ሕወሃት በቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ እስከ ቅዳሜ ጎንደር ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል

14 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ታህሳስ 12 ቀን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ከ80 በላይ መሞታቸውንና የሃገሪቱ ሁኔታ በጣም እንዳሳሰባት ጠቅሳ፡ የማዕቀብ እርምጃ ቡጁምቡራ ላይ እንደምትወስድ አሰምታለች።

ታዲያ አሜሪካ ምንም የሕወሃት ወዳጅ ብትሆንም፡ ሃገሪቱ ውስጥ በተለይም በቤተ እምነት ውስጥ ቦም የሚወረውረውን፤ ኦሮሚያ ወጣት ተማሪዎችን በየቀኑ የሚረሽነውን አሸባሪ አስተዳደር፡ በአልሸባብ ምክንያት በጸጥታና በትዕግሥት መመልከቷ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ግራ እያጋባ ነው!

አሜሪካ በሶማልያ ባለው ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ባላት ግንኙነትም ምክንያት ሃገሪቱ ከመፍረስ እንድትረፍ፡ ሕዝቡም የሞሶሎኒነና የሂትለርን ፈለግ ከሚከተለው ሕወሃት መታደግ ይኖርባታል። ዛሬ የም ዕራብ ሃገሮችን ድጋፍ ለማግኘት፡ ሕወሃት ኢትዮጵያ ለአሸባሪዎች የተጋለጠች ለማሰመሰል፡ ብዙ ወንጀል በሃገሪቱ ላይ ሊፈጸም ስለሚችል በኢትዮጵያ ሕዝብም ህነ በውጭ መንግሥታት በኩል ሁኔታውን በጥሞና መከታተል ያስፈልጋል!

ጎንደር ውስጥ ያለውም ሁኔታ፡ በሁለት ጎሣዎች መካከል ሕወሃት የፈጠረው ግጭት ለብዙ ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኖአል። አሜሪካ ይህን በግድየለሽነት ብትመለከት፡ ነገ ለሚደርሰው የሕይወት መጥፋትና ለሃገሪቱ መናድ የርሷም አስተዋጾ እንዳለበት ልትገነዘግ ይገባል! እንዲሁም እንግሊዝና ሌሎቹ የምዕራብ መንግሥታት!

ከሶስት ዓመታት በላይ በአንዋር መስጊድ ኢትዮጵያውያን እስላሞች በዲሲፕሊን ለእምነታቸው መከበር ተቃውሞ ባሰሙበት ቦታ፡ የሕወሃት የስለላ ድርጅት የእጅ ቦምብ ወርውሮ አማኒይኑን መጉዳቱ፡ ምንም ቢሆን ከአንድ የመንግሥት ድርጅት የሚጠበቅ ጉዳይ አለመሆኑ በላይ ለ– ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳሳየው በቦምብ መጫወት የሚወደው ሕወሃት ወዳጅ የሚያፈራለት አይመስልም!

ለነገሩ የምዕራቡ ዓለምም ለቅሶ አልደረሰለትም!

ከቦምቡ ፍንዳታ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰብዓዊ መብቶች ቀን ስለኢትዮጵያ የተነሳ ነገር ቢኖር፡ የሕወሃትን አስተዳደር የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እጅግ ዘግናኝ መሆኑን ነበር። ዘጋባቸው ይህንኑ ሲያብራራ እንዲህ ይላል፡

“Everyday we grapple with issues that range from how to preserve civil society space in Kenya, to speaking out against criminalization of LGBTI members in Uganda, or fighting repressive restrictions in Ethiopia and Sudan against opposition parties and human rights activists.”

ጎንደር ሆነ ኦሮሚያ፡ እንዲሁም ግጭትና የሰብ ዓዊ መብቶች መጣስ በተጠናከረባቸው የሚታየው ውጥረት የሕወሃት ዘራፊነትና ፋሽታዊ ጭካኔው ያስከተለው ችግር ነው!

semien gondar conflict

%d bloggers like this: