“ዕቅዱ ተቀባይነት ካላገኘ አይተገበርም፤ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱም ተዘግቷል” ይላሉ፤ ዕቅዱ መቋረጡን አረጋግጦ ብሔራዊ ዕርቅ እንዲወርድ ብርሃን ያለው አልተሰማም! በደም የተዋጀው ታጥቦ ጭቃ አይሁን!

17 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ መሪ ዕቅድ ዙሪያ ግልጽነት ለመፍጠር እንደሚሰሩ ታንትንት ረቡዕ ታህሳስ 7 ቀን 20015 የተናገሩበት ድምፅ ማሚቶው ሳይጠፋ፣ – እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉ – ዕቅዱ በሕዝብ ዘንድ “ተቀባይነት ካላገኘ አይተገበርም፤ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱም ተዘግቷል፡ በማለት መግለጫ ሠጥቱል

የሚያስገርመው ነገር ግን፣ የአስተዳደሩ የራሱን ጥፋት በሌሎች ለማላከክ የሚያደርገው ጥረት ነው። በዚህም መሠረት፣ የአባይ ፀሐዪን የምሣ ሰዓት ከውስኪ መልስ የየካቲት 2015 ሃዋሣ ላይ ያሰማው ብልግንናና ድንፋታ ያልነበረ ይመስል፣ የሠጠው አሳፋሪ መለጫ ይዘት ነው፦

“የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ሙያተኞች ነን በሚሉ አካላት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ስራ ላይ እንዳለ አስመስለው በተለያ ጊዜያዊ ህትመት ሚዲያዎች መግለጫዎችና የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን እያወጡ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡

በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የተላለፉ መረጃዎች በሙሉ የከተማ አስተዳደሩንም ሆነ የኦሮሚ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን የማይወክሉ መሆኑን እየገለጽን ካሁን በኋላም በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ስም የሚወጡ መረጃዎች ካሉም ተቀባይነት አይኖራቸውም ብሏል መግለጫው፡፡”

ለነገሩማ፣ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውም “ዕቅዱ በረቂቅነት ያለ፡ ሕዝቡ ተወያይቶበት ሊሻሻል የሚችል የሕዝቡን ይሁንታን ካላገኘም እስከመቅረት የሚሄድ መሆኑን” ገልጿል።

ዋናው ነገር የትኛውም ወገን ዕቅዱ ከዛሬ ጀምሮ በሥራ ላይ አይውልም ያለ የለም።

ቢባልስ? ሕዝቡ እስከዛሬ ሕወሃት በጠላትነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በየአካባቢው ጥጋብና ብልግና የመሬት ዘረፋው አቆመ ማለት አይደለም! እስካሁን ለተፈጸሙት ከባድ የዘረፋ፡ የሰቆቃና የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች ተጠያቂነት የሚኖርበት ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ፡ ታጥቦ ጭቃ ነው የሚሆነው!

ሰለሆነም፥ በዚህ ጉዳይ ላይ የትላንቱና የዛሬው የኦሮሞ ኅብረተሰብ ትግል የኦሮሞች ብቻ ወይንስ የመላው ኢትዮጵያ? ያቀረብነውን እያስታወስን፡ በውስጡም አስፈላጊ ዝርዝሮቹን እንደገና እዚህ ላይም እንደሚከተለው እንጠቅሳቸዋለን፡

  (ሀ) በ24 ሰዓት ውስጥ የታሠሩትን የሁለተኛ ደረጃና ይኒቨርሲቲ ተማሪዎችንና መምህራንን መፍታት

  (ለ) በ24 ሰዓት ውስጥ የታሠሩትን ወላጆች፡ የየከተማና ቀበሌ ነዋሪዎች፥ የፖለቲካ ድርጅቶችን አመራሮችና አባላትን መፍታት

  (ሐ) በ24 ሰዓታት ውስጥ በሕወሃት ለተሠውት ዜጎች ቤተሰብች አገዛዙ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሣ በአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ለመክፈል ቃል አሁኑኑ እንዲገባ

  (መ) በሕዝብ ነብረቶች ላይ ለደረሱት ጉዳቶችና መደምሰሶች ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል

  (ሠ) ለሕዝብ መብቶች ሲታገሉ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው መቀመቅ የተወረወሩት የፖለቲካ እሥረኞች – ጋዜጠኞችን ጨምሮ – በሶስት ቀናት ጊዜ ውስጥ በነጻ እንዲለቀቁ

  (ረ) በዝርያቸውና ቋንቋቸው ምክንያት የታሠሩ እሥር ቤቶችን ያጣበቡት የኦሮሞ ፖለቲካ እሥረኞች ባስቸኳይ ነጻ እንዲለቅቁና፣ ለተፈጸመባችውም ግፍ ተገቢው ካሣ እንዴከፈላቸው አስፈላጊው የሕግ ሁኔታ እንዲመቻችላቸው

  (ስ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወደፊቱ የሚያስፈልገውን የአስተዳደር ሁኔታ በነጻ ፍላጎቱ መመሥረት ይችል ዘንድ፡ የፖለቲካ ኃይሎች መሰባሰብና መነጋገር እንዲችሉ ሁኔታውን ለመጠቀም የሚያደርጉትን ጥረት በማናቸውም

  (ሽ) ለሱዳን ሊሠጥ ቃል የተገባው የኢትዮጵያ መሬት ውል ያላንዳች ማወላወል መሠረዙን ያላንዳች መቀባጠር በማያወላውል መንገድ ግልጽ እንዲድደረግ

  (ቀ) በኢጋድ አማካይነትና በሁለትዮሽ መሰተጋብር ከአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች ጋር በስደት ከሃገር የወጡትን ዜጎም የዓለም አቀፍን ሕግ በመጣስ የሚያደርገው አስገድዶ የመመለስ ወይንም የማፈን ተግባር ያላንዳች ማመንታት አስፈላጊውን ሜሞራንደም በመላክ ሕወሃት በዚህ ረገድ ሲያደርግ የነበረው ጥረታና ጎርቤቶችን የማስገደድ ሁኔታ መሠረዙን ማስታወቅ

  (በ) በዚህ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ከፕሮፓጋንዳ ነጻ የሆነ ሚዲያ እንዲኖረው፡ የመናገር፡ የመጻፍ፡ የመሰብሰብ፣ በነጻ የመደራጀትና የእምነት መብቱን ያላንዳች ዕገዳ እንዲጠቀም የተጣሉበት ማቀቦች በሙሉ እንዲነሱ። ይህንንም በሚመለከት የወጡት አዋጆች፡ ሕጎችና ደንጋጌዎች በሙሉ እንዲሻሩ

  (ተ) በአኤአ በ2009 ዓ.ም. የወጡት የጸረ ሽብርና (Proclamation No. 652/2009) መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አሠራር በመመዝገብ ስም ዓላምው ግን የማኅበራዊ ኑሮን ሰብዓዊ መብቶች መከበርን ዕርዳታ ለመግታት የወጣው ሕግ አዋጅ ቁጥር 621/2009 (Proclamation No. 621/2009) በዚሁ በአንደ ወር ውስጥ እንዲሻሩ።

  (ቸ) በአዲስቷ ኢትዮጵያ፡ ለሃገር ደህነነትና ጥበቃ ዋናው ኃይል ሕዝቡ ራሱ እንጂ የሃገር ዳር ድንበር ለሱዳን የሚሸጥ አሰተዳደር አለመሆኑ ግንዛዜ ውስጥ ሊገባ ይገባል። በተመሳሳይ መንገድም ይህም ሕወሃት ከሱዳኑ ዓለም አቀፍ ወጀለኛ አል በሽር ጋር የሚያደርገው ስምምነት – ታህሳስ 4፣ 2013 ካርቱም ላይ የተፈራሙትንና የቀሞዎቹን ከመለስ ዜናዊ ጋር የተደረጉትን ጨምሮ – በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተሽረው ይኸው መረጃ ለሕዝቡ በሕዝብ መገናኛ መሣሪያዎች ሊገለጽለት ይገባል።

 

%d bloggers like this: