በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ደረጃ ሕወሃት የአሜሪካ ድምጽን በምሽት በዕለተ ቅዳሜ በጥርቆ እምብርቱ ውስጥ ሲገባ ሣር ፈላጊ በግ ሆኖ፣ ወይስ የተለመደ የሚዲያ አፈና ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ?

28 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

አበበ ገላው እንደገለጸልን ከሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ መንግሥት ሃብትና የፕሮፓጋንዳ መሣሪያው በሆነው በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የተገኙትና የአማርኛ ፕሮግራሙ ጋዜጠኞችን የሰበሰቡት ቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም.ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ሶስት ሰዓት ነበር። በሌላ መንግሥት የደህነንትና መረጃ መሣሪያ በሆነው ሃብትና ንብረት ውስጥ ምን ይሠሩ ነበር የሚለው ቀዳሚ ጥያቄ ነው!

ለነገሩ ይህንን ጥርጥር ከሚያእጥናክሩት ጉዳዮች አንዱ፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ማናቸውም በዚያ ስበሰባ ላይ የተገኘ ግለሰብ (የአሜርካ ፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች) በምሽቱ የተደረገውን ውይይት መሰል አመራር አሰጣጥ ሪኮርድ አንዳይዘግብ መከልከላቸው ነው! የአሜሪካ መንግሥት ወይንስ ግንቦት ሰባት እንዳይሰማ?

የአበበ መረጃ ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ፡ ሚኒስትሩ ቃለ መጠይቅ ይሰጡ ነበርን? ከሆነስ ዜናውን ለኢትዮያና ለዓለም ሕዝብ የሚሠጡት መረጃ ቋንጣ እንዳይሆን፡ እስካሁን በተለያየ መልኩ በጽሁፍ ወጥቶ ልናነበው በቻልን ነበር? ምናልባትም ዶኪመንተሪ ከሆነ ይሠሩ የነበሩት፡ አንዳንድ ፍንጮች ወጥተው እስክሁን ብዙ በሰማን ነበር! ነገሩ አይደለምና በጋዜጠኛው የተነሱትን ጥርጥሮች ባለጭብጥ ያደርጋቸዋል።

ይህንንም የሚያሰኘኝ የአበበ ጠቋሚ ጥርጥሮች ብቻ ሳይሆኑ፣ እንዳጋጣሚ ሆኖ ሪፖርተር ላይ “ልማታዊ ዴሞክራሲ መቶ በመቶ ፓርላማውን ከተቆጣጠረ በኋላ ያነጣጠረበት ሌላው ዘርፍ” በሚል በመለስ ዜናዊ ሃሣብና ዓላማ ላይ ተመሥርቶ የተጻፈው አርቲክል ነው።

መለስ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ – ሪፖርተር እንደጠቀሰው – የሚከተለውን ዓላማ ለፓርቲው አስቀምጧል፦

    “ምርጫ 2002 በአገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊ አካኋን ፀረ ሕገ መንግሥት ኃይሎችን ማርጅናላይዝ (ጥግ ማስወጣቱ) ማድረጉና ተመልሰው የሚያገግሙበትን ዕድል በጣም ጠባብ መሆኑን ማረጋገጡ አንድ አዲስ ስትራቴጂካዊ ምዕራፍ መጀመሩን ያሳያል…በምርጫ 2002 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ የማይሆኑበት ደረጃ ላይ ስላደረስናቸው ሥራችን ተጠናቋል አልቋል ማለት አይደለም፡፡ ፀረ ሕገ መንግሥታዊ አቋማቸውን እስካልቀየሩ ድረስ መብታቸውን በጥብቅ አክብረን በማያቋርጥ ዴሞክራሲያዊ ትግል አሁን ከደረሱበት ደረጃ እንዳያልፉና እንዳያንሠራሩም በርትተን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡”

ይህም ጥልቅ ምርምር የያዘ ሃሣብ ሳይሆን፡ የመለስ ጥረትና ዓላማ በትግራይ ሕዝብ ስም፡ ማጠፊያው እንኳ ሲያጥርባቸው እንዴት አድርገው በትግራይ ሕዝብ ስምና ለዚሁ በተቋቋመው ‘ነጻ አውጭ ግንባር’ (ሕወሃት) አማክይነት ሁሉን አተራምሰው ሥልጣን ላይ መቆየት ነው!

ሪፖርተር ይህንኑ መሠረት አድርጎ ኤኮኖሚው ላይ ተመሥርቶ የመለስን ዓላማ ሲያብራራ እንዲህ የሚከተለውን ሃሣብ ያስቀምጣል፦

    “በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሥርዓቱ ማኅበራዊ መሠረቶች ሰፊው የአርሶና የአርብቶ አደር ማኅበረሰብ፣ በከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች፣ ላብ አደሮች፣ በመንግሥት ሥራ ላይ የተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ልማታዊ ባለሀብቱ መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለው የኢኮኖሚ አሠላለፍ ሲመረመር አሠላለፉ ልማታዊ የዕድገት አማራጭ አስፈላጊነት የግድ የሚልበት ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ይገልጻል፡፡

    በዚህ የልማታዊ ዴሞክራሲ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ውስጥ የኒዮሊበራል የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲን ይዞ መቀጠል አዋጭ እንዳልሆነ ረቂቁ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኒዮሊበራል አቅጣጫ ለጥቂት ቱጃሮች ጥቅም የቆመ በመሆኑ፣ ዋነኛ የሕዝብ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል የሚችልበት ዕድል ከአፈጣጠሩና ከሚወክለው ማኅበራዊ መደብ አንፃር ጠባብና ዝቅተኛ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍን ቀጣይ አቅጣጫ ለመተለም ከገዥው የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት መሠረታዊ አቅጣጫዎችና ከማኅበራዊ መሠረት አወቃቀር ጋር የተመጋገበና የተጣጣመ ሆኖ የበላይነቱን ይዞ መቀጠሉ የማይቀር መሆኑን ይገልጻል፡፡

    በመሆኑም በኢትዮጵያ በቀጣይ እንዲፈጠር የሚፈለገው የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መገናኛ ብዙኃን ተልዕኮ አብዛኛው ሕዝብ በመሠረታዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ አመለካከት እንዲይዝ ወቅታዊና ተከታታይ መረጃዎችን በማሠራጨት የሕዝቡን በመረጃ ላይ የተመሠረተ ንቅናቄና ሁለገብ ንቁ ተሳትፎ እንዲቀጣጠል ማድረግ ነው ይላል፡፡ በዚህም ሕዝቡን ለልማት፣ ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ተግባራዊነት ማነሳሳት አንደኛው ነው፡፡ በሌላ በኩል በአፈጻጸም ሒደት የሚከሰቱ ድክመቶችንና ውስንነቶችን ነቅሶ በማውጣት፣ ችግሮቹንና ውስንነቶቹን ከነምንጮቻቸውና የመፍትሔ አቅጣጫዎቻቸው ተንትኖ በማስቀመጥ፣ የሥርዓቱ ፖለቲካዊ ጤንነት ተጠብቆ እንዲጓዝ የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኖ ማገልገል እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ “

በዝርዝር ለመከታተል፡ የአበበ ገላውን ጹፍ እና የሪፖርተርን አስተያየት እዚሁ ማንበብ ይችላሉ።
 

%d bloggers like this: