የኢትዮጵያዊው ጀግና ፓይለት ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 3/2015 በኦአክላንድ፣ ካሊፎርኒያ ይፈጸማል!

2 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

Wings over the Ogaden: The Ethiopian-Somali War 1978-1979 በተሰኝው Tim Cooper በጻፉት መጽሐፍ ውስጥ የሶማሌ ጦር ጥቃት ተጠናክሮ ግፊቱ ወደፊት ሲሄድ፡ ከኢትዮያ የምድር ጦርና ሚሊሺያ ይልቅ፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በጥቂት ቆራጥ ፓይለቶችና ብቁ የጦር አመራር ሶማሌን ለመመከትና ለቅብጠቷም እስከዛሬ ያለችበትን መቀመቅ ለመልበስ አስገድደዋታል።

ይህን “አትንኩኝ አልነካችሁም” የምትለውን ሃገር የዚያድ በሬ መንግሥት በመድፈሩ የቀድሞው አየር ኃይላችን በሰማይ መደበኛ ሥራውን፡ በምድር ደግሞ ወታደሮቻችንን ከሶማሊያ ደብዳቢ አውሮፕላኖች በመከላከል፡ ሶማልያን ለውርደትና የመጨረሻ ሽንፈት ዳርገዋታል!


 
Tim Cooper እንደዘገቡት፡ ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ ክጅኔራል ለገሠ ተፈራ ጋር ተባብረው ሲበሩ፣ ጄኔራል ለገሠ አራት የሶማሌ ሚግ 21ዶች ፎርሜሽን ወደርሳቸው አቅጣጭ ሲመጣ ተመልክተው፡ ባልታሰበ ቅጽበት ወደ ሰማይ በመመንደግ ሁለቱን የሶማሌ ሚጎችን እርስ በእርስ ካጋጩ በኋላ፡ ሶስተኛውን አሳደውት ቁጥጥር አጥቶ ወድቆ እስኪከሰከስ ድረስ ማሳዳደቻውን ቲም ኩፐር ጠቅስዋል።

ኮሎኔል ባጫም ከዊንግማን አፈወርቅ ኪዳኑ ጋር በመሆን የዚህ ታዛቢ ስለነበሩ፣ በሚያበሩት አውሮፕላን አራተኛውን ሚግ-21 አሳደው በታጠቁት መሣሪያ አጋይተውታል። በተጨማሪም፡ ከጄኔራል አሸናፊ ገብረጻዲቅ ጋር ሶማልያ ውስጥ በአውሮፕላን ስለላ ትዕዛዝ (reconnaissance) ተሰጥቷቸው ሶማልያ ድረስ ገብተው ምን ያህል አውሮፕላኖች እንደቀራት አጣርተው መረጃ ለሃገር አድርሰዋል!

ዋናው ነገር ሶማልያ ካደረሰቸው ጥፋት አናጻር፡ በሕይወት ያሉት ጄኔራል አሸናፊና ሁለተኛውን አውሮፕላን የያዙት ኮለኔላ ባጭ፡ ስሜታዊነት ሳያጠቃቸውና የታጠቁትን መሣሪያዎች በሚጎቹ ላይ ሳይተኩሱ/ሳያፈነዱ መረጃውን ይዘው ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል!

ዝርዝሩ ባይኖረኝም፡ ኮልኔል ባጫ አውሮፕላናቸው ተመቶ እስከ ወደቁበት ድረስ፡ ሌላም የጠላት አውሮፕላኖች መጣላቸው ይነገራል።

በዚህ አጋጣሚ፡ በኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ሳይሆን ለእኝህ የቀደሞው አየር ኃይላችን ምርጥ ሰውና ጀግና ከበሬታዬን ለመግለጽ ዕድል ከማግኘቴም በላይ፡ በእርሳቸው ዕረፍት ቤተሰቦቻቸውን የሚሰማቸው ኃዘን እኔንም ይሰማኛል – የእናት የአባቴ ልጅም በዚያው የኦጋዴን ጦርነት ላይ ለሃገሩ ክብር ሲፋለም ወደቋልና!

ኩሁሉም አሳዛኙና አሳፋሪው እነዚህ ሃገራቸውንና ዳር ድንበራቸውን በደማቸውና በነፍሳቸው የዋጇትን የጀግኖች ሃገር፡ ዛሬ ወንበዴው ሕወሃት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን እየቸበቸበ ይገኛል!

ንጹሃን ዜጎችና ጀግኖች ሃገርና ክብር የማይኖራችው በሕወሃት አስተዳደር ብቻ ሳይሆን አይቀርም!

ከእንባችን ጋር ለነፍሳቸው የሰላም ዕረፍት እንመኛለን!
Updated.
 

%d bloggers like this: