ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ:የጋራ ጠላት የሆነውን ነፍሰ ገዳዩንና ዘራፊው ሕወሃትን ኢትዮጵያውያን በጋራ መድረክ መዋጋት አለብን አለ – ኦባማም ሰምቷል!

18 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)


 

የአርበኞች ግንቦት 7 የእምቢተኝነት እምቢልታዎች

(ቃል በቃል የተወሰደ ባይሆንም)፣ የግንቦት7 መሪ ብርሃኑ ነጋ የሚከተሉትን ስድስት ጥሪዎች አድርጓል፡

  1.   በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ትግሉ ከአሁኑ በተሻለና በተጠናከረ መንገድ እንዲቀጥል፤

  2.   በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብሄረስቦች ባሰቸኳይ ትግሉን እንዲቀላቀሉ፤

  3.   የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ሚሊሽያዎች የኢትዮጵያ ልጆችት እንደመሆናቸው በወገናቸው ላይ አፈሙዛቸውን ከማዞር እንዲቆጠቡ፣ ቢቻልም ወገኖቻቸው ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል እንዲቀላቀሉ አርበኞች ግንቦት7 ጥሪ ያደርጋል፤

  4.   ለሕወሃት/ኢሕአዴግ መካከለኛና አነስተኛ ካድሬዎች፡ እንዲሁም የመንግሥት ባለሥልጣናት ሃገራችሁን መታደግ እንደምትችሉ ልታውቁ ይገባል። ግፍ መሥራታችሁን ከቀጠላችሁ አለቆቻችሁ የዘረፉትን ለመብላት ሲሯሯጡ ትተዋችሁ ይሄዳሉ። አብሮአችሁ ከሚኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አትጣሉ!

  5.   የሰላም ድርድሩ አሁኑኑ እንዲጀመር ሁኔታዎችን ፍጠሩ

  6.   በመሣሪያም ሆነ በሌላ መንገድ ያሉ ሁሉ እንዲደባሰቧን የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ጅምር መሥመር ለማስያዝ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ!

 

የታህሳስ 18 የኢሳት ዜና የሃገራችን ችግር መካረሩን፡ ሕወሃትም የፈለገውን እየረሸነ፡ እየደበደበና እያሰረ መሆኑን ያሳውቀናል፦


 
===========0000==========
 

አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ተባ ቸል እያለች፡ የኢትዮጵያውያንም ሕይወት ዋጋ እንዳላት ተሰምቷል። እርምጃቸው በመዘግየቱ ቅር ቢያሰኝነም፡ አሁን ላሳዩት ፊት ማዞርም እንከታተላለን፣ መስማታቸውንም መስማታችንን እንዲያውቁ ከምስጋና ጋር እንገልጻለን!

የእሜሪካ ነገር የገረመኝ ኃያል ሃገርም እንቅልፍ ይወስደዋል ለካ የሚለውን ሰለሆነ በተለይም በኦባማ አስተዳደር ሳልናገር ብቀር ሃስተኛ ሆናለሁ ብዬ ሰግቼ ነው አሁን የማነሳው!
 

%d bloggers like this: