አዲስ ስምምነት ካርቱም ላይ በተፈረመ ማግሥት የግብጹ ፕሬዚደንት በሕዳሴ ግድብ ምክንያት ጭንቀት እንዳይሰማው የግብጽን ሕዝብ ሲያበረታቱ፣ ድንቁርናና ብልግናው ተንፍሶ አየር ያጣ ጎማ የመሰለው ሕወሃት እስካሁን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሠጠውን ቃል ፈልጎ ያገኝ አይመስልም !

31 Dec
የካርቱም ስምምነት የሶስቱ ሃገሮች ተደራዳሪዎች (ከፋና)

የካርቱም ስምምነት የሶስቱ ሃገሮች ተደራዳሪዎች (ከፋና)

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

አህራም ኦንላይን ረቡዕ ከቀትር በኋላ እንደዘገበው፣ ግብጽ አዲስ የካርቱምን ስምምነት ማክሰኞ ታህሳስ 29/2015 በአንድ በኩል የሕዳሴ ግድብ ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያና በሌላ ደግሞ የታችኛው ተፋሳሽ ሃገር ከሆነቸው ሱዳን ጋር “በተፈረመ 24 ሰዓት ውስጥ” የግብጹ ፕሬዚደንት ሲሲ የፋርፋራ ኦኤሲስ [Farafra oasis] የግብርና መሠረተ ልማት ምረቃ ላይ ተግኝተው ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ይህንን አሉ:-

“ኢትዮጵያ አባይ ላይ እየገነባችው ያለችውን ግድብ በተመለከተ፣ አይዟችሁ ምንም ነገር ሊያስጨንቃችሁ አይገባም!”

በኢትዮጵያ ስም ተክፋይ የሆነው የሕወሃት መል ዕክተኞች ያሉት ነገር የለም። በሚድያም ላይ ሮይተርና አህራም የጻፉትን ተርጉሞ ከማቅረብ ውጭ፡ የሃገሪቱን እጅ አሳስረው ለሕዝቡ ድፍንፍን ከማድረግ ውጭ ምንም ሊሉ አልቻሉም! አይችሉም!

በዘረፋ ብቻ ልባቸው የተደፈነና ዐይናቸው የታወረው ‘የሕወሃት መኳንንት’ እንዳሰሉት ሳይሆን፡ ግብጽ ያላትን ዕቅድና ዝግጅት ግልጽ ማድረግ ከጀመረች ሰንበት ብሏል! በተጨማሪም፡ ግንባሩ ሃገራችንን እየመራ ያለበትና ዛሬ ያደረሳት ሥፋራ ለዚህ የግብጽ ዒላማ አመች እንዳደረጋት አያጠራጥርም!

ሲሲ የአባይን ግድብ ጉዳይ፥ ለራሳቸውም ሥልጣን መጠናከርና የሕዝባቸውን ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሊያደርጉት እንደሚችሉ በኢትዮጵያ በኩል 24 ሰዓት መታሰብ ነበረበት።

በተደጋጋሚ በዚህ አምደ ላይ፣ የግብጽ ሕዝብና የግብጽ መንግሥት በግልጽነትና በቀጥታ መነጋገር የሚችሉበት ነገር ቢኖር፡ በአባይ ጉዳይ ነው በማለት ደጋግመን ጽፈናል። ነውም። ሁለቱም አንድ የሚስማሙበት አቋም ለማግኝትና በዚያም ላይ በመተማመን ሲሠሩ ኖረዋል። ከሥልጣን ከወረወሩት የሙባራክ ዘመን እንኳ፡ አባይን በተመለከተ ጠንካራ እምነት ተንዶ አያውቅም! በሞርሲ አጭር ዘመን፣ ግብጾች በተደጋጋሚ ምነው ሙባረክ በኖረ ማለታቸው እንዴት ተዘነጋን?


ከካርቱም ስብሰባ በፊ ትሲሲ ሁለት ዋነኛ ሚኒስትሮቻቸውን ጠርተው የመጨረሻውን መመሪያ ሠጥተው ነበር። አንዱ እዚያ ላይ ግልጽ የሆነው፣ የፕሬዚደንቱ መመሪያ አህራም የጠቀሰው “..time is a critical factor in reaching “positive results” that would satisfy all parties.” የሚለውን ነበር። (Cr: Ahram)

የሚያሳዘነው ግን፣ ሃገር ከሃዲ በሆነው ሕወሃት ምክንያት፡ በአባይ ጉዳይ እንኳ ሳይቀር ኢትዮጵያውያን ተከፋፍለውና፣ በሃገራቸው መሠረታዊ ጉዳይ እንኳ ባዕድ ተደርገው፣ ሕወሃት የሚፈልገው ገንዘባችውንና መዋጮዋቸውን ብቻ ሆኖ ቆይቷል።

የአባይ ጉዳይ፣ ሕወሃት ሃገራችንን ግራ ባጋበበት የአጭበርባሪነት መንገድ ብቻ የሚከናወን እንዳልሆነ ከግብጾች በኩል የተለሳለሱ ወይንም የተዘናጉ የሚያስመስሉ ምልክቶች – በዲፕሎማቲክ ቋንቋ feelers – ሲያሳዩ ቆይተዋል። ይህ ተጨባጭ ሁኔታ ባይኖር እንኳ፣ ፕሬዚደንት ሲሲ ሊፈጥሩትም ሁኔታው በሳቸውም በኩል አስገዳጅ ሆኖ መቆየቱ እንዴት ሊታሰብ አልተቻለም የሚለው ጥያቄ ወደፊት በሠፊው እንደሚነሳ ጥርጥር የለኝም!

ታህሳስ 15/2015 በጻፍኩት ርዕሰ አንቀጽ፣ Worried about its Nile water share in the face of stalled talks, Egypt mulls options – hostilities redux!፣ በአባይ ጉዳይ ላይ በሥነ ሥርዓት ዘላቂ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ፣ በአፍቅሮተ ገንዘብ የደነዘዙትን የሕወሃት ሰዎች በተባበሩት ኤምሬትስ በኩል መወያየታቸው በጣም እንደመረረኝና ተስፋ እንዳስቆረጠኝ ጠቅሼ ነበር።

ግብጾች ወደ ካርቱም ለስበሰባ ከማቅናታቸው በፊት ከተለያዩ አካሎች ግን አንድ ዓላማ ያላቸው አመለካከቶች ነበሯቸው። ለምሳሌ ኅዳር 18/2015፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸሪፍ እስማኤል ሻርም ኤልሼክ ላይ በነበራችው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ግብጽ ሶስት ችግሮች አሏት አሉ። እነዚህም:-

    (ሀ)   ግብጽ በአባይ ላይ ያላት ‘ታሪካዊ የውሃ መብት’

    (ለ)   የኢትዮጵያ ግድብ በምንም መልኩ የግብጽን የውሃ ድርሻ እንዳይነካና

    (ሐ)   የሕዳሴ ግድብ በግብጽ ላይ የፖለቲካ መሣሪያ እንዳይሆን ማድረግ ነው ነበር ያሉት።

ይህንኑ በተመለከተ፡ ከካርቱም ስብሰብስ ሁለት ሣምንት ቀደም ብሎ የመስኖ ሚኒስትሩ ሆሳም ሞጋዚ ቴክኒካዊ ጥናቶቹ ሳይካሄዱ፡ ግድቡ እየተሠራ ያለበት ፍጥነት፣ ውሃ በአስቸኳይ ሞልቶ ወሳኝ እንዲሆን (fait accompli) ለማድረግ በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት/ዝግጅት መኖሩን አሰምተው ሃገራቸው ይህንን በምንም መልኩ እንደማትቀበል ዛቻቸውን ሠንዝረዋል

ሌላው ‘ማምታቻ’ መሣሪያ ሲሲ የተባበሩት ኤምሬትስን አማላጅነት ኢትዮጵያ ላይ ሲጭኑ፣ ያቺ ሃገር ከኢትዮጵያ ለሚዘረፈው ገንዘብ መውጫ በር በመሆኗና ሕወሃት የበለጠ እንዲታወር እንጂ፡ እውነትም ለግድቡ የግብጽ ችግር መፍትሄ ለመሻት አልነበረም።

ነገሩ በደንብ ታስቦበት ነው ቢባል እንኳ፣ ምንድነው ያቺ ሃገር በዚህ ጉዳይ ላይ ያላት የተለየ ዕውቀት ወንም አስተዋጽዖ! ምንም! ቢኖራት እንኳ እንደ ሌሎቹ አረቦች ሁሉ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም የአረብ ውሃ ምክር ቤት [Arab Water Council] አባል ናትና ዓላማዋም፣ አባይን ጭምር የአረብ ውሃ አድርጎ ከመመልከት የራቀ አይደለም – በተለይም በግብጽና በኤሚሬትስ መካከል በሃገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በመሪዎቹ መካከል ያለው ቅርበት ሲታይም!

ለዛውም፣ የሕወሃትን ባለሥልጣኖች ከግብጽ ጋር እንዲያስማማ የተመረጠ ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደ ‘ተላላኪ’ የሚጠቀሙበትና ባህሪውና አሠራሩ (የፍልሥጤም የደኅንነት ሚኒስትር ነበርና) በብዙ መልኩ ለትዕዝብትና ጥርጣሬ የተጋለጠው ነው! ግለሰቡ Mohammed Dahlan የካርቱሙ የመጋቢት 2014 ስምምነትም የእርሱ እጅ አለበት የሚሉ ቢኖሩም፣ ሚናው ግን በውል ተለይቶ አልታወቀም!

ያም ሆነ ይህ፣ ፕረዚደንት ሲሲ ሙሉ ለሙሉ ግብጻዊ ናቸው። በዚህም ምክንያት ሃገር ይሸጣሉ፣ ይለውጣሉ ተብለው ባይጠረጠሩ እንኳ፡ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ረገጣቸው እንደ ሕወሃት ግፍ ሁሉ፡ ግብጻውያንን የሚያሳስብ ችግር ቢሆንም፡ ለሃገሪቱ ደህንነት ግን መሥራታቸው ጥርጥር ላይ ወድቆ እንደ ኢትዮጵያውያን መከፋፈያቸው አልሆነም – ምንም እንኩ ሁኔታቸው ገና መሬት ያልቆነጠጠ ቢሁንም!

ለማንኛውም ረቡዕ ዕለት ባልተጠበቀ መንገድ፣ ሥልጣን ከያዙ ጊዜ ጀምሮ ያደቡበትን ነገር ፕሬዚደንት ሲሲ ገሃድ አደረጉት። እንዲህም ሲሉ ቃል ኪዳናችውን ለግብጽ ሕዝብ እንደገና አደሱ!

“ጭንቀታችሁ ይገባኛል፣ ከውሃ የበለጠ የሞትና ሕይወት ጥያቄ የለምና!” ፕሬዚደንቱ ቀጥለውም “ከዚህ በፊት ወደ ምድረ በዳ አልመራኋችሁም! አሁንም ወደዚያ አልመራችሁም!” አሉ!

በአንጻሩ፣ ‘የሕወሃት መኳንንት’ ግፈኝነታቸውን አጠናክረው በዚህች ሰዓት ወጣቶቻችንን በመጨፍጨፍ ላይ ሲሆኑ፣ የገቡት ቃል ኪዳን በጉልበትና በማስፈራራት ጭምር ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ ገንዘብ እየነጠቁ በመሠራት ላይ ያለውን ግድብ አስመልክተው ምን አዘቅት ውስጥ እንደከተቷት አንዳችም ለመተንፈስ አልደፈሩም – ግብጽ ታላቅ ዱላ ይዛ እስቲ ከመጋቢት 23 ቀን 2014 ስምምነት ነቅነቅ በላትና ብላ መቆሟን ፕሬዚደንት ሲሲ በቀጥታ ባይጠቅሱትም፣ ግልጽ ማድረጋቸው ግን በሕወሃት በኩል ተደማጭነት ያገኘ ይመስላል!

በሚገርም መንገድ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልም – የዘር ጽንፈት ውስጡ ባለበት አባባልና ኩራት – የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብትና ንብረት መሆኑ ቀርቶ፣ በETHIOPIAFIRST.COM ብንያም ከበደ አማካይነት በቪዲዮ በተቀረጸ መልዕክት – የራሱ መኩራሪያና የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ለማስደረግ ሃሣብ እንዳለና እርሱም እንደሚደግፈው ሲናገር አንጀቴ ብግን ብሎ ነበር።

ይህንኑ ከአንባቢዎቼ ጋር ከሰሞኑ በቲዊተር ተካፍየዋለሁ።

ከደሃው ጉሮሮ ተነጥቆ፡ እስካሁን ስምንት ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ሰሞኑን ሕወሃቶች እሰምተው ነበር። ያ ሃብት እንደ ከፍተኛ የሕዝብ መዋጮ መቆጠሩ ቀርቶ፡ ደብረጽዮን ስለ ሕወሃት ታላቅነት፡ ስለ METC ኢትዮጵያን ወደ ዘመነ ቴክኖሎጂ ማሸጋገሩ ነበር የተደሰኮረልን? ማዳመጥ ይቻላል ከቪዲዮው፣ ከግብጽ ጋር በአሁኑ ወቅት ጥሩ የመግባባትና የመተማመን ደረጃ ላይ መደረሱን በዚያው አጋጣሚ እያብራራ…
ይህንን ሁሉ ‘ተዓምር’ የሠሩ ‘የሕወሃት መኳንንት’ የሕዳሴን ግድብ ባለቤትነት እንዴት ለግብጽ እንዳስረከቡ ለምን አሁን አይነግሩንም?

ይህ ሊደርስ እንደሚችል፣ ቀደም ተብሎ የሕውሃት ሰዎች አልተመከርንም እንዳይሉ፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ምሁሮች በተለያየ ገጽታው ላይ በማተኮር ብዙ ሃሣቦችን ለግሠው ተመልክተናል። ይህም አምድ፣ ግብጽ በካርቱም የመጋቢት 23/2014 ስምምነት የኢትዮጵያን እጅ በዘላቂነት ልታሥር እንደምትችል ለማመላከት ሞክሯል።

ምናልባትም አምና ሕወሃት የኦሮሞ ሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚጨፈጭፍበት ውቅት ሰለነበር፡ ለዚህ ትኩርት አጥቶ ሊሆን ይችላል – አሁንም ሰሞኑን በካርቱም ስብሰባ ወቅት ተመሳሳይ ግድያዎችንና እሥራትን ሲፈጽም እንደቆየ ሁሉ!

ለማንኛውም፣ ከብዙዎቹ በጥቂቱ ለመጥቀስ – ለምሳሌም ያህል – በዚህ አምድ ላይ ስለ ካርቱም ስምምነት አሳሳቢነት ሚያዝያ 1/2014 በሠነዘርነው አስተያየት The Khartoum Declaration on GERD & the 1997 UN Convention on the Law of Non-navigational Uses of International Watercourses የሚከተለውን አስፍረን ነበር ፦

“Unless proper care is taken, with new possibilities created by the Great Ethiopian Renaissance Dam (GERD), the new tool in the hands of Egypt to realize its longstanding goal of circumscribing Ethiopia’s uses of Blue Nile waters could now be translated into reality. Limiting the size and operation of GERD may come in handy.

In other words, while Article III. Principle of Equitable and Reasonable Utilization is an internationally accepted principle now, it is also open and malleable to becoming poison pill against upper riparians such as Ethiopia. That would render the Blue Nile waters the exclusive preserve of Egypt and the Sudan.

As I indicated in my initial reaction of March 24 on the declaration, the operation of GERD itself could fall into joint ownership and management, already Article V, in sub-article (b) paving the road for the morphing of a body that would eventually become managing board/authority. It is already indicated that the three states may issue guidelines or rules how GERD is managed, the two non-owner states, i.e., Egypt and the Sudan, at par and in full authority. The declaration describes the purposes of this as facilitating “the annual operation of GERD, which the owner of the dam may adjust from time to time.”

More particularly, giving flesh and blood to this are the sub-articles listed in paras (a) – (i) of Article III; they speak about “the relevant guiding factors” “but not limited” to those outlined therein.

Anyone one coming up with all sorts of hardsell interpretations requesting cooperation in accepting the efforts of these three states, as represented by the Khartoum Declaration, would be making senseless effort. This is because what is foreseen by the declaration is not consistent with meaning of ownership, when at the same time the owner is bound by trilateral agreement to receive guidelines from others regarding the dam’s management and operations.

For that matter, the Khartoum Declaration has not made any reference to the concept of “participation” in Article III, much in the same manner as in the UN Convention’s Articles 5 and 6, which deal with the principle of “Equitable and reasonable utilization” shared water resources. Such provision would have helped in restricting its scope to the right to ‘utilizing’ the watercourse, instead of the present amorphous and possibly insidious Article 5. Principle to Cooperate on the First Filling and Operation of the Dam in the declaration, which in essence is a backdoor to dam ownership.”

የተፈራው የቀረ አይመስልም! የማይሰማ ንጉሥ አለ ዓመት አይነግሥ ይሉ የል! ዛሬ የሕወሃት መጥፎነት በዛሬው ትውልድ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በመጭዎቹም ትውልድ ላይ መጥፎ ፍርድ ሊሆን ነው!

የሕወሃት ተንኮል እጅግ አስገራሚ ነው። ካርቱም በድርድሩ ወቅት በመጋቢት 2015 የተፈራረመው ያን መርዘኛ የሆነውን ስምምነት – ማለትም የግድቡን ባለቤትነት ለግብጽና ሱዳን የሚያከፋፍለውን – በማስታወስ፣ ‘እባካችሁ ይህንን ብዙ አትጫኑብኝ’ (“Ethiopia’s delegation has expressed concern that any concession would spark tension with the Ethiopian public,” )፣ በማለት ሲማጸን፣ ‘ይህንን ካደረጋችሁብኝ ሃገር ውስጥ ውጥረትና ጣጣዬ መባባሱ ብቻ ሳይሆን፣ ኦሮሞችም ይጠቀሙበታል’ ማለቱን ጋዜጠኞች ጽፈውታል (“The delegation fears Ethiopia’s Oromo opposition ethnicity would use such a concession, especially with the dam having become a matter of national interest.”)።

*Updated.

 

%d bloggers like this: