መደመጥ ያለበት!                                         ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር ከ2015 ምርጫ የሕወሃት አሰመራጭነታቸው ባሻገር፡ አሁን ደግሞ ‘በኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽነርነታቸው’ የግንባሩን መሬት ዘረፋና የሕዝብ ጭፍጨፋ ሕጋዊ ለማድረግ ሲጥሩ፣ ሁለት ኢትዮጵያውያን ምሁራን በዶቼ ቬሌ ሃይ ሲሏቸው!

28 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን ሕወሃት ምርጫውን መቶ በመቶ ባሸነፈበት ማግሥት ሪፖርተር ዘግቧል፡፡


 
ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ያለፉትን ሁለት አጠቃላይ ምርጫዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ 547ቱንም የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉበትን የ2007 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ በመምራት በሕግ የተፈቀደላቸውን የሥልጣን ዘመን አጠናቀዋል ይላል የሪፖርተር ዘገባ፡፡

ወደ ጎን እያዩ ወደፊት የሚሄዱ የሚመስላቸው ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር (ፎቶ ሪፖርተር)

በስም ዋናው የምርጫው አስፈጻሚ ዶ/ር መርጋ በቃና በጃፓናዊ ስለምታ አጎንብሰው ምክትላቸውን በስግደት ሲሸኟቸው፡ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔርም ወደ ጎን እያዩ ወደፊት የሚሄዱ እየመሰላቸው በማምራት ላይ እንዳሉ ይታያሉ! (ፎቶ ሪፖርተር)

አሁን ደግሞ በአዲሱ የሹመት ቦታቸው እንደ ሕወሃትት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነርነታቸው፤ የግንባሩን መሬት የመዝረፍና ሕዝብን የመጨፍጨፍ መብት በመደገፍ ሲከራከሩ ላዳመጠ ሰው፡ ማናቸውም ዜጋ ሊገባውና ሊፈርደው በሚችል መጠን ያንን መንግሥታዊ መዋቅር በማራከስ ለእኩይ የዘረኝነት ድጋፋቸውን መሠጥታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ብሎ እኝህን ግለሰብ ሊፋረዳቸው ይገባል!

አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ማናቸው?

የአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከአዲስ አበባ ለስቴት ዲፖርትመንት በ1997 ምርጫ ሰሞን የጻፉትን ጠቅሶ፣ ዊኪሊክስ እንደዘገበው፣ ዶ/ር አዲሱ በብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽ ውስጥ የሚታወቁት የሕወሃትን ፍላጎቶች አስፈጻሚ መሆናቸው ሲሆን፡ ይኸውም እንደሚክተለው ተገልጿል፦

“Tigrayan political scientist widely believed to be the “enforcer” at the NEB” [National Election Board].

አሁንም የዘር ሃረጋቸውና ዘላቂ ጥቅሞቻቸው አመዝነውባቸው፣ በተሸፋፈነ ቋንቋ፣ ሕወሃት ኦሮሞችንና ሌሎቹን ኢትዮጵያውያን የመደምሰስ ወይን ረግጦ የመግዝት ፍላጎቱን በመደገፍ “ምን ታደርጉኛላቹ በሚል ንቀት?” ሲከራክሩ ነው በዶቼ ቬሌ የሚደመጡት!
 

ተዛማጅ ጉዳይ፡

    ሃቢታት ሆምስ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከቤት አስሪዎቹ ጋር በፈጠረው ውዝግብ መንግስት 190 ሚልየን ብር ገቢ አላገኘም

    አስፈሪው፣ አሳሳቢውና አሳፋሪው የሕወሃት መሬት ዘረፋሥርወ መሠረትና ዓላማዎች!

    በኦሮሚያ በተፈጸመው ጭፍጨፋ የሰው ልጅ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም፤ ገና ከአሁኑ በሕወሃት አባሎችና/ደጋፊዎቹ መካከል ቅሬታን ታች አውርዷል! ግንባሩ ግን ቅጥፈት፣ እሥራቱንና ምሥጢራዊ ግድያውን እያፋፋመ ነው!

    የዛሬውንና ነገ የሚከተለውን ኢትዮጵያውያን ለሕወሃት አባሎች ባርነትና ግርድና ከወዲሁ ለማቆም፥ ዜጎች በጋራ ለክብራቸውና ነፃነታችው ትግላቸውን ማፋፋም ይገባቸዋል!

%d bloggers like this: