10ኛው የመቀሌው የኢሕአዴግ ጉባዔ በሕወሃት የራሱ ካድሬ ሲበለት – ከፓርቲው የሻገተ አስተሳሰብና አፍቅሮተ ፕሮፓጋንዳና ጸዳ ያለ ባርኔጣ የሚነሳለት ትንተናና አመለካከት!

9 Sep

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

የጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬውን የፓርቲውን ሊቀመንበር ንግግር በአፋጣኝ ዘሎ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሠይፈ ኃይሉን ማዳመጡ አዳሽ ቢሆንም፡ በሌላ ቅደም ተከትል ከተደረገ ግን አደጋው እጅግ ከፍተኛ ነው – ወደማጡ መሄዱ የሚያስከትለውን ችግር ዐይነት!

የሚያሳዝነው ግን፣ ኢትዮጵያን የመሠለች ሃገርና ጨዋው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት እነዚህ ዐይነት ወንበዴዎች እጅ መውደቁ የታሪክን እንቆቅልሽ ያሳያል። ለማንኛውም፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ “በቃኝ! ከእንግዲህ አልረገጥም!” ማለት በመጀመሩ የአዲስ ታሪክ ዋዜማ ላይ የምትገኝ ሃገር ያደርጋታል!

ስለዚህ የኢትዮጵያ መዋረድ ዘወትር ደጋግሜ የምጠቅሰው፡ በ2011-2015 የኢትዮጵያን እንግሊዝ የጋር ትብብር ፕሮግራም፣ የእንግሊዝ መንግሥት ኤጀንሲ የሆነው DFID በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ የጻፈው እንዲህ የሚለው ነው፡ –

    “The Government of Ethiopia (GoE) is capable and committed to growth and development and is a proven partner in making rapid progress towards the Millennium Development Goals (MDGs). But its approach to political governance presents both substantive challenges to sustainable development and reputational risks to partners.” [የኢትዮጵያ መንግሥት ልማትን በማፋጠን በተለይም የተባበሩት መንግሥታትን የመጀመሪያው 15 ዓመታት የልማት ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ አስተማማኝ አጋር ነው፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ አያያዙና አስተዳዳሩ ለዘላቂ ዕድገትና ልማት ብቻ ሳይሆን ለአጋሮቹ ስምም ጠንቀኛ ነው።”]

በመሆኑም፡ ሌላው ቀርቶ፡ እንዳሁኑ ድርቅ በተስፋፋበት ሁኔታ እንኳ – ሰሞኑን በዲያስፖራ መድረክ እንደተነገረው – ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውም ሸምጠጥ አድርጎ ውርደቱን በሃስት በአወንታዊ መልኩ ዕርዳታውን የተከለከ አስመስሎ ሊጠቀምበት መሞከሩ፣ ሃገሪቱን የዘፈቁበትን የመቀመቅ ጥልቀት የሚያመላክት ከመሆኑም በላይ፡ ለጋሽ ሃገሮች ለኢትዮጵያ ዕርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ይህ የሕወሃት አስተዳደር በሌሎች ምን ያህል በጽያፌ መታየት አንደጀመረ አመላካች ነው!

እርጉዝ በሕወሃት አጋዚና ፖሊስ በየመንገዱ የምትደበድብባት ሃገር፣ ቤቶች በነዋሪዎች አናት ላይ የሚፈርስባት ሃገር፡ ምን ዐይነት ፋሽስቶች የሚያስተዳድሯት ሃገር ናት? በተራው በአሁኑ ወቅት፡ ወላይታ ውስጥ፡ ቤቶቻቸው በዚህ መልክ የፈረሰባቸው ሰዎች አቤቱታ ካሰሙ፣ ኃዘናቸውን ካሣዩ፡ እንባቸውን በአደባባይ ካረገፉ እስከ ሣምንት እንደሚታሠሩ በዚህ ሣምንት ከኢሣት ቃለ መጠይቆች ማዳመጣችን ሃገራችን ላይ ለመቆናጠጥ እየሞከረ ያለውን ከትግራይ የመጣውን ፋሽስታዊ ቡድን በመጣበት መልኩ ለመመለስ በኢትዮጵያውያን በኩል የተጀመሩት እንቅስቃሴውች ሌላ አማራጭ የመጥፋት አመላካቾች መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባናል!

በመሆኑም፡ ከራሱ ከወንበዴው ፓርቲ እምብርት ውስጥ አሁን ጎላ ብሎ የሚሰማው ድምጽ የችግሩን ውስብስብነት አመላካች ነው! እውነቱን ለመናገር – የማንም ፓርቲ አባል ባልሆንም፣ ይህ አስተዳደር መደፋቱን ከመደገፍ ባሻገር – በሃገር-ጠል ቀጣፊዎች ቡድን እስካሁን መገዛታችን እንደ እሳት ያቃጥለኛል!
 

ቃለ መጠይቁን ያዳምጡ፡ –
 

 


 

 

%d bloggers like this: