የኦርቶዶክስ ገቢ በቢሊዮን ቢቆጠርም የምዕመናኑ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ካድሬው ፓትሪያርክ በተሰበረ ልብ ለሕዝብ ይፋ አደረጉ

25 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትታወቀው የታረዘውን በማብላትና ማልበስ፡ መንፈሱ የተሰበረውን በመደገፍና በማፅናናት፡ የተረገጠውን ከለላ በመስጠት ሲሆን፡ ካድሬዎቹና ዓለማውያኑ አቡኖች ጳውሎስና ማቲያስ፡ የዘር ፖለቲከኞች ከመሆናቸው በማሻገር፡ ኢትዮጵያውያንን ለአደጋና የጨቋኙን የሕወሃት መሣሪያ ሆነው የማገልገል ተልዕኮ ነበራቸው፤ አላቸውም!

የኢትዮጵያይቷ ቤተ እምነት የራስፑቲን ቅጂ በነበሩት በአቡነ ጳውሎስ ዘመንም ቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ ብልግና አይታለች፤ ውርደትም ደርሶባታል። ከነዚህም መካከል – – ልክ ሕወሃት እንደሚያደርገው – በሌሊት አቡንን አሳፍኖ እስከ ማስደብደብና አቋም እስከማስቀየር ድረስ?

ይህች ቤተ ክርስቲያን በእውነትም የክርስቶስ፡ የማርያምና የሐዋርያው ጳውሎስ ነበረችን? ናትስ?

በተመሣሣይ መንገድ፡ ከዚህ በፊት በዚህ ገጽ ላይ በትክክል እንዳስቀመጥነው፡ በትረ ወንበሩን በተረከቡ ማግሥት ነው አቡነ ማትያስ በማኅበረ ቅዱሳንና ኢሣት ላይ ዘመቻ የጀመሩትና። ያለፈውን በጭንቅላታችን ይዘን ነው፡ ይህንን እንደተመለክትን ነው አስከፊውን የአቡኑን ተግባር በተመለከተ ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችን በተለያዩ ጊዜዎች ለማውጣት የተገደድነው – ለምሣሌም ያህል ሲመታቸውን በተመለከተ፡ የዘር ፖለቲካ ይገፋሉ የሚል ስሞታ በሠፌው በተናፈሰ ወቅት፡ ወጣቱን ከቤተ ክርስቲያን ማሳደድ ሲጀምሩ፡ ወዘተ የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ሲኖዱ የሚከተሉትን ዕገዳ በአቡነ ማትያስ ላይ በጣለባቸው ወቅት፣ ካድሬው ፓትርያርክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው! የዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ውሎ በድንገት ተቋረጠ በሚል ስለግለሰቡ ማንነት በደንብ የሚያስጨብጠውን፣ እንዲሁም ሲኖዱ የጣለባቸውን ዕገዳ የያዘውን ጽሁፋችንን ከሲኖዱ ውሳኔ ጋር አውጥተናል፦

  *   “ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡” /ቅዱስ ሲኖዶሱ/

  *   “በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡

  *   “ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡”

  *   “ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!”

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን ቤተ ክርስቲያኗን መተው ጀመረ ይሆን?

ምናልባትም፡ አማኒያኑ ከቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊ መልክ ካድሬዎቹን ላለማየት አንሄድም ብለው ይሆናል እንጂ – ከኢትዮጵያ ታሪክና ባህል ጋር የተቆራኘችው ቤተ ክርስቲያን – በአማያኑ ልብ ውስጥ እንደምትኖር ጥርጥር የለኝም!

አሁን የአቡነ ማትያስና – እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ሁሉ – ዙርያቸው እንዲከቧቸው የተደረጉት የደኅንነት ሰዎችም በዋና አማካሪዎቻቸው ስም፡ በዘር የተመለመሉ ናቸው – የእርሳቸው ይሻላል ከጠ/ሚሩ በዝርያም አንድ ናቸውና! ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው አማካሪ ተብሎ ከተቀመጠለት የሕወሃት ተወካይ (አሁን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር) በቅርብ መመሪያ እየተቀበለ ይሠራ ነበር እንጂ አንዳች ሃሣብ በራሱ አፍልቆ (ደግነቱ እርሱም ስለሌው) ስለማይሠራ ጸጸት ይኖረዋል ብዬ አልገምትም።

ይህን ሁሉ በሕወሃት ስም በቤተ ክርስቲያኗ የሚያቀነባብሩት የሥልጣን ደላላው ስብሃት ነጋና የስኳር ፕሮጄክታችንን ገንዘብ የዘረፈው ዐባይ ፀሃዬ ናቸው። እነዚህ ኅሊናቸው የደነዘዘ ግለሰቦች፡ ለሃገራቸው ፍቅርና ክብር የቆሙትን ምዕመናን በማሳደድና በረሃ እንዲገቡ በስማድረግ፣ መነቃነቅ ያልቻሉትን በእሥር ቤት በማጎር አልያም በምሥጢር በማስገደል በሃገራችንና በዓለም ላይ ከሁለቱ ቀደምቶች ቤተ እምነቶች አንዷ የሆነችው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን ለማስጠፋት የሞከሩት ደባና ወንጀል በቀላሉ የሚገመት አይደለም!

አማንያኑ ገንዘብ አዋጥተው ሲሰጡ ዋነኛ ተጠቃሚዎቹ አቡነ ጳውሎስ፡ አሁን ደግሞ አቡነ ማትያስና ዙሩያቸው የተሠገሠጉት የሕወሃት መልዕክተኞችና ቁራዎች፡ ከፍተኛ የሕወሃት ባለሥልጣኖችና ቤተ ዘመዶቻቸው (የመለስን ሚስትና ዝርያዎቿን ጨምሮ) ሰለመሆናቸው ባለፉት 24 ዓመታት ብዙ ዘግቧል!

አሁን ጳጳሱ ብዙ ቢሊዮኖች ብር አገኘን ግን አማንያን ሸሹን ቢሉ ምን ያስገርማል! ድሮም ቤተ ክርስቲያኗ ድሃ አልነበረችም – መዓት መሬት ስላላት፡ ቤቶች ስለምታከራይ፡ ንግድ ውስጥ ስለገባችና ም ዕመናኑም ከዕለት ጉርሳቸውና ልብሳቸው ቀንሰው በየጊዜው ይለግሷታልና። ሥነ ሥር ዓት ያለው ወጭና ገቢ የሚያሳይ ሌጀር እንኳ ማዘጋጀት የቻለችው በያዘነው 2015 መሆኑ ራሱ የምያሳዝንና የማያሳፍርም ዘረፋ የተካሄደባት ቤተ እምነት ናት!

የዝሙት ርሃባቸው ከፍተኛ በመሆኑ ፈጸሙ የሚባለው ሥጋዊ ተግባር፡ ከሆሊውድ እንጂ ከኢትዮጵያ እምነት ቤት የመጣ አይመስልም! በተለይም አስከፊው በሽታቸው ደግሞ የሚያውቋቸው ግለሰቦች ምሽቶች መሆናቸው፡ አሥርቱት ዕዛዛትን ምን ያህል አርቀው እንዳሽቀነጠሩ የሚያመላክት ነው! ታዲያ አቡነ ጳውሎስ በትዳር ያሉ ሴቶችን ሲያቀያይሩ የነበሩት ቤተ ክርስቲያኗን በመድፈር አልነበረምን?

አቡነ ማትያስ ታሪካዊ የቤተ ክርስትያን ሥፍራዎች በልማት ስም እየታረሱ ነው፤ በየደብሮቹ ምዕመናን ሆነው፣ ከዓለም ርቀው የነበሩ ኢትዮጵያውያን አጽም ያረፉባቸው ሥፍራዎች በሕወሃት አለመከበራቸው ሲነገራቸው – ጥናት እንኳ ሳይስጠኑ – መንግግሥት ይህን የሚያደርገው ለሃገር ልማት ታስቦ ነው ብለው ፋይሉን መዝጋታቸው ታማኝነታችው ለቄሣር መሆኑን በማለዳው አረጋግጠዋል!

ፓፓ ፍራንሲስና ካርዲናል ሱራፌል (ፎቶ ካቶሊክፊሊ)

ፓፓ ፍራንሲስና ካርዲናል ሱራፌል (ፎቶ ካቶሊክፊሊ)

ሰሞኑን ከርሳቸው ለየት ባለመንገድ ፖፕ ፍራንሲስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሾሟቸው ኢትዮጵያዊው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በኢትዮጵያ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ደምረው ሱራፌል ሰሞኑን ሮም ስብሰባ ከተከታተሉ በኋላ ስለኢትዮጵያ ትኩረት የሚሹት ጉዳዮች ተብለው ዜኒት በተሠኘው የካቶሊክ ጋዜጣ ሲጠየቁ የሰጡት አስተያየት (INTERVIEW: Head of Ethiopian Catholic Church: Human Rights Crises Merit More Attention at Synod)፡ ከአቡነ ማትያስ የዝርያ ፖለቲካ ርቀው ስብዓዊነትን መሠረት በማድረግ፡ ሃገሪቱን ጥልቅ ድህነት፡ የወጣቱ በገፍ መፍለስ፡ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ትክክለኛ ትኩረትን እንዲያገኝ የመሥራትን አስፈላጊነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አሥምረውበታል!
 

የአቡኑ የምዕምናን ጠፉብኝ ኃዘኔታ ከልብ የመነጨ? ወይንስ የመቀሌ ጉባዔ ግልባጭ?

  *   “ምዕመናንን የመጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣን አይደለም”

    *”የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ሥራ ለምዕመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ ነው”
  – አቡነ ማትያስ

የሚከተለው ጽሁፍ ከሪፖርተር የተዋስነው ነው
 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰበካ ጉባዔ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር የነበረ ቢሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቢሊዮኖች ብር ማደጉን የገለጹት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ፣ የምዕመናኗ ቁጥር ግን እየቀነሰ መሆኑን አስታወቁ፡፡

ፓትርያርኩ 34ኛውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔን አስመልክቶ ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቤተ ክርስቲያኗ ገቢ በቂ ነው ባይባልም፣ በየጊዜው እያደገ መጥቶ ከመቶ ሺዎች ብር ወደ ቢሊዮኖች ብር አድጓል፡፡ ይኼ የሆነውም ቤተ ክርስቲያኗ ከልጆቿ (ምዕመናን) ከምታገኘው ገቢ ባለፈ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፏ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የምዕመናን ዕድገት የኋልዮሽ እየሄደ መሆኑን የጠቆሙት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ዕድገቱ የኋልዮሽ መሆኑን የሚያውቅ ይኖር ይሆን? ችግሩንስ በሚገባ ተገንዝቦና በቁጭት ተነሳስቶ ችግሩን ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ አለ?›› የሚሉ ጥያቄዎቹን በማንሳት፣ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚቆየው የሲኖዶስ ጉባዔ ምላሽ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የኦርቶዶክሳውያን ተልዕኮ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ መሆኑን ሁሉም የዕምነቱ ተከታዮች፣ በተለይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አባቶች እንደሚያውቁ የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ከህሊና መቆርቆር እስከ ሕልፈተ ሕይወት የሚዘልቅ የመስዋዕትነት ዋጋ የሚጠይቅም መሆኑን መዘንጋት እንደሌለባቸው ለጉባዔው ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡

ባህር አቋርጦ፣ ድንበር ተሻግሮ፣ እስከ ምድር ጽንፍ ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በአገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምዕመናንን ማባዛት ብዙ እንዳልተሄደበት ፓትርያርኩ አስታውቀዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ትናንትና ስመ ክርስትና ሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆቿ፣ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደ ሌላ ጎራ መቀላቀላቸው እየናረ መምጣቱን አክለዋል፡፡

በምዕመናን መጥፋት ልባቸው የተሰበረው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ (ፎቶ ሪፖርተር)

በምዕመናን መጥፋት ልባቸው የተሰበረው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ (ፎቶ ሪፖርተር)

“ለመሆኑ ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምፕ ለመሄድ ለምን መረጡ? የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው? የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት? አስተዳደሩ የማያረካ ሆኖ? የካህን እጥረት? ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው?” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱት ፓትርያርኩ፣ መልሱን የጉባዔው ተሳታፊዎች የሚያውቁት ቢሆንም፣ ለሲኖዶሱ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ ምዕመኗን የመጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣች ባለመሆኗ ባዶዋን ከመቅረቷ በፊት፣ ለተደራጀና ድንበር የለሽ ትምህርተ ወንጌል መነሳት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ሥራ ለምዕመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ መሆኑን የገለጹት ፓትርያርኩ የሃይማኖቱን መርህ ጠብቀው፣ አስተዳደሩ የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጽ፣ ተዓማኒና ተጠያቂነትን ያሰፈነ፣ የምዕመናንን ልብ የሚያረካ ሥራ መሥራት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻው የሕዝብና ቤት ቆጠራ አሥር በመቶ ምዕመናን ቁጥር መቀነሱ የታወቀ መሆኑን፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አበ እምኔት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ፣ በየገዳማቱ የሚኖሩ መነኮሳትና ሌሎች በድጋሚ ቆጠራ የተደረገላቸው ቢሆንም፣ እንዳልተካተተና ለምዕመናኑ ቁጥር መቀነስም ሌላው ምክንያት መሆኑንም የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምርያ ዋና ኃላፊ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጨ ተናግረዋል፡፡ ለምዕመናን ትምህርተ ወንጌልን በማዳረስ አማኙን ለማብዛት እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት መምርያ ኃላፊው፣ በጋምቤላ ክልል በራሳቸው ቋንቋ ወንጌልን በማዳረስ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ ኃላፊዎችን የሃይማኖቱ አባላት ማድረግ መቻሉን አክለዋል፡፡

ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ ቤተ ክርስቲያኗ ጠንክራ እየሠራች መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ትልቅ ሙስና ይፈጸምበታል የሚባለው የቤተ ክርስቲያኗ ሰፋፊ መሬት ጥናት ተደርጐበት መጠናቀቁን አስረድተዋል፡፡

በተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጥፋት ፈጽመው ሲገኙ፣ ከአንዱ ቤተ ክርስቲያን ተነስተው ወደ ሌላ መዘዋወራቸው ቀርቶ ሙሉ በሙሉ የሚባረሩበት፣ በዘር፣ በመግባባትና ያለችሎታ የሚመደቡበት አሠራር ቀርቶ፣ በዕምነቱ ጥንካሬ፣ በላቀ ዕውቀት ምዕመናኑን በአግባቡ ሊያስተምር የሚችል የታመነበት አስተዳዳሪ የሚሾምበት አሠራር መዘርጋቱን የመምርያ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
 

%d bloggers like this: