የሕወሃት ፋና ብሮድካስት የሕወሃት አመራሮችን ማጋለጡ የሚድያ ስታንዳርድ መቀየሱን ለማሳየት ወይንስ እስከ ዛሬ የደረሰውን ዘረፋ፣ ጉድለትና ጥፋት ለማድበስበስ? ተጠያቂውስ ማን ሊሆን? ዘራፊው ሕወሃት ይህን ማድረግ ይችላልን?

15 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በትድሃር ኮንስትራክሽን ሲገነቡ የነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሌላ ኮንትራክተር ሊሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2008 (ኤፍ. ቢ. ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰሞኑን የጥራት ችግር አለባቸው ያላቸው ከአቡነ ጴጥሮስ ፓስተር ዊንጌት፣ ከ6 ኪሎ ፈረንሳይ ጉራራ እና ከመገናኛ ውሃ ልማት ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሌላ ኮንትራክተር ሊሰሩ ነው።

በነዋሪዎች እና በባለሙያዎች ትችት ሲሰነዘርባቸው የነበሩ እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶችን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ የጥራት ችግር የለባቸውም ብለው ማስተባበላቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

ትድሃር የተሰኘው የእስራኤሉ ኩባንያ እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ሲሰራ በነበረበት ጊዜ ጉቦ በመስጠት እና በታክስ ስወራ ወንጀሎች ተከሶ በቁጥጥር ስር መዋሉም የሚታወስ ነው።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እነዚህን የአፈጻጸም ችግር የሚስተዋልባቸውን የመንገድ ፕሮጀክቶች ነው ዛሬ በራሱ በባለስልጣኑ የራስ ሀይል የስራ ሂደት እና አይ ኤፍ ኤች በተባለ የቻይና ኩባንያ ለማጠናቀቅ የፊርማ ስነስርአት ያከናወነው።

በዚሁ ወቅትም የአቡነ ጴጥሮስ ፓስተር ዊንጌት እና የ6 ኪሎ ፈረንሳይ ጉራራ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ባለስልጣኑ በስድስት ወራት አጠናቆ እንደሚያስረክብ ነው የተገለጸው።

የመገናኛ ውሃ ልማት መንገድ ቀሪ ስራን ደግሞ የቻይናው አይ ኤፍ ኤች ተቋራጭ በ500 ሚሊየን ብር በሰባት ወራት ገንብቶ ለማስረከብ ስምምነት ተፈራርሟል።

በሌላ በኩል የጉርድ ሾላ የመንገድ ፕሮጀክት ተሻጋሪ ድልድይ እና 300 ሜትር ርዝመት ያለው የመቃረቢያ መንገድን ከ171 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለመገንባት እንይ ኮንስትራክሽን ውል ተፈራርሟል።

ባለስልጣኑ የቂሊንጦ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለማስገንባት በጥቃቅን እና አነስተኛ ከተደራጁ 11 የስራ ተቋራጮች ጋርም ስምምነት ተፈራርሟል።
 

%d bloggers like this: