በኦሮሚያ በተፈጸመው ጭፍጨፋ የሰው ልጅ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም፤ ገና ከአሁኑ በሕወሃት አባሎችና/ደጋፊዎቹ መካከል ቅሬታን ታች አውርዷል! ግንባሩ ግን ቅጥፈት፣ እሥራቱንና ምሥጢራዊ ግድያውን እያፋፋመ ነው!

25 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

– ክፍል አንድ –

በዚህች በአሁኗ ሰዓት፣ በተለይ በኦሮሚያ የሕዝብ ተቃውሞ ጋብ ብሏል በሚባልበት ሁኔታ እንኳ፣ የሕወሃት አስተዳደር በግፍና ምሥጢራዊ መንገድ ሰዎችን – በተለይ ኦሮሞችን – በማጥፋት ላይ ነው። እንዲሁም፥ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ከአራት ያላነሱ የኦሮሞ ፌዴራል ኮንግሬስ አባላትና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከአዲስ አበባና ከዚያ ውጭም ያሉ አክቲቪስቶች ከፈረንጆች ገና ዋዜማ ጀምሮ በመታሠር ላይ እንደሚገኙ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና አቶ በቀለ ነገዓ ለኢሣት ታህሳስ 24 አረጋግጠዋል።

የሕወሃት ዩኒቨርሲቲዎችም – ከጥምንቱ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ተማሪዎች ወግና ባህል በተለየ መንገድ የሕወሃት የእሥራቱና ግርፋቱ ተባባሪ በመሆን – ያላንዳች ሕግን የተከተለ መንገድ (without due process) የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ስማቸውን በመለጠፍ ኦሮሞ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ላልተወሰነ ጊዜና ለዘለቄታውም በማባረር ላይ ናቸው።

ለምሳሌም ያህል፡ የጂማና ሃረማያ ዩኒቨርሲቲዎች፥ ገመችስ ታከለ፣ አሸናፊ ሌንጂሳ፣ አለማየሁ ገመቹ፣ መብራቱ ጅሬኛ፣ መሃመድ ሸምሲዲን፣ አብዲሳ በንቲ፣ ፋጂ ሙላት፣ አብደላ ተስሳ፣ ዘነበች ጌታቸው ፣በሻቱ ቃናአ፣ ቢራ ነጋሽ ደመቀ እንዲሁም አሰፋ ፋና የተባሉት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዎቹ ድረስ መጥተው (ለማሠር እንዲመቻቸው) ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ አስታውቀዋል
 
– ክፍል ሁለት –

ስለሆነም፥ አሁን የምንመሰክረው የሥልጣን ብልግና ሂደት፥ ለእንስሳት፥ ዛፍና ቅጠል ሳይቀር መንከባከብና መሳሳት ባህል በሆነበት በተለይ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) እንደፈለገው የዜጎቻችንን ሕይወት እየቀጠፈ 25ኛ ዓመቱን ለማስቆጠር መቻሉን ነው። የዛሬ አሥር ዓመት፣ በ2005 ዓ.ም. ሶስተኛው ዙር ምርጫ ወቅት፥ በሕዝብ መተፋቱን እንደ ሕዝባዊ ውሳኔና ዴሞክራቲክ ምርጫ ውጤት ባለመቀበል፥ በማግሥቱ በወታደራዊ ኃይል ራሱን ነት አከናንቦ፥ “ድምጻችን ይከበር!” ያሉትን ወጣቶችና ሽማግሌዎችን እንደ ተለመደው እንደ ዕርድ ከብት ብዙ ኢትዮጵያውያንን መጨፍጨፉ ይታወሳል።

ከዚያን ወቅት ጀምሮ እስከዛሬ፥ ያም አስከፊ ሁኔታ ኢትዮጵያውያንን ከዳር እስከ ዳር እንዳስቆጣ መቀጠሉና የሃገሪቷ ፖለቲካ ፍጹም የተበላሸና ዘረኛነቱ በጉልህ በወጣበት ማግሥት፣ ያ አረመኔያዊ ነፍሰ ገዳይነት አንሶ ሕወሃት መቶ በመቶ አምስተኛውን ዙር ምርጫ አሸንፊያለሁ ባለ በሰባተኛ ወር – ጥጋበኞቹ ያለተጠያቂነት የዜጎችን መብቶች እየረገጡ በሥልጣን እንዴቀጥሉ – እንደገና ላለፉት አምስት ሣምንታት ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ የሆነ የኦሮሞና የአማራ ብኄረሰቦች አባላትን ጭዳ ሲያደርግ ስንብቷል (86 በኦሮሚያ ብቻ እየተባለ ነው) – በተለመደ ቅጥፈቱ ሕወሃት በተደጋጋሚ አምስት ብቻ፣ ማለትም ከጠቅላላ ሙታኑ 5.8 ከመቶ፣ መገደላቸውን በቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ አማካይነት ቢያምንም!

ፋሽስታዊው ሕወሃት መጀመሪያ ኦሮሞ ላይ ተኩስና ግደል ከዚያ በኋላ "የሟቾቹን ቁጥር ለኔ ተውልኝ" ጌታቸው ረዳ – "አምስት ናቸው አይደል?" (ፎቶ ኦሮሚያን ኤኮኖሚስት)

ፋሽስታዊው ሕወሃት መጀመሪያ ኦሮሞ ላይ ተኩስና ግደል ከዚያ በኋላ “የሟቾቹን ቁጥር ለኔ ተውልኝ” ጌታቸው ረዳ – “አምስት ናቸው አይደል?” (ፎቶ ኦሮሚያን ኤኮኖሚስት)

በጋዜጠኞች፡ በሃገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ስብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና የሃገር ውስጥ ሕጋዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮችና አዳንድ መንግሥታት እንደተገለጸው – ከሟቾቹ መካከል የስባት ወር ነፍሰ ጡር በመገደሏ፡ ሬሳዋን ለመደበቅ በተደረገ ጥረት ይመስላል በድብቅ ገዳዮቿ ቀብረዋት ሬሣዋ በፍለጋ ከጫካ ጉድጋድ ወጥቶ በሃኪም ግድያዋ ክተመረመረና ከተመሰከረ በኋላ፡ ዘመድ አዝማድ፡ መንገደኛው፡ ከቅርብና ሩቅ ሌላው ሃዘንተኛ በተግኙበት የቀብር ሥነ ሥርዓቷ መፈጸሙ በሚገባ ተዘግቧል – ሁኔታው ለግድያዋ አመራር ሰጭዎችና ስለገዳዮቿ ጭካኔ ቅንጣትም ሳይሰውር!

እንዲሁም፣ ክሙታኑ አንዱ የሆነው የአሥር ዓመት ልጅ በቅርብ ርቀት ግንባሩን በጥይት ተመቶ፣ የ19 ዓመት አዲስ ባለ ትዳር ሴት፣ እናትና ልጅም ከሌሎች ሟች የሁለተኛ ደረጃና የይኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በገፋፊዎችና ልባቸው በጥጋብ በተደፈነ ነፍሰ ገዳዮች ትዕዛዝ አሁንም ኢትዮጵያውያ እንደገና አያሌ ዜጎቿን አጥታለች!

አስከፊ ድርጊቶቻቸውን ከሕዝቡ ለመሠውር፡ ዲከታተሮች መከንበያቸው ሲደርስ፡ ውሽትና ድንፋታ ያበዛሉ እንደሚባለው፤ ለምሣኬም ያህል ጋዳፊ እንዲሁም ሳዳም ሁሴን ለቃል አቀባዮቻችውም (ሙሣ ኢብራሂምሙሃመድ አል ሳሃፍ – ኮምኩ ዓሊ) የሚሠጣቸው መመሪያና ዝግጅታቸው ሁሉም ቦታ ተመሣሣይ ነው – መዋሸት፥ ተቃዋሚ የሚሉትን ጎራ ማስፈራራትና ቀበሮ መሰከረችልኝ የሚለውን የያዘ መሆኑ በርተደጋጋሚ ታይቷል – የኢትዮጵያን ወራሪዎችንም ሥራ ጨምሮ! ብዙ ይወጣጠራሉ።

ለምሳሌም ያህል፡ የሕወሃትንም ልብ ብሎ ላዳመጠ ስው የስብሃት ነጋ ምልምልም ጌታቸው ረዳ በመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫና አሁን ደግሞ በተከታታይ በኦርሞች ጭፍጨፋ ዙሪይ ሲያሰማ የነበረው የጥጋብ አነጋገር – ማለት ኦሮሞችን ከአጋንንት ጋር ማመሳሰሉ፣ የሊቢያው መሪ ተቃዋሚዎችን በበረሮዎች (COCKROACHES) መመሰሉ፤ የኢራኩ ቃል አቀባይ ሞሃመድ ሳኢድ አል ሻፋ (ኮሚኩ አሊ) ደግሞ የአሜሪካንን ጦር ለፕሮፓጋንዳ ዓላማ ከአይጥና እባብ መለየት አይቻልም ማለቱ ያላቸውን ልዮነቶች አንባብያን ሊፈርዱት ይችላሉ።
 
ከዚህ የባሰና የከፋ ኢትዮጵያ ምን ጥቃትና ጥፋት ሊደርስባት ይችላል?

ብልሹ አስተዳደር የዴሞክራሲ ምህዳርን በማስፋትና ቀጣይነት ባለው የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ በወሳኝነት ይፈታል! በሚል ርዕስ የሕወሃት የቀድሞ አየር ኃይል አዛዥ ሜ/ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት ለግንባሩ ያላቸውን ታማኝነት ጥርጥር ውስጥ የማይገባ ባይሆንም፣ መስከረም 2015 የጻፉት የሚከተለው ትንቢተኛ መልዕክት ብዙም ሣይቆይ ተፈፃሚ ሆኖአል፦

  “ባጠቃላይ ሲታይ ብዙ ማንነቶች፤ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች፤መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አጋሮቹ 100% መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር፤አንድም ባጠቃላይ ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ወይም ተግባራዊነት ላይ ችግር እንደነበረበት ነው፤ 100% እሚባል ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ፡፡ ይሄ ዉጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው የአደጋ እንጂ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጠር አይችልም። መሬት ላይ ያለዉን የተለያየ ፖለቲካዊ ፍላጎት እማያንፀባርቅ የምክር ቤት ሁኔታ የስጋት እንጂ የኩራት ምንጭ መሆን አይችልም።”

ከምርጫው በኋላም በተደረገው የፓርቲው ጉባዔ ወቅት እንደታየው፡ ወጣት ትግሬዎች እንደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ አመራሩ በሙስናና ለሃብት ስግብግብነት ምክንያት መልካም አስተድዳር በሃገሪቱ አለመኖሩን በድፍረት መናገራቸው ይታወሳል። እንደውም በካድሬዎቹ በኩል የነበረው ግልጽ ፍላጎት፣ ሥርዓቱ ውስጥ የተሰገሰጉት ዘራፊዎች እንዲጋለጡና እንዲባረሩ ነበር።

አሁን ግን፣ ከካድሬዎቹ ፍላጎት ባሻገር፣ ሕዝቡ በመላ ሃገሪቱ፡ ሕዝቡ በጸሎትም ሣይቀር የሕወሃትን ጀርባ ለማየት ከምን ጊዜውም በላይ ደፈር ያለ መጋፋትን በማሣየት ላይ ይገኛል። ስለሆነም ዋናው ጥያቄ እንደ በፊቱ ይኼ ዘረኛ ከሥልጣን ይወርድ ሣይሆን፡ ቀኑ መቼ ነው የሚለው መሆን ያለበት ይመስለኛል። ሰሞኑንም የሐረር ሕዝብ (ካድሬዎችን ጨምሮ) የሕወሃት አስተዳደር ኦሮሚያ ውስጥ የፈጸመውን ድርጊት ማውገዙ ይታወሳል።
 
– ክፍል ሶስት –

ለምን ይህ ጽሁፍ አሁን? በዚህ የግርጎርያን ገና ማግሥትና የአዲስ ዓመት ዋዜማ ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ፡ በኢሣት ራዲዮ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ከተላለፉት የአንባብያን ደብዳቤዎች መካከል፣ አንድ ስማቸውን ያልገለጹ ዜጋ በድምጽ ከቨርጅኒያ ያሰሙት – ጨዋነት የተላበሰ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያተኮረው ወቀሳቸውና ጥሪ ራሳቸውንና ድርጊታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያሳውቁና እንዲገልጹ ሲሉ የጠየቁበት መልዕክት ነው። የድምጻቸውን ቅጂ ከዚህ በታች ባለው ኦዲዮ ማዳመጥ ይቻላል።

እስከ ዛሬ የትግራይ ተወላጆች – በስማቸው አያሌ ደባዎችንና ዘረፋዎችን የሚፈጽመውን ሕወሃት አቅፈው ደግፈው በሃገራችን ላይ በድጋፋቸው የተከሉት የማፊዮዞ ድርጅት – ይህንን ሁሉ ወንጀል ሲፈጽም፡ ትግራዊ ያልሆነው ወንድማቸው፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደም በክንቱ መፍሰስ ስሜት ያልሳጣቸው፣ እንዲሁም ከጎንደር የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ለመሰጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ እየታወቀ፡ ዝምታቸው ኢትዮጵያም ሃገራቸው መሆኗን ዘንግተው ወይንም ባለመቀበላቸው ይሆን በማለት ባለደብዳቤው በማዘንና በመገረም፡ “አይደለም!”ይሉ ይሆናል የሚል ባለተስፋ መልሳቸውን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስል፡ ድምጻቸው ኃዘናቸውን እያስተጋባ ጥያቄዎቻቸውን በተሰበረ ልብ አቅርበዋል።

እኔም ፕሮግራሙን ሳልጨርስ፥ በተከፋ ስሜት አቋርጨው፥ ኮምፒውተሬን ዘግቼ ወደ ጉዳይ አቀናሁ። ነገር ግን ከቤቴም ወጥቼ፡ የግለሰቡ መልዕክት ኮምፒውተሬ ውስጥ ከመቅረት ይልቅ ከኔው ጋር ተከትሎኝ ዋለ! እውነቱን ለመናገር፥ ተገድጄ በጉዳዩ ላይ እንዳተኩር ብደረግም፥ እንዴት እስከዛሬ ይህ ግለሰብ እነዚህን ሰዎች እንዴት አላወቃቸውም የሚለው ቅሬታዬ ደብዝዞ በደፈናው ነገሩን ወደማሰላስል አጋደልኩ።

በእኔ በኩል ያለው ላለፉት አሥር ዓመታት ያህል በውስጤ የዳበረው አመለካከት – እስካሁን በተገነዘብኩት – ሕዋታውያን ውስጣዊ ስምምነታቸውና አስተሳሰባቸው ጭምር፣ የፈለገ ሰው ይለቅ ሕወሃትና እነርሱ ብቻ ይለምልሙ የሚል መሆኑን ነው! ይህ ደግሞ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚጋሩት ከመሆኑም በላይ፥ የሕወሃትን ሰዎች ቀንና ማታ ውስጣቸውን የሚመዘምዝ ቁስል በመሆኑ፥ እነርሱም አበክረው ያውቁታል።

ማስረጃ ቢያስፈልግ፥ ካለፈው ምርጫ በኋላ፡ የትግራይ ፕሬዚደንት ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያምና በተግባር የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ የሆኑት የደኅንነቱ ኃላፊ የአቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም አቶ ዳንኤል አሰፋ፡ አንድ መቶ ያህል የትግራይ ተወላጆችን በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋሽንግቶን ዲ.ሲ. ሰብስበው ባመካከሩበት ወቅት፥ ከታዳሚዎቹ የተነሣው ጥያቄ “የኢትዮጵያ ሕዝብ፡ ብሄር ብሄረሰቦች ለምንድነው የሚጠሉን?” የሚል ነበር።

ለዚህ በሁለቱ የወሃት ባለሥልጣኖች የተሠጠው መልስ “ባለን ቦታና ሚና ይበልጥ እየተከበርን እንገኛለን…የሚጠሉን ከሕወሃት ያፈነገጡ [ከሕወሃት] ግለሰቦች ናቸው” የሚል ጊዜያዊ መደለያና ማባበያ ነበር።

ወደ ጀመርኩት ጉዳይ ስመለስ፥ ያንኑ ዕለት ማምሻውን ስለ ኢትዮጵያ ዜና ያገኘኹትን ለማንበብ ከገጽ ወደ ገጽ ስሸጋገር በአጋጣሚ የትግራይ ኦን ላይንን – ፕሮፓጋንዳውን፡ የመከፋፈል ሥራውንና ‘የወረራ ሞቅ ሞቅ አቀራረቡን’ በእጅጉ ብጠላም፡ ከነእርሱ ሠፈር ያለውን በአብዛኛው ጊዜ የሠጠው የገዳይ ፉከራ ከአርዕስቶቹ ለማየት ጎራ ስል፣ Have your say, How did the EPRDF handle the recent crisis in Ethiopia?http://www.tigraionline.com/articles/have-your-say-dec.html የሚለውን ተመለከትኩ።

እስቲ ምን አሥፍረዋል ብዬ ጥቂቱን ገርፍ ገረፍ ማድረግ ስጀምር፥ ከዚህ በፊት ባላየሁት መንገድ በእነርሱም መካከል አንዳንዶቹ በኦሮሚያ በተፈጸመው ቅር ከመሰኘት አንስቶ እስከ ማዘን፡ ከዚያም አልፈው ሕወሃት ስህተት መፈጸሙም የተሰማቸው መኖራቸውን በመገርም ተመለክትኩ። እውነቱን ለመናገር፣ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ – በተለይም በምሁራኖቻቸው በጣም እንዳዘነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ – እኔ በእነርሱ ተስፋ ከቆረጥኩ ስንበት ብያለሁና ይህንን ከትግራይ ኦን ላይን አንባቢዎች አያለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር።

በተመሣሣይ ሁኔታ፣ የማይሆን ወይንም ያልሆነ ተስፋ ላለመፍጠር፡ አንባቢዎች እንዲገነዘቡት የምሻው፡ “የተወሰደው እርምጃ በቂ አይደለም” የሚሉ መኖራቸውንም ነው!

ቆይቶም፣ ልቤ ደብዳቤ ጸሃፊውን እንዴት እነዚህን ሰዎች እስከዛሬ አላወቃቸውም የሚለውን መገላመጡን ትቶ፡ የ2005 ቁጣና የመረረ ንዴት በቆይታ ተቀምጦ፡ የ2015ቱ የሕዝብ ዕርድ ሃገሪቱን ወዴት ሊወስዳት ይችል ይሆን ወደሚለው የሩቁን ወደ ቅርብ ማማጣት የታቸለ አስመስሎ ሰለ ሁኔታው አንድ ግምት ለመፍጠር – ረግራጋ መሬት ቢሆንም – ማለትም ፈረንጆች SPECULATION ወይንም CONJECTURE ወደሚሉት ዓለም ጭልጥ አልኩ።

በሌላ አባባል፥ በትግራይ ሰዎች መካከል ያለውን መከፋፈል ትግራይ ኦን ላይ ያሸተተውን መነጽር አድርጌ፥ መጭዋን ኢትዮጵያን ለመፈለግ ጀመርኩ። የ2005 ጭካኔ የተመላበትን ጭፍጨፋ ለጊዜው እንኳ ከገሃድ አሰተሳሰቤ ወደ መደረደሪያ እንዲገባና 2015ቱን ያልተጠናቀቀውን ግድያ ለማመንዥግ ዕድል አንኳ አልሰጠኝም።

አንድ የደረስኩበት አስፈሪ መደምደሚያ፡ ሃገራችን ለብዙ ዓመታት ከተጀመረው መፈረካከስ ትተርፍ ይሆን የሚለው ጥያቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ብዙ ቢንገዋለልም፣ አስተማማኝ ሁኔታ አይቻለሁ ለማለት አልደፍርም – ምንም እንኳ በእኔ ትንተና

ሁላችንም አሁን ያለንበትን አስተሳሰብና አመለካከት ለረዥም ጊዜ ስለተላበስነው፣ ከዚያ መላቀቁ ቀላል አይሆንም። ሰላምን ለሃገራችን ለማምጣትና ሃገራችን በደሞክራሲ መንገድ እንድትራመድ ለማስቻል፥ በስላም አብረን ለመኖር የሚያስችለንን ምዕራፍ ለመክፈት መስኮቱ ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም። ሆኖም ለዚህ ጥረት መሳካት ተቀራርቦ ያላንዳች ፍርሃትና ሥጋት መወያየት የማስፈለጉን ያህል የወንጀለኞች ለፍርድ እስከዛሬ አለመቅረብ ከፍተኛ እንቅፋት ሆኗል።

እስከዛሬ በሃገሪቱ ውስጥ ለተፈጸሙት ሁሉ አስከፊ ድርጊቶች በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ፥ ሕወሃት ተቀባይነት ያለው ባህሪ አድርጎት ይኸው ባለፉት አምስት ሣምንታት መብቶቻቸውን ለማስከበር በወጡ የሁለተኛ ድረጃና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ፣ እነርሱን በመደገፍ በተቀላቀሉ ወላጆቻቸው ላይ፡ መንደርተኞች ላይ – እስካሁን የሚሰማው ቁጥር ትክክል ከሆነ – አንድ መቶ በላይ ዜጎች ማለቃቸውን የዓለም አቀፍ ኅብረተሰብም ሰምቶ ከለዘብተኛ ወቀሳ የበለእጥ ነገር የለም!

ይህ እስካልተደረገ ድረስ፥ በሕዝባችን ላይ የተጫነው የሕወሃት ረገጣ መቀጠሉ ብቻ ሳይሆን፥ እንደ ክረምትና በጋ የተለመደው የሕዝብ ዕርድም ወደፊት ይቀጥላል። ይህም የሚያሳየው የዲክታተሮችን ሶስቱን ትልልቆቹን ዕጦቶቻቸውን – ማክስ ቬበር (Max Weber) እንዳለው – ሕሊና – መጠንን ለመገንዘብ አለመቻልና የኃላፊነት ስሜት አለመኖር፥ (awareness, senses of proportion and responsibility) ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ ትግራዊያን ናቸው የሚል እምነት ባይኖረንም፡ አንዳንዶቹ ግን በስማቸው መሠረትና በቋንቋ አጠቃቀማቸው ትግሬዎች ናቸው ብለን እናምናለን። ዋናው ትርጉም የሚሰጠው ግንዛቤ ግን ፣ ግንባራቸውን ለሕወሃት ጥይት እንደሰጡት የኢትዮጵያ ተማሪዎችና እንደውጭው የዓለም ኅብረተሰብ ሁሉ ኢትዮጵያውያን የሕወሃትን ወንጀለኛ ድርጊቶች መቃወማቸው መሆን ይኖርበታል!
 
በእያንዳንዱ መንደርና ቀበሌ በመግባት ሕዝቡን ለመፍጀት የተደረገው የሕወሃት ጥረት ማስታወሻ!

በእያንዳንዱ መንደርና ቀበሌ በመግባት፣ ሕወሃት የኦሮሞሚያን ሕዝብ ያደረገው መጨፍጨፉን የዘገበ ማስታወሻ!

– ክፍል አራት –

በትግራይ ኦን ላይ አስተያየት ከሠጡት 128 ግለሰቦትች ወስጥ በቀጥታ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ አስተያየት የሠጡት 84 በቁጥር፥ ማለትም 66 ከመቶ፥ ብቻ ተለይተው ግምገማ ተደርጓል።

ከነዚህ መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ 60 ከመቶ የሚሆኑት፥ ማለትም 50 ግለሰቦች በቁጥር፥ ሕወሃት በኦሮሚያ በፈጸማቸው ግድያዎችና ተራ ዱርዬነት ቅሬታቸውን ከመግለጽ ባሻገር፥ ይህንን ባህሪውን እንዲቀይር፡ መጣል የሚገባቸውን መጥፎ ፖሊሲዎቹን እንዲያራግፍ ምክራቸውን ለግሠውታል።

ባንጻሩ፡ ፍርድ ለመስጠት በቂ መረጃ የለንም ያሉትን ጨምሮ፡ 40 ከመቶ የሚሆኑት፥ ወይንም 34 ግለሰቦች በቁጥር፡ የሕወሃት አስተዳደር – ኤርትራን ጨምሮ – ጠላቶቹን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችለውን ትምህርት ማግኘቱን ቢገልጹም፡ በነዚያ አምስት ሣምንታት ውስጥ ትንፋሻቸው ልትቆም መድረሷን በተለያየ መንገድ አሳውቀዋል። የእነርሱም ምክር ለአስተዳደሩ የረበሹት ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያሳስብ ነው!

(ሀ) የሕወሃትን ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ በመውሰዱ አስተዳደሩን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ

አንዳንድ ግለሰቦች የኦሮሞ ሕዝብ ምሬቱንና ጉዳቱን በዚህ መልክ የማሰማቱን ሁኔታ ሕጋዊነት ሲያሰምሩበት፡ በአኢህ ዙሪያ የተነሱት ሃሣቦች የሚከተለውን ፍሬ ነገሮች አነጽባርቋል፦

  * ስዎች በክልላቸው ለሚደረጉትና ላልተደረጉት ጉዳዮች ሁሉ ቀደምት ኃላፊነት እንዳላቸውና በፌዴራል መንግሥት ደረጃ በዚህ ላይ ዋና ባለቤት ሆኖ መቅረብ በቀጥታ ሕገ መንግሥቱን የሚቃወም ብቻ ሳይሆን፡ አለ የሚባለውን ፌዴራሊዝም ባዶነት የሚያረጋግጥና ሕወሃትም ሕዝቡን ማዳመጥ እንደማይችል የሚያረጋግጥ ነው ብለውታል (ሃጎስ፣ ኢቲ ፈርስት፣ ደቢስ፣ ደርበው፣ ለምለም፣ ዮሃንስ 4ኛ፡ ፍሥሃ፣ ሳል፣ ሮማን፣ ገብረሕይወት…)

  * ዕድገትና ልማት በቀዳሚነት ሕዝብ ተኮር መሆንና መሬት ነጠቃው መቆም እንደሚገባው (አባ፣ ዳኒ፣ ዴቨ፣ እሌኒ፣ ዓለም፣ ጆስ፣ …)

  * የሕዝብ ቁጣው መፈንዳቱ በማስተር ፕላኑ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በኤኮኖሚ ችግሮች፡ ሙስና መበራከት፣ (ብርሃነ፣ አውራሪስ፣ ዮሃና ዘራጽዮን፣ አጋዚ ኮማንዶ፣ ሳል፣ እሌኒ፣ ያለው፣ ጌስት፣ ኃይሌ…)

  * ዘረኛው ብሄር ላይ የተመሠረተው አስተዳደር የችግር፡ የጭቆናና የብልሹ ፖለቲካ ማህጸን መሆኑ (ጌስት፣ ሳል፣ እሌኒ፣ ዳዊት፣ ፒተር፣ ለማ ከበደ፣ ሽሮ ሜዳ፣ አ. ገብሬል፣ ሙፍቲ፣ ዳዊት …)

(ለ) የውጭ ጣልቃ ገብነት (ኢርትራ፣ ግንቦት 7 የኦርሚያ ሕዝብ ደንቁርና) በኦሮሚያ ለተከሰተው ችግርና ደም መፋሰስ ምክንያት ሆኗል

  * ኢርትራና አመራሯ ገንዘብ እያፈሰሰም ሆነ፣ በፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን በሕወሃት አስተዳደር ላይ እያነሳሳ በመሆኑ፣ ግንባሩ የውስ ጥችግሩን መፍታት የሚችለው በቅድሚያ አሠመራ ላይ እርምጃ በመውሰድ ነው (በኦሮሚያ ባለው ችግር ዙርያ፡ የሕወሃት ደጋፊዎችን የሚያስተባብረው ሃሣብ ምንጩ ኤርትራና ጣልቃ ገብነቷ ነው ብለው ያምናሉ)

  * ሕወሃትን ቢደግፉም፣ በሕወሃት ውስጥ ያለው ሙሰኝነት እንደሚያሳስባቸውና የመልካም አስተዳደርና ፍትህ መጥፋት ተነስቷል (ጽዮን፣ እውነቱ፣ ባህረ ነጋሽ፣ ጌስት፣ …)

  * ሕወሃት አሸባሪዎችንና ረባሾችን በሚገባ መልቀም አለበት (ጌስት፣ ኑዋይት፣ እሊጃህ፣ ሃይሎም፣ ማሞ፣…)

– ክፍል አምስት –

በሁለቱም ኖች በኩል፣ አንዳንድ ግለሰቦች የሠጧቸው አስተያየቶች እጅግ ጠቃሚ በመሆናቸው፥ ለናሙና ጥቂቶቹን እንዳሉ እንደሚከተለው አቀርባቸዋለሁ፦

  “Azmatch

  I am afraid unless the government works to eliminate corruption, corruption, corruption and create a level playing field based on the law of the land similar uprising will happen on a regular basis and the country might become like the former Yugoslavia. I think all government action must also be transparent and the general public needs to be informed on a regular Democracy and human rights must be the guiding principles. The next uprising is going to be led by seniors and that will be deadly.”
  ======000======

  “Hagos:-

  Oromo: Oromo’s have right to protest against issues that affect their kilil. They should not destroy property for the purpose of protest, and the GOE have no right to take the life of protesters. Both sides are wrong, but their will to protest is right. All those police that shot unarmed people should go to jail.

  Eritrea: We cannot blame Shabiya for all issues that come, but we need to stop their meddling in our politics.

  Drought: Feeding our people need to be #1 priority and the addis ababa master plan does not really seem like it will help in that but it does help in the expanision of infrastructre in that specific area. We need more to be done in afar, tigray, somali and parts of amhara kilil because they get hit hard from drought.

  All in all we need to focus on the goal of development and at the same time hold those accountable in public government positions (police etc) for breaking the law and or committing crimes against the people they are suppose to protect.”
  ======000======

  “Observer

  It was a week full of apprehension and anxiety. I understood that Ethiopia will not develop without problems: there going to be a lot of obstacles in the way.

  Probably most of the problems arise from bad PR work. There should a good consultation system where by people participate in forums and discuss issues that concern them.

  Probably, the Addis Master Plan is not inherently bad for the surrounding municipality If there was a good campaign of information things wood have gone differently and hamburger parties would not had an opportunity to exploit it”
  ======000======

  “Maximos

  They have destroyed public and private properties ! The next step is destroying the country ! OMG ! I don’t want to see that .We need to stop the violators first and then FIX the problems such as lack of governance and corruption . Don’t sleep : There is Billions of dollar money transaction up there by DAHLAK Area . Try to gather information about it . Know for how long ? And get the answer.
  ======000======

  “Kelelom

  I hope EPRDF learned their lessons from what happen in Oromia and Amara(Gondar). They should listen to the people instead of taking matters by their own. They should discuss things big or small with the people, otherwise the unrest will continue. If Abay Woldu and other TPLF/EPRDF members try to sale Badem to Shaebia we will see another big unrest and the end of TPLF/EPRDF.”

  “Et, first

  We pray to God, things will turnout peaceful and the government will see and understand the frustration of the people accumulated for long long time, this is not about the Masterplan of the city huge frustration in many area is fueling the nation,correction in policy is urgent before the worst comes and it will definitely do, if not know ?

  Napoleon has lost, the Ottoman empire too it is not about having the strongest army and the most advanced weapon in the world, we have to recognize, see,and make a wise policy other wise even the nuclear bomb will not stop people.

  We all pray to God to open the mind and eyes of our leaders.”
  ======000=======

  “Guest

  We talk a lot but we do nothing for our country. everybody knows of history , during Haile selassie and derg Shabia worked undercover. Now those old Shabia leaders who leaves by the name of opposition in the heart of our country still working with the devil isayas and destroying our country. All diaspora opposition knows that those old shabia works for the dictator. We all know but we just talk and talk…. no one take any action to stop them.”

ማጠቃለያ

በዜና ማሠራጫዎች ሃገር ውስጥ ጭምር በሠፊው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔን (ሰመጉ) በመጥቀስ እንደተዘገበው፥ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ጥርጣሬና ሥጋት የገባቸው ዜጎች ተቃውሞአቸውን ሥርዓት ባለው መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ የሚገልጹበት ሁኔታ በአስተዳደሩ ባለመመቻቸቱ፣ “በሁኔታዎች አያያዝ ጉድለት የተነሳ ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ሠልፍ በወጡ ዜጎችና የፀጥታ ኃይሎች መካከል አላስፈላጊ ውጥረትና ግጭት ተከስቷል፤” በዚህም ሁኔታ ለደረሰው ጥፋት ሁሉ፡ ሰመጉ የሕወሃትን አስተዳደር ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል። የኛም አቋም ከዚህ የተለየ አይደለም!

ዛሬ በዚህ ሕጋዊ መርሆ ላይ በመመሥረት፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠያቂው ካላደረገው፥ ነገም ትላንትናና ከዚያ በፊት እንደሆነ ሁሉ፥ ኅሊና የሌለው፣ በሥልጣን ጉጉት የታወረው ሕወሃት – ከዚህ ቀደም እንዳልኩት – አህያ የነከሰ ፈሪ ጅብ ይመስል – የራሱን ሥልጣንና ሥልጣንም ያከናነበውን ምቾቶች ላለማስነጠቅ ሲል፣ አሁንም ሕዝባችንን ነክሶ የያዘው ቡድን ከማረድ እንደማይመለስ እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል!

ሕወሃት ኋላ ቀርና ባርባሪክ ከመሆኑ የተነሳ፡ አስተዳደሩና አገዛዙ፣ በ12ና 13ኛው ክፍለ ዘመን ቢመሰልም፣ ባህሪው ግን ከብዙ ሽህ ዓመታት በፊት ከነበረው የአዝቲኮች (Aztecs) የመሥዋዕት ማቅረብ ሃይማኖታዊ ባህል ጋር ተመሳሳይ ነው።

ውሃ ይጠፋ ይሆናል፡ ወይንም የመሬት መንቀጥቀጥ ያጠፋናል ብለው በመሥጋት፡ ከአንድ እስከ አምስት ዓመታት የሚሆናቸውን እስከ አምስት የሚጠጉ ወንዶች ልጆችን በየዓመቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሕዝቡ በተሰበሰበበት ሥነ ሥርዓት ላይ ቀሳውስቱ የልጆቹን ጭንቅላቶች ቀጥቅጠው ለራሳቸው ደኅንነት መላው ኅብረተሰብ ድኅነነት መዋጃ ማድረጋቸውን ስናስታውስ፡ በእርግጥም ሕወሃት ለራሱ ደህንነት (ለቡድኑ አባላት) ዛሬ ከሚያደርገው የበላይነትና ጥቅማ ጥቅሞች መጠበቅ ፍላጎትና ይህም ያስከተለው የኅብረተሰባችን መረገጥና መገደል ጋር ልይነቱን ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነው።

ይህ ባርባሪክ የሆነ አስተዳደር፣ ለዘላለም እንዲህ መቀጥል የለበትም! በዚህም ምክንያት “በቃ!” ብሎ በህዳር 2015 የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ቁጣ ለዚህ አስከፊ ሁኔታ መልስ መሆኑን ስለምናምን፣ ረመጡ አዲስ እሳት መለኮሱን እንደሚቀጥል ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለንም – ይህም የዓለም ኅብረተሰብ የለውጥን ሕግ የተከተለ ነውና!
 
3 Responses to “በኦሮሚያ በተፈጸመው ጭፍጨፋ የሰው ልጅ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም፤ ገና ከአሁኑ በሕወሃት አባሎችና/ደጋፊዎቹ መካከል ቅሬታን ታች አውርዷል! ግንባሩ ግን ቅጥፈት፣ እሥራቱንና ምሥጢራዊ ግድያውን እያፋፋመ ነው!”

 1. Yoseph Berhane December 25, 2015 at 22:07 #

  የትግራይ ህዝብን ዝምታ ሲተረጎም

  “… የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ሰው ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም። ”

  ከዚህ በመነሳት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም እንዲህ ጠየቁ:

  “አብርሃ ደስታ፤ ያልከውን አምናለሁ፤ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህና አንተ በተመቸህ መንገድ መልስልኝ፤ በትግራይ ሰዎች ሲበደሉና ሲጠቁ ሌላው ሰው ዝም የሚለው በምን ምክንያት ነው?”

  መልስ – አብርሃ ደስታ

  ኣብዛኛው የትግራይ ሰው የህወሓት መንግስት በዜጎች በደል ሲያደርስ ከመቃወም ይልቅ “ብኡ የሕልፎ” የሚል ብሂል (ወይ ኣባባል) ተግባራዊ ያደርጋል። “ብኡ የሕልፎ” የትግርኛ ኣባባል ሲሆን Literally ‘በዛ ይለፍልን’ (ወይ ‘የባሰ ኣታምጣ’) ዓይነት ትርጉም ኣለው።

  (1) ደርግ በትግራይ ህዝብ ብዙ ግፍ ያደረሰ ቢሆንም ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ገዳይ መሆኑ የትግራይ ህዝብ በደምብ ያውቃል። የህወሓት የኣገዳደል ወይ ጭቆና ስልት በጣም የረቀቀ ነው። በዚህ የረቀቀ መንገድ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ወይ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ነው’ ብሎ ያስባል፤ ይፈራልም። ለምሳሌ እኔ ህወሓትን ፊት ለፊት ስቃወም ብዙ ጓደኞቼ ህወሓት ሊገድለኝ እንደሚችል ስጋታቸው ያካፍሉኛል። (የህወሓት ተግባር በደምብ ስለሚረዱ)። ይህም ሁኖ ግን በኣሁኑ ሰዓት ብዙ የሚቃወም ኣለ። (ፓርቲውም እየተዳከመ ነው)።

  (2) የትግራይ ህዝብ: ህወሓት ደርግን ማሸነፍ በመቻሉ (ደርግ ኣስፈሪ ነበር) ‘ሃይለኛ ነው’ የሚል የሃሰት ግምት ተሰጥቶታል። በዚ መሰረት ህወሓት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ ይችላል የሚል እምነት የለውም። የህወሓት ካድሬዎች (ፖሊት ቢሮ ኣባላትን ጨምሮ) ለህዝቡ የሚናገሩት ይሄንን ነው። “ጫካ ገብተን፣ ብዙ መስዋእት ከፍለን ያመጣነው ስልጣን በምላሳቸው ለሚቃወሙን የደርግ ርዝራዦች ስልጣን ኣሳልፈን ልንሰጥ ኣንችልም ይላሉ።

  የትግራይ ህዝብ ታድያ እንዴት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ የማይችልን ስርዓት ይቃወም? ህዝቡ ህወሓቶች ከስልጣን እንደማይወርዱ ኣምኖ ከተቀበለ ፣ መቃወም ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መረዳቱ ኣይቀርም። መቃወማቸው ዉጤት ካላመጣ የሚቃወሙ ሰዎች ይገለላሉ፣ የባሰ በደል ይደርሳቸዋል። (የEDU ደጋፊዎች ነበሩ ተብለው የተፈረጁ ሰዎች እስከኣሁን ድረስ በመጥፎ ዓይን ይታያሉ)።

  ከተቃወሙ ስራ ኣያገኙም ወይ ከስራቸው ይባረራሉ። የመንግስት ኣገልግሎት (መብታቸው ቢሆንም) ይነፈጋሉ። ለምሳሌ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የደገፉ ሰዎች፣ ከመንግስት ምንም ዓይነት ድጋፍ (የፖሊስ፣ ዳኝነት፣ የደህንነት ከለላ ባጠቃላይ) ‘ኣንፈልግም’ ብለው እንዲፈርሙ (መቃወምን ከመረጡ ማለት ነው) የሚያስገድድ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል (በተለይ በገጠር ኣከባቢ)።

  ስለዚ በትግራይ መቃወም ማለት የመንግስት (ፓርቲ) ለውጥ ለማምጣት መታገል (ከተሳካም ገዢው ፓርቲ መቀየር) ማለት ሳይሆን የመንግስትን ኣገልግሎት ላለማግኘት መወሰን (በራስ ላይ ችግር መፍጠር) ማለት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር በትግራይ መቃወም ክፉኛ እንደሚጎዳ ነው። ለዚህ ነው ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም የሚለው።

  (3) የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ ወይ ፕሮፓጋንዳ ሌላው ምክንያት ነው። ህወሓት ደርግን የፈፀመው ግፍ እንደ ጥሩ ኣጋጣሚ በመጠቀም “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ይለናል። በደርግ ዘመን ደርግና ህወሓት ትግራይን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጦርነት የትግራይ ህዝብ ብዙ ስቃይ ኣሳልፈዋል። በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ግድያ ነበረ፣ ትምህርት ኣልነበረም፣ ሰላም (መረጋጋት ማለቴ ነው) ኣልነበረም፣ ገበሬው፣ ነጋዴው … በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ኣልቻለም ነበር። ባጠቃላይ ያ ዘመን ለትግራይ ህዝብ (ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብም ጭምር) መጥፎ ነበር። ህወሓት ታድያ (ደርግን በማባረሩና ጦርነቱ ጋብ ስላለ) ‘ከዚህ ሁሉ ችግር ያዳንኳቹ እኔ ነኝ። እኔ ባልኖር ኖሮ የደርግ ወታደር ይበላቹ ነበር። ህወሓቶች ከሌለን ደርግ መጥቶ ይገድላችኋል” ይለናል።

  ይባስ ብሎ ደግሞ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት የደርግን ኣስከፊነት ያስታውሳል፤ የተከፈለ መስዋእትነት 24 ሰዓት ይተርካል። ይህ የትግራይን ህዝብ ቁስል በመንካት ድጋፉን እንዲሰጥ የማስቻል ስትራተጂ ነው። ለዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ኣንድ ሬድዮ (ድምፂ ወያነ) ና ሦስት ኤፋኤም FM ሬድዮ ጣብያዎች ኣሉ።

  ከዚህ በተያያዘ ህወሓት ህዝብን ሲሰብክ ደርግን ኣማራ ኣድርጎ ያቀርበዋል (የደርግን ዓይነት ጨቋኝ ስርዓት የመምጣት ዕድል እንዳለ ለማመልከት ተፈልጎ ነው)። ደርግ ላይመለስ ሞተዋል። ስጋት ሊሆን ኣይችልም፣ ተመልሶ ሊመጣ ኣይችልም። ህወሓት ግን ህዝቡን ለማጭበርበር እስከኣሁን ኣደጋው እንዳለ ለመጠቆምና የትግራይን ህዝብ ድጋፍ እንዳይለየው ለማድረግ ‘ፀረ ደርግ’ የነበረ ትግል ‘ፀረ ኣማራ’ እንደሆነ ኣድርጎ ኣቀረበልን። (በኣንደኛ ደረጃ ትምህርታችን ሳይቀር ተምረነዋል።)

  በኣሁኑ ሰዓት ታድያ ሰው (ከትግራይ) ሲቃወም: “ከነዚህ የጠላት ቡድኖች (በብሄር ደረጃ ኣማራ ወይም ሸዋ) ወይ የደርግ ርዝራዦች ወግኖ ደርግን ወደ ስልጣን ለማስመለስ ህወሓትን ይቃወማል” በሚል ሰበብ ስሙ ይጠፋል። (እኔ ህወሓትን ስለ ተቃወምኩ የሚሰጠኝን ስም መመልከት ይቻላል)። ይሄ ነገር ታድያ እየታፈንክ ዝም ኣያሰኝም???

  (4) ደርግ የትግራይን ህዝብ ጠላት ተደርጎ ነው የሚወሰደው (በፈፀመው ግፍ)። የትግራይ ህዝብ ያን የደርግ ኣገዛዝ ኣይፈልግም። ‘ደርግ ይመለሳል’ ከተባለ ታድያ (ማመዛዘን ቢያስፈልግም) ህዝቡ ከደርግ ህወሓትን መምረጡ እንዴት ይቀራል?

  የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ሲቃወም ከተቃዋሚዎች ጎራ እንደተሰለፈ ይቆጠራል። ተቃዋሚዎች ደግሞ ‘ደርጎች’ መሆናቸው ነው ለህዝቡ ሲነገር የቆየው። ስለዚ ኣንድ ሰው (ወይም ብዙ ሰዎች) ህወሓትን ከተቃወመ ከደርግ ጋር እንደተባበረ ነው የሚቆጠረው። በትግሉ ወቅት ከደርግ ጋር የተሰለፈ ሰው ምን ዓይነት ቅጣት ይሰጠው እንደ ነበር ህዝቡ በደምብ ያውቃል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘የመቃወም ቅጣት’ ይፈራል። ፈርቶም … ሲጨቆን ዝም ይላል (የባሰ ኣታምጣ ወይ ብኡ የሕልፎ ብሎ)።

  (5) ኣብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድሃ ነው። ድህነት በራስ የመተማመን ዓቅማችን ያሽመደምደዋል። ለመቃወም የኢኮኖሚ ነፃነት ወይም ዓቅም መገንባት ያስፈልጋል (ከገዢው መደብ ለሚደርሱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሽብሮች ለመቋቋም)። ድሃ ጭቆናውን ቢቃወም እንደውጤቱ የባሰውን ይጨቆናል። ለኣምባገነኖች ጭቆና ተቃውሞን ለመቀነስ ይጠቀሙታል። ስለዚ የባሰውን ጭቆና ለማስቀረት ያለውን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ መቀበል (የትግራይ ህዝብ) እንደኣማራጭ የወሰደው ይመስለኛል።

  ሌላው ችግር ደግሞ የትግራይ ህዝብ የመረጃ ዓፈና (ከሌሎች ክልሎች በባሰ ሁኔታ ሊባል በሚችል ሁኔታ) ይፈፀምበታል። የመረጃ ችግር ኣለ። ወደ ትግራይ የሚገባ መረጃና ከትግራይ የሚወጣ መረጃ በተቻለ መጠን ሳንሱር ይደረጋል። የትግራይ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ ይደረጋል። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ስለ የኢትዮዽያ ፖለቲካ በቂ መረጃ ኣለው ብዬ ኣላምንም።

  በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ የሚፈፀሙ ችግሮች፣ በደሎች፣ ጭቆናዎች የሚዘግብና የሚያጋልጥ ሚድያ የለም። በፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚድያ ሚና የማይናቅ ነው። በትግራይ ያሉ ችግሮች በኣግባቡ ስለማይዘገቡ ሰሚ ኣያገኙም። ሰሚ ካላገኙ (1) ሰዎቹ ተቃውመው ምንም ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ስለሚረዱ እየተጨቆኑም ዝም ብለው ዝም ይላሉ፤ (2) ካልተዘገቡ በሌሎች ህዝቦች በትግራይ ችግር እንደሌለ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

  ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ዓፈናን ለመሸፈን ዓፈናን (ራሱ) እንደመሳርያ ይጠቀመዋል። እንደውጤቱም በትግራይ ተቃውሞ እንኳ ቢኖር ስለማይዘገብ ህዝቡ ህወሓትን እንደሚደግፍ ወይ እንደማይቃወም ተደርጎ ይወሰዳል። ትልቁ ችግር ይሄ ነው።

  (6) የትግራይ ህዝብ የገዢው ፓርቲ ዓፈናን ተቋቁሞ ዝምታን የሚመርጥበት ዋናው ምክንያት ስለተቃዋሚዎች ትክክለኛና በቂ መረጃ ስለሌለውና ተቃዋሚዎችም ለህዝቡ ቀርበው በማነጋገር ዓላማቸውና ማንነታቸው በግልፅ ማስረዳት ባለመቻላቸው ነው።

  ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በሙሉ ህወሓትን እንደሚደግፍና ‘ጠላት’ እንደሆነ ኣስመስለው እንደሚያቀርቡ በብዙ የትግራይ ተወላጆች (በህወሓት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት) ይታመናል። ይህንን እምነታቸው ህወሓትን የሚጠቀመው “ተቃዋሚዎች ደርጋውያን ናቸው፣ ደርግ ሙሉ በሙሉ ሞቶ ስላልተቀበረ ህወሓት እስከኣሁን ድረስ ከደርግ ጋር እየተዋጋ ነው ወዘተ” የሚል የማጭበርበር ፕርፓጋንዳ ለመቀበል ይገደዳሉ።

  በዚ መሰረት ህወሓትን እየተቃወመም ቢሆን የተቃዋሚ ድርጅቶች ግን ከህወሓት ሊብሱ ይችላሉ ብሎ እንዲያስብ ስለሚገደድ ግራ ተጋብቶ ‘የባሰ ኣታምጣ’ ብሎ ኣብሮ ዝም ይላል።

  ስለዚ ተቃዋሚዎች ከትግራይ ህዝብ ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ሳያውቁት (በሚጠቀሙት የፖለቲካ ስትራተጂ) የትግራይን ህዝብ (target የሚያደርጉ ስለሚመስሉ) በህወሓት ቢጨቆን እንኳ ህወሓትን ላለመቃወም እንዲወስን (የባሰ እንዳይመጣ) ያደርጉታል።

  ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ምክንያት ኣለው (ህወሓት ስለሚደግፍ ግን ኣይደለም)።

  “የትግራይ ህዝብ” የሚወክለው ኣብዛኛውን ህዝብ እንጂ ጥቂት የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚዎችን ኣያጠቃልልም። ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሚሰሩት ተግባር ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሓት እንደሚደግፍ ኣስመስለው ለማቅረብ ስለሚሞክሩ ሌሎች ሰዎች እውነት ሊመስላቸው ይችላል።

  … ግን ዝምታ መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም።

  See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/1156#sthash.VQVrzjmb.dpuf

  የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

  የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤

  በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤

  በትግሬነታቸው ብቻ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

  ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤

  የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፡፡

  በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው?

  ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤

  በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

  ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? ያለፈው አልፏል፤ በመጪው ጊዜያት ይህን ፍርሃት አሸንፎ ትግርኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ የለውጡ አካል ለማድረግ፣ ለሥርዓት ቅየራው የሚካሄደው ትግል ዘርን መሰረት ያደረገ አግላይ የመከራ መስቀልን በጋራ ለመሸከም ዝግጁ መሆንን የሚያካትት ሊሆን ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡

  ምክንያቱም ጠረጴዛው ላይ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነውና፤ ወይ አብሮ መውደቅ፣ አልያም በህብረት መነሳት፡፡

  የትግራይን መስቀል ስለመሸከም ….ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

  “እናንተ ክዳችሁናል! ለ17 ዓመታት ልጆቻችንን በጦርነት ማግዳችሁ ስታበቁ፤ ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀማችሁት ነገር የለም፡፡ እንዲያውም በሌሎች ክልሎች ላይ በሚገኙ ወገኖቻችንን ላይ በምታደርሱት በደል በጠላትነት እንድንመለከት ነው ያደረጋችሁን፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ አናምናችሁም!!” – የትግራይ ህዝብ

  “ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ (ማሌሊት) ለትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ጠበቃ መስሎ በመቅረብ በሌሎች ሕዝቦች ላይ እየፈፀማቸው ባሉ ግልፅና ስውር ወንጀሎች ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ በገዛ አገሩ በአይነ-ቁራኛና በጥርጣሬ እንዲታይ ማድረጉ ነው፡፡” – የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/

  See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31331

  Like

 2. Yoseph December 25, 2015 at 22:15 #

  የትግራይ ህዝብን ዝምታ ሲተረጎም (አብርሃ ደስታ – ከመቀሌ)

  “… የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ሰው ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም። ”

  ከዚህ በመነሳት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም እንዲህ ጠየቁ:

  “አብርሃ ደስታ፤ ያልከውን አምናለሁ፤ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህና አንተ በተመቸህ መንገድ መልስልኝ፤ በትግራይ ሰዎች ሲበደሉና ሲጠቁ ሌላው ሰው ዝም የሚለው በምን ምክንያት ነው?”

  መልስ: አብርሃ ደስታ

  ኣብዛኛው የትግራይ ሰው የህወሓት መንግስት በዜጎች በደል ሲያደርስ ከመቃወም ይልቅ “ብኡ የሕልፎ” የሚል ብሂል (ወይም ኣባባል) ተግባራዊ ያደርጋል።

  “ብኡ የሕልፎ” የትግርኛ ኣባባል ሲሆን Literally ‘በዛ ይለፍልን’ (ወይ ‘የባሰ ኣታምጣ’) ዓይነት ትርጉም ኣለው።

  (1) ደርግ በትግራይ ህዝብ ብዙ ግፍ ያደረሰ ቢሆንም ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ገዳይ መሆኑ የትግራይ ህዝብ በደምብ ያውቃል። የህወሓት የኣገዳደል ወይ ጭቆና ስልት በጣም የረቀቀ ነው። በዚህ የረቀቀ መንገድ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ወይ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ነው’ ብሎ ያስባል፤ ይፈራልም። ለምሳሌ እኔ ህወሓትን ፊት ለፊት ስቃወም ብዙ ጓደኞቼ ህወሓት ሊገድለኝ እንደሚችል ስጋታቸው ያካፍሉኛል። (የህወሓት ተግባር በደምብ ስለሚረዱ)። ይህም ሁኖ ግን በኣሁኑ ሰዓት ብዙ የሚቃወም ኣለ። (ፓርቲውም እየተዳከመ ነው)።

  (2) የትግራይ ህዝብ: ህወሓት ደርግን ማሸነፍ በመቻሉ (ደርግ ኣስፈሪ ነበር) ‘ሃይለኛ ነው’ የሚል የሃሰት ግምት ተሰጥቶታል። በዚ መሰረት ህወሓት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ ይችላል የሚል እምነት የለውም። የህወሓት ካድሬዎች (ፖሊት ቢሮ ኣባላትን ጨምሮ) ለህዝቡ የሚናገሩት ይሄንን ነው። “ጫካ ገብተን፣ ብዙ መስዋእት ከፍለን ያመጣነው ስልጣን በምላሳቸው ለሚቃወሙን የደርግ ርዝራዦች ስልጣን ኣሳልፈን ልንሰጥ ኣንችልም ይላሉ።

  የትግራይ ህዝብ ታድያ እንዴት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ የማይችልን ስርዓት ይቃወም? ህዝቡ ህወሓቶች ከስልጣን እንደማይወርዱ ኣምኖ ከተቀበለ ፣ መቃወም ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መረዳቱ ኣይቀርም። መቃወማቸው ዉጤት ካላመጣ የሚቃወሙ ሰዎች ይገለላሉ፣ የባሰ በደል ይደርሳቸዋል። (የEDU ደጋፊዎች ነበሩ ተብለው የተፈረጁ ሰዎች እስከኣሁን ድረስ በመጥፎ ዓይን ይታያሉ)።

  ከተቃወሙ ስራ ኣያገኙም ወይ ከስራቸው ይባረራሉ። የመንግስት ኣገልግሎት (መብታቸው ቢሆንም) ይነፈጋሉ። ለምሳሌ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የደገፉ ሰዎች፣ ከመንግስት ምንም ዓይነት ድጋፍ (የፖሊስ፣ ዳኝነት፣ የደህንነት ከለላ ባጠቃላይ) ‘ኣንፈልግም’ ብለው እንዲፈርሙ (መቃወምን ከመረጡ ማለት ነው) የሚያስገድድ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል።

  ስለዚ በትግራይ መቃወም ማለት የመንግስት (ፓርቲ) ለውጥ ለማምጣት መታገል (ከተሳካም ገዢው ፓርቲ መቀየር) ማለት ሳይሆን የመንግስትን ኣገልግሎት ላለማግኘት መወሰን (በራስ ላይ ችግር መፍጠር) ማለት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር በትግራይ መቃወም ክፉኛ እንደሚጎዳ ነው። ለዚህ ነው ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም የሚለው።

  (3) የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ ወይ ፕሮፓጋንዳ ሌላው ምክንያት ነው። ህወሓት ደርግን የፈፀመው ግፍ እንደ ጥሩ ኣጋጣሚ በመጠቀም “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ይለናል። በደርግ ዘመን ደርግና ህወሓት ትግራይን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጦርነት የትግራይ ህዝብ ብዙ ስቃይ ኣሳልፈዋል። በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ግድያ ነበረ፣ ትምህርት ኣልነበረም፣ ሰላም (መረጋጋት ማለቴ ነው) ኣልነበረም፣ ገበሬው፣ ነጋዴው በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ኣልቻለም ነበር። ባጠቃላይ ያ ዘመን ለትግራይ ህዝብ (ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብም ጭምር) መጥፎ ነበር።

  ህወሓት ታድያ (ደርግን በማባረሩና ጦርነቱ ጋብ ስላለ) ‘ከዚህ ሁሉ ችግር ያዳንኳቹ እኔ ነኝ። እኔ ባልኖር ኖሮ የደርግ ወታደር ይበላቹ ነበር። ህወሓቶች ከሌለን ደርግ መጥቶ ይገድላችኋል” ይለናል።

  ይባስ ብሎ ደግሞ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት የደርግን ኣስከፊነት ያስታውሳል፤ የተከፈለ መስዋእትነት 24 ሰዓት ይተርካል። ይህ የትግራይን ህዝብ ቁስል በመንካት ድጋፉን እንዲሰጥ የማስቻል ስትራተጂ ነው። ለዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ኣንድ ሬድዮ (ድምፂ ወያነ) ና ሦስት ኤፋኤም FM ሬድዮ ጣብያዎች ኣሉ።

  ከዚህ በተያያዘ ህወሓት ህዝብን ሲሰብክ ደርግን ኣማራ ኣድርጎ ያቀርበዋል (የደርግን ዓይነት ጨቋኝ ስርዓት የመምጣት ዕድል እንዳለ ለማመልከት ተፈልጎ ነው)። ደርግ ላይመለስ ሞተዋል። ስጋት ሊሆን ኣይችልም፣ ተመልሶ ሊመጣ ኣይችልም። ህወሓት ግን ህዝቡን ለማጭበርበር እስከኣሁን ኣደጋው እንዳለ ለመጠቆምና የትግራይን ህዝብ ድጋፍ እንዳይለየው ለማድረግ ‘ፀረ ደርግ’ የነበረ ትግል ‘ፀረ ኣማራ’ እንደሆነ ኣድርጎ ኣቀረበልን። (በኣንደኛ ደረጃ ትምህርታችን ሳይቀር ተምረነዋል።)

  በኣሁኑ ሰዓት ታድያ ሰው (ከትግራይ) ሲቃወም: “ከነዚህ የጠላት ቡድኖች (በብሄር ደረጃ ኣማራ ወይም ሸዋ) ወይ የደርግ ርዝራዦች ወግኖ ደርግን ወደ ስልጣን ለማስመለስ ህወሓትን ይቃወማል” በሚል ሰበብ ስሙ ይጠፋል። (እኔ ህወሓትን ስለ ተቃወምኩ የሚሰጠኝን ስም መመልከት ይቻላል)። ይሄ ነገር ታድያ እየታፈንክ ዝም ኣያሰኝም???

  (4) ደርግ የትግራይን ህዝብ ጠላት ተደርጎ ነው የሚወሰደው (በፈፀመው ግፍ)። የትግራይ ህዝብ ያን የደርግ ኣገዛዝ ኣይፈልግም። ‘ደርግ ይመለሳል’ ከተባለ ታድያ (ማመዛዘን ቢያስፈልግም) ህዝቡ ከደርግ ህወሓትን መምረጡ እንዴት ይቀራል?

  የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ሲቃወም ከተቃዋሚዎች ጎራ እንደተሰለፈ ይቆጠራል። ተቃዋሚዎች ደግሞ ‘ደርጎች’ መሆናቸው ነው ለህዝቡ ሲነገር የቆየው። ስለዚ ኣንድ ሰው (ወይም ብዙ ሰዎች) ህወሓትን ከተቃወመ ከደርግ ጋር እንደተባበረ ነው የሚቆጠረው። በትግሉ ወቅት ከደርግ ጋር የተሰለፈ ሰው ምን ዓይነት ቅጣት ይሰጠው እንደ ነበር ህዝቡ በደምብ ያውቃል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘የመቃወም ቅጣት’ ይፈራል። ፈርቶም ሲጨቆን ዝም ይላል (የባሰ ኣታምጣ ወይ ብኡ የሕልፎ ብሎ)።

  (5) ኣብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድሃ ነው። ድህነት በራስ የመተማመን ዓቅማችን ያሽመደምደዋል። ለመቃወም የኢኮኖሚ ነፃነት ወይም ዓቅም መገንባት ያስፈልጋል (ከገዢው መደብ ለሚደርሱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሽብሮች ለመቋቋም)። ድሃ ጭቆናውን ቢቃወም እንደውጤቱ የባሰውን ይጨቆናል። ለኣምባገነኖች ጭቆና ተቃውሞን ለመቀነስ ይጠቀሙታል። ስለዚ የባሰውን ጭቆና ለማስቀረት ያለውን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ መቀበል (የትግራይ ህዝብ) እንደኣማራጭ የወሰደው ይመስለኛል።

  ሌላው ችግር ደግሞ የትግራይ ህዝብ የመረጃ ዓፈና (ከሌሎች ክልሎች በባሰ ሁኔታ ሊባል በሚችል ሁኔታ) ይፈፀምበታል። የመረጃ ችግር ኣለ። ወደ ትግራይ የሚገባ መረጃና ከትግራይ የሚወጣ መረጃ በተቻለ መጠን ሳንሱር ይደረጋል። የትግራይ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ ይደረጋል። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ስለ የኢትዮዽያ ፖለቲካ በቂ መረጃ ኣለው ብዬ ኣላምንም።

  በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ የሚፈፀሙ ችግሮች፣ በደሎች፣ ጭቆናዎች የሚዘግብና የሚያጋልጥ ሚድያ የለም። በፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚድያ ሚና የማይናቅ ነው። በትግራይ ያሉ ችግሮች በኣግባቡ ስለማይዘገቡ ሰሚ ኣያገኙም። ሰሚ ካላገኙ (1) ሰዎቹ ተቃውመው ምንም ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ስለሚረዱ እየተጨቆኑም ዝም ብለው ዝም ይላሉ፤ (2) ካልተዘገቡ በሌሎች ህዝቦች በትግራይ ችግር እንደሌለ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

  ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ዓፈናን ለመሸፈን ዓፈናን (ራሱ) እንደመሳርያ ይጠቀመዋል። እንደውጤቱም በትግራይ ተቃውሞ እንኳ ቢኖር ስለማይዘገብ ህዝቡ ህወሓትን እንደሚደግፍ ወይ እንደማይቃወም ተደርጎ ይወሰዳል። ትልቁ ችግር ይሄ ነው።

  (6) የትግራይ ህዝብ የገዢው ፓርቲ ዓፈናን ተቋቁሞ ዝምታን የሚመርጥበት ዋናው ምክንያት ስለተቃዋሚዎች ትክክለኛና በቂ መረጃ ስለሌለውና ተቃዋሚዎችም ለህዝቡ ቀርበው በማነጋገር ዓላማቸውና ማንነታቸው በግልፅ ማስረዳት ባለመቻላቸው ነው።

  ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በሙሉ ህወሓትን እንደሚደግፍና ‘ጠላት’ እንደሆነ ኣስመስለው እንደሚያቀርቡ በብዙ የትግራይ ተወላጆች (በህወሓት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት) ይታመናል። ይህንን እምነታቸው ህወሓትን የሚጠቀመው “ተቃዋሚዎች ደርጋውያን ናቸው፣ ደርግ ሙሉ በሙሉ ሞቶ ስላልተቀበረ ህወሓት እስከኣሁን ድረስ ከደርግ ጋር እየተዋጋ ነው ወዘተ” የሚል የማጭበርበር ፕርፓጋንዳ ለመቀበል ይገደዳሉ።

  በዚ መሰረት ህወሓትን እየተቃወመም ቢሆን የተቃዋሚ ድርጅቶች ግን ከህወሓት ሊብሱ ይችላሉ ብሎ እንዲያስብ ስለሚገደድ ግራ ተጋብቶ ‘የባሰ ኣታምጣ’ ብሎ ኣብሮ ዝም ይላል።

  ስለዚ ተቃዋሚዎች ከትግራይ ህዝብ ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ሳያውቁት (በሚጠቀሙት የፖለቲካ ስትራተጂ) የትግራይን ህዝብ (target የሚያደርጉ ስለሚመስሉ) በህወሓት ቢጨቆን እንኳ ህወሓትን ላለመቃወም እንዲወስን (የባሰ እንዳይመጣ) ያደርጉታል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ምክንያት ኣለው (ህወሓት ስለሚደግፍ ግን ኣይደለም)።

  “የትግራይ ህዝብ” የሚወክለው ኣብዛኛውን ህዝብ እንጂ ጥቂት የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚዎችን ኣያጠቃልልም። ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሚሰሩት ተግባር ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሓት እንደሚደግፍ ኣስመስለው ለማቅረብ ስለሚሞክሩ ሌሎች ሰዎች እውነት ሊመስላቸው ይችላል።

  … ግን ዝምታ መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም።

  See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/1156#sthash.VQVrzjmb.dpuf

  የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

  የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤

  እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤

  ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤

  ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤

  አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

  ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤

  የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤

  አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው

  በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው?

  የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው?

  ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤

  በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

  ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? ያለፈው አልፏል፤ በመጪው ጊዜያት ይህን ፍርሃት አሸንፎ ትግርኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ የለውጡ አካል ለማድረግ፣ ለሥርዓት ቅየራው የሚካሄደው ትግል ዘርን መሰረት ያደረገ አግላይ የመከራ መስቀልን በጋራ ለመሸከም ዝግጁ መሆንን የሚያካትት ሊሆን ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡

  ምክንያቱም ጠረጴዛው ላይ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነውና፤ ወይ አብሮ መውደቅ፣ አልያም በህብረት መነሳት፡፡

  See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30571

  የትግራይን መስቀል ስለመሸከም ….ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

  “እናንተ ክዳችሁናል! ለ17 ዓመታት ልጆቻችንን በጦርነት ማግዳችሁ ስታበቁ፤ ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀማችሁት ነገር የለም፡፡ እንዲያውም በሌሎች ክልሎች ላይ በሚገኙ ወገኖቻችንን ላይ በምታደርሱት በደል በጠላትነት እንድንመለከት ነው ያደረጋችሁን፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ አናምናችሁም!!” – የትግራይ ህዝብ

  “ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ (ማሌሊት) ለትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ጠበቃ መስሎ በመቅረብ በሌሎች ሕዝቦች ላይ እየፈፀማቸው ባሉ ግልፅና ስውር ወንጀሎች ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ በገዛ አገሩ በአይነ-ቁራኛና በጥርጣሬ እንዲታይ ማድረጉ ነው፡፡” – የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/

  See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31331

  Like

  • THE ETHIOPIA OBSERVATORY December 26, 2015 at 00:05 #

   The Editor writes:

   “በኦሮሚያ በተፈጸመው ጭፍጨፋ የሰው ልጅ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም፤ ገና ከአሁኑ በሕወሃት አባሎችና/ደጋፊዎቹ መካከል ቅሬታን ታች አውርዷል! ግንባሩ ግን ቅጥፈት፣ እሥራቱንና ምሥጢራዊ ግድያውን እያፋፋመ ነው!” የሚለውን ጽሁፍ ብወጣሁ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ አቶ ዮሴፍ ብ. ከዚህ በታች የቀረበውን አስተያየት ላኩልኝ።

   እኔም ይዘቱና አቀራረቡ በግለሰቦችና ብሎም በሕዝባችን መካከል መግባባት እንዲፈጠር ይረዳል በሚል ወዲያውኑ ከጽሁፌ ሥር ደብዳቤዎች የሚቀመጡበት ሥፍራ አሰለፍኩት።

   ደብዳቤያቸው ከታተመ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፡ ይህንን የአቶ ዮሴፍን ደብዳቤ ብዙ ሰው በደንቡ እንዲያነበውና፡ አንባብያንም ከመረጡ ወደ ተከታታይ ውይይት እንዲያመራቸው ለምን በኢትዮጵያ ኦብዘርቫቶሪ ላይ፡ ከአንድ መግቢያ ጋር እንደ አርቲክል አላወጣውም ከሚል ማውጣት ጋር ብዙ መከራከሬ አልቀረም።

   ነገር ግን ቀደም ብሎ አብርሃ ደስታ እንደጻፈው ተነቧልና ከላይ የመጣውን ሃሣብ ውድቅ አደረግሁት። እዚህ ውሳኔ ላይ ከደረስኩ በኋላ ግን፣ አቶ ዮሴፍ እንደገለጹልን ከሆነና ሃገር ውስጥ ያሉት ትግራውያን ሕወሃትን በመፍራት ሊቆጠቡ ይችላሉ የሚለውን ልንቀበል እንችል ይሆናል – ይህ የእያንዳንዱ ዜጋ ውሳኔ ነው።

   ሆኖም፥ ውጭ ሃገሮች የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ትግሬዎች – ድርጅታቸውን መክረው ከጥፋትና አጥፊነት ሊያድኑት ሲገባ – ብዙዎቹ በብዙ መልኩ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን ሲያስተጋቡ በብዙ አጋጣሚዎች በኃዘን ተመልከተናል።

   ከዚያ በላይም ከስሜን አሜሪካ በማኅበራቸው አማካይነትም ከ2005 ጀምሮ፣ ከሕወሃት ጋር እጅና ጓንት በመሆን፥ በወንጀሉ ጭምር ተባባሪ እስኪመስሉ ድረስ ለግንባሩ የሰጧቸውን ደጋፎችና አጋጣሚዎች አንድ ሁለት ብሎ መቁጠር ይቻላል!

   አቶ ዮሴፍ በዚህ ረገድ ያላቸውን አመለካከት፥ በነገሩ ላዘኑትና ለተረበሹት ኢትዮጵያውያን ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የሚለግሱት አስተያየት ካለ በዚህ የደብዳቤዎች አምድ ለማስተናገድ ዝግጁነቴን አረጋግጥላቸዋለሁ!

   ሌላው ትንሽ ያስገረመኝ፡ አቶ ዮሴፍ ይህንን ሌላ ሰው የጻፈውን ደብዳቤ ሲልኩልኝ፡ ሕወሃት በሃገራችን ውስጥ ባለፉት አምስት ሣምንታት ስለ ኦሮሞች ጭፍጨፋ አመለካከታችውን በአንድ መሰመር እንኳ የጠቀሱት ነገር አለመኖሩ፡ ፖለቲካውን ጠሉት ወይንስ፡ እርሳቸውም ስዊደን ተቀምጠው ሥጋት ተሰምቷቸው ይሆን ለሚለው መልስ አላገኘሁም!

   ከእርስዎ ለመስማት ዐይንም ጆሮ ሆኜ ጠብቃለሁ!

   Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: