ሕወሃት ‘አሸባሪ’ ብሎ ለማጥፋት የሚሻቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላት ሰለኢትዮጵያ ድርቅ መግለጫ ሰጡ፤ ግንባሩ ትምህርት አግኝቶ ይሆን?

3 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)


 

ተ.መ.ድ. ኅዳር 30/2015 ባወጣው ዘገባ የሚከተለውን ገልጿል፦

    “The impact of the failed spring belg (mid-February-May) rains was compounded by the arrival of the El Niño weather conditions that weakened summer kiremt (June-September) rains, whose harvest feeds 80 to 85 per cent of the country. This greatly expanded food insecurity, malnutrition and affected livelihoods across six regions of the country. The level of acute need across virtually all humanitarian sectors has already exceeded levels seen in the Horn of Africa drought of 2011 and is projected to be far more severe throughout an 8 to 10 months period in 2016.”

ሃገሪቱንና ሕዝቧን ላጋጠማት ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ፡ ድርቁና ርሃቡ በገጽታው ላይ ስለሚኖረው ጉዳት በመወጠሩ፣ ሕወሃት ሰሞኑን ለግብረ ሠናይ ድርጅቶች መመሪያ መሥጠቱ ይነገራል፡ ለአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከሃገር ውስጥ ባገኘው መረጃ መሠረት እንደዘገበው።

መመሪያው የሚከተለውን ፍሬ ሃሣብ ይዟል፦

    “NGO’s are being warned not to use the words “famine, starvation or death” in their food appeals. Neither are they to say that “children are dying on a daily basis,” or refer to “widespread famine” or say that “the policies of the government in Ethiopia are partially to blame.” Neither are they allowed to “compare the current crisis to the famine of the eighties.” Instead, the latest drought in Ethiopia is to be described as “food insecurity caused by a drought related to El Nino.””

በማየት ብቻ የሚያምኑ ይመስል፡ የሕወሃት አመራሮች ከኢትዮጵያ ችሎታ ውጭ የሆነ ድርቅና ርሃብ ሃገሪቱ ውስጥ የለም ሲሉ እስከ ኅዳር 16/2015፣ ማለትም ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳልተሽሞነሞነበት ሁሉ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ከሁለት የሪፖርተር ጋዜጠኞች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ከሁለት የሪፖርተር ጋዜጠኞች ጋር ኅዳር 29 ባደረገው ቃለ መጠይቅ የሚከተለውን የአመለካከት ለውጥ አድርጓል – የፖሊሲና የአሠራር ለውጥ ማድረጉ ባይታወቅም።

ለውጡ በሚከተለው አባባሉ ውስጥ የታቀፈው ነው፡-

    “በኢትዮጵያ ውስጥ በእንዲህ ዓይነት ስፋት ድርቅ ተከስቶ አያውቅም፡፡ ይሄ ድርቅ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከተከሰተው ድርቅ ሰፋ ያለ ነው፡፡ የሸፈነው አካባቢም በጣም ሰፊ ነው፤ ስለዚህ ጉዳዩ የቁጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ ማንም የማይቆጣጠረው ሰፊ አካባቢ በድርቁ ተጠቅቷል፡፡”

 

%d bloggers like this: