በድርቅ የተጎዳውንና የምግብ ድርሻውን ሊወስድ የሚመጣውን ረሃብተኛ በዕርዳታ ለተገኘ እህል በአባይ ግድብ ሰም ብር200 ማስከፈል በወንጀል ያስጠይቃል!

22 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ሃገሪቱ ለምንድነው ዘወትር በመልካም አስተዳደር ዕጦት የምትቸገረው? ሥርወ መሠረቱ ሥልጣን ላይ ተቀምጦ ከተጠያቂነት ነጻ መሆን፣ የአመራርና የመርህ ድህነት ችግር ነው! 
እዚህ የኢሣት ዜና ላይ የምንሰማው፡ የአንድ 12 ገበሬ ማኅበራት ያሉባት የዳባት ችግር ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ኢትዮጵያ ችግር ነው!

የዳባት ሕዝብ መንገድ እንዲሠራለት ገንዘብ እንዲያዋጣ ከስምንት ዓመታት በፊት ተጠይቆ 200 በሬዎችን አዋጥቶ መስጠቱን ቃለ መጠይቁ ላይ ተጠቅሷል።

በሬዎቹም ለወረዳ አስተዳደሩ ተሰጡ፣ ከስምንት ዓመታት በኋላ ዳዊቱም ዝም ቄሱም ዝም ሆኖ ስለመንገዱ የሚያነሳ ባለሥልጣን የሚያነሳም ሰው የለም!

አሁን ገበሬዎቹ እኛ ለሕወሃት ግብርም አንከፍለም፡ አንድም ባለሥልጣን ለማንኛውም ምክንያት ወደ አካባቢያችን ዝር እንዳይል ብለው አስጠንቅቀው፣ ፍቻያቸውን ግልጽ አድርገዋል!

ማን ይፈርድባቸዋል ከጅቦች ጋር እየኖሩና በየቀኑ እየታለሉ አስቸጋሪውን ሕይወት መግፋት አቅቷቸው ታክስ አንከፍልም ዘራፊዎችም እንዳይቀርቡን ቢሉ?
====================
 

ዳባትም በረሃቧ መጠን ተለከታ እዚሁ ካርታ ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ አደጋ ላይ ትታያለች

ዳባትም በረሃቧ መጠን ተለከታ እዚሁ ካርታ ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ አደጋ ላይ ትታያለች

[ለማጉላት ይጫኑኝ]
 
እዚያው ከዳባት ሳንወጣ፣ በድርቅ ከተጠቁት የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተባበሩት መንግሥታት የዕርዳታ ድርጅቶች በሶስተኛ ደረጃ ተጠቂነት ተመዝግባ የዕርዳታ እህል እንዲቀርብላት እየተደረገ ነው።

የሚያሳዝነው ግን ሕዝቡ በድርቅና በርሃብ ተጠቅቶ ባለበት ሁኔታ፣ ከቃለ መጠይቁ ማዳመጥ እንደሚቻለው፡ ገበሬው የዓለም መንግሥታት ያዋጡለትን የምግብ ዕርዳታ ለመቀበል ሲመጣ፡ ለአባይ ግድብ ማሠሪያ ብር 200 በነፍስ ወከፍ ካልከፈለ 20 ኪሎ ማሽላው እንደማይሰጠው ግልጽ እንደተደረገለት በቃለመጠይቁ ተነስቷል!

ምነው የውጭው ዓለም በሕዝባችን ላይ በመጣው ድርቅና ርሃብ ምክንያት ርህራሄውን ሲያሳይ፡ የሕወሃትን ሰዎች ልብ ድንጋይ አድርጎ አሁንም የሚታያቸው ዘረፋ ብቻ ሆነ?
=====================
 
የሕወሃት ሰዎች በሕዝቡ ላይ ሌላው ቀርቶ በሚዲያና በአደባባይ ሲባልጉ በክልል ደረጃ ያሉት ተክሎቻቸው ደግሞ እንዴት የሕዝቡን ልብ እያቆሰሉ፡ ራሱን እየረገጡት እንደሚኖሩ ምንም ጥርጥር የለውም። ማስረጃ ቢያስፈልግ፡ አባይ ፀሃዬ የአዲስ አበባ ዙሪያ መሬትን ለመዝረፍና ለማዘረፍ ስላለበት ኃላፌነት እንዴት ሕዝቡን እንደሚረግጥና እንደሚያስረግጥ በኦዲዮ ያለው መረጃ ይታወሳል! ወኔ ስሌለው በቪዲዮ እኔ አላልኩም ብሎ ካደ!

ሌሎቹ ምን ያህል አስከፊ ወንጀሎችን እንደሚፈጽሙ መዘንጋት የለበትም!
 

One Response to “በድርቅ የተጎዳውንና የምግብ ድርሻውን ሊወስድ የሚመጣውን ረሃብተኛ በዕርዳታ ለተገኘ እህል በአባይ ግድብ ሰም ብር200 ማስከፈል በወንጀል ያስጠይቃል!”

  1. Shawel at 03:47 #

    More and more sons of farmer parents are being disobedient to their parents which is making the problem worse than it already is. Many children of farmers left their elderly parents to starve while they go in exile with no form of communication from their destination. Family councilors need to engage fully in dialogue to bring this epidemic of communication break down at an early age between fathers and sons . Sons of farmers within Ethiopia need to be heard and their issue need to be adrresed concentrating on why they choose not to communicate with their own birth parents to reverse the severity of the problem.

    Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: