የሞያሌው ኮሌራ ወደ መሃል ኢትዮጵያ በመዛመት ላይ ነው ይባላል! የሕወሃት ጦር እንደገና ኬንያን እስኪወር ለጊዜው ስላም መውረዱም ይነገራል!

7 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ባለፉት አሥር ቀናት ሞያሌ በኮሌራ የተመታች ሲሆን፡ በሽታውም ከጠረፍ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ መሃል ሃገር የመዛመት ምልክቱ ቢታይም፡ እስካለፉት ሁለት ቀናት ድረስ መውረዱም ይነገራል በኩል ምንም እርምጃ እንዳልተወሰደ ይነገራል።


 
በተጨማሪም፡ ላለፈው አንድ ወር የኢትዮጵያና የኬንያ ድንበርም፡ ሕወሃት የመልካም ጉርብትና መርህ ከሚፈቅደው ውጭ፡ የኬንያን ድንበር በወታደራዊ ኃይል በመጣስና በመግባት ከመውረሩም ባሻገር፣ እስከ አሥር የሚደርሱ የኬንያ የድንበር ፖሊሶችን መግደሉ በተለያዩ የኬንያ ጋዜጦችና ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል።

የዚህ ዐይነቱ ተግባር በሕወሃት በኩል በተደጋጋሚ ሲካሄድ ቆይቷል። የግንቦቱ 2015 ምርጫ ሲካሄድም፡ የኦሮሞ ተግንጣዮችን በማሳደድ ስም ለወራት የኬንያን የድንበር ከተሞች ይዞ እንደነበር ይታወሳል። ከዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ፣ የሕወሃት ጦር የኬንያን ግዛት በ ኢሌሬት፡ ሶሎሎና ሞያሌ (Illeret, Sololo and Moyale) ሶስት ወረራዎች ፈጽሟል ይላሉ ኬንያኖቹ!

ኬንያም ራስን መክላከል በሚለው መርህ መሠረትወታደሮቿን በአስቸካይ ድንበሯ ላይ አሥፍራለች። ይህም ሁኔታ ወንድም የሆነውን የኬንያ ሕዝብ አላስቆጣውም ማለት አይደለም – ዘ ስታንዳርድ እንደዘገበው።

ከብዙ ምልክቶቹ በጥቂቱ እንኳ የቅርቡን ወረራ በሚመለከት፡ የደቡብ ሶሎሎ ባለሥልጣን የሆኑት ሙሃመድ ዓሊ እንደተናገሩት ከሆነ፣ የሕዝቡ ውስጥ ለውስጥ ቁጣ ጠንካራ ነው። ለማዕከላዊው መንግሥት ደውለውም ዓሊ እንዲህ ነበር ወረራውን የገለጹት፦

    “We are a sovereign state and this (invasion) is bad because Ethiopia is considered a friendly neighbour. It is high time our government sends a strong signal to them”.

================
 

የኮሌራውን ሁኔታ በሚመለከት፡ አንድ ነገር ትዝ ይለኛል። በዓለም አቀፍ ትብብርና ፕሮቶኮል መሠረት አንድ ተላላፊ በሽታ አንድ ሃገር ውስጥ ሲከሰት፡ በአስቸኳይ ሃገሮች የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን (WHO) እንዲያስታውቁ ይጠበቅባቸዋል። እስካሁን በኢትዮጵያ በኩል በሽታው በግዛትዋ ውስጥ መዛመቱን ለሕዝቧ ባታሳውቅም፡ ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ግን በዚህ በኩል ዓለም አቀፍ ግዴታዋን ተወጥታለች ብለን ለደቂቃም ቢሆን መገመት እንወዳለን!

ለዚህ ይመስለናል – ማለትም በኢትዮጵያ በኩል ለሃገር ውስጥ እንክብካቤ በቂ እርምጃ ባለመወስዱ – የተባበሩት መንግሥታት የጤና ጥበቃ ድርጅት – ኢትዮጵያ ውስጥ ከድርቁ ጋር በተያያዘ፡ የተለያሉ ዐይነት በሽታዎች ይከሰታሉ በሚል ሰበብ ስሞኑን መድሃኒቶችና የጤና ጥበቃ ባለሙያዎች ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የተባበሩት መንግሥታት የዘገበው።

ኃላፌነት የሚሰማው መንግሥት ሁሉንም ነገር ሸፋፍኖና ደብቆ የሕዝብን ዕልቂት ከመጋበዝ ይልቅ፡ ለሕዝቡ እውነቱን በግልጽነት ተናግሮ፡ ሌላው ቢቀር ፍራፍሬ በጥሬው እንዳይበላ፡ ውሃ ክተቻለ እንዲያፈላና እንዲጠጣ፡ አልያም ንጹህ ውሃ በማቅረብ መታደግ ተገቢ ነበር። በሕወሃት እጀ ሰባራነት ምክንያት ሕዝባችን ሊታደል አልቻለችም!

ሕወሃት ቅንጣት የመንግሥትነት ባህሪና ይህን የማድረግ ብቃት ስለሌለው፣ ድብብቆሽ እየተጫወተ ሕዝቡን ረግጦ ለመግዛት ብቻ ቀና ደፋ ሲል ይታያል!

በመሆኑም፣ ሃገራችን መልካም አስተደደርና ሕዝብን በማገልገል ተኮር የሆነ ፖሊስ ኖሯት አያውቅም፤ አሁንማ ይባስ ብሎ አገዛዙ ወደ ቦጫቂ ጅብነት ተለውጧል!
===============
 

በሁለቱ ሃገሮች መካከል ወደ ግጭት ዞሮ የነበረውን ግንኙነት ለማሻሻል፡ በኬንያ ታጋሽነት ምክንያትና በተባበሩት መንግሥታት ደርጅቶ ፕሮግራም አዘጋጅነት ኢትዮጵያና ኬንያ በዛሬው ዕለት በ$197 ሚሊዮን ወጭ የአካባቢውን ሕዝብ የኤኮኖሚ ችግሮች ለማስወገድና ትብብር ለመፍጠር መስማማታቸውንና መፈራረማቸውን የዜና ማሠራጫዎች ዘግበዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ሃገሮች አስተዳደሮች መልካም ምኞታቸውን ገልጸው፣ በማርሳቢት ግዛትና በኢትዮጵያውያን ቦረናዎች መካከል ወደፊት ግጭት እንዳይነሳ መታሰቢያ አኑረዋል

ዋናው ጥያቄ ግን ኬንያ ጎረቤት ሃገር እንደመሆኗና በተለይም እስከዛሬ ለኢትዮጵያ አንዳችም የፖለቲካ ችግር የማትፈጥርባት ጎረቤት መሆኗን በተግባር ያስመሰከረች ሆና ሳለ፣ በተደጋጋሚ ሕወሃት በዚያች ሃገር ላይ የሚፈጸመው ውንብድናና ወረራ ዘላቂ የሥጋት ምንጭ ነው! ለነገሩ ዛሬ እንዳሁኑ አንድ ስምምነት ይደረስ እንጂ – በኬንያ ታጋሽነት ምክንያት – ሕወሃት የመልካም ጉርብትና መርህን የማይከተል ሌሎች ብልግና በኬንያ ሊፈጽም መቻሉ ጥርጥር ውስጥ መግባት የለበትም።

በሌላ በኲል ደግሞ፡ ሁለቱ ሃገሮች በኢትዮጵያ ተጽዕኖ ኦርሞችንና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ኪንያ ውስጥ ሰላም በማሳጣትና ለማጥቃት ተጨማሪ ስምምነት መፈራረማቸውን መገመት ይቻላል።

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ይህንን የፖለቲካ ችግር በሚመለከት የሠነዘርነውን አስተያየት ጠቃሚነት እያስታወስን፣ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯ ሥር ሠዶ ሃገሪቷን ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ ሊፈለግበት ሲገባ፣ ጎረቤት ሃገሮች ውስጥ ጠላቶቼ አሉ በሚል ፈሊጥ፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን መፈጸም፣ ወይንም ዓለም አቀፍ ሕግ የሚቃወማቸውን የአፈና ተግባሮችን እንዲፈጸሙ ማድረግ፣ ወይንም ከሱዳን ጋር እንደሚደረገው የኢትዮጵያን መሬት ሸራርፎ በመሥጠት ሌሎችን ሃገሮች የሕወሃት ወንጀሎች ተባባሪ ማድረግ በሕግ ደረጃ ከተጠያቂነት ማምለጥ አያስችልም።

ይህ ሁኔታ የሕዝቦችን ሰላማዊ ግንኙነት ከማሻከርም አይገታም!

ለዚህም ዋናው ምክንያት፡ ሕወሃት በጎረቤቶች ላይ – በተለይም ኬንያ ላይ – እየፈጸመ ያለው ብልግና ማንነቱን ያሳያል። ይኸው ባህሪው ነው ለኢትዮጵያውያን መብቶች መረገጥና ለሕዝባችንና በሃገራችን ላይ ልዩ ጠባሳ እየሆነ የመጣው!
 

%d bloggers like this: