ከሕወሃት ጋር በኦሮሚያ የተጀመረው ትንቅንቅ እየተፋፋመ ሕዝባዊ አመጹም እየተስፋፋ ነው፤ በሰላም ያላንዳች ደም መፋሰስ ሕወሃት የዴሞክራሲና የነጻነትን በር በ6 ወራት በመክፈት የለውጥ ዝግጅት ይጀመር! ሊተፋው የደረሰው ታሪክ ይዋጀዋል! 

15 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)


 
ከዚህ በላይ ባለው ቪዲዮ ውስጥ፡ የሚታየው በአንድ በኩል አንጀት ብግን ያደረገውን በመሬት ዘረፋው ዙሪያና በአሁኑ ወቅት የውጭ ጦር ሃገሪቱን የደፈረ ይመስል በወጣት ተማሪዎች ላይ የሕወሃትን ፋሽስታዊ ግድያዎች አበክሮ የሚቃወም ነው!

ስለሆነም በቪዲዮው የሚታዩት ተቃውሞአቸውን በዕሪታ የሚያሰሙት፣ ሕወሃት በየቦታው እንድሚያደርገው በካድሬዎቹ አማክይነት በማሰፈራራትና ገንዘብ በመበተን የተገዙ ግለሰቦችን አይደሉም! ሰሞኑን በኦሮሚያና አማራ (ጎንደር) እንሽላሊት ይመስል እይተሽሎከሎከ ሲፈጽማቸው የነበሩት ደባዎች ምንም ጊዜም የሚዘነጉ አይደሉም።

በአንዳንድ ቦታ በገንዘብ ደጋፊዎች እየገዛ አሉኝ የሚላቸው የሴቶች ሊግና አለያም እንደ ወትሮው እያስገደደ የሚያቀርባቸው ደጋፊዎችም ሆኑ ተለጣፊዎቹ፡ ሃቀኛ የኢትዮጵያን ልጆች አያማልሉ ም!

ለሃገር ደንታ የሌለው ሕወሃት በመለስ ዜናዊ ሙትና ቀብር ጊዜ ለ15 ቀናት በየቀኑ ከሃምሣ እስከ 300 ብር እየተከፈላቸው ደጋፊዎቹ አሰመስሎ ያቀረባቸው የቀበሌ አልቃሾችና አስለቃሺዎች ሥራውን ማን ይዘነጋል?

ይህ የአሁኑ የሕዝብ ቁጣ የሚያሳየውና የሚጠይቀው፣ ሕዝቡ በምሬት በየሥፍራው የሚያሰማውን የቁጣ ጩኸት ልብ ብሎ ግንባሩ ሊያዳምጥና ከእንግዲህ በዲሞክራሲያዊ መንገድና በነጻነት ሕይወቱን መምራት እንዲችል ኬሻውን ስብስቦ ሥልጣኑን በስላም ለመልቀቅ ሊዘጋጅ ይገባል የሚል መልዕክት ይዟል።

ሕወሃት ግን ልቡ ሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅሞች ላይ ብቻ በመቸንከሩ፡ “ምን ያለበት… የቆመን አያይም” እንዲሉ የሚካሄደውንና በሃገሪቱም ላይ ያደረሰባትን ከፍተኛ ኪሣራና ውድቀት አይገነዘብም። ዛሬ በተለቀቀው የተባበሩ መንግሥታት የ2015 የሰው ሃብት ልማት ሪፖርት (የትምህርት፣ የጤናና የድህነት መለኪያ) ላይ ኢትዮጵያ ከ2011 ጀምሮ በ173ኛ ደረጃ ላይ ተቸክላ የከረመች ሃገር፣ ይባስ ብሎ በ2015 አዝቅጣ 174ኛ ሆናለች።

ዕፍረት ከማጣቱ የተነሳም፣ ዘራፊውና ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት በመሬት ዘረፋውና በግድያው ምክንያት ተቃውሞው ሲጠናከርበት የእጅ ቦምብ መስጊድ ውስጥ እስከ መወርወር ሄደ። መንግሥት ነኝ የሚል ተቋም (የደኅንነት ቢሮው) ይህንን መፈጸሙ ሃገሪቱ እስካሁን ድረስ በምን ዐይነት አስተዳደር ሥር እንደነበረችም እንደተአምር የሚታይ ነገር ነው!

እርሱም አልሆን ብሎት ሕዝባዊው ተቃውሞ ሲባባስ ታህሳስ 4 ቀን – ፋና አንደዘገበው፡ – “የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማደናቀፍ ተማሪዎችን ለብጥብጥ የሚያነሳሱ ፀረ-ሰላም ቡድኖችን አጥብቀው እንደሚታገሉ የባሌ ሮቤና አከባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ” በማለት ፈጠራውን እያቅራራ መቅረቡ እጅግ የሚያስገርም ነው!።

ይህም ከላይ የተጠቀሰውን ብዙ የተቆመረበትንና አሁን ዋጋ ያጣውን የድርጅቱን ቅጥፈትና ኪሣራ የሚያሳይ ነው።

እንዲሁም ታህሳስ 4 ቀን የአጋሮ ሴቶችም “የዕድገታችን ዋስትና የሆነውን ሰላማችን በማስጠበቅ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ከዳር ለማድረስ እንሠራለን” አሉ በማለት በሴቶች ዙሪያ ብቻ የሚያውጠነጥን ትርጉሙ ግልጽ ያልሆነ ድጋፍና ሰላም ፈላጊነት ሲደሰኮር ነበር።

በተመሳሳይ መንገድ፡ ታህሳስ 3 ቀን “በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ሁከትና ብጥብጥ የፀረ ሰላም ቡድኖች እኩይ ተግባር በመሆኑ አጥብቀው እንደሚቃወሙት የኦህዲድ ሴቶች ሊግ አባላትና ደጋፊዎች ገለፁ” የሚል በቀዳሚነት የተነገረው ሌላው አስገራሚው ማደናበሪያ ነበር።

ወንዶቹ ድንጋይ እየተወራወሩ ነው ለማለት ነው ወይንስ አንበገር/አንደለል አሉ ለማለት ነው? ይህም አያስኬድም!

በሃገሪቱ ሕወሃት አደጋ ላይ የጣለውን ሰላም ሴቶች እርሱ በሚሰጣቸው ትእዛዝ መሠረት ፈልገው አምጥተው የሞቱንና ገና የሚጨፈጭፉትን ወንድሞቻቸውን ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን ያድኑበታል ነው ሕወሃት የሚላቸው?

ደግነቱ ከላይ በቪዲዮው እንደታየው ያልተበገሩለት ከወንዶች ወንድሞቻቸውና የትግል አጋሮቻቸው በቆራጥነት የሚቆሙ ሴቶች መኖራቸውን ሕወሃት እንዴት ሊገነዘብ እንዳልቻለ አይገባኝም!

ከዚህ ሁሉ ፍሬ ቢስ ግርግርና የማያስፈልግ ደም መፋሰስ፡ ሕወሃት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሰጥ የሚችለው ገጸ በረከት (ለራሱም ጭምር) በሰላም ሥልጣን የሚለቅበትን መንገድ መምረጥ ነው። የተጠላና የተናቀ ድርጅት በመሆኑ፡ ከእንግዲህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐውሃት እንደበፊቱ ሊገዝ የሚችልበት ዕድል ተሟጧል።

ኃይል ሁልጊዜም አስገዳጅ ነው። ሕዝብ ከቆረጠና ለመጋፈጥ ከወሰነ በሁላ ኃይል ምኩን ነው!
 

ተዛማጅ ጽሁፎች፦

    የትላንቱና የዛሬው የኦሮሞ ኅብረተሰብ ትግል የኦሮሞች ብቻ ወይንስ የመላው ኢትዮጵያ?

    #Oromoprotests & Ethiopia’s drought may heighten the end of TPLF’s rule

    Oromo students trying to end TPLF’s land grab widen their protests; parents & residents throughout region involved; student casualty stands at 15; many injured & over 500 imprisoned by int’l Human Rights Day, Dec 10!

 

%d bloggers like this: