በሱዳን መሪዎች ግፊቱ ተጠናክሮበት፣ ድንበር በማካለል ስም ሕወሃት 250ሺ ስኩዌር/ኪ የኢትዮጵያን ድንበር መሬት ለሱዳን ሊስጥ ነው!

25 Nov

የአዘጋጁ አስተያየት:

  ጉዳዩ የተያዘውና ምክክሩ የተካሄድው በሕወሃት አመራር ደረጃ እንጂ በኢሕአዴግ ውስጥ አይደለም።

  ከሱዳን ጋር በሰላም መኖር ለሕወሃት የተከታታይና ቀጣዩ የሥልጣን መሠረት በመሆኑ፡ ሱዳን የምትፈልገውን የድንበር መካለል እንፈጽምና እንገላገል ያሉ ይመስላል። ሰሞኑን በወጣው ዜና ውይይቱ የኢኮኖሚ ትሥሥር ቢያስመስሉትም፡ አዲሰ አበባ ላይ ውይይቱ በሕወሃት በኩል የተመራው በደህነነትና ተወካዮችና መገናኛ፣ መረጃና ቴኮኖሎጂ ሚኒስትሩ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መሆኑን ካርቱም ሮድ የተሰኘው መጽሔት ቀደም ብሎ ፍንጭ ፍንጭ ሰጥቷል።

  ዛሬ ደግሞ ሪፖርተርም የዚህን ጭብጥ አግኝቶታል፤ እንዲህ ሲልም ዘግቧል፦

   “የሱዳን ሁለተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሳቦ መሐመድ አብዱልራህማን ኅዳር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር መወያየታቸውን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው የኢትዮጵያ ብሮካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢገልጽም፣ ከውይይቱ ጭብጦች መካከል የድንበር መካለሉን ጉዳይ አልጠቀሰም፡፡ ይሁን እንጂ የቴሌቪዥን ጣቢያው የሁለቱ አገሮች የጋራ ኮሚሽን ነፃ የኢኮኖሚ ዞን፣ አመቺ ነፃ የንግድ ሥርዓትና የባንክ ትብብር ለማድረግ መስማማቱን ዘግቧል፡፡”

   

  የነጻ ኢኮኖሚክ ዞን ከሶስት ወራት የባለሙያዎች ጥናት በኋላ እንደሚከናወን ዶር ደብረጽዮን ተናግረዋል። ይህ ሽፍንፍን ያስፈለገበትን ምክንያት ኢትዮጵያውያን ልብ ሊሉት ይገባል!

  ይበልጥ ሕወሃትም ኢትዮጵያውያንን ሊንቅና እርጋጫውን ሊያጠናክር የሚችለው፡ ሃገራችንን እንወዳለን እያልን ይህንን ውንብድና ይሁን ብለው ዝም ያሉት እንደሆን ነው!

  ዋናው ነገር፣ በሱዳን በኩል የኢትዮጵያ ገበሬዎች መሬታችንን አሳልፈን አንደጥም በማለት የሚይካሄዱት የጥቃትና መከላከል ሁኔታ በመጠናከሩ ሱዳንን እጅግ አሳስቧታል። ሱዳንን መሬት ለተቃዋሚዎች መጠቀሚያ እንዳይሆንየካርቱም እንድትዘጋባቸው ለማድረግ የታቀደ ስለሆነ፣ ባለቢትነቱ ለ110 ዓመታት ያህል በስምምነት ያልተፈታውን ድንበርና ሁለቱም የባለቤትነት ጥሪ እንዳሰሙ ሳለ በድንገት ከ2005 ምርጫ መደናገጥ በኋላ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን መሬት አሳልፌ ሰጣለሁ በማለት በክህደት በገባው ቃል መሠረት እንዲፈጸም፣ ሱዳን ግፊቷን አጠናክራለች!

  ዋናው ጥያቄ የኢትዮጵያ ገበሬ በአንድ በኩል በሱዳን ጦር በሌል በኩል ደግም በአጋዚ በስተጀርባ እየተዋጋ ዳር ድንበሩን ለማስከበር ሲታገል፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዝም ብለው ይመለከቱታል ወይ? ይህ እንዲሆን ሌላው ኢትዮጵያዊውስ ለቆመባትና ለሚቀመጥበትስ መሬት ምን ዋስትና አለው?

  የሕወሃት ዓላማ ከነገዋ ነጻይቱ ትግራይ ጋር የተያያዘ ነው!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

– የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ መረጃ የለውም – በኬንያ ድንበር የተፈጠረው ግጭት የተለመደ ነው ብሏል

የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን የማካለል ሥራ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መግለጻቸውን፣ ሱዳን ትሪቡን የተባለው የሱዳን ድረ ገጽ ዘገባ አመለከተ፡፡

የሱዳን ሁለተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሳቦ መሐመድ አብዱልራህማን ኅዳር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር መወያየታቸውን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው የኢትዮጵያ ብሮካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢገልጽም፣ ከውይይቱ ጭብጦች መካከል የድንበር መካለሉን ጉዳይ አልጠቀሰም፡፡ ይሁን እንጂ የቴሌቪዥን ጣቢያው የሁለቱ አገሮች የጋራ ኮሚሽን ነፃ የኢኮኖሚ ዞን፣ አመቺ ነፃ የንግድ ሥርዓትና የባንክ ትብብር ለማድረግ መስማማቱን ዘግቧል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ከማል አልዲን ኢስማኤል ለሱዳን ትሪቡን ገለጹ እንደተባለው ግን፣ የሱዳን ሁለተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ሐሳቦ መሐመድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር በተወያዩበት ወቅት ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የድንበር ማካለል ይገኝበታል፡፡

ከዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር የድንበር ማካለሉ የሚከናወንበትን ወቅት የሁለቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች እንዲወስኑ ተስማምተው ነበር፡፡

ማካለሉ የሚከናወነው በተለይ ሁለቱ አገሮች በአማራ ክልል ውስጥ በሚዋሰኑበት ድንበር የሚገኝ 250 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ በሱዳን በኩል የይገባኛል ጥያቄ በመኖሩ ነው፡፡

የድንበር ማካለሉ ሥራ በታኅሳስ ወር ይጀመራል ቢባልም፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የሱዳን ሁለተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት በዚህ ጉዳይ ላይ ስለመወያየታቸውም ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር በተቀሰቀሰ ግጭት ሦስት የኬንያ ፖሊሶች መገደላቸውን ተከትሎ፣ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን የኬንያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡

ዘ ሲትዝን የተባለው የኬንያ ጋዜጣ እንደዘገበው ሦስት የኬንያ ፖሊሶች በኢትዮጵያ ወታደሮች ከተገደሉ በኋላ፣ የኬንያ የመከላከያ ኃይል ሶሎሎ በተባለችው የኬንያና የኢትዮጵያ ድንበር እንዲሰማሩ ተደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች ግድያውን የፈጸሙት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላትን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት መሆኑን ዘገባው ያመለክታል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ፣ በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ ያለው ግጭት በተደጋጋሚ የሚከሰት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው ያሉ አማፂያን በሁለቱም አገሮች ድንበር በመዝለቅ የሚፈጽሙት ችግር እንደሆነ፣ ይህንን ችግር ለመፍታትም የሁለቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎች እየተወያዩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህ ችግር ጠንካራ በሆነው የኢትዮጵያና የኬንያ ወዳጅነት ላይ ተፅዕኖ ሳይፈጥር መስተካከል የሚችል መሆኑን የገለጹት አቶ ተወልደ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ አሸባሪ የሆነውን አልሸባብን ለመታገል የተሠለፉ አገሮች መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡
/ሪፖርተር
 

Related materials:

  Ethiopia, Sudan approve to launch free trade zone

  Turmoil on Ethio-Sudan border

  Yet again, another evidence of TPLF handing over of Ethiopian farmlands to Sudan

  CRY MY BELOVED COUNTRY! Ethiopian group kills 16 Sudanese farmers: TPLF’s trade in nation’s sovereign territory with Sudan for Front’s permanence in power backfires

  Ten Sudanese soldiers reportedly killed by ‘unidentified militia’ along Ethiopian border

  Choking landlocked Ethiopia signs agrt with Sudan to use Port Sudan in its foreign trade; Djibouti nationals given special status

  Open Letter to UN Sec.-Gen. Ban Ki-Moon by Ethiopian Borders Affairs Committee

 

%d bloggers like this: