የመጀመሪያው ኩላሊት ነቀላ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕወሃት ቀዶ ጠጋኝነት መከናወኑ እንዲታመን ፋና የሚያስፈራ/የሚያሳዝን /የሚያሳፍር የዘረኝነት ጥረት አደረገ!

30 Sep

በከፍያለው ገብረመድኅን – Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ስለመጀመሪያው የኩላሊት ነቀላ ሕክምና ኢትዮጵያ ውስጥ መሞከር ዜናውን የሕወሃት ገጽ ላይ ሳነብ እጅግ ደስ አለኝ – ደስታዬም ብዙ ላይቆይልኝ!

እንዳውም ፋና ገጽ ስምንተኛው አንቀጽ (paragraph) ላይ እስክደርስ ድረስ በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ሃኪሞች እንደሚደረግ አላወቅሁም ነበር። በእርግጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች (ፋና ስማቸውን መጥቀስ አልፈለገም) በነቀላ ሥራው ላይ ተሳታፊ ቢሆኑም፡ ፋና የመረጠው ታማሚዎቹን በመክፈቱም ሆነበ ነቀላው ምንም አስተዋጽኦ ያልነበራቸው የዶክተር ብርሃኔ ረዳይ (የጳዎሎስ ሆስፒታል የሕክምና ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት) ስም ላይ ማተኮር ነበር።

የዚህ ዐይነት አሠራር ማለትም “ሁሉንም ነገር ወደ ትግራይ ወይንም ለትግራይ” ተብሎ የሚታወቀው የዘቀጠና የቅሌት ፖለቲካ ትክክል ባለመሆኑ፡ በቅሬታ መልክ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲያውቁ – ‘11 አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው ጥር ግንባታቸው ይጀመራል ይላል ሕወሃት ያሉትን እንኳ በሚገባ ማስተዳደር ሳይችል!‘ በተሰኘው ጽሁፌ ውስጥ አንስቼው ነበር።

ዜጎች ሃገራቸው ውስጥ ሳይፈሩና ሳይሰጉ፡ ሁለተኛ ድረጃ ዜግነት ስሜት ሳይሰማቸው በእኩልነትና ነጻነት ለመኖር መቻል አለባቸው። ይህን ማድረግ ካልተቻለ፡ ሃገሪቱ ባለሙያ ልታፈራና ልታካብት ብላም ልታድግ አትችልም!

በዚያ ከትምህርት መስፋፋትና ጥራቱ ስለመሻሻል አስፈላጊነት ጋር ባቀረብኩት ጽሁፍ ውስጥ የሚከተለውን ሃሣብ ነበር ያሠፈርኩት፦

    “ለነገሩ ኩላሊት ነቀላ ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀመረ ተብሎ ዜናው ለሕዝባችን ሲገለጽ በቴክኒኩ መስክ እንኳ ሥራውን ያካሄዱት ትግራዊ ያልሆኑ ሰዎች እያሉ፡ ትግራዊ ፕሮፌሰር ተጠርቶ አብራሪ እንዲሆን መጋበዙ፡ ምን ያህል ሃገራች ይህ ሕወሃት በዘራው የዘር አደጋ ውስጥ እንደገባች ያመላክታል።”

ፋና የዘገበው ዜና ውስጥ “ባለሙያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሱ ህክምናውን የሚሰጡ ሲሆን፥ በያዝነው 2008 ዓመተ ምህረት ለ50 ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላውን ለማከናወን ታቅዷል” ይላል።

እንዴት ይሆኑ እነዚህ ሕሙማን የሚመረጡት? በሃኪሞች ኮሚቴ መሆኑን ከሌሎች ሃገሮች ልምድ አውቃለሁ! ሕወሃት ምን ችግር አለበት የራሱን ኮሚቴ ለመትከል – በየመሥሪያ ቤቱና በየቀዳዳው ሁሉ እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው – በሕጋዊነትና በስብዓዊነት ሳይሆን ማለት ነው። በሌላ አባባል እንደ ኮንዶሚኒየም ሁሉ፡ ኩላሊትም በዘር ቢታደል ምን ያስገርማል የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ!

Dr. Punch, center, and Ethiopian transplant team (Health System - Univ Michigan)

Dr. Punch, center, and Ethiopian transplant team (Health System – Univ Michigan)

እነዚያ ለፋና ስማቸው የጠፋበት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን የሚችጋን ዩኒቨርሲቲ እትም እንደገለጸው ከሆነ ዶክተር እንግዳ አበበ (General Surgeon and transplant fellow) እና ዶክተር ሞሚና ሞሃመድ (transplant fellow) ናቸው። ዋናው የቡድኑ መሪ Surgeon Jeffrey D. Punch ነበሩ።

ሰለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ተባባሪዎቻቸው የኩላሊት ነቀላው ሥራ አፈጻጸም የሚከተለውን ነበር የሰጡት አስተያየት፡-

    “The surgeons and internists in Ethiopia are first rate, and St. Paul’s management is going about everything in the right way, upgrading anesthesia, laboratory, pathology, nursing, pharmacy and radiology services to make sure patients do well in the long run.”

በብሄረስብና የትውልድ ወረዳ በመቁጠር የተጀለተው ሕወሃት ግን ሙያን ሳይሆን ደምና አጥንት ሲመረምር፡ ኢትዮጵያን በየዘርፉ ባለሙያ ሊያሳጣትና ሲያሳጣት ቆይቷል!

የፋናንም ሆነ የሚቺጋን ዩኒቨርስቲ ሰለኩላሊት ነቀላው የጻፉትን ለአንባብያን ግንዛቤና ትዕዝብት ከዚህ በታች አሥፍሬዋለሁ።

የሚችጋን ዩኒቨርሲቲ ስለተከናወነው ሥራ የጻፈውን ሊንኩን እዚህ ተወዋለሁ

ፋና ወሬውን ሰለሚደብቅ ወይንም ስለሚቀያይር የዚያን ዝርዘር የስክሪን ፎቶውን ቅጂ ነው የማቀርበው።

kidney transplant
 

የሆስፒታሉ ምክትል ዲሬክተር ዶክተር ብርሃኔ ረዳይ በቀዶ ጥገናው ላይ ተሳታፊ አልነበሩም፤ ዶክተር ፐንችም ስለሳቸው ያነሱት ነገር የለም! ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ግን በሥራው ተሳታፊ በመሆን ወገኖቻቸውን ለመርዳት ልምድ ቀስመዋል – ሃገሪቱ ውስጥ የሕወሃት ብልግና የሚያሠራቸው ከሆነ!

እረባካችሁ የሕወሃት ሰዎች! ዓለም ማርስ ላይ ስላለው ውሃ ክምችና ተጠቃሚነት በክፍተኛ ምርምር ውጤቱ ሰሞኑን ይደሰታል። መንግሥት ተብየው ግን ውዲቷ ሃገራችን ውስጥ ጥንታዊቷን ሃገር በዘር መርዙ ለማፈራረስ በየቁኑ መርዙን ይረጫል።

እረባካችሁ የሕወሃት ሰዎች! ሃገሪቱ መሄድ ወደማይገባት አቅጣጫ አትውሰዷት! ሕዝብ እየታዘባችሁ መሆኑን እንኳ የጫነባችሁ ጥላቻ ይሉኝታ አሳድሮባችሁ ከዚህ ብልግናችሁ ቆጠብ በሉ! የሕዝብ ቁጣ ጎርምቶ ይህ ችግር እኮ በቀላሉ ከእጅ ሲያመልጥ እናንተም፡ ኢትዮጵያውያን ነን የሚለው ሁሉ የሚወዳትን ሃገር ያጣል!

ለምን? ምንን ወይንስ ማንን ልትጠቅሙ ይሆን? ለልጆቻችሁስ እንዴት አድርጋችሁ ትገልጹላቸዋላችሁ ሃገር ስታሳጧቸው?
*Updated.
 

%d bloggers like this: