ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለምክትላቸው ሞላ አስገዶም መክዳት የሠጡት መግለጫ የክስተቱን አዎንታዊ መልክ ብቻ ይስላል!

20 Sep

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ዶ/ር ብርሃኑ እንዳሉት ገና ትግሉ ሲጀመር፡ የሞላ አስገዶም መክዳት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ የሚኖረውን ጉዳት ከፍተኛነት ማሳየታቸው ትክክል ቢሆንም፣ ችግሩን በጥልቀት ሳይመረምሩ “በእፎይታ” ለማለፍ መሞከራቸው ምክንያቱ ግልጽ አይደለም።

ዶ/ር ብርሃኑ እንደ መጽናኛ አድርገው የወሰዱት – ደምሒት ካለው የሰው ኃይል ብዛት አንጻር – ብዙ ጉዳት ሳይደርስ ሞላ በማሳሳት ይዞ የሄደው ኃይል ውስን መሆኑ በአንደ በኩል ድርጅታዊ ዕድገት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ አመላክተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የግለሰቡ መክዳትና ሞላ ይዞ የሄዳው ኅይል አናሳ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዶር ብርሃኑ ይህም በበጎጎ ገጽታ እንዲታይ መክረዋል።

አሁን እንደምናየውና ዶ/ር ብርሃኑ እንደነገሩን ከሆነ፡ ውስጣዊ ምርመራውን የሚያካሂደው ደምሒት ራሱ ነው። ለወደፊቱ ችግሩ ሁለተኛ እንዳዳይደገም ምናልባትም ቁጥጥር ማጠናከሩ መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ ስለሚችል፡ የዚህም አግባብ ለወደፊቱ ሊታስብበት ይገባል።

በሌላ አባባል በኃይል የተያዘ ኃይል በኃይል ገዥ ሊሆን ስለሚችል፣ የዴሞክራሲ ርሃብ ያጠቃው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊና ለሕግ የሚገዛ ኃይል፣ ይህ ባህል ላለመዳበሩ ምክንያት እንዳይሆንበት ጥንቃቄ ሊደረግ የሚገባ ይመስለናል።


 

ስለሆነም፡ ዶ/ር ብርሃኑ ደምሒት ካለው የሰው ኃይል አንጻር ዛሬና ነገ የሚኖረውን ሁኔታ እየገመገምነው ነው ብለው፡ ውጤቱን ወደፊት በዝርዝር እንገልጻለን ቢሉ ለብዙዎቻችን ይመቸን ነበር።

ስለሞላ አስገዶም መክዳትና በተቃራኒ አስተሳሰቦችና አባባሎች በዚህ ገጽ ላይ የሠጠነውን እዚህ መድገም ስለማንፈልግ፡ መመልከት ቢያስፈልግ እዚሁ ተጭነው ያንብቡ

ዋናው ጥያቄ ግን በዚህ ዐይነት ትግል ውስጥ ዋናው የጥንካሬ ምንጭ አመራሩና ጦሩ ተባብሮና ተማምኖ በጋር አብሮ ለመሥራት መቻሉ ነው። ስለሆንም ዶ/ር ብርሃኑ ትግሉ መስቀለኛ መስመር ላይ ደርሷል ያሉትን ብንቀበልም፡ አሁን በተደረሰበት ደረጃ በተለይም በዝርያ ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች የእምነት ሥንቃቸው ምን ያህል ፈርጣማና አስተማማኝ እንደመሆኑ በብርቱ ሊታሰብበት ይገባል!
 

%d bloggers like this: