዲሆኑ ሾመ!

3 Sep

በከፍያለው ገብረመድህን – The Ethiopia Observatory (TEO)

    የአቶ ዛይድ አዲሱ ሹመት በአቪዬሽን ባለሙያዎች ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆኖ የሚሾመው ሰው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የሠራ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቋሚ ተወካይ ማስቀመጥ ከጀመረች 14 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም ወቅት ሁለት ግለሰቦች ቋሚ ተወካይ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እነርሱም አቶ መሸሻ በላይነህና አቶ ተፈራ መኮንን ናቸው፡፡ ሁለቱም ግለሰቦች የተሾሙት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡

    “አቶ ዛይድ የተከበሩ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ምንም ዓይነት ልምድ የላቸውም፡፡ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቋሚ ተወካይ ሆኖ ለማገልገል የአቪዬሽን ዕውቀትና ልምድ ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ባለሙያዎች እያሉ፣ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ምንም ዓይነት ልምድ የሌላቸውን ግለሰብ መሾም የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ቅር አሰኝቷል፤” ብለዋል ምንጮች፡፡

አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል (ፍቶ ሪፖርተር)

አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል (ፍቶ ሪፖርተር)

አቶ ዛይድ የትግራይ ሰውና የሕወሃት አባል ስለሆኑ፡ በኢመባ በነበሩበት ዘመን (11 ዓመት) በሥልጣን ባልገው ለመንገድ ተቋራጭ የሚሆነው ትግራዊ ግለሰብና ኩባንያዎች ነበሩ! ሙስና በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ተስፋፋ! ከእንግዲህ ግን ከካናዳ እንዲህ በጎላ መንገድ ኢትዮጵያን ላይጎዱ ይችላሉ።

ሰሞኑን ስለ discretionary power ስነመካከር ነበርን። እንደገና በሌላ ተጨባጭ መልኩ ተከትሎን መጥቷል!

በዘርና በደም ለመጠቃቀም ሲፈልጉ፡ ዛይድ የነበረው አለመግባባት ከትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጋር ቢሆንም፡ ሚኒስትሩ አፍንጫውን ተይዞ፡ በሕወሃት ትዕዛዝ የሹመቱን ደብዳቤ አስፈርመውታል! ድሮ እንደ ሚደረገው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይንም የኢትዮጵያ የአቪየሽን ቢሮ ለምን አልፈረመም?

ሕውሃት ዐይኑና ጆሮው ወይ ገንዘብ ላይ ወይ ዝርያ ላይ ሆኖ ለእነዚህ ምልከታም አይሰጥም! አቶ ዛይድ ላይ ግን የሥራ ባልደረቦቻቸው እንዴት እንደ ተሾሙ ነገ ጣት በመጠንቆል ሃሜታችውን ያሽከረክሩታል!

አንድ ወቅት ላይ መለስ ዜናዊ አስረስ አንድ አምባሳደር የፖለቲካ ወዳጁን ለመጥቀም አማራውን አምባሳደር ከኒውዮርክ በሁለተኛ ሣምንቱ አስነስቶ ወደ ጂኒቫ አንደላከው አስታውሳለሁ። ዋና ፀሐፊው ከሁለት ሣምንት በኋላ የሌላ የኢትዮጳምባሳደር ደብዳቤ ሲቀበል፣ “በምን መንገድ ልረዳ እችላለሁ?” ብሎ መጠየቁ፣ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ውስጥ የመጭውን አምባሳደር ምንነት ዋጋ አሳጥቶት ነበር! ይህ ደግሞ ከፈረሱ የተገኘ የተገኘ መረጃ ነው!

ለታዋቂውና ዝነኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቶ ተወልደ ወደ “ትግራይ አየር መንገድነት” ለመለወጥ ብዙ ቢሠራም፣ ስሙ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆኖ ይቀጥላል! ዳሩ ግን እርስ በእርስ ይጠቃቀሙበት እንጂ፣ ምንጊዜም ‘የትግራይ አየር መንገድ ሆኖ ከመሬትም አይነሳም!

ዳሩ ግን እነ አቶ ተወልደ በሕወሃት አመራር ከእንግዲህ በአየር መንገዱ ላይ የሚያደርሱት የጥፋት ሥራ እነርሱን ብቻ ሳይሆን – አቶ ዛይድም ከዚህ ስለማይመለሱ – በዓለም አቀፍ አየር መንገድ ውስጥ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከውስጥ ካሉት ጋር በመተባበር የሚያደርጓቸው ጥረቶች እነርሱንም ጭምር የሚያጠፉ መሆናችውን ሊገነዘቡ ይገባል – አለያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕጣ ፈንታ እንደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል ይሆናል – ሕወሃት ኢትዮጵያን የጎዳ መስሎት አየር ኃይሉን ብቁና ቆራጥ አብራሪዎቹንና እውቅ ቴክኒሽያኖቹን በትግራውያን ለመሙላት ሞክሮ!

አየር መንገዱ ውስጥ ያለው የሠራተኛው ጥላቻና የውጭ ዕዳውን ጫናውን ገበያው ስለማይቀበለው፡ ውድቀቱን ያፋጥነዋል! ታሪክ ያን ጊዜ በእነዚህ ሃገር ከሃዲዎች ላይ ሠይፉን ይመዛል!

ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርነት የተነሱት አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል፣ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ተሾሙ፡፡

ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል ሆኖ የዓለም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን የሚቆጣጠር ድርጅት ነው፡፡ ዋና መሥሪያ ቤቱም ሞንትሪያል ካናዳ ይገኛል፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚገኙ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ዛይድ የተሾሙት በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አቶ ዛይድ የኢትዮጵያን መንግሥት ወክለው በውጭ አገር የሚሠሩ በመሆናቸው፣ እንደ ዲፕሎማት የመደባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ አቶ ዛይድ ሹመቱን ተቀብለው ከሦስት ሳምንት በፊት ወደ ካናዳ ማቅናታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተፈራ መኮንን በዚሁ ድርጅት ሥራ በማግኘታቸው፣ በፈቃዳቸው ሥራቸውን ከስድስት ወራት በፊት መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሠሩ አንድ ዲፕሎማት ላለፉት ስድስት ወራት በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኢትዮጵያን በጊዜያዊነት ወክለው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

አቶ ዛይድ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ባለፈው ጥቅምት ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በተጻፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡

የአቶ ዛይድ አዲሱ ሹመት በአቪዬሽን ባለሙያዎች ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆኖ የሚሾመው ሰው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የሠራ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቋሚ ተወካይ ማስቀመጥ ከጀመረች 14 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም ወቅት ሁለት ግለሰቦች ቋሚ ተወካይ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እነርሱም አቶ መሸሻ በላይነህና አቶ ተፈራ መኮንን ናቸው፡፡ ሁለቱም ግለሰቦች የተሾሙት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡

“አቶ ዛይድ የተከበሩ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ምንም ዓይነት ልምድ የላቸውም፡፡ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቋሚ ተወካይ ሆኖ ለማገልገል የአቪዬሽን ዕውቀትና ልምድ ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ባለሙያዎች እያሉ፣ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ምንም ዓይነት ልምድ የሌላቸውን ግለሰብ መሾም የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ቅር አሰኝቷል፤” ብለዋል ምንጮች፡፡

አቶ ዛይድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ በመጀመርያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በትራንስፖርት ኢኮኖሚ በእንግሊዝ አገር ሊድስ ዩኒቨርሲቲ ሠርተዋል፡፡ አቶ ዛይድ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ልምድ ባይኖራቸውም በየብስ ትራንስፖርት የ30 ዓመታት ልምድ አላቸው፡፡ በትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ በትራንስፖርት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አገልግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የገቡት በ1990 ዓ.ም. ሲሆን፣ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡ አቶ ዛይድ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በታዩ መጓተቶችና ደካማ አፈጻጸም ላሳዩ ኩባንያዎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲሰጡ አድርገዋል በሚል፣ ከአቶ ወርቅነህ ጋር በተፈጠሩ አለመግባባቶች እንደሆነ ምንጮች ይናገራሉ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የአቶ ዛይድን መሾም አረጋግጦ፣ በሹመቱ ዙሪያ የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ዝርዝር መረጃ የለኝም ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
 

ተዛማጅ ጽሁፎች:

    አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል ከሥልጣናቸው ተነሱ

    የሕወሃት አባል የመንገድ ባልሥልጣን ኃላፊ የሕወሃት አባል ባልሆኑት ጠ/ሚኒስትር ከሥራ መባረር የፈጠረው ትኩሳት የበኽር ልጅ ነን በሚሉትና ሃገር የበኽር ልጅ አላትን በሚሉት መካከል የኢንተርኔት ውዝግብ አስነሳ

    የሕወሃት ሱር ኮንስትራክሽን የባለ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ያለተጫራች ተረከበ

 

%d bloggers like this: