ሕወሃት የኦሮሚያን ሕዝባዊ ተቃውሞ አከሸፍኩ ብሎ መፎከሩን ሳያቆም፣ለምን እንደገና አገረሸ?

29 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ለሣምንት ጋብ ብሎ የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ካለፈው አርብ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ጀምሮ በምዕራብ ወለጋ፣ በም ዕራብና ሰሜን ሸዋ በተለያሉ ከተሞች ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤቶች ተቀጣጥሎ መቀጠሉን ኢሣት የሃገር ቤት ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ምክንያቱን ዘግቧል።
 

እስካ ሣምንት በፊት በነበረው የአምስት ሣምንት የሕዝብ ተቃውሞ 122 ሰዎች በሕወሃት ወታደሮችና ፖሊሶች ተገድለዋል፣ እንዲሁም ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች በእሥር ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። እሥሩም፣ ግለሰቦች የደረሱበት ቦታ አለመታወቁ ቀጥሏል።

ባለፈው ዓመትና አሁንም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተፈጸመበት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢሣት እንደዘገበው፣ የዩኒቨርሲቲው ካምፐስ ወታደራዊ ካምፕ በሚመስል መልኩ በሠራዊት መጥለቅለቁን ለማወቅ ተችሏል።

ምንግግስት ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ስብሰባ እንዲሳተፉ ያደረገው ጥሪና ግፊት ተማሪዎቹን እንዳስቆጣችው ይነገራል።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በፖሊስ ዱላ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ዕርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ወደ እሥር ቤቶች ተግዘዋል።

አብዛኛው ተማሪ ግን ካምፐሱን ለቆ ወጥቷል።

የአምቦ ተማሪዊች ለኢሣት እንደገለጹት፣ አሁን ባለው ሁኔታ ‘መንግሥትና’ ሕዝብ ሆድና ጀርባ ሆነዋል ይላሉ። በወለጋ በሆሮ ጉድሩ፣ በሰሜን ሸዋ ኢጅሬና ሂጃቡ አቦ ተማሪዎች ክፖኪስና ወታደራዊ ኮምንዶች ጋር መጋጨታቸው ተገልጿል።

ሰሞኑን ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂ የኦሮሞ መሪዎች እየተለቀሙ መታሠራቸው ቀደም ብሎ የተዘገብ ሲሆን፡ የአስተዳደሩ ጥቃት ኦሮሞና ኦሮሞ ያልሆኑ ጋዜጠኞችም ላይ ጥላውን አጥልቷል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች ደረጃም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) የመጀመሪያው ግንባር ቀደም ተጠቂ ሲሆን፣ ሌሎችም – ለምሣሌ እንደ ሰማያዊ ፖርቲ/አንድነት ዐይነቶችም – አንዳንድ አባሎቻቸውን በማሠር ዱላው አርፎባቸዋል።

አሁን ካለው ሁኔታ የሚታየው፣ ሁሉን ረግጦና አስፈራርቶ የመግዛት የሕወሃት የጠብ ያለሽ በዳቦ ለመሆኑ ምንም አያጠራጥም። ውድቀት ሲቃረብ፣ የዚህ ዐይነቱ ቀቢሰ ተስፋ በታሪክ በተደጋጋሚ መመዝገቡ ይታወቃል!
 

%d bloggers like this: